Get Mystery Box with random crypto!

♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹

የቴሌግራም ቻናል አርማ desupome — ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹
የቴሌግራም ቻናል አርማ desupome — ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹
የሰርጥ አድራሻ: @desupome
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.82K
የሰርጥ መግለጫ

☞ የስብህና ልቀት ለማምጣት ከመፃህፍት ጋር እናዉጋ
☞ በዚህ ቻናል ተወዳጅ የሆኑ ግጥሞችንና አስተማሪ ታሪኮችን ይቀርቡበታል
ለሃሳብ አስተያዬታች
@Almnu6
@Almnu6
መነጋገር ይቻላል
ገጣሚ ማለት በአጭረር አነጋገር እረጅም ሃሳብን መግለፅ ነዉ፡፡

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-21 14:10:08 የቀድሞው የዙምባቤ ፕሬዚዳንት #ሮበርት ሙጋቤ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር ፦ "የአፍሪካ የትምህርት ስርዓት አስገራሚ ውጤቶች አሉት ።" ካሉ በኋላ

አንደኛ ደረጃ የሚይዙ ቀለሜና ጎበዝ ተማሪዎች ጥሩ ውጤት አምጥተው #ኢንጂነሪንግና #ሜዲሲን እንዲማሩ እድል ያገኛሉ ።

ሁለተኛ ደረጃ የሚይዙት ደግሞ #ህግና #ማኔጅመንት ነገር ተምረው አንደኛ ደረጃዎቹን ያስተዳድሯቸዋል ።

ዝቅ ብለው በሶስተኛ ደረጃ የሚገኙት ተማሪዎች ደግሞ #ፖለቲካ ውስጥ ይገቡና አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያሉትን ከላይ ሆነው ይቆጣጠራሉ ።

በትምህርት ውዳቂዎች ደግሞ #ፖሊስና #ወታደር ይሆናሉ ። እነዚህ ደግሞ ፖለቲከኞችን ይቆጣጠራሉ ደስ ያላላቸውን ፖለቲከኛ ደግሞ እስከ መግደል ድረስ ይደርሳሉ ።

ከሁሉም ከሁሉም ግን ምርጡ ጭራሽ ክላስም ሆነ ትምህርት ቤትም ገብቶ የማያውቀው ሰው ደግሞ #ነብይና #ጠንቋይ ይሆናል ። ይሄን ደግሞ ሁሉም ይከተሉታል ። ብለው ነበር ።

እኛስ በሃገራችን ያየነው ይህንን ነው ወይስ ሌላውን ነው ?
═════════❁✿❁ ═════════
360 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 21:06:45 አለማየው ገላጋይ (በእውነት ስም)

" ውትድርና ሌላ ሳይሆን የመታዘዝ አዙሪት ነው። የአለቃህ አለቃህ ያዘዋል። እሱም ታዞ ነው። እሱም አንተን ያዝሀል ጥሩ ፣ አንተ ደግሞ ያንን ትዕዛዝ ለሚፈፅሙ ሰዎች ታደርሳለህ። መታዘዝ በስንት ጣዕሙ ፣ ጥሩ ያዘዝከው ባዘዝከው መሰረት ሄዶ ህይወቱን ሊያጣ ይችላል፣ አካሉ ሊጎድል ይችላል፣ አንዳንዴ የሞት ፍርድ ትሰጣለህ። በፈንጂ እንዲረማመድ ትዕዛዝ ታስተላልፍለህ.! ያንተ ፀፀት ከሰውዬው ሞት ይከፋል ......"

" የአንዳንድ ጥያቄዎች መልሳቸው መተው ብቻ የሚሆንበት ጌዜ አለ። የሰው ልጅ ሁሉ እጣ ፈንታችንን የሚጠቅመንና፣ የማይጠቅመንን የምንደርስበትንና የማንደርስበትን ማሰብ ሆኗል። ከጠቀመን ጥሩ! ካልጠቀመን መተው! ከደረስንበት ጥሩ ካልደረስንበት ለሚደርስበት ትውልድ መተው ... የሰው ልጅ ውስንና ፍፁምነት የሚጎለው ፍጡር መሆኑን መገንዘብ "

