Get Mystery Box with random crypto!

EBS TV NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebs_tv_news — EBS TV NEWS E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebs_tv_news — EBS TV NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ebs_tv_news
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.53K
የሰርጥ መግለጫ

BREAKING NEWS ABOUT WORLD!!!

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-06-19 07:40:46
#DiamondLeague #Paris2022

በፈረንሳይ #ፓሪስ የዳይመንድ ሊግ ውድድር በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ውድድር ኢትዮጵያዊው ሰለሞን ባረጋ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ፤ ሌላው ኢትዮጵያዊ ሙክታር እድሪስ በሶስተኛ ደረጃ አጠናቋል።

@EBS_TV_NEWS
8.3K views04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 09:16:05 ተፈትኖ የወደቀው ፌስቡክ

ፌስቡክ ፤ በኢትዮጵያ ሶስት ብሔሮች ላይ ያነጣጠሩ #የጥላቻ_ንግግሮች ያዘሉ ማስታወቂያዎች ይለይ እንደሆነ የተሰጠውን ፈተና መውደቁ ተሰምቷል።

ፌስቡክን የሙከራ ማስታወቂያዎችን በመጠቀም የፈተኑት " ግሎባል ዊትነስ " እና " ፎክስ ግሎቭ " የተባሉ ሁለት ተቋማት ከቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት መምህር ዳግም አፈወርቅ ጋር በመተባበር ነው። 

ምርመራው የተከናወነው የፌስቡክ የጥላቻ ንግግር መለያ ምን ያህል ጥሩ እንደሆነ ለመፈተን እና የኩባንያው የደህንነት መቆጣጠሪያ ስልቶች ሁከት የሚያባብሱ ማስታወቂያዎችን መከላከል ይችል እንደሁ ለመፈተሽ ነበር።

በአማርኛ ቋንቋ በፌስቡክ የተጻፉ 12 የከፉ የጥላቻ ንግግሮችን የለዩት ምርመራ አድራጊዎቹ እነዚሁኑ ይዘቶች ለኩባንያው እንደ ማስታወቂያ በማቅረብ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴው ለመለጠፍ ይፈቅድላቸው እንደሁ ሙከራ አድርገዋል።

የኩባንያውን የቁጥጥር አቅም ለመፈተሽ በምሳሌነት የተመረጡት የጥላቻ ንግግሮች የተካተቱባቸው ማስታወቂያዎች፤ የአማራ፣ የትግራይ እና የኦሮሞ ብሔሮች ላይ እኩል ያነጣጠሩ ናቸው።

በማስታወቂያዎቹ አረፍተ ነገሮች መካከል " ሰዎች እንዲገደሉ፣ እንዲራቡ ወይም ከአንድ አካባቢ እንዲጠፉ በቀጥታ ጥሪ የሚያደርጉ፤ ሰዎችን ከእንስሳት ጋር የሚያነጻጽሩ እና ሰብዓዊነት የጎደላቸው” ገለጻዎች እንዳሉበት ተገልጿል።

አብዛኞቹ የማስታወቂያዎቹ ይዘቶች የዘር ማጥፋት እንዲፈጸም ጥሪ የሚያቀርቡ መሆናቸውም ተገልጿል። ከእነርሱ ውስጥ አንዳቸውም ለመተርጎም ውስብስብ እንዳልነበሩ ተመላክቷል።

ግሎባል ዊትነስ ፤ " የትኞቹንም ማስታወቂያዎች አላተምናቸውም። የሚታተሙበትን ቀን ወደ ፊት እንዲሆን በማድረግ፤ ፌስቡክ ማስታወቂያዎቹን መቀበል እና አለመቀበሉን ካሳወቀን በኋላ አጥፍተናቸዋል " ብሏል።

የጥላቻ ንግግሮቹ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴው ለህዝብ ይፋ አለመደረጋቸውን አረጋግጧል።

በምርመራው መሰረት ፌስቡክ የቀረበሉትን 12ቱንም የጥላቻ ንግግሮች በማስታወቂያ መልክ በገጹ እንዲቀርቡ ፈቃድ ሰጥቷል።

ሁሉም ማስታወቂያዎች ፌስቡክ በአጠቃቀም መመሪያው (community standards) የጥላቻ ንግግር ብሎ ከሚበይናቸው ውስጥ የሚካተቱ ናቸው።

