Get Mystery Box with random crypto!

እንዲያው እንደምን ነሽ ዝም ብለን ዝም ያልነው ለካስ ለነገር ነው የሚል ፍልስፍና ባሰጠማት ሀገር | ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹

እንዲያው እንደምን ነሽ

ዝም ብለን ዝም ያልነው
ለካስ ለነገር ነው
የሚል ፍልስፍና ባሰጠማት ሀገር
ድምፅ አይቆጠርም ካልጮኹ በስተቀር
እውነት ስልሽ ውዴ...
የጠመንጃ አረር የሚለፈልፍን አንደበት ካልዘጋ
በካድሬወች መንደር ጨለማም አይነጋ
እና ደግሞ ሌላው...
ብዙ ጭንጋፍ ካድሬ
አጀብ አስከትለው በገደሏት ሀገር
ሀገሬ አልሞተችም በሚል አንድ ዜማ ይዋላል ሲጨፈር
.......................................

ግን አንቺ እንዴት ነሽ...
እንዴት ነሽ በብዙ እንዴት ነሽ በአያሌው
በዘመናት ክፍተት አይኖችሽን ሳላይ ብዙ ስለቆየው
እንዴት ነሽ? እላለሁ

(አማኑኤል ደርበው/አማን ዘ:ታቦር)