" መፀሀፍት ለጥያቄዎችህ ቀጥተኛ ምላሽ ባይኖራቸው እንኳን የማሰብ ልምምድህን በማፍጠን የጥያቄህን ምላሽ እራስ እንድታገኘው ያግዙሃል።

"የሴት ጣውንትዋ ሌላ ሴት ከመሰለችህ ተሳስተሀል። ወዳጄ የሴት ጣውንትዋ ባልዋ የሚወደውና ቀልብን የሰጠው ነገር ሁሉ ነው ። ልብ በል ፤ ሌላው ቀርቶ ልጅህን እንኳን ከወደድክ የገዛ ልጇን ወደ ጣውንትነት ትቀይራለች ። "
402 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 20:33:01 ሰላም ውድ የቻናሌ አብራኮች እስኪ የቻናል ማስታወቂያ እንሰራ በሚቀጥለው አዲስ አመት 5k እንሙላ ስለዚህ በናንተ በኩልም የምታግዙት ነገር አለ እስኪ እኔ አለሁ የሚል
368 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 06:50:12 አቋራጭ ሲፈትሽ ፥ ኑሮን ለማሸነፍ
ጠጠር ቋጥኝ ሆኖ ፥ ከእግሩ ሥር ሲወተፍ
ማፍቀር መውደድ ሲሻ ፥ ተፈቅሮ ተወዶ
ከአፍቃሪ ከወዳጅ ፥ ሲደርስ የጥል መርዶ
ቀኑ ጭልም ሲል ፥ ፀሐይ በጧት ወጥታ
ሊስም የቀረበ ፥ በጥፊ ሲመታ
ልብን ሲቃ ይዟት ፥ ዓይን እንባ ሲያዘራ
ከሰው ወዲያ ለሰው ፥ ማን አለ እሚራራ?
ተፃፈ ደሱ ለተጨማሪ መሳጭ ግጥሞችና አባባሎች

https://t.me/Desupome/764
https://t.me/Desupome/764
395 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 03:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 22:19:48 ነው፡፡ የንጋት ወጋገን ሲፈናጠቅ ልጆች በከባድ ድምጽና በጅራፍ ጩኸት የሚታጀብ፣ በገደላገደል ስር እንዲያስተጋባ ተደርጎ ብዛት ባላቸው ህጻናት በከፍተኛ ድምጽ የሚዘመር ነው ቡሄ ። የጅራፉ ጩኸትም እግዚአብሔር አብ “የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት” ሲል ሐዋርያት ራሳቸውን ስተው የወደቁበትን የመለኮት ድምፅ ለማስታወስ ነው፡፡

ደብረታቦር ወይም ቡሄ በአብነት ተማሪዎች “ስለ ደብረ ታቦር" እያሉ እህል፣ ፣ ለምነው ጠላውን ጠምቀው፣ ዳቦውን ጋግረው፣ ቆሎውን ቆልተው ለደብረ ታቦር ዕለት ሊያስቀድሱ የመጡትን ምዕመናን በመጋበዝ በታላቅ ድምቀት ያከብራሉ፡፡ ይህ ትውፊት መምህረ ሐዋርያት የነበረው ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ተማሪዎቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ደብረ ታቦር ይዞ ሄዶ የተገለጠ ምስጢር ስለሆነ ከመምህራቸው ጋር በመሆን በዓለ ደብረ ታቦርን /ቡሄን ያከብራሉ፡፡ ስሙን ይጠራሉ፡፡

የበዓሉ እረዴት በረከት ይደርብን አሜን

ሼር በማድረግ ለሌላው ያዳርሱ ዘንድ በፍቅር እጠይቃለሁ
462 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 22:19:48 +++ ደብረ ታቦር (ቡሄ ) +++
❖❖❖

የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው ዘጠኝ ዓበይት የጌታ በዓላት አንዱ የደብረ ታቦር በዓል ነው። በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን የሚከበረው ይህ በዓል መሠረቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ደብረ ታቦር ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀመዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደ ፀሐይ የበራበት፣ ልብሱም እንደብርሃን ነጭ የሆነበት፣ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ነው።

ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ። እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር።

ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና፡ ተነሡ አትፍሩም አላቸው። ይህ የሆነው በደብረ ታቦር ነው ፡- ታቦር እንዴት ያለች ‘እግዚአብሔር የወደዳት’ ተራራ ናት? [ደብር ዘሠምሮ እንዲል] ሐዋርያትና ነቢያት በአንድነት ቆመው የሚተያዩባት ፤ ብሉይና ሐዲስ የተዋወቁባት ፤ ጥላና አካል የተጋጠሙባት ይህች ተራራ እንዴት የተመረጠች ናት? ‘ታቦርና አርሞናዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል’ እንደተባለ ነቢያትና ሐዋርያትን በግራ በቀኙ አድርጎ በሰማያዊ አባቱ ‘የምወደው ልጄ’ ተብሎ ሲጠራ ስሙን ሰምታ ታቦር ምንኛ ደስ ይላት ይሆን? የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት አጣን እንጂ ነቅለን ወደ ሀገራችን ከምናስገባቸው ተራሮች አንዱ ታቦር በሆነ ነበር፡፡

በታቦር ተራራ ሐዋርያትና ነቢያት በአንድ ወንበር ከሊቀ ሊቃውንት ክርስቶስ ትምህርት ተምረው ተመለሱ፡፡ ሐዋርያቱ የነቢያት ጌታ መሆኑን ሲማሩ ነቢያቱ ደግሞ የሐዋርያት አምላክ መሆኑን አወቁ፡፡ ነቢያት ደክመው የዘሩትን ከሚያጭዱ አጫጆች ሐዋርያት ጋር ተዋወቁ፡፡
ነቢያት አምላክነቱን ያውቃሉ ፤ ሐዋርያት ደግሞ ሰውነቱን ያውቃሉ፡፡ በታቦር ተራራ ግን አዲስ ትምህርት ተማሩ፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ይላል ፦ ‘‘ነቢያቱ አይተውት የማያውቁትን ሰውነቱን አይተው ተደሰቱ ፤ ሐዋርያቱ አምላክነቱን አይተው ተደሰቱ’’

ሐዋርያት ደነገጡ ፤ እነርሱ ባልነበሩበት በዮርዳኖስ የተናገረውን የእግዚአብሔር አብን ድምፅ በታቦር ተራራ ሰሙ ፤ ጴጥሮስ ‘አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ’ ያለው በሰማይ ያለው አብ ገልጦለት ነበረ ፤ አሁን በልቡ ያንን ቃል ያስቀመጠውን የአብን ድምፅ ሰምቶ ዓለቱ ስምዖን በፍርሃት ወደቀ፡፡ የጌታን ፊት አብርቶ ሲያይ ሳያይ ያመነውን አምላክነቱን አወቀ፡፡ ‘ሐዋርያት በአንድ ቀን ሁለት ፀሐይ ወጥቶ አዩ ፤ አንደኛው የተለመደችው ፀሐይ ስትሆን ሁለተኛው ደግሞ የሚያበራው የጌታ ፊት ነበር’ ይላል ቅዱስ ኤፍሬም፡፡ እውነትም ስሙን ለሚፈሩ ሐዋርያት የጽድቅ ፀሐይ ክርስቶስ በታቦር ተራራ ላይ ወጣላቸው፡፡

ቅዱስ ኤፍሬም በታቦር ተራራ ነቢያትና ሐዋርያት መገናኘታቸውን እንዲህ ሲል ያደንቃል ፦
‘የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች የሐዲስ ኪዳን ጸሐፊዎችን አዩ ፤ ቅዱሱ ሙሴ ቅዱስ ጴጥሮስን አየው የአብ እንደራሴ የወልድን አገልጋይ ተመለከተው፡፡ የብሉይ ኪዳኑ ድንግል ዮሐንስ የሐዲስ ኪዳኑን ድንግል ዮሐንስን አየው፡፡ በእሳት ሰረገላ ላይ የተሳፈረው ኤልያስ ወደ እሳታዊው ክርስቶስ ደረት የተጠጋውን ዮሐንስን አየው፡፡ የታቦር ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ሆነ ፤ ክርስቶስም ሁለቱን ኪዳናት አዋሐዳቸው!’

