Get Mystery Box with random crypto!

እንቆቅልሽ፦ ምናውቅልህ እንዳትይኝ ስለ ፍቅር መንገብገቤን፣ በማጀትሽ ፀ'ላይ መንፈስ እኔነቴን መነ | ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹

እንቆቅልሽ፦
ምናውቅልህ እንዳትይኝ ስለ ፍቅር መንገብገቤን፣
በማጀትሽ ፀ'ላይ መንፈስ እኔነቴን መነጠቄን፣
እንቆቅልሽ፦
ምናውቅልህ እንዳትይኝ በጎ ሀሳብ ተቀብሮ፣
ስብናን መናፈቅ ትርፉ ድካም እንጂ ም'ን ሊገኝ ዘንድሮ፣
እንቆቅልሽ፦
ምናውቅልህ እንዳትይኝ ጊዜ በዘመኑ አ'ግጦ ሲወረዎር፣
ሰው በሰው ሲበላ ሲቃን ስናነባ ፍትሃችን ስትቀበር፣
እንቆቅልሽ፦
ምናውቅልህ እንዳትይኝ ፍቅር በዲናር ስትረገጥ፣
በአለም ፍኖት ተመዝና ገነታዊ መለኮቷን ስትለውጥ፣
እንቆቅልሽ ያልኩሽን፣
ምናውቅልህ እንዳትይኝ፣
እውነትስ ከየት አውቀሽ፣
እኔስ ብሆን ምን አውቄ፣
መጥፍ እድል እንዳይደል ሰበብ የሚያመጣ፣
ወንጀል እንዳይደለ በህግ የሚያስገጣ፣
ሀ'ጢያታችን ተሽሞንሙኖ በእርቃን ጀንበር ሳይሞሸር፣
ሀገርን ታህል ባ'ዕት ሳትከፈል በየጢሻው በክልል ዘር፣
የእኔስ እንቆቅልሽ መልሱ ምንአውቅልህም አልነበር፣
ሀገሬ አንቺ ነበርሽ በፍቅርሽ ሰዳፍ የጨለጥሽኝ፣
በኤዶም ገነት ያለ ከልካይ ጥሩ ሽቶ የረጨሽኝ፣
ከጉያሽ ስር ሰፊ ገዳም ማንነቴን የጋረድሽኝ፣
ግና እጣፈንታችን፦
አንችም እንደ ሀገሬ ፍቅርን ገድለሽ ቀብረሽው፣
የአፅሜን ጉዝጓዝ ተንተርሰሽ ለንቦጭሽን አሳመርሽው፣
እወቂና የጭንቀቴን ሸማ ከነክብሩ ደርቢልኝ፣
እውነት መርጠሽ በትንሳኤሽ ጥያቄየን መልሽልኝ፣
በእንቆቅልሽ እንዳልከስም ምን አውቅልህ አትበይኝ።
ተፃፈ ደሱ ለተጨማሪ መሳጭ ግጥሞችና አባባሎች

https://t.me/Desupome/764
https://t.me/Desupome/764