Get Mystery Box with random crypto!

' ሰላተል ኢስትስቃ ' ነገ በመላ ሀገሪቱ 'ሰላተል ኢስ ትስቃ' እንዲሰገድ  የኢትዮጵያ  እስልም | EBS TV NEWS

' ሰላተል ኢስትስቃ '

ነገ በመላ ሀገሪቱ "ሰላተል ኢስ ትስቃ" እንዲሰገድ  የኢትዮጵያ  እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ጥሪ አቅርቧል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቦረና ዞን በዝናብ እጥረት ምክንያት የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ  " ሰላተል ኢስ ትስቃ " እንዲሰገድ ለመላው ምዕመን ጥሪ አድርጓል።

ነገ ሰኞ በመላው ሀገሪቱ እንዲሰገድ ጥሪ የቀረበው " ሰላተል ኢስትስቃ " ዝናብ በሚርቅበት ጊዜ የሚሰገድ ሰላት መሆኑን ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በሌላ በኩል ፤ ጠቅላይ ም/ቤቱ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን ዕርዳታ የሚውል ድጋፍ ማሰባሰቢያ የባንክ ቁጥሮችን ይፋ አድርጎ ድጋፍ እያሰባሰበ እንደሆነ ተሰምቷል።

ጠቅላይ ም/ቤቱ ይፋ ያደረጋቸው የባንክ ቁጥሮች ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሣብ ቁጥር 5582 ፣ ዳሸን ባንክ ሂሣብ ቁጥር 795571270973፣ ዘምዘም ባንክ ሂሣብ ቁጥር 222255፣ ሂጅራ ባንክ ሂሣብ ቁጥር 308010 ፣ ኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ቁጥር 1000093406226 ናቸው።

@EBS_TV_NEWS