Get Mystery Box with random crypto!

EBS TV NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebs_tv_news — EBS TV NEWS E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebs_tv_news — EBS TV NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ebs_tv_news
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.53K
የሰርጥ መግለጫ

BREAKING NEWS ABOUT WORLD!!!

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-04-01 10:08:14 ኡጋንዳውያኑ ለምን ኢትዮጵያ መጡ ?
ከኡጋንዳ ምሥራቃዊ ክፍል በመቶዎች የሚቆጠሩ ኡጋንዳውያን ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱት " የምፅዓትን ቀን ሽሽት ነው " መባሉ ሐሰት መሆኑን የኛንጋቶም ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ሎኪኛኒጋ ሙርሌ ለቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ተናግረዋል።
ምክትል አስተዳዳሪው ሎኪኛኒጋ ሙርሌ ምን አሉ ?
" ኡጋንዳውያኑ በወረዳችን ይገኛሉ። አመጣጣቸው አካባቢውን ለማየትና የቤተክርስቲያን መልዕክት ለማድረስ ነው።
ይህንንም ከፌደራል ደኅንነት መ/ቤት ለመጡ አካላት አስተድተናል።
በቁጥር ህጻናት እና ሴቶችን ጨምሮ 277 ይደርሳሉ ፤ በቤተክርስቲያን የእንግዳ መቀበያ እና በግለሰቦች መኖሪያ ተጠልለው ነው የሚገኙት።
ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱት የምጽዓትን ቀን ሽሽት ነው የተባለው የተሳሳተ መረጃ ነው።
በወረዳችን ከዚህ ቀደም በተዘጋጀ ፌስቲቫል ላይ ከኬንያ ቱርካና፣ ከደቡብ ሱዳን እና ከኡጋንዳ አንድ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ተሳትፈው ነበር።
እነርሱ የመጡት በታሪክም ኛንጋቶም ማኅበረሰብ ከኡጋንዳ ነው የመጣው ብለው ስለሚያምኑ አካባቢውን ለማየት ነው።
ኡጋንዳውያኑ ታኅሳስ ወር ውስጥ ነው ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ፤ እንመለሳለን ከማለት ውጭ መቼ እንደሚመለሱ አልገለፁም።
እነርሱ ሲመጡ ዝናብ አልነበረም። ዝናብ እስከሚዘንብ ድረስ ቆይተን ለእናንተ ዘር ሰጥተን ነው የምንሄደው እግዚአብሔር የነገረን መልዕክት ይህ ነው። ከዚያ በኋላ እንመለሳለን ነው ያሉት።
አሁን ላይ ግን በአካባቢው ከፍተኛ ዝናብ እየዘነበ ቢሆንም ኡጋንዳውያኑ አሁንም በሥፍራው ይገኛሉ። "
NB. በኢትዮጵያ በድርቅ ከተጎዱ አካባቢዎች አንዱ የደቡብ ኦሞ ዞን፣ ሲሆን በድርቁ ሳቢያ በርካታ እንስሳት ሞተዋል ፤ በሰዎችም ላይ ጉዳት ደርሷል።
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ምንድነው ያሉት ?
አምባሳደር መለስ ዓለም ኡጋንዳውያኑ የምጽዓት ቀን በአካባቢያችን ይኖራል። ሞት መፈናቀል ይኖራል ብለው በመስጋት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አናዱሉ ምን ብሎ ነበር ?
የቱርክ ዜና ወኪል አናዶሉ ከአንድ ወር በፊት ፣ የኡጋንዳን ፖሊስ ጠቅሶ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኡጋንዳውያን የአንድ ሃይማኖታዊ ቡድን ተከታዮች ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸውን ዘግቦ ነበር።
በዘገባው የሃይማኖት ቡድኑ ተከታዮች የዓለም ፍፃሜ ኡጋንዳ ውስጥ ከሚኖሩበት አካባቢ ይጀምራል ብለው በማመን ከጥፋቱ ለመሸሽ እንደተሰደዱ ፖሊስ በምርመራዬ አረጋግጫለሁ ማለቱን አስነብቦ ነበር።
Via BBC NEWS AMHARIC
@EBS_TV_NEWS
1.4K views07:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 10:06:01 የነጻ ትምህርት ዕድል !
በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ወይንም Menschen für Menschen Foundation ስር የሚተዳደረው የሐረር ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በ2015 የትምህርት ዘመን ብቁ የሆኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐግብር ሙሉ ወጪያቸውን ሸፍኖ ማስተማር ይፈልጋል፡፡
የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ተማሪዎች ከመጋቢተ 18 - 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ባሉት የስራ ቀናት በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።
የመመዝገቢያ መስፈርቶች ፦ ትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ዓ.ም. ያወጣውን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርት የሚያሟሉ ወይንም በአገር አቀፍ ፈተና 50% እና ከዚያ በላይ ያመጡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች፡፡