በሙከራ ደረጃ ፌስቡክ የተፈተነባቸው ማስታወቂያዎች በማህበራዊ መገናኛ ዘዴው ላይ ለዕይታ ቢበቁ ኖሮ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከ57 አመታት በፊት የጸደቀውን ስምምነት የሚጥሱ ነበሩ።

ስምምነቱ ማናቸውም አይነት የዘር መድሎዎ ለማስወገድ የጸደቀ ነው።  

በድርጅቶቹ ምርመራ የተገኘው ውጤት በስተመጨረሻ የቀረበለት ፌስ ቡክ፤ ማስታወቂያዎቹ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴው እንዲታተሙ መፈቀድ እንዳልነበረበት ማመኑን ግሎባል ዊትነስ አሳውቋል።

ፌስቡክ ለኢትዮጵያ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች የደህንነት ቁጥጥሩን ለማጥበቅ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን መግለጹንም ምርመራውን ካከናወኑት ድርጅቶች አንዱ የሆነው ግሎባል ዊትነስ አመልክቷል።

@Ebs_tv_news
10.9K views06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 21:48:09
#ETHIOPIA

ሀገራችን #ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር ያደረገችውን ፍልሚያ በማሸነፏ ፤ ማላዊ ደግሞ በጊኒ በመሸነፏ ምድቧን #በአንደኛነት መምራት ጀምራለች።

ጊኒ እና ማላዊ ያደረጉት ጨዋታ ጊኒ 90+1' ላይ በሊቨርፑሉ ተጫዋች ኬታ ባስቆጠረችው ጎል 1 ለ 0 ማሸነፍ ችላለች።

@EBS_T_NEWS
8.0K views18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 14:17:01
#ETHIOPIA

በኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር የኢትዮጵያ ሰብዓው መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን “በፌደራል መንግስት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል” ዳግም እየተካረረ የመጣው የጦርነት ስጋት እንዳሳሰበው ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

ተቋሙ በመግለጫው እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ አሳስቧል።

ከ19 ወራት በፊት በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በርካቶች ለተለያዩ አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደተጋለጡ ያወሳው ኢሰመኮ አሁንም ዳግም ወደ ጦርነት ለመግባት እያደገ የመጣው መካረር ሊቆም እንደሚገባ ገልጿል።

ጦርነቱ በአፋር፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች ለከፋ እንግልት እንዲዳረጉ፣ የሚወዷቸውን ሰዎች እንዲያጡ፣ ህይወታቸውን በእርዳታ ላይ እንዲመሰረቱ፣ መሰረታዊ የዜጎች አገልግሎቶችን እንዲነፈጉ እና የሌሎችን ጉዳቶችን እያስተናገዱ እንደሚገኙም ተቋሙ ከዚህ በፊት ባደረኳቸው ተደጋጋሚ ምርመራዎች አረጋግጫለሁ ብሏል።

የፌደራል መንግስትን ጨምሮ የሰሜን ኢትዮጵያ ሶስቱ ክልሎች ዋነኛ ትኩረት ሊሆን የሚገባው በጦርነቱ ለተጎዱ ዜጎች ያለምንም ገደብ የሰብዓዊ መብት ድጋፎች እንዲደርሱ ማድረግ እንደነበርም ኢሰመኮ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል።

ከዚህ በፊት በተካሄደው ጦርነት ለተጎጂዎች ተገቢውን ድጋፍ ሳይደረግ፣ በሁሉም በኩል ያሉ አጥፊዎች ሳይጠየቁ፣ የወደሙ መሰረተ ልማቶች ሳይጠገኑ እና ሌሎች አስፈላጊ ስራዎች መከናወን እያለባቸው ወደ ሌላ ጦርነት መገባት እንደሌለበት ገልጿል።

ያንብቡ ፦ telegra.ph/EHRC-05-15

ምንጭ፦ አልዓይን / ኢሰመኮ

@EBS_TV_NEWS
13.5K views11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 14:33:04
#Update

የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆኗል።

ትምህርት ሚኒስቴር የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ አድርጓል።

የ2013 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች ምደባ ተደርጓል።

ከዚህ በፊት በተገለጸዉ የመቁረጫ ነጥብ እና ከኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋርና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተጨማሪ ተማሪዎች ምደባ የሚያስገኝላቸው ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለማየት በድህረገፅ፡-https://result.ethernet.edu.et ፣ በSMS፡- 9444 እንዲሁም በቴሌግራም፡- @moestudentbot መጠቀም ይችላሉ።

