Get Mystery Box with random crypto!

የሰው ልጅን በኦሾ እይታ ስለ ሰው ልጅ ብዙ ብዙ ያለው ኦሾ በዚች ምድር አምሳያውን የሚገድል ፍጡር | ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹

የሰው ልጅን በኦሾ እይታ
ስለ ሰው ልጅ ብዙ ብዙ
ያለው ኦሾ በዚች ምድር አምሳያውን የሚገድል ፍጡር ቢኖር
የሰው ልጅ ብቻ ነው በማለት ያስቀምጥና የትኛውም እንሰሳ
መርዝ አወጋጅቶ ስለት ስሎ ሰዋራ ቦታ ጠብቆ ወይ በገመድ
አንቆ አልያም ጥይት ተኩሶ አምሳያውን የገደለበት አጋጣሚ
በአለም አልታየም ይለናል
ሌላው በትምህርታዊ ነገር ስለ ሰው ልጅ የገለፀልን ነገር
እንዲህ ይላል በአንድ ሆስፒታል ውስጥ የመጀመሪያው ታማሚ
ክፍል የተዘጋ በር ላይ ' በእባብ የተነደፈ ሰው በህክምና ላይ
የሚገኝ ሲሆን ከ30 ደቂቃ ቦኃላ ድኖ ይወጣል ' ይላል
ሁለተኛው በር ላይ " በአንበሳ የተነከሰ ሰው በህክምና ላይ
ይገኛል ከአንድ ሰአት ቦኃላ ድኖ ይወጣል " ይላል ሶስተኛው በር
ላይ ደግሞ በሰው የተነከሰ ሰው በህክምና ላይ ይገኛል ህይወቱ
ስለ መትረፉ እንኳን እርግጠኞች አይደለንም " በማለት የሰው
ልጅን እርኩሳዊ ባህሪ ሊያስረዳን ሞክሯል ቅዱስ ሆናችሁ
ተወልዳችሁ ሰይጣን ሆናችሁ ትሞታላችሁ የሚለን እሾ
እርኩስም ቅዱስም የመሆን ምርጫው እኛው ጋር እንዳለ
አስረግጦ ያሳስበናል
የትኛውም እንሰሳ የተራክቦ ስሜቱን የሚወጣው የሴቷን ሽንት
አሽትቶና እርጉዝ አለመሆኗን አረጋግጦ ሲሆን ይህንንም
ለማድረግ ወቅትና የሴቷን ፈቃደኝነት ተከትሎ ነው የሰው ልጅ
ግን ስግብግብ በመሆኑ ያለ ሴቷ ፍቃድና አስገድዶ ደፋሪ ሆኖ
ከእንሰሳ በታች የዘቀጠ የስብዕና ኖሮት አለማፈሩ አስገራሚ
ፍጡር ያደርገዋል ።ኦሽ/Osho
ለተጨማሪ መሳጭ ግጥሞችና አባባሎች

https://t.me/Desupome/764
https://t.me/Desupome/764