Get Mystery Box with random crypto!

EBS TV NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebs_tv_news — EBS TV NEWS E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebs_tv_news — EBS TV NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ebs_tv_news
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.53K
የሰርጥ መግለጫ

BREAKING NEWS ABOUT WORLD!!!

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-03 18:02:33
የሪሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ዛሬ መሰጠት ይጀምራል፡፡

በ2014 ዓ.ም የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የነበሩና በተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማጠናከሪያ ትምህርት ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች የሪሚዲያል ፈተና ከዛሬ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ይሰጣል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናውን ለሚሰጡ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የላከው የጊዜ ሰሌዳ እንደሚያሳየው ፈተናው ዛሬ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 መሰጠት ይጀምራል፡፡

የፈተና የፍተሻና የክፍል ቅድመ ዝግጅት በየዕለቱ ከቀኑ 8:00 የሚጀምር ሲሆን ፈተናው ደግሞ ከቀኑ 9:00 መሰጠት ይጀምራል። (የፈተናው መርሃ ግብር ከላይ ተያይዟል፡፡)

ተፈታኝ ተማሪዎች ለፍተሻ እና የክፍል ቅድመ ዝግጅት ሥራ 8:00 ላይ በመፈተኛ ክፍላቸው  በር ላይ እንዲገኙ ተብሏል፡፡

Via : t.me/+RYD_4tbNBwRoKR2h

@EBS_TV_NEWS
2.0K views15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-23 07:14:47 #Agew
ከ1 ዓመት በላይ ጊዜ ወስዷል የተባለው " አንታጉ " የተሰኘ የአገውኛ ፊልም ዛሬ ተመረቀ።
ለመጀመሪያ ጊዜ በ " አገወኛ ቋንቋ " የተሰራው " አንታጉ " የአገወኛ ፊልም የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንግዳ ዳኛውን ጨምሮ የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።
በፊልሙ የምረቃ ስነሥርዓት ላይ አቶ እንግዳ ዳኛው ፤ " አንታጉ የአገውኛ ፊልም አገዎች የቀደምት የጥበብ ባለቤት መሆናቸውን ማሳያ ነው " ብለዋል።
መረጃው ከአዊ ኮሚኒኬሽን የተላከ ነው።
@EBS_TV_NEWS
5.2K views04:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 15:13:41 #AddisAbaba
ዛሬ በአዲስ አበባ ፤ " አንዋር መስጂድ " ከጁመአ ስግደት መጠናቀቅ በኃላ የፀጥታ ኃይሎች በተከፈቱት ተኩስ ጉዳት ስለመድረሱ በአካባቢው የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።
በአሁን ሰዓት የተጎዱ ሰዎች እርዳታ እንዲያገኙ ጥሪ አቅርበዋል።
በመስጂዱ በነበረው ሁኔታ የአደጋ ጊዜ አዛን መሰማቱ ተነግሯል።
ከዚሁ ጋር በተያየ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ፤ " በታላቁ አንዋር መስጂድ የጁምዓ ሰላቱን ለመስገድ ከቤቱ የወጣን እና በመስጂድ ያለን ንፁሃን ህዝበ ሙስሊም ላይ ያለምንም ርህራሄ በጥይት የሀይል እርምጃ መውሰድ ኢ ሰብዓዊ ተግባር ነው " ብለዋል።
" ባዶ እጁን ለሰላት በወጡ ንፁሀን ላይ እየተወሰደ ያለውን የኃይል እርምጃ የፀጥታ ኃይሎች ያቆሙ ዘንድ አሳስባለሁ " ያሉቱ ኡስታዝ አቡበከር " በመስጂዱ ተጠልለው የሚገኙ እና ያለህራሄ በጥይት ተመትተው በመስጂዱ ውስጥ እና ዙሪያውን ወድቀው የሚገኙት ወንድሞቻችን በአስቸኳይ ወደ ህክምና ቦታ ይወሰዱ ዘንድ አምቡላንስ ወደ ቦታው እንዲገባ መንገዱን ክፍት ልታደርጉ ይገባል " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ስለ ዛሬው የአንዋር መስጂድ ሁኔታ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እንዲሁም የአ/አ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሚሰጡት መረጃ / መግለጫ ካለ ተከታትለን እናሳውቃለን።
