Get Mystery Box with random crypto!

' በብሔራዊ ፈተናው ከ600 በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲ ወጪ እንሸፍናለን ' - አማ | EBS TV NEWS

" በብሔራዊ ፈተናው ከ600 በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲ ወጪ እንሸፍናለን " - አማራ ባንክ

በ2014 ዓም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው በመላ ሀገሪቱ ከ600 በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲ ወጪ እንደሚሸፍን አማራ ባንክ አሳውቋል።

ባንኩ በመላው ሀገሪቱ ከ600 በላይ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው በወር 750 ብር እየከፈለ እንደሚያስተምር የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሄኖክ ከበደ ገልጸዋል።

ይህ ውሳኔ የባንኩ የማኀበረሰባዊ አገልግሎት አካል መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ለአሚኮ ጠቁመዋል።

በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር እውቅናና ሽልማት ይሰጣቸዋል መባሉ ይታወሳል።

@EBS_TV_NEWS