Get Mystery Box with random crypto!

የቀድሞው የዙምባቤ ፕሬዚዳንት #ሮበርት ሙጋቤ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር ፦ 'የአፍሪካ የት | ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹

የቀድሞው የዙምባቤ ፕሬዚዳንት #ሮበርት ሙጋቤ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር ፦ "የአፍሪካ የትምህርት ስርዓት አስገራሚ ውጤቶች አሉት ።" ካሉ በኋላ

አንደኛ ደረጃ የሚይዙ ቀለሜና ጎበዝ ተማሪዎች ጥሩ ውጤት አምጥተው #ኢንጂነሪንግና #ሜዲሲን እንዲማሩ እድል ያገኛሉ ።

ሁለተኛ ደረጃ የሚይዙት ደግሞ #ህግና #ማኔጅመንት ነገር ተምረው አንደኛ ደረጃዎቹን ያስተዳድሯቸዋል ።

ዝቅ ብለው በሶስተኛ ደረጃ የሚገኙት ተማሪዎች ደግሞ #ፖለቲካ ውስጥ ይገቡና አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያሉትን ከላይ ሆነው ይቆጣጠራሉ ።

በትምህርት ውዳቂዎች ደግሞ #ፖሊስና #ወታደር ይሆናሉ ። እነዚህ ደግሞ ፖለቲከኞችን ይቆጣጠራሉ ደስ ያላላቸውን ፖለቲከኛ ደግሞ እስከ መግደል ድረስ ይደርሳሉ ።

ከሁሉም ከሁሉም ግን ምርጡ ጭራሽ ክላስም ሆነ ትምህርት ቤትም ገብቶ የማያውቀው ሰው ደግሞ #ነብይና #ጠንቋይ ይሆናል ። ይሄን ደግሞ ሁሉም ይከተሉታል ። ብለው ነበር ።

እኛስ በሃገራችን ያየነው ይህንን ነው ወይስ ሌላውን ነው ?
═════════❁✿❁ ═════════