የምዝገባ ቦታዎች በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ በሚገኘው የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ዋና መ/ቤት፤ ሐረር በኮሌጁ ቅጥር ግቢ፤ የድርጅቱ ፕሮጄክት ጽ/ቤቶች በሚገኙባችው በተጨማሪም በድረ-ገጻችን http://www.mfmattc.edu.et ላይም መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0256663738/1139 ወይም 0114714579 ደውሎ ማንጋገር ይቻላል፡፡
(ሰዎች ለሰዎች ድርጅት Menschen für Menschen Foundation) @EBS_TV_NEWS
1.3K viewsedited  07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 16:15:28 የቤት ማፍረስ ዘመቻው ቀጥሏል።
አዲስ በተመሰረተው ሸገር ከተማ አሁንም የቤት ፈረሳ ዘመቻው መቀጠሉን የየአካባቢው ነዋሪዎች እየገለፁ ይገኛሉ።
መንግሥት ቤቶችን እያፈረሰ የሚገኘው " ህገወጥ ነው " በሚል እንደሆነ ከዚህ ቀደም ገልጿል።
ቤት እየፈረሰባቸው ያሉ ወገኖች ስለጉዳዩ ምን ይላሉ ?
⮕ በርካታ ቤቶች ናቸው እየፈረሱ ያሉት፤ እነዚህ ቤቶች ከገበሬ የተገዙ እና ረጅም ዓመታት ጭምር ሰዎች ሲኖሩባቸው የነበሩ ናቸው።
⮕ ከፈረሱት ቤቶች ውስጥ ዜጎች ለዓመታት ለፍተው የሰሯቸው ይገኙበታል።
⮕ ምትክ ቦታ/ ማረፊ ሳይመቻች ነው ሜዳ ላይ የተጣልነው።
⮕ መንግስት ዛሬ ላይ ህገወጥ ነው እያለ የሚያፈርሰው ቤቶቹ ሲገነቡና ይህን ሁሉ ዓመት ሲኖርባቸው የት ነበር ?
⮕ በአንዳንድ ቦታዎች ቤት የሚፈርሰው በለሊት ጭምር ነው፤ ሰዎች በተኙበት ምንም ሳይዘጋጁ እንዲፈርስባቸው ይደረጋል።
⮕ እየፈረሱ ካሉት ቤቶች መካከል አንዳንዶቹ የመብራት የውሃ ክፍያ፣ የአፈር ግብርም የፈፀሙ ናቸው።
⮕ ከቤት ማፍረስ ዘመቻው ጋር በተያያዘ አንዳንድ ቤቶችን ማንነትን/ ብሔርን ለይቶ ማፍረስም ይስተዋል።
⮕ የሰብዓዊነት ጉዳይ ጭራሽ ከምንም የማይቆጠርበት ሁኔታ ነው እየተፈጠረ ያለው ፤ ነፍሰ ጡር እና በእድሜ የገፉ እናቶች እንዲሁም ህፃናትን ጨምሮ በርካቶች #ሜዳ ላይ ወድቀዋል። እቃ እንኳን እንዳይወጣ ላያቸው ላይ ቤታቸው ፈርሷል።
ስለሚፈርሱ ቤቶች ከዚህ ቀደም የከተማው ከንቲባ ዶ/ር ተሾመ አዱኛ ምን ምላሽ ሰጥተው ነበር (አንከር ለተሰኘ ሚዲያ)?
➣ የሚፈርሱት ለአንድ ከተማ ፀር የሆኑ ህገወጥ ግንባታዎች ናቸው።
➣ ህገወጥ ግንባታዎችን እናፈርሳለን ህጋዊ ከተማ መልክ እንዲይዝ እናደርጋለን።
➣ በአስተዳደር ችግር ፣ ጠንካራ የሆነ አስተዳደር በፊት አለመኖር ምክንያት የግንባታ እና የመሬት ባለቤትነት፣ የግንባታ ፍቃድ ሳይኖር መብራት ማውጣት ይሄ ስራ አሁን ከሚፈለገው የከተማ ሂደት ጋር የማይሆኑ ነገሮች ነው የተፈጠሩት እነሱ በመኖራቸው አይፈርሱም የሚል ሳይንስ የለም። አንድ ሰው በስርዓት ካርታ መውሰድ አለበት፣ በስርዓት የግንባታ ፍቃድ ማግኘት አለበት፣ የክልሉ ህግና ስርዓት ጠብቆ መሄድ አለበት እነዚህ ሳይሟሉ በራሳችን መዋቅር ድክመት / አሰራር መብራት ስላልስገባ / ውሃ ስላስገባ የማይፈርስ የለም። ያ እንደጥፋት የምናየው ከአሁን በኃላ መደገም የለበትም።
➣ ሰብዓዊነት እኛም ይሰማናል መታየት ያለበት ግን ህግ መከበር አለበት፤ እኛ ይሄንን ከጨረስን በኃላ በክልል ደረጃም ይሁን በከተማ ደረጃ አንድ ሰው ቤት ማግኘት ሰብዓዊ መብቱ ስለሆነ እኛ በምናወጣቸው ፕሮግራሞች አካተን ያለውን ችግር መፍታት እንችላለን።
➣ የምናፈርሰው ግልፅ የሆነ አንድ ዘመናዊ ከተማ ላይ እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎችን ታሳቢ በማድረግ ነው። ከእንቅፋቶቹ አንዱ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የመሬት ወረራ እና ህገወጥ ግንባታዎች ነው ይሄን መሰረት አድርገን ነው የምንሄደው (የግንባታ ፍቃድ የሌላቸው፣ በስርዓት መሬት ያልወሰዱ፣ ካርታ የሌላቸው) ይሄን ነው የምንከተለው ፈረሳው ብሄርን / ዘርን መሰረት ያደረገ አይደለም። ማንንም ዒላማ አድርገን አይደለም የምንሰራው።
➣ ቅደመ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል ፣ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ብቻ ሳይሆን ማህበረሰቡን አወያይተን ፣ ህገወጥ እንዳሆኑ ነገረን ፣ ህገወጥ ያደረጋቸው ምን እንደሆነ አስረድተን፣ ምልክት አድርገን ነው የምናፈርሰው ፤ በእኛ ሀገር ' ቤት ሰባቴ ካልፈረሰ ቤት አይሆንም ' የሚል የማይሆን አመለካከት ስላለ በአንድ በኩል አያፈርሱም ብለው ያስባሉ ቢፈርስም ትንሽ ዞር ሲሉ መልሰን እንገባበታለን የሚል ነገር አለ ስለዚህ እየነገርን እየታወቀ ነው ፈረሳው የሚደረገው።
@EBS_TV_NEWS
354 views13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 09:50:36 #ባጃጅ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች / ባጃጅ መታገዱን በተመለከተ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አጭር ማብራሪያ ሰጥቷል።