ተማሪዎች ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችው ማንኛውም ጥያቄ በድህረገፅ https://complaint.ethernet.edu.et በማመልከት ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ሚያዝያ 24/2014 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@EBS_TV_NEWS
14.3K views11:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 13:53:43
በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

በዓሉን ስናከብር ፤ የተቸገሩ ወገኖቻንን አለንላችሁ በማለት ፣ የወደቁትን በማንሳት ፣ በሀዘን ላይ ያሉ ወገኖችን በማፅናናት፣ ከክፉ ድርጊት እና ሀሳብ ርቀን ሊሆን ይገባል።

በዚህ የትንሳኤ በዓል ፤ በሰላም እጦት ፣ በግጭት ፣ በድርቅ ክፉኛ የተጎዱ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በገዛ ቄያቸው ከሞቀው ቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የወደቁትን፤ በፀሃይና ዝናብ የሚንከራተቱትን ፤ የተቸገሩትን ፣ የሚወዱትን ተነጥቀው በጥልቅ ሀዘን ላይ የሚገኙትን ፣ ታመው በየሆስፒታሉ የተኙትን ፣ በየሰው ሀገር በስደት ስቃያቸውን እያዩ ያሉ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በግልም ፤ በሀገርም ላለብን ችግር ሁሉ አምላክ መፍትሄ እንዲያበጅልን እየተማፀንን እንድናሳልፍ አደራ እንላለን።

የሰላም፣ የመተሳሰብና የበረከት በዓል ያድርግልን !
ፈጣሪ ሀገራችን ሰላም ያድርግልን ፤ በምድር ላይ ያሉ የሰው ልጆችን ሁሉ ይጠብቅልን።

መልካም በዓል !


@EBS_TV_NEWS
10.4K views10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 20:37:23
#BalderasParty

አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎችም የባልደራስ አመራሮች አርባ ምንጭ ከተማ መታሰራቸውን ፓርቲው አስታወቀ።

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ፕሬዝዳንቱ አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው አመራሮች በፖሊስ እንደታሰሩበት አስታውቋል።

ፓርቲው አመራሮቹ የታሰሩበት አርባ ምንጭ ከተማ መሆኑን ገልጿል።

አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎችም የፓርቲው ልዑካን ዛሬ ወደ አርባምንጭ ያቀኑ ሲሆን ወደ አርባ ምንጭ የሄደቱ በደቡብ ክልል የፓርቲውን የሀገር አቀፍ ፊርማ ንቅናቄ ለማስጀመር እንደሆነ ተገልጿል።

ፓርቲው የፊርማ አሰባሰቡን ንቅናቄ ለማስጀመር በአርባ ምንጨ እና በወላይታ ሶዶ ህዝባዊ ስብሰባዎች ለማድረግ ጠይቆ ከተፈቀደ ቦኃላ፣ " ከበላይ የመጣ ትዕዛዝ ነው " በሚል ስብሰባዎቹ እንዳይደረጉ እንደተከለከሉበት አስረድቷል።

ከዚህ በኃላ ነው ፓርቲው ፕሬዜዳንቱን ጨምሮ ወደ አርባ ምንጭ የሄዱት ልዑካን በፖሊስ መታሰራቸውን ያሳወቀው።

ባልደራስ እስሩ ያለምንም ምክንያት የተፈፀመ ነው ብሏል።

@EBS_TV_NEWS
10.4K views17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-17 09:10:31 ታላቅ የምስራች ለኢትዮጵያውያን በሙሉ

#ሳፋሪኮም

በመጀመሪያ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት በተደረገልን ግብዣና መልካም አቀባበል ትልቅ ምስጋናን እያቀረብን ድርጅታችን የማህበረሰባችንን የዘመናዊ የቴሌኮም ችግርን ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሚጠበቅበትን ሀላፊነት ለመወጣት 10 ሚሊየን ብር በጀት ልዩ የሆነ "ቤተሰባችንን ይቀላቀሉ Program " ጀምረናል

በዚህም መሰረት የቴሌግራም ቻናላችንን ለሚቀላቀሉ እና ወደ ግሩፓችን ዘመድ ወዳጆቻቸውን ለሚጋብዙ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ልዩ የሆነ ሽልማት ተዘጋጅቷል።

