Get Mystery Box with random crypto!

ኡጋንዳውያኑ ለምን ኢትዮጵያ መጡ ? ከኡጋንዳ ምሥራቃዊ ክፍል በመቶዎች የሚቆጠሩ ኡጋንዳውያን ወደ | EBS TV NEWS

ኡጋንዳውያኑ ለምን ኢትዮጵያ መጡ ?
ከኡጋንዳ ምሥራቃዊ ክፍል በመቶዎች የሚቆጠሩ ኡጋንዳውያን ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱት " የምፅዓትን ቀን ሽሽት ነው " መባሉ ሐሰት መሆኑን የኛንጋቶም ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ሎኪኛኒጋ ሙርሌ ለቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ተናግረዋል።
ምክትል አስተዳዳሪው ሎኪኛኒጋ ሙርሌ ምን አሉ ?
" ኡጋንዳውያኑ በወረዳችን ይገኛሉ። አመጣጣቸው አካባቢውን ለማየትና የቤተክርስቲያን መልዕክት ለማድረስ ነው።
ይህንንም ከፌደራል ደኅንነት መ/ቤት ለመጡ አካላት አስተድተናል።
በቁጥር ህጻናት እና ሴቶችን ጨምሮ 277 ይደርሳሉ ፤ በቤተክርስቲያን የእንግዳ መቀበያ እና በግለሰቦች መኖሪያ ተጠልለው ነው የሚገኙት።
ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱት የምጽዓትን ቀን ሽሽት ነው የተባለው የተሳሳተ መረጃ ነው።
በወረዳችን ከዚህ ቀደም በተዘጋጀ ፌስቲቫል ላይ ከኬንያ ቱርካና፣ ከደቡብ ሱዳን እና ከኡጋንዳ አንድ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ተሳትፈው ነበር።
እነርሱ የመጡት በታሪክም ኛንጋቶም ማኅበረሰብ ከኡጋንዳ ነው የመጣው ብለው ስለሚያምኑ አካባቢውን ለማየት ነው።
ኡጋንዳውያኑ ታኅሳስ ወር ውስጥ ነው ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ፤ እንመለሳለን ከማለት ውጭ መቼ እንደሚመለሱ አልገለፁም።
እነርሱ ሲመጡ ዝናብ አልነበረም። ዝናብ እስከሚዘንብ ድረስ ቆይተን ለእናንተ ዘር ሰጥተን ነው የምንሄደው እግዚአብሔር የነገረን መልዕክት ይህ ነው። ከዚያ በኋላ እንመለሳለን ነው ያሉት።
አሁን ላይ ግን በአካባቢው ከፍተኛ ዝናብ እየዘነበ ቢሆንም ኡጋንዳውያኑ አሁንም በሥፍራው ይገኛሉ። "
NB. በኢትዮጵያ በድርቅ ከተጎዱ አካባቢዎች አንዱ የደቡብ ኦሞ ዞን፣ ሲሆን በድርቁ ሳቢያ በርካታ እንስሳት ሞተዋል ፤ በሰዎችም ላይ ጉዳት ደርሷል።
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ምንድነው ያሉት ?
አምባሳደር መለስ ዓለም ኡጋንዳውያኑ የምጽዓት ቀን በአካባቢያችን ይኖራል። ሞት መፈናቀል ይኖራል ብለው በመስጋት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አናዱሉ ምን ብሎ ነበር ?
የቱርክ ዜና ወኪል አናዶሉ ከአንድ ወር በፊት ፣ የኡጋንዳን ፖሊስ ጠቅሶ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኡጋንዳውያን የአንድ ሃይማኖታዊ ቡድን ተከታዮች ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸውን ዘግቦ ነበር።
በዘገባው የሃይማኖት ቡድኑ ተከታዮች የዓለም ፍፃሜ ኡጋንዳ ውስጥ ከሚኖሩበት አካባቢ ይጀምራል ብለው በማመን ከጥፋቱ ለመሸሽ እንደተሰደዱ ፖሊስ በምርመራዬ አረጋግጫለሁ ማለቱን አስነብቦ ነበር።
Via BBC NEWS AMHARIC
@EBS_TV_NEWS