Get Mystery Box with random crypto!

ደግሞ እሙኝ አሏችሁ በፖለቲካ ዝም ከምል በሚል፦ ስለ ዘመኑ እውነት ስለ ሰው እውነታ፣ ግጥም ል | ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹

ደግሞ እሙኝ አሏችሁ በፖለቲካ
ዝም ከምል በሚል፦
ስለ ዘመኑ እውነት ስለ ሰው እውነታ፣
ግጥም ልፅፍ ወሰንኩ በቀለም ጠብታ፣
ጀመረኩ ተዘጋጀሁ
አግድሙን ለሚረግጥ ወከባው ለነዳው፣
ማስመሰልን አምኖ እሱነቱን ላጣው፣
ከህሊናው መንፍቆ ለሰፊ ሆዱ ለሚኖረው፣
ለዘመኑ ትውለድ
ሰውነት ለመግጠም
ሆ'ሂያት መፈለግን ቆም ብየ ሳስበው፣
ለካስ ጅላንፎ ነኝ፣
ለካስ ትልቅ ጅል ነኝ፣
ለካስ ጅላጅል ነኝ፣
በእስራቴ ገመድ ጅራፌን የሰራው፣
ሰው ነህ በምለው ፍጡር እኔነቴን ያጣው፣
በዘር ተቀልሜ ብኩርናየን ክጄ ምስሬን የበላው፣
አዎይ የኔ ነገር፦
ሰው ፍለጋ ኳተንኩ ሰው በሌለው ዘመን፣
ተፃፈ ደሱ ለተጨማሪ መሳጭ ግጥሞችና አባባሎች

https://t.me/Desupome/764
https://t.me/Desupome/764