Get Mystery Box with random crypto!

የቤት ማፍረስ ዘመቻው ቀጥሏል። አዲስ በተመሰረተው ሸገር ከተማ አሁንም የቤት ፈረሳ ዘመቻው መቀጠሉ | EBS TV NEWS

የቤት ማፍረስ ዘመቻው ቀጥሏል።
አዲስ በተመሰረተው ሸገር ከተማ አሁንም የቤት ፈረሳ ዘመቻው መቀጠሉን የየአካባቢው ነዋሪዎች እየገለፁ ይገኛሉ።
መንግሥት ቤቶችን እያፈረሰ የሚገኘው " ህገወጥ ነው " በሚል እንደሆነ ከዚህ ቀደም ገልጿል።
ቤት እየፈረሰባቸው ያሉ ወገኖች ስለጉዳዩ ምን ይላሉ ?
⮕ በርካታ ቤቶች ናቸው እየፈረሱ ያሉት፤ እነዚህ ቤቶች ከገበሬ የተገዙ እና ረጅም ዓመታት ጭምር ሰዎች ሲኖሩባቸው የነበሩ ናቸው።
⮕ ከፈረሱት ቤቶች ውስጥ ዜጎች ለዓመታት ለፍተው የሰሯቸው ይገኙበታል።
⮕ ምትክ ቦታ/ ማረፊ ሳይመቻች ነው ሜዳ ላይ የተጣልነው።
⮕ መንግስት ዛሬ ላይ ህገወጥ ነው እያለ የሚያፈርሰው ቤቶቹ ሲገነቡና ይህን ሁሉ ዓመት ሲኖርባቸው የት ነበር ?
⮕ በአንዳንድ ቦታዎች ቤት የሚፈርሰው በለሊት ጭምር ነው፤ ሰዎች በተኙበት ምንም ሳይዘጋጁ እንዲፈርስባቸው ይደረጋል።
⮕ እየፈረሱ ካሉት ቤቶች መካከል አንዳንዶቹ የመብራት የውሃ ክፍያ፣ የአፈር ግብርም የፈፀሙ ናቸው።
⮕ ከቤት ማፍረስ ዘመቻው ጋር በተያያዘ አንዳንድ ቤቶችን ማንነትን/ ብሔርን ለይቶ ማፍረስም ይስተዋል።
⮕ የሰብዓዊነት ጉዳይ ጭራሽ ከምንም የማይቆጠርበት ሁኔታ ነው እየተፈጠረ ያለው ፤ ነፍሰ ጡር እና በእድሜ የገፉ እናቶች እንዲሁም ህፃናትን ጨምሮ በርካቶች #ሜዳ ላይ ወድቀዋል። እቃ እንኳን እንዳይወጣ ላያቸው ላይ ቤታቸው ፈርሷል።
ስለሚፈርሱ ቤቶች ከዚህ ቀደም የከተማው ከንቲባ ዶ/ር ተሾመ አዱኛ ምን ምላሽ ሰጥተው ነበር (አንከር ለተሰኘ ሚዲያ)?
➣ የሚፈርሱት ለአንድ ከተማ ፀር የሆኑ ህገወጥ ግንባታዎች ናቸው።
➣ ህገወጥ ግንባታዎችን እናፈርሳለን ህጋዊ ከተማ መልክ እንዲይዝ እናደርጋለን።
➣ በአስተዳደር ችግር ፣ ጠንካራ የሆነ አስተዳደር በፊት አለመኖር ምክንያት የግንባታ እና የመሬት ባለቤትነት፣ የግንባታ ፍቃድ ሳይኖር መብራት ማውጣት ይሄ ስራ አሁን ከሚፈለገው የከተማ ሂደት ጋር የማይሆኑ ነገሮች ነው የተፈጠሩት እነሱ በመኖራቸው አይፈርሱም የሚል ሳይንስ የለም። አንድ ሰው በስርዓት ካርታ መውሰድ አለበት፣ በስርዓት የግንባታ ፍቃድ ማግኘት አለበት፣ የክልሉ ህግና ስርዓት ጠብቆ መሄድ አለበት እነዚህ ሳይሟሉ በራሳችን መዋቅር ድክመት / አሰራር መብራት ስላልስገባ / ውሃ ስላስገባ የማይፈርስ የለም። ያ እንደጥፋት የምናየው ከአሁን በኃላ መደገም የለበትም።
➣ ሰብዓዊነት እኛም ይሰማናል መታየት ያለበት ግን ህግ መከበር አለበት፤ እኛ ይሄንን ከጨረስን በኃላ በክልል ደረጃም ይሁን በከተማ ደረጃ አንድ ሰው ቤት ማግኘት ሰብዓዊ መብቱ ስለሆነ እኛ በምናወጣቸው ፕሮግራሞች አካተን ያለውን ችግር መፍታት እንችላለን።
➣ የምናፈርሰው ግልፅ የሆነ አንድ ዘመናዊ ከተማ ላይ እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎችን ታሳቢ በማድረግ ነው። ከእንቅፋቶቹ አንዱ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የመሬት ወረራ እና ህገወጥ ግንባታዎች ነው ይሄን መሰረት አድርገን ነው የምንሄደው (የግንባታ ፍቃድ የሌላቸው፣ በስርዓት መሬት ያልወሰዱ፣ ካርታ የሌላቸው) ይሄን ነው የምንከተለው ፈረሳው ብሄርን / ዘርን መሰረት ያደረገ አይደለም። ማንንም ዒላማ አድርገን አይደለም የምንሰራው።
➣ ቅደመ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል ፣ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ብቻ ሳይሆን ማህበረሰቡን አወያይተን ፣ ህገወጥ እንዳሆኑ ነገረን ፣ ህገወጥ ያደረጋቸው ምን እንደሆነ አስረድተን፣ ምልክት አድርገን ነው የምናፈርሰው ፤ በእኛ ሀገር ' ቤት ሰባቴ ካልፈረሰ ቤት አይሆንም ' የሚል የማይሆን አመለካከት ስላለ በአንድ በኩል አያፈርሱም ብለው ያስባሉ ቢፈርስም ትንሽ ዞር ሲሉ መልሰን እንገባበታለን የሚል ነገር አለ ስለዚህ እየነገርን እየታወቀ ነው ፈረሳው የሚደረገው።
@EBS_TV_NEWS