Get Mystery Box with random crypto!

#Update የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰላም ስምምነት ተከትሎ በሽረ፣ አላማጣ እና ኮረም ከተማዎች | EBS TV NEWS

#Update

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰላም ስምምነት ተከትሎ በሽረ፣ አላማጣ እና ኮረም ከተማዎች በሚገኙ ቅርንጫፎቹ ከውጭ ሀገር እና ከሀገር ውስጥ የሚላኩ ገንዘቦችን የመቀበል እንዲሁም ገንዘብ የማስቀመጥ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ዛሬ ምሽት አሳውቋል።

ባንኩ በቀጣይ ሁኔታዎች እንደፈቀዱ አገልግሎቱን በማስፋትና በየደረጃው በሁሉም ቅርንጫፎች ላይ አገልግሎት ለማስጀመር እንደሚሰራ ገልጿል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል በነበረው ጦርነት ሳቢያ ለበርካታ ወራት የትግራይ ክልል አካባቢዎች የባንክ አገልግሎት ማግኘት ሳይችሉ እንደቀሩ ይታወቃል።

@EBS_Tv_News