Get Mystery Box with random crypto!

የዕለቱ ምርጥ..! ስለ ገንዘብ - በድሃ ፊት አትናገር! ስለ ጤንነትህ - ህመምተኛ ፊት አታውራ | ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹

የዕለቱ ምርጥ..!

ስለ ገንዘብ - በድሃ ፊት አትናገር!
ስለ ጤንነትህ - ህመምተኛ ፊት አታውራ!
ስለ ጥንካሬህ - ደካሞች ፊት አትናገር!
ስለ ደስታህ - በተከፋ ሰው ፊር አታውራ!
ስለ ነጻነትህ - እስረኞች ፊት አትናገር!
ስለ ልጆችህ -መሃን ፊት አታውራ!
ስለ እናት እና አባትህ -ወላጅ አልባ ሰዎች ፊት አትናገር!

..ምክንያቱም ቁስሎቻቸውን ከበፊቱ በበለጠ እንዲቆስል እና እንዲደማ ምክንያት ትሆናለህና። ለምትሰጠው ነገር ሁሉ ትንሽ ፈገግ በል፣ ከልብህም ደስታን ጨምርበት፣ ለማንኛውም ሰው ጆሮ ስጥ፣ ግን ድምጽህን ቀንስ ሁሉንም ውደድ ጥቂቶቹን እመን፣ ማንንም ግን አትበድል። የውሸት ጓደኛ እና ጥላ አንድ ናቸው። ሁለቱም የሚቆዩት ጸሃይ እስክትጠልቅ ድረስ ብቻ ነው። መልካም ሰው ከሰው ልጅ የመንፈስ ምግብ ነው የማንም ሰው ህይወት ስህተት ወይም ትክክል መሆኑ የሚታወቀው ተፈትኖ ካለፈ ወይም ከወደቀ ብቻ ነው።ለተጨማሪ መሳጭ ግጥሞችና አባባሎች

https://t.me/Desupome/764
https://t.me/Desupome/764