በተመሳሳይ በመንግስት / በከተማው አስተዳደር በኩል የሚሰጥ ማብራሪያ ካለ ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።
ባለፈው ሳምንት ጁመአ በአንዋር መስጂድ በሸገር ከተማ እየተከናወነ ያለው የመስጂዶች ፈረሳ ተግባር በአፋጣኝ እንዲቆም ጥሪ በቀረበበት ወቅት በተወሰደ እርምጃ የሰዎች ህይወት ማለፉ የሚዘነጋ አይደለም።
@Ebs_tv_news
3.7K views12:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 06:26:31 በትግራይ #ኔትዎርክ ተቋርጧል።
በትግራይ ክልል ከምሽት 12 ሰዓት አንስቶ የኔትዎርክ አገልግሎት መቋረጡን በዚህም ምክንያት " ምን ተፈጥሮ ነው ? " በሚል ጭንቀት እንደገባቸው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰቡን አባላት መልዕክት ይዞ ኢትዮ ቴሌኮምን አነጋግሯል።
ኢትዮ ቴሌኮም ፤ እውነት ነው ኔትዎርክ ተቋርጧል ሲል አረጋግጦልናል።
" ኔትዎርክ የተቋረጠው ፋይበር ተቆርጦ " ነው ያለው ኢትዮ ቴሌኮም " ሰራተኞቻችን በጥገና ላይ ናቸው " ብሏል።
" ከማዕከል የሚያገናኘው ፋይበር ሁለት ቦታ ተቆርጧል፤ ዋናው እና የመጠባበቂያውን ጨምሮ " ያለው ኢትዮ ቴሌኮም ፤ ከመቐለ ፣ ከደሴ እና ከሰመራ ሰራተኞች ተሰማርተው በርብርብ እየሰሩ ይገኛሉ ሲል አሳውቋል።
የጉዳቱን መጠን በተመለከተ ላቀረብነው ጥያቄ " ምሽት በመሆኑ የጉዳቱን መጠን ማረጋግጥ አልተቻለም " ተብለናል።
@EBS_TV_NEWS
486 views03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 18:32:10 #EHRC
" ... ጉዳዩ ከዚህ የበለጠ ሳይባባስ ፓርላማው የመንግስት አስፈፃሚ አካሉን በአስቸኳይ ሊያሳስብ ይገባል " - ዶ/ር ዳንኤል በቀለ
ዛሬ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የ9 ወራት የእቅድ አፈፃፀሙን ሪፖርት ለህ/ተ/ም/ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርቧል።
በዚህም ወቅት የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ በአማራ ክልል የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች አሳሳቢ እንደሆኑ ቀጥለዋል ብለዋል።
ከቅርብ ጊዜ አንስቶ መንግሥት በአማራ ክልል እያካሄደ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከሰብዓዊ መብቶች አንፃር በጣም የሚያሰጋነው ሲሉ ገልጸዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ ፤ በአሁን ወቅት በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ #በሲቪል ሰዎች ላይ ፦- የሞት፣
- የንብረት መውደም፣ - የመፈናቀል ጉዳት መድረሱን በዚህም የሰብዓዊ መብት ስጋቱም መቀጠሉን አንስተዋል።
" መንግሥት የፀጥታ እርምጃ በአማራ ክልል በማካሄድ ላይ የሚገኝ መሆኑን አሳውቋል ፤ " ያሉት ዶ/ር ዳንኤል " ነገር ግን ይህ ወታደራዊ እርምጃ የሰብዓዊ መብት እንድምታ ስላለው ፣ የሰብዐዊ መብት ተፅእኖ ስለሚፈጥር ይሄን በቅርበት እየተከታተልን ነው " ብለዋል።
" እስካሁን ባለው መረጃ በመነሳት ከሰብዓዊ መብቶች አንፃር በጣም የሚያሰጋ ስለሆነ ኢሰመኮ #ውይይት እና #ሰላማዊ መፍትሄ አስፈላጊነትን አበክሮ በማሳሰብ ጉዳዩ ከዚህ የበለጠ ሳይባባስ ፓርላማው የመንግስት አስፈፃሚ አካሉን በአስቸኳይ ሊያሳስብ ይገባል። " ሲሉ አክለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ዶ/ር ዳንኤል ባቀረቡት ሪፖርት የዘፈቀደ እስር ፣ ሰዎች ሲታሰሩ የሚያዙበት መንገድ፣ ለሰብዓዊ ጉዳዮች አሳሳቢ ሆኖ ቀጥሏል ብለዋል።
ዶ/ር ዳንኤል ፤ " በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈፀመው የዘፈቀደ እስር እና በእስር ወቅት የሚፈፀሙ ተገቢ ያልሆኑ አያያዞች / አንዳንድ ቦታዎች ድብደባን ጨምሮ ተገቢ ያልሆነ አያያዝና እስራት እንዲሁም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለመከበርም ቀጥሏል " ብለዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ ፤ አንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚፈፀሙት የዘፈቀደ እስሮች #የቤተሰብ አባላትን ጭምር ለማጥቃት የሚውሉ ናቸው ሲሉ ለፓርላማው በሪፖርታቸው አሳውቀዋል።