በማብራሪያው ፤ " መንግስት የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችን #የነዳጅ_ድጎማ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረጉ እየታወቀ የባለሶስት ጎማ ወይም በተለምዶ አጠራራቸው የባጃጅ አሽከርካሪዎች ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ እንዲሁም የተወሰኑት በወንጀል ድርጊቶች ላይ በመሰማራት የከተማችን ነዋሪ የቅሬታ ምንጭ ሆነዋል " ብሏል።

የከተማ አስተዳደሩ የባጃጅ አገልግሎትን ስርዓት ለማስያዝ የአሰራር ማስተካከያ እያደረገ መሆኑን ገልጾ ይህ ተግባራዊ እስከሚሆን ድረስ በከተማድ ሁሉም አካባቢዎች የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት #እንዲቆም መወሰኑን ገልጿል።

የተሸርካሪዎቹ ከስራ መውጣት በነዋሪው ላይ የትራንስፖርት ጫና እንዳያሳድር አስተዳደሩ ሌሎቹ የትራንስፖርት አገልግሎቶች በሙሉ አቅማቸውና በቅንጅት አገልግሎት የሚሰጡበትን ሁኔታ መመቻቸቱን አመላክቷል።

(የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሌሎች ጉዳዮችንም ያነሳበት የዛሬ መጋቢት 1 ቀን 2015 ዓ.ም መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@EBS_TV_NEWS
1.6K views06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 15:13:13
' ሰላተል ኢስትስቃ '