ሐዋርያት ወድቀው ‘የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት’ የሚል ቃል ከሰሙ በኋላ ሲነሡ ከክርስቶስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም፡፡ በእርግጥም ‘የምወደው ልጄ ይህ ነው’ ተብለው ማሳሰቢያ ከተሠጣቸው በኋላ ቀና ሲሉ ማግኘት ያለባቸው ‘የሚወደው ልጁን’ ክርስቶስን ብቻ ካልሆነ አዋጁ ስለማን እንደሆነ ግራ ይገባቸው ነበር ይላል ማር ኤፍሬም፡፡

ሐዋርያት ቀና ሲሉ ሙሴ የለም ፤ ኤልያስም የለም፡፡ ለነገሩ ከሙሴም ከኤልያስም የሚልቀው ጌታ ከእነርሱ ጋር ካለ ምን ይፈልጋሉ? ባልወለደው ፈርኦን የልጅ ልጅ ተብሎ ከተጠራው ሙሴ ይልቅ ባልወለደው ዮሴፍ የዮሴፍ ልጅ ተብሎ የተጠራው ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር ነው፡፡ ከፈርኦን ሰይፍ ተርፎ እስራኤልን ነጻ ካወጣው ሙሴ የሚበልጠው ከሔሮድስ ሰይፍ ተርፎ ዓለምን ነጻ ያወጣው ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር አለ፡፡ እናቱ ሞግዚቱ ሆና ካሳደገችው ሙሴ በላይ ‘እናትና ገረድ ማርያም ደስ’ ብሏት ያሳደገችው ክርስቶስ አይሻላቸውም? ግብፃዊውን ገድሎ ለማንም አትናገሩ ከሚለው ሙሴ ይልቅ ዕውራንን አብርቶ ለምፃምን አንጽቶ ፊቱ እንደ ፀሐይ አብርቶ ለማንም አትናገሩብኝ የሚለው ክርስቶስ አብሮአቸው ካለ ምን ይፈልጋሉ፡፡ ‘የቆምህበት ሥፍራ የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ’ ተብሎ ከተነገረው ሙሴ ይልቅ ‘የጌታ እግር በሚቆምበት እንሰግዳለን’ ‘የጫማህን ጠፍር እንኳን ልፈታ አይገባኝም’ እየተባለ የተዘመረለት ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር ነውና ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት የሙሴ መሔድ አላስደነቃቸውም፡፡

ኤልያስንም ስላላዩ አላዘኑም ፤ በእሳት ሰረገላ ከሔደው ኤልያስ በላይ ልብሱ እሳት ቀሚሱ እሳት የሆነው አምላክ ከእነርሱ ጋር ነው፡፡ ኤልያስ ለደቀ መዝሙሩ ወደ ሰማይ ሲሔድ መጎናጸፊያውን ትቶለት ሔዶ ነበር፡፡ የሐዋርያት መምህር ክርስቶስ ግን ሲያርግ ልብሱን አልወረወረላቸውም፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳለ እርሱ ሲያርግ ለደቀ መዛሙርቱ የተወላቸው ልብሱን ሳይሆን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ነው፡፡ ስለዚህ ኤልያስ ቢሔድ ሙሴም ቢሰወር ደቀ መዛሙርቱ ጌታችንን ከብበው ከታቦር ተራራ በደስታ ወረዱ፡፡

ማቴ. ፲፯፡፩-፭ በቤተ ክርስቲያን ደብረታቦር ከቤተክርስቲያን ውጭ አከባበሩ ቡሄ እየተባለ የሚከበረው በዓል በሀገራችን በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡ ቡሄ ሲመጣ የክረምቱ ጨለማነት አልፎ ወደ ብርሃን፣ ወደ ጥቢ የሚያመራበት፣ ወደ መፀው የሚዘለቅበት ወገግታ ፣ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት፣ የሚሸጋገርበት ወቅት በመሆኑ ከቡሄ በኋላ የጠነከረ ክረምት አይኖርም፡፡ በዚህ መሰረት የክረምቱ አፈና ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየውም በዚህ በዓል አካባቢ ስለሆነ ይቺ ዕለት 'ቡሄ' የሚለውን ስያሜ አገኘ። ቡሄ ማለት ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት፣ ብረሃን የታየበት ድምጸ መለኮት የተሰማበት ስለሆነ፤ ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓልም ይባላል፡፡

