Get Mystery Box with random crypto!

#ETHIOPIA በኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር የኢትዮጵያ ሰብዓው መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ | EBS TV NEWS

#ETHIOPIA

በኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር የኢትዮጵያ ሰብዓው መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን “በፌደራል መንግስት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል” ዳግም እየተካረረ የመጣው የጦርነት ስጋት እንዳሳሰበው ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

ተቋሙ በመግለጫው እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ አሳስቧል።

ከ19 ወራት በፊት በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በርካቶች ለተለያዩ አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደተጋለጡ ያወሳው ኢሰመኮ አሁንም ዳግም ወደ ጦርነት ለመግባት እያደገ የመጣው መካረር ሊቆም እንደሚገባ ገልጿል።

ጦርነቱ በአፋር፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች ለከፋ እንግልት እንዲዳረጉ፣ የሚወዷቸውን ሰዎች እንዲያጡ፣ ህይወታቸውን በእርዳታ ላይ እንዲመሰረቱ፣ መሰረታዊ የዜጎች አገልግሎቶችን እንዲነፈጉ እና የሌሎችን ጉዳቶችን እያስተናገዱ እንደሚገኙም ተቋሙ ከዚህ በፊት ባደረኳቸው ተደጋጋሚ ምርመራዎች አረጋግጫለሁ ብሏል።

የፌደራል መንግስትን ጨምሮ የሰሜን ኢትዮጵያ ሶስቱ ክልሎች ዋነኛ ትኩረት ሊሆን የሚገባው በጦርነቱ ለተጎዱ ዜጎች ያለምንም ገደብ የሰብዓዊ መብት ድጋፎች እንዲደርሱ ማድረግ እንደነበርም ኢሰመኮ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል።

ከዚህ በፊት በተካሄደው ጦርነት ለተጎጂዎች ተገቢውን ድጋፍ ሳይደረግ፣ በሁሉም በኩል ያሉ አጥፊዎች ሳይጠየቁ፣ የወደሙ መሰረተ ልማቶች ሳይጠገኑ እና ሌሎች አስፈላጊ ስራዎች መከናወን እያለባቸው ወደ ሌላ ጦርነት መገባት እንደሌለበት ገልጿል።

ያንብቡ ፦ telegra.ph/EHRC-05-15

ምንጭ፦ አልዓይን / ኢሰመኮ

@EBS_TV_NEWS