ነገ በመላ ሀገሪቱ "ሰላተል ኢስ ትስቃ" እንዲሰገድ  የኢትዮጵያ  እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ጥሪ አቅርቧል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቦረና ዞን በዝናብ እጥረት ምክንያት የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ  " ሰላተል ኢስ ትስቃ " እንዲሰገድ ለመላው ምዕመን ጥሪ አድርጓል።

ነገ ሰኞ በመላው ሀገሪቱ እንዲሰገድ ጥሪ የቀረበው " ሰላተል ኢስትስቃ " ዝናብ በሚርቅበት ጊዜ የሚሰገድ ሰላት መሆኑን ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በሌላ በኩል ፤ ጠቅላይ ም/ቤቱ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን ዕርዳታ የሚውል ድጋፍ ማሰባሰቢያ የባንክ ቁጥሮችን ይፋ አድርጎ ድጋፍ እያሰባሰበ እንደሆነ ተሰምቷል።

ጠቅላይ ም/ቤቱ ይፋ ያደረጋቸው የባንክ ቁጥሮች ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሣብ ቁጥር 5582 ፣ ዳሸን ባንክ ሂሣብ ቁጥር 795571270973፣ ዘምዘም ባንክ ሂሣብ ቁጥር 222255፣ ሂጅራ ባንክ ሂሣብ ቁጥር 308010 ፣ ኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ቁጥር 1000093406226 ናቸው።

@EBS_TV_NEWS
1.7K views12:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 14:10:00
#Repost

የካራማራ ድል !

የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ/ም የሱማሊያን ዚያድባሬ ጦር ለመመከት በካራማራ ጀግኖች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የህይወት መሰዋዕትነት ከፍለው ወራሪውን ጦር ከሀገር ያባረሩበትና የሀገራቸውን ሰንደቅ ያውለበለቡበት ቀን ነው።

ዘንድሮ ይህ ድል 45ኛ አመት ሞልቶታል ቀኑም እየታሰበ ነው።

ከጦርነቱ በፊት ለረጅም ጊዜ የሶማሊያ ጦር በሶቪዬት ኅብረት ይደገፍ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ ከአሜሪካ ጋር ወዳጅነት ነበረው። በወቅቱ አሜሪካ እና የሶቪየት ህብረት በቀዝቃዛ ጦርነት ውስጥ ነበሩ።

በቅድሚያ በሶቪየት ህብረት ከፍተኛ ድጋፍ የመጣው የዚአድባሪ ጦር የእናት ሀገር ጥሪ እያለ በተሰበሰበው የኢትዮጵያ ጦረኛ ካራማራ ላይ ድባቅ ተመትቶ ወደ መጣበት ተመልሶል፡፡

በጦርነቱ መጀመሪያ ሶማሊያን ስትደግፍ የነበረችው  ሶቪየት ህብረት ወደ ኢትዮጵያ አዘንብላ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ እገዛ አድርጋለች ፤ አሜሪካ ደግሞ ወደ ሶማሊያ ፊቷን አዙራለች።

በጦርነቱ ኩባ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ የመንና ምሥራቅ ጀርመንን ጨምሮ ሌሎች አገራት አጋርነታቸውን ለኢትዮጵያ አሳይተዋል።

ከ16 ሺ በላይ የኩባ ወታደሮች በውጊያው እንደተሳተፉ መዛግብት ያሳያሉ። ደቡብ የመንም ጦሯን ለኢትዮጵያ አሰልፋ ነበር።

በተለያየ የፖለቲካ የትግል ሁኔታ፣ በተለያየ ቅራኔ ውስጥ የነበሩ የኢትዮጵያ ሀይሎች ሁሉ ስለ ሀገር አንድ ሆነው የዚያድባሬን ጦር የመከቱበት የካራማራ ጦርነት የኢትዮጵያ አንድነት ዳግም በጉልህ የታየበት ስለመሆኑ ይነገርለታል፡፡

በየአመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰበው የ " ካራማራ ድል " ዘንድሮም ለ45ኛ ጊዜ እየታሰበ ይገኛል፡፡

@EBS_TV_NEWS
1.9K views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 07:56:02
" በብሔራዊ ፈተናው ከ600 በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲ ወጪ እንሸፍናለን " - አማራ ባንክ

በ2014 ዓም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው በመላ ሀገሪቱ ከ600 በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲ ወጪ እንደሚሸፍን አማራ ባንክ አሳውቋል።