በገጠርም ሆነ በየከተማው ልጆች ጅራፋቸውን ገምደው ሲያጮሁ ይሰነብታሉ። እናቶችም ለበዓሉ ዝግጅት ስንዴ ሲለቅሙ፣ ሲፈትጉ፣ ሲፈጩ ይሰነብታሉ። መነሻ የሆናቸው ትውፊት ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ዕለት ጊዜው ምሽት ነበር፡፡ እረኞችም ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጥተዋል ፡፡ያንን ለማስታወስ «ቡሄ» ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና ችቦ በማብራት በዓሉን የሚከበረው ከዚህ በመነሣት
416 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 21:53:03 "ሁላችንም የተጎሳቆለ ልብስ እና ጥራት የሌለው የቤት እቃ የሚያሳፍረን ከሆነ የተጎሳቆሉ አስተሳሰቦች እና ጥራት የሌላቸው ፍልስፍናዎችም ሊያሳፍሩን ይገባል......እንግዲህ፣ ከውስጥ ካለው ስጋ ይልቅ ከላይ ያለው የስጋው መጠቅለያ የተሻለ ጥራት ያለው ከሆነ አሳዛኝ ሁኔታ ነው የሚሆነው።"

#አልበርት_አንስታይን
566 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 20:56:43 .ሞት ያስመኜ ፍቅር....
ከሩቅ አድማስ ከ'ሩቅ
ከግግሩ ሰማይ በታች ስለ ፍቅር ተንበርክኬ፣
በጎደለው ማንነቴ
ሙሉ ሁነሽ ስትደምቂ እኔነቴን ተማርኬ፣
ሳታውቂልኝ አፈቀርኩሽ፣
ስለ ፍቅርሽ ገጠምኩልሽ፣
በጣቶችሽ ጥበብ
የስታየን ሊለካ ምስልሽ በልቤ ጎጆውን ቀለሰ፣
ዝም ያለው ሂዎቴን
ፍቅርሽ አፍ አውጥቶ ሰርስሮት አረሰ፣
ሁሌም ታምር ሰሪው አንቺን ቀማሪ አድርጎሽ፣
እኔ ተቀማሪ
ነፍሴን ሀሴት ሞላት ጣርና ሰቀቀን ከማጀቷ ሲሸሽ፣
ጉድለቴን ስትሞይው፣
ወንድነቴን ስትረችው፣
ስለ ፅኑ ፍቅርሽ ላንጎራጉር ክራሬን አማተርኩ፣
በጥልቅ ተመስጦ
በእዝልና አራራይ ክብርሽን አወደስኩ፣
የመውደዴን ፅናት የደስታዬን ብስራት በዜማዬ ነገርኩ፣
ደግሞስ አንቺ ማለት ውዴ፣
ለእይታ ብቻ እንኳን ቀልብን የሚሰርቁ፣
በብዙ አይነት ቀለም ዉበት እዬተፉ ዉበት በሚያስንቁ፣
ዕልፍ አበባ አግኝቼ ቀልቤ ቢሰረቅም፣
እዉነት እልሻለዉ፦
አንቺን የሚመስል ከአበቦቹ ሁሉ አበባ አይገኝም፣
ከአይንሽ የሚተነዉ የፍቅር እንፋሎት፣
የመንፈስ ስንቄ ነዉ እንደ ዘዉትር ፀሎት፡፡

እንኳንስ ተበልተዉ ገና ሲያዩዋቼዉ ፣
ጣፋጭ የሚለዉ ቃል
ጣፍጦ እማይገልፃቼዉ ጥዑም ፍራፍሬ፣
ለመብላት ስጣደፍ ምላሴን ነክሼ ደም ሳዘራላቼዉ፣
መድማቴ እስኪጠፋኝ
አዎይ ጣም እያልኩኝ እጅግ ብደነቅም፣
እወዉነት እልሻለዉ
ከከንፈርሽ በላይ ከፍሩቱ ሁሉ ጥፍጥናን አላውቅም፣
ደግሞስ ብትይ ፍቅሬ፦
በእቅፍሽ ሰማዬሰማያት በገነትሽ መንበር፣
ለኔ ልበ ባተሌው ፍቅርሽ ሲዘራ ህያው ሁኜ ለመኖር፣
እጉያሽ ስር ሞቴ ይሁን
በፅድቅሽ አድማስ ሁሉ የኔ ገነት እንዲፈጠር።
ተፃፈ ደሱ ለተጨማሪ መሳጭ ግጥሞችና አባባሎች

https://t.me/Desupome/764
https://t.me/Desupome/764
528 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 21:53:24 እንቅልፌን ተይልኝ

