Get Mystery Box with random crypto!

አለማየው ገላጋይ (በእውነት ስም) ' ውትድርና ሌላ ሳይሆን የመታዘዝ አዙሪት ነው። የአለቃህ አለ | ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹

አለማየው ገላጋይ (በእውነት ስም)

" ውትድርና ሌላ ሳይሆን የመታዘዝ አዙሪት ነው። የአለቃህ አለቃህ ያዘዋል። እሱም ታዞ ነው። እሱም አንተን ያዝሀል ጥሩ ፣ አንተ ደግሞ ያንን ትዕዛዝ ለሚፈፅሙ ሰዎች ታደርሳለህ። መታዘዝ በስንት ጣዕሙ ፣ ጥሩ ያዘዝከው ባዘዝከው መሰረት ሄዶ ህይወቱን ሊያጣ ይችላል፣ አካሉ ሊጎድል ይችላል፣ አንዳንዴ የሞት ፍርድ ትሰጣለህ። በፈንጂ እንዲረማመድ ትዕዛዝ ታስተላልፍለህ.! ያንተ ፀፀት ከሰውዬው ሞት ይከፋል ......"

" የአንዳንድ ጥያቄዎች መልሳቸው መተው ብቻ የሚሆንበት ጌዜ አለ። የሰው ልጅ ሁሉ እጣ ፈንታችንን የሚጠቅመንና፣ የማይጠቅመንን የምንደርስበትንና የማንደርስበትን ማሰብ ሆኗል። ከጠቀመን ጥሩ! ካልጠቀመን መተው! ከደረስንበት ጥሩ ካልደረስንበት ለሚደርስበት ትውልድ መተው ... የሰው ልጅ ውስንና ፍፁምነት የሚጎለው ፍጡር መሆኑን መገንዘብ "

" መፀሀፍት ለጥያቄዎችህ ቀጥተኛ ምላሽ ባይኖራቸው እንኳን የማሰብ ልምምድህን በማፍጠን የጥያቄህን ምላሽ እራስ እንድታገኘው ያግዙሃል።

"የሴት ጣውንትዋ ሌላ ሴት ከመሰለችህ ተሳስተሀል። ወዳጄ የሴት ጣውንትዋ ባልዋ የሚወደውና ቀልብን የሰጠው ነገር ሁሉ ነው ። ልብ በል ፤ ሌላው ቀርቶ ልጅህን እንኳን ከወደድክ የገዛ ