Get Mystery Box with random crypto!

#Repost የካራማራ ድል ! የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ/ም የሱማሊያን ዚያድባሬ ጦር ለመመከት | EBS TV NEWS

#Repost

የካራማራ ድል !

የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ/ም የሱማሊያን ዚያድባሬ ጦር ለመመከት በካራማራ ጀግኖች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የህይወት መሰዋዕትነት ከፍለው ወራሪውን ጦር ከሀገር ያባረሩበትና የሀገራቸውን ሰንደቅ ያውለበለቡበት ቀን ነው።

ዘንድሮ ይህ ድል 45ኛ አመት ሞልቶታል ቀኑም እየታሰበ ነው።

ከጦርነቱ በፊት ለረጅም ጊዜ የሶማሊያ ጦር በሶቪዬት ኅብረት ይደገፍ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ ከአሜሪካ ጋር ወዳጅነት ነበረው። በወቅቱ አሜሪካ እና የሶቪየት ህብረት በቀዝቃዛ ጦርነት ውስጥ ነበሩ።

በቅድሚያ በሶቪየት ህብረት ከፍተኛ ድጋፍ የመጣው የዚአድባሪ ጦር የእናት ሀገር ጥሪ እያለ በተሰበሰበው የኢትዮጵያ ጦረኛ ካራማራ ላይ ድባቅ ተመትቶ ወደ መጣበት ተመልሶል፡፡

በጦርነቱ መጀመሪያ ሶማሊያን ስትደግፍ የነበረችው  ሶቪየት ህብረት ወደ ኢትዮጵያ አዘንብላ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ እገዛ አድርጋለች ፤ አሜሪካ ደግሞ ወደ ሶማሊያ ፊቷን አዙራለች።

በጦርነቱ ኩባ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ የመንና ምሥራቅ ጀርመንን ጨምሮ ሌሎች አገራት አጋርነታቸውን ለኢትዮጵያ አሳይተዋል።

ከ16 ሺ በላይ የኩባ ወታደሮች በውጊያው እንደተሳተፉ መዛግብት ያሳያሉ። ደቡብ የመንም ጦሯን ለኢትዮጵያ አሰልፋ ነበር።

በተለያየ የፖለቲካ የትግል ሁኔታ፣ በተለያየ ቅራኔ ውስጥ የነበሩ የኢትዮጵያ ሀይሎች ሁሉ ስለ ሀገር አንድ ሆነው የዚያድባሬን ጦር የመከቱበት የካራማራ ጦርነት የኢትዮጵያ አንድነት ዳግም በጉልህ የታየበት ስለመሆኑ ይነገርለታል፡፡

በየአመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰበው የ " ካራማራ ድል " ዘንድሮም ለ45ኛ ጊዜ እየታሰበ ይገኛል፡፡

@EBS_TV_NEWS