@EBS_TV_NEWS
2.1K views15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 09:09:51 #ዒድ_አልፈጥር
ውድ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆናችሁ ቤተሰቦቻችን በሙሉ እንኳን ለ1444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ዒድ ሙባረክ !
በዓሉ የሰላም ፣ የአንድነት ፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።
በዓሉን ስታከብሩ የተቸገሩት ፣ ያጡትን ፣ በችግር ላይ የወደቁትን ፤ በሰላም እጦት የሚሰቃዩትን ፣ በጦርነት እና በግጭት ወገን ዘመዶቻቸውን ከጎናቸው የተነጠቁትን ፣ ከሞቀው ቄያቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የቀሩ ወገኖቻችን በማሰብ ይሆን ዘንድ አደራ እንላለን።
ሀገራችንን ፈጣሪ ይጠብቅልን!!መልካም በዓል !
ፎቶ፦ አቤል ጋሻው (ፋይል)
@EBS_TV_NEWS
1.3K views06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 13:34:45 " ስቅለት "
በክርስትና አስተምሮ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለ በደል ያለ ጥፋት ንጹሕ እና ጻድቅ የኾነውን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰቀሉበት ዕለት ነው።
ዕለቱ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ዂሉ መድኀኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልዕልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የሚታሰብበት ታላቅ ቀን ነው።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን #በስግደት እና #በጾም የሚታሰብ ሲሆን በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረትም በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች ታስቦ ይውላል፡፡
በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከንጋታው ጀምሮ እስከ ማምሻው በዕለቱ የተፈጸሙትን ክስተቶች በሰዓት ከፍላ በልዩ መንፈሳዊ ሥርዓትና በስግደት ታከብረዋለች ፦
ዓርብ ጠዋት
ዓርብ ጠዋት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ፊት በፍርድ አደባባይ መቆሙ ይታሰባል። የካህናት አለቆችና ሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ፤ አስረውም ወሰዱት ፥ ለገዢው ለጰንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።
በ3 ሰዓት
ጲላጦስ በወቅቱ በነበረው ሕዝብ ግፊት መሠረት ወንጀለኛውን በርባንን ከእስር አስፈትቶ በምትኩ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠበት፤ አካሉ እስኪያልቅም 6,666 የገረፉት ከሊቶስጥራ - ቀራኒዮ እርጥብ መስቀል አሸክመው የወሰዱበት ነው።
በ6 ሰዓት
ኢየሱስ ክርስቶስን እጆቹን እና እግሮቹን ቸንክረው በቀራንዮ ጎልጎታ ተራራ በ2 ወንበዴዎች መካከል የተሰቀለበት ነው።
በ9 ሰዓት
በእምነቱ አስተምሮ ይህ ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ከሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ የለየበት ወደ ሲዖል ወርዶም የታሠሩትን ሁሉ ያስፈታበት ነው።
11 ሰዓት
ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብር እና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር የቀበሩበት ነው።
#Repost@EBS_TV_NEWS
1.2K views10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 18:40:32 #Amhara

ልዩ ኃይሉን ምን አስቆጣው ?

መንግሥት በአማራ ክልል የልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀት እንቅስቃሴ ውስጥ ምን ስህተቶችን ፈፀመ ?


የአማራ ክልል ብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ትላንት ምሽት በክልሉ ቴሌቪዥን ቃለምልልስ አድርገዋል።

በዚሁ ቃለምልልስ ወቅት በአማራ ክልል ከልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ተፈፀመዋል ስላሉት ስህተቶች አብራርተዋል።

በተጨማሪ በክልሉ ህዝብ ዘንድ ስለሚነሱት ስጋቶች፣ጥያቄዎች ቅሬታዎች ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ ግርማ የሺጥላ አተገባበሩንና የተፈፀሙ ስህተቶችን፣ እና ያጋጠሙ ችግሮችን በተመለከተ ምን አሉ ?

" ...በተገባበር በኩል በአማራ ክልል ሁኔታ ለየት ያሉ ችግሮች ገጥመዋል። ውሳኔው ሀገራዊ ውሳኔ ነው፤የሁሉንም ይሁንታ ያገኘ ነው። ይልቁንም በውሳኔ ደረጃ ከተመለከት ነው ይህ ጉዳይ መፍጠን ነበረበት ተብሎ የሚወሰድ ነው።

አሁንም ቢሆን አልመሸም ነበርና ከተወሰነ በኃላ አፈፃፀሙ ዝርዝር እቅድ ወጥቶለት እንዲከናወን ሲደረግ በአማራ ክልል የገጠመ ችግር አለ።

የገጠመው ችግር አንደኛው እና ዋነኛው ስራውን እንዲካከናውን የተደጋጀው ኃይል የተከተለው መንገድ ብዙ እቅዱን የተመረኮዙ ስራዎች ቢሆንም የተፈፀሙ ስህተቶች አሉ።

የመጀመሪያው የተፈፀመው ስህተት የቅድመ እውነቶች፤ፖለቲካ ስራዎች ቀድመውናል። አንደኛው ልዩ ኃይሉን መልሰን እናደራጃለን የሚል እቅድ ይዘን ለመንቀሳቀስ ስራ ስንሰራ 'ልዩ ኃይሉን ለማፍረስ መንግሥት ወሰነ' የሚል የፖለቲካ ስራ በስፋት ተሰራጨ።

2ኛው ልዩ ኃይሉ እየተጠቀማቸው ያሉ የጦር መሳሪያዎች እና ተተኳሾች እንዲሁም ልዩ ልዩ ግብአቶችን በተመለከተ በእቅዱ ላይ የተመላከተው በዋነኛነት ክልሉን ለማጠናከር፣ ይሄን ኃይል ይዞ ለማጠናከር እንደሚውሉና ተነግሮት አውቆ አምኖበት በወታደራዊ ዲሲፕሊን ለየሚፈለግበት ስራ እንደሚያውል ተደርጎ የተቀመጠውን ትጥቅ ' ሊፈታ ነው ' እና የአማራን ክብር እና ሞገስ የሚያዛባ አይነት ስራ እንደሚሰራ ተደርጎ ተገለፀ።

3ኛው ይሄ ኃይል ሪፎርም ሲደረግ በዋነኛነት የክልሎችን የፀጥታ ተቋም እንደሚያጠናክር ሳይሆን ወደ መከላከያ ግባ እንደተባለና የመከላከያ ኃይል በጉልበት እንደሚያደርገው ተደርጎ ተቀነቀነ።

በዚህ ምክንያት የአማራ ክልል የስራው ባለቤቶች ስራው ወደ ክልል መጥቶ ሲጀመር ስርዓት ባለው መንገድ በአግባቡ ውይይት፣ ንግግር ሲደረግ በመሃል ከስራ አስፈፃሚዎች መካከል 'ትጥቅ እንዲያወርድ' የሚል ደብዳቤ የመንግስት መሪዎች፣ የፖለቲካ መሪዎች ባላወቅነው መንገድ ሾልኮ ይልቁንም ሰራዊቱ ሳያውቀው በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር ተመለከትን።

በዚህ በእጅጉ አዝነናል፤ አንደኛ የሰራዊቱንም የህዝቡንም ክብር ይነካል። ሁለተኛ ለቆምንለት አላማና ለምንሰራው ስራ በፍፁም የሚመጥን ደብዳቤ አይደለም።

ያለው የፖለቲካ ሴራ እንዲህ አይነት ነዳጅ ሲያገኝ የበለጠ ተጋጋለ በመጋጋሉ ምክንያት ልዩ ኃይሉ ሊወያይ ካለበት ቀን በፊት ለምንድነው የተበደልኩት? ለምንድነው ላደረኩት አስተዋፅኦ እንዲህ አይነት ደብዳቤ ሳይነገረኝ ሳልወያይ የከፈልኩት መስእዋትነት ደሙ ሳይደርቅ እንዲህ አይነት በደል ለምን ይሰርስብኛል ብሎ ተቆጣ፤ መቆጣቱ ትክክል ነው።

የእሱ (የልዩ ኃይሉ) አመራሮች ግን ተወያይተዋል። እኔ እራሴ ባለሁበት፣ ክቡር ምክትል ፕሬዜዳንቱ ባሉበት፣ የሀገሪቱ ምክትል ኢታማዦር ሹም ባሉበትና ሌሎች አካላት ባሉበት የሁሉም የአማራ ክልል የ21ዱ ዞንና ከተማ አስተዳደሮች የመንግሥት እና ፖለቲካ አመራሮች፣ የፀጥታ ' ሚኒ ካቢኔ ' በተለምዶ ይሄ አካል በተሳተፈበት ውይይት ተካሂዷል። "