ባንኩ በመላው ሀገሪቱ ከ600 በላይ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው በወር 750 ብር እየከፈለ እንደሚያስተምር የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሄኖክ ከበደ ገልጸዋል።

ይህ ውሳኔ የባንኩ የማኀበረሰባዊ አገልግሎት አካል መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ለአሚኮ ጠቁመዋል።

በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር እውቅናና ሽልማት ይሰጣቸዋል መባሉ ይታወሳል።

@EBS_TV_NEWS
3.3K views04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 18:44:28
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን ተማሪዎች ከዛሬ ለሊት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ተፈታኞች ከዛሬ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም #ከሌሊቱ 5፡30 ጀምሮ ፡-

• በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ወይም
• በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም
• በቴሌግራም ላይ https://t.me/eaesbot
ማየት የሚችሉ መሆኑን ተገልጿል።

ማሳሰቢያ፡-

• ማንኛውም ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልግ እስከ ጥር 26/2015 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ላይ Compliant የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል።

• ተማሪዎች ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አድራሻ ላይ ብቻ እንዲጠቀሙ #ከተመሳሳይ እና #የተዛባ_መረጃ ለማሰራጫት ከሚሞክሩ አካላት እራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክት ተላልፏል።

ምንጭ ፦ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

@EBS_TV_NEWS
5.9K views15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-20 06:55:46
#Update

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰላም ስምምነት ተከትሎ በሽረ፣ አላማጣ እና ኮረም ከተማዎች በሚገኙ ቅርንጫፎቹ ከውጭ ሀገር እና ከሀገር ውስጥ የሚላኩ ገንዘቦችን የመቀበል እንዲሁም ገንዘብ የማስቀመጥ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ዛሬ ምሽት አሳውቋል።

ባንኩ በቀጣይ ሁኔታዎች እንደፈቀዱ አገልግሎቱን በማስፋትና በየደረጃው በሁሉም ቅርንጫፎች ላይ አገልግሎት ለማስጀመር እንደሚሰራ ገልጿል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል በነበረው ጦርነት ሳቢያ ለበርካታ ወራት የትግራይ ክልል አካባቢዎች የባንክ አገልግሎት ማግኘት ሳይችሉ እንደቀሩ ይታወቃል።

@EBS_Tv_News
1.2K views03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 19:24:03
#USA #AFRICA

ለ3 ቀናት የተካሄደው የአሜሪካ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ትናንት ሐሙስ ተጠናቋል።

የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን በጉባኤው ምን አሉ ?

- ከሰሃራ ግርጌ ወዳሉ የአፍሪካ አገሮች በቅርቡ ጉብኝት እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ከሰሃራ ግርጌ ወዳሉ የአፍሪካ አገሮች የሚያደርግት ጉብኝት እንደ ፕሬዝደንት የመጀመሪያው ነው። ቀኑን እና የትኞቹ ሀገራትን እንደሚጎበኙ ግን አላሳውቁም።

- አፍሪካ እድገት እያስመዘገበች መሆኑን ገልፀው አሜሪካ ትኩረቷን እንደምትጨምርም ጠቁመዋል።

- ከፍተኛ አማካሪዎቻቸውን ወደ አፍሪካ እንደሚልኩ ገልፀዋል። ወደ አፍሪካ ከሚላኩት ውስጥ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንተኒ ብሊንከን፣ የገንዘብ ሚኒስትሯ ጃነት የሊን እና የንግድ ሚኒስትሯ ጂና ሬይሞንዶ ይገኙበታል።

- በሚቀጥለው ዓመት ለሚደረጉ ምርጫዎች 165 ሚሊዮን ዶላር እንደሚመደብ ቃል ገብተዋል።

ፕሬዚደንት ባይደንና ባለቤታቸው ጂል ባይደን የአፍሪካ አገራት መሪዎችንና ቀዳማዊ እመቤቶቻቸውን በዋይት ሃውስ የእራት ግብዣ አድርገውላቸዋል።

በሌላ በኩል ፤ በአሜሪካ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ሊሳተፍ ወደ አሜሪካ አቅንቶ የነበረው የኢትዮጵያ ልዑክ ወደ ሀገር መመለሱን የጠ/ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ አመሻሹን አሳውቀዋል።

#ቪኦኤ #አምባሳደር_ሬድዋን_ሁሴን

@EBS_TV_NEWS
1.7K views16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