Get Mystery Box with random crypto!

አውነትን ልጨብጥ ከውሸት ልቀርን ወጣሁ ከራማየ፣ወደ እልፍኝ ገዳሜ፣ አዘቅቱን ጨልፌ፣ውቅያኖስ ፈልሜ | ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹

አውነትን ልጨብጥ
ከውሸት ልቀርን
ወጣሁ ከራማየ፣ወደ እልፍኝ ገዳሜ፣
አዘቅቱን ጨልፌ፣ውቅያኖስ ፈልሜ፣
ደግሞ ወጣሁ
ከእልፍኝ ገዳሜ
ወጣሁ ወደ አድማሱ፣ካገር ጫፍ ጠረፉ፣
ዳመናን ዘርግቼ፣ውሸታም ኮከቦች ፍፁም እንዲጠፉ፣
አሁንም ወጣሁ
ካገር ጫፍ ጠረፉ
ህዋውን መንፍቄ ሸሸው፣
እውነትን ፍለጋ ፈጋው፣
ግን የት ነው እውነት?፣
ሳሰላስል ለዘመናት፣ልዳኝ ስለውሸት፣
ጉራንጉር ሸለቆውን፣ስመረምር ስመፀውት፣
መልስ አገኜው ከኔው ማህፀን ከኔው አንደበት፣
የት እንዳለ የናፈኩት፣ሙሉው እውነት፣
በአንደበቴ ተፀንሶ፣በእስትንፋሴ የሚወገር፣
በንግሬ የሚረገጥ፣በቃላቴ የሚታሰር፣
ያ'ነው እውነት፦
በኔው ልብ ውስጥ፣ለውሸት ክብር የሚቀበር።
ተፃፈ ደሱ