(ሙሉ ቃለምልልሱ ከላይ ተያይዟል)

Video:AMC (196 MB)

@EBS_TV_NEWS
217 views15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 14:31:08 #SpecialForce
" ሂደቱ ከትጥቅ ማስፈታት ጋር የሚገናኝ አይደለም " - ወ/ሮ ሰለማዊት ካሳ
መንግሥት እያካሄደ ያለው የልዩ ኃይል አባላትን መልሶ የማደራጀት መርሃ ግብር ትጥቅ ከማያስፈታት ጋር እንደማይገናኝ አሳወቀ።
የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ፤ " የሁሉንም ክልል ልዩ ኃይል አባላት መልሶ የማደራጀት ስራ ነው የሚሰራው እንጂ ሂደቱ ከትጥቅ ማስፈታት ጋር የሚገናኝ አይደለም " ብለዋል።
የተጀመረው መልሶ የማደራጀት ሂደት የሀገር ሉዓላዊነትን ከማስጠበቅ፣ ከሀገር ውስጥ ሆነ ከውጭ የሚሰነዘርን ማንኛውም አይነት ጥቃት ከመከላከል አንፃር ጠንካራ የመከላከያ ኃይል ለመገንባት የሚያስችል ዕድል ነው ሲሉ ገልጸዋል።
" ህወሓትን በተመለከተ ፤ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ትጥቅ የመፍታት ሂደቱ ያለማወላወል የሚፈፀም ነው " ያሉት ወ/ሮ ሰላማዊት " ሂደቱ ከሌሎች ሀገራዊ እቅዶች ጋር የሚገናኝ አይደለም / የሚጣረስም አይደለም እራሱን ችሎ በራሱ መርሀግብር የሚከናወን ነው " ሲሉ አስረድተዋል።
ይህንን ሂደት ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች እየተከታተሉት መሆኑ መታወቅ አለበት ሲሉ አክለዋል።
ወ/ሮ ሰላማዊት የክልል ልዩ ኃይል አባላትን መልሶ ማደራጀት " በሁሉም ክልሎች በተመሳሳይ ወቅት እየተተገበረ ያለ ነው " ያሉ ሲሆን ሂደቱ በጥንቃቄ እና በጋራ መግባባት እየተመራ ያለ ነው ሲሉ አሳውቀዋል።
በሂደቱ በሁሉም ክልሎች ሰላም እና ደህንነትን ለማረጋገጥ በተለይ የፀጥታ ስጋት / የማህበረሰብ ጥያቄ ያለባቸው ቦታዎች ላይ ሀገር መከለከያ ሰራዊት ሁሉም ቦታዎች ስምሪት ወስዶ እየተንቀሳቀሰ ነው በዚህ ረገድ ክፍተት አይፈጠርም ብለዋል።
እየተካሄደ ባለው የመልሶ ማደራጀት ስራ በልዩ ኃይል ውስጥ ያሉ አባላት እንደምርጫቸው / እንደ ፍላጎታቸው ፦- በሀገር መከላከያ ሰራዊት
- በፌዴራል ፖሊስ- በክልል ፖሊስ አባልነት መካተት ይችላሉ ተብሏል።
ወደነዚህ የፀጥታ መዋቅሮች የሚቀላቀሉት ትጥቃቸውን እንደያዙ መሆኑ ተመላክቷል።
በዚህ ውስጥ መካተት የማይፈልጉ የልዩ ኃይል አባላት መብታቸው እንደሚጠበቅ እና ወደ መደበኛ ሲቪል ህይወት እንደሚገቡ መንግሥት የማቋቋም ስራ እና ድጋፍም እንደሚያደርግ ገልጿል።
@Ebs_tv_news
1.2K views11:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 11:24:43 #NewsAlert
ዶ/ር ጫላ ዋታ ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ።
የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት የነበሩት ዶ/ር ጫላ ዋታ የመንግስት ግዥ ህግ ከሚፈቅደው አሰራር ውጭ በሰሩት ስራ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቷል።
ምክር ቤቱ በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ነው ያለመከሰስ መብታቸው የማንሳት ውሳኔን ያፀደቀው።
አንድ ድምፀ ተአቅቦ ያደረጉት እራሳቸው ዶ/ር ጫላ ዋታ ናቸው።
(ዝርዝር ይኖረናል)
@EBS_TV_NEWS
1.9K views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