ቁርጥ ከሆነ መራቅሽ
እውነት ከሆነ ጉዞሽ
ፍፁም ላትመለሽ ከቶ ላታገኝኝ
የፍቅሬን ጩኸት ቅንጣት ሳትሰሚኝ፣
ሂጅ አልከተልሽም
ሰተሽ የነፈግሽኝ መውደድሽ ያንቺ ነው፣
ራቂ የኔ ቤቴ ይዳብዝ ጨለማ ይውረሰው፣
ግን ደግሞ አለሜ፣
አንቺን የሌለሽበት
ድቅድቅ ያለበሰኝ የፍቅርሽ ወላፈን፣
ከጨለማ ሊለቅ ህልም አለኝ እንደሆን፣
እንቅልፌን ተይልኝ
ስጋደም አትምጪ ከህልሜ ጋር
ልሁን።
ተፃፈ ደሱሱ
547 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 21:37:25 .መልስ አልባ ጥያቄ....
በዚህ በኔ ዘመን
በዚህ በኔ ጊዜ
ሰው ማለት ምንድን ነው?ተብሎ ለሚጠየቅ፣
መልስ የሚሆነው ጥያቄ ነው ሲረቅ፣
ኩሏን ተ'ኳኩላ
በቀለም ደ'ማምቃ
እንደ አደይ አበባ፣በአሪቲፊሻል ለዛ የምትፈነድቅ፣
ሴት ናት ትባላለች፣በንቅሳት ቀለም አካላቷ ቢደምቅ፣
በሂውማን ሄር ታጥራ፦
ተተፈጥሮን መንፍቃ፣መዋቢያ ፍለጋ በየሸቀጡ ሱቅ፣
ለሜካፕ ዘሙታ ውላ አድራለች ሴቷ ሰውነቷን ስትፍቅ፣
እስኪ ተመልከቱ፦
በደንብ አስተውሉ፣
ቆንጆ ነን የሚሉት
ውቦች ነን የሚሉት
በዘፈን እርከን ላይ የሚያሰሙት ዜማ፣
ለሰላምታ ራሱ
የሚሰቀጥጥ ድምፅ፣
ልክ እንደ ጅብ ጩኸት ጆሮን የሚያደማ፣

ህሊናውን ሽጦ፣አንሶና ኮስሶ ክብሩን የቀበረ፣
ሰፊ ጉድጓድ ምሶ፣በቃል ያሰረውን የእምነት ሰንሰለት፣
ለታይታ የሚያሳይ፣
ይሉኝታ አልባ ትውልድ፣
ወንድ ነው ያሉኝ'ለት፣ደርቄ ቀረሁኝ ቆምኩኝ ባለሁበት፣
በጣቶቹ ጥበብ፣ክፋትን ለክቶ፣
ሚስጊኑ ወገኑን፣በሚፈራርሰው ጉም ቋንቋው ገምቶ፣
አፈር የሚጋግር፣የወገኑ እምባ በደም ጎርፍ አቡክቶ፣
ለቃሉ የማይኖር ያልገዛው ህሊና ሰው እየተባለ፣
ፍቅር አልባውን ትውልዱ፦
ወንድ ነው ይለኛል በዘረኝነት ደዌ ተማርኮ እየዋለ፣

ግን ሰው የት ሄደ?
ልክ እንደ በፊቱ ፣ድሮ ድሮ ድንጋይ ዳቦ እያለ፣
ሰማይ እንዲህ ሳይርቅ፣ፍፁም ዝቅ እንዳለ፣
ፍቅርን የሚለግስ፣ሰውን በሰው አምሳል የሚመዝን ሁሉ፣
ያ የእምነት ባለ ኪዳን፣ትህትናን ያሰረ በማይሻር ቃሉ፣
የት ሄደ ሰው ሁሉ??
ተፃፈ ደሱ ለተጨማሪ መሳጭ ግጥሞችና አባባሎች

https://t.me/Desupome/764
https://t.me/Desupome/764
531 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