1ኛ = ለ5,000 ሰዎች ለእያንዳንዳቸው 400 ብር የሞባይል ካርድ እና ያልተገደበ የ1 ወር ነፃ የስልክና የዳታ ጥቅል።

2ኛ = ለ4000 ሰዎች ለእያንዳንዳቸው ያልተገደበ የድምፅና የዳታ ጥቅል።

3ኛ = ለ2000 ሰዎች ለእያንዳንዳቸው የ1 ወር 4GB የኢንተርኔት ጥቅልና የ1000 ደቂቃ ጥቅል።

4ኛ = ለ1000 ሰዎች ለእያንዳንዳቸው የ2GB የኢንተርኔት ጥቅልና የ500 ደቂቃ ጥቅል።

5ኛ = ለ500 ሰዎች ለእያንዳንዳቸው የ1GB የኢንተርኔት ጥቅልና የ250 ደቂቃ ጥቅል ለመስጠት ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል።

........ ⓢⓐⓕⓐⓡⓘⓒⓞⓜ.........

ይሳተፉ

ልብ ይበሉ፦ በእድሉ ተጠቃሚ ለመሆን እነዚህን 3 መንገዶች በጥንቃቄ ይከተሉ።

1. ከታች በሚገኘው ማስፈንጠሪያ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

@safaricom_ethiopia1
2. በመቀጠል ይህንን መልዕክት ለ50 ሰዎች ያስተላልፉ።

3. ከዚያም በመወያያ ግሩፓችን ላይ ከ100 ሰዎች በላይ Add በማድረግ ያስገቡ። ይህ ለሽልማቱ እጩ የሚያደርግዎት መስፈርት ነው።

@Safaricom_official
4. በመጨረሻም ስልክ ቁጥሮትን ከታች ባለው የደንበኞች ሽልማት ማስተላለፊያ አካውንት ስልክ ቁጥሮትን በመላክ ሽልማቶት ይደርሶታል።

@SAFARI_ADMIN1

ይሳተፉ። መስፈርቱን በማሟላት የሽልማቱ ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡

Safaricom Official
10.6K views06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-13 21:30:52
#EthioTelecom #SafaricomEthiopia

ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሰረተ ልማት መጋራት እና ትስስር ላይ ያደጉት ዘርፈ ብዙ ድርድሮች በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ተገልጿል።

በቅርቡ በኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም መካከል ስምምነት ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኢትዮ ቴሌኮም የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በሌላ በኩል ፥ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሚያዚያ 1 /2014 አገልግሎት ለመጀመር እቅድ እንደነበረው ከዚህ በፊት መግለፁ ይታወሳል፤ ነገር ግን በተባለው ቀን አገልግሎት ያልጀመረ ሲሆን በቅርቡ አገልግሎት እንደሚጀምር ይጠበቃል።

@EBS_TV_NEWS
9.1K views18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-12 12:38:15
#Afar

" በእሳት አደጋው 160 የሚጠጉ ሱቆች እና የመኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " - ሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ

በአፋር ክልል ሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ በድንገት በተከሰተ የእሳት ቃጠሎ በግምት ከ160 በላይ የሚጠጉ ሱቆች እና መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውን የወረዳው አስተዳድር አሳውቋል።

የሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ አስተዳድር አቶ ሀሰን ሀንዲ ለአፋር ብዙሀን መገናኛ በሰጡት ቃል ፤ " የእሳት ቃጠሎ አደጋው የደረሰው ወደ 10 : 00 ሰዓት አካባቢ በድንገት ከቢንዝል መሸጫ ቤት በተነሳ እሳት ነው " ብለዋል።

በድንገተኛው የእሳት አደጋ ምክንያት የደረሰው ውድመት ወደፊት የሚጣራ ሁኖ በግምት ግን ከ80 በላይ መኖሪያ ቤቶች እንደዚሁም ወደ 80 ሊጠጋ የሚችል የተለያዩ የንግድ ሱቆች ወድመዋል።

በእሳት አደጋው በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ አሳውቀዋል።

በአካባቢው ላይ ከፍተኛ ንፋስ መኖሩ እና የውሀ እጥረት በመኖሩ ቃጦሎው በፍጥነት በመባባሱ ምክንያትም እሳቱን ለመቆጣጠር ባለመቻሉ ከፍተኛ ውድመት መከሰቱን አስተዳዳሪው አስረድተዋል።

ለተጎጂዎቹ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግም ጥሪ አቅርበዋል።

በብዛት የቢንዚል ሽያጭ ከሚከናወንበት ቦታም በቀላሉ የእሳት አደጋ እየተፈጠረ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቂ ሊደረግ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

መረጃው የአፋር ብዙሀን መገናኛ ድርጅት ነው።

@EBS_TV_NEWS
9.0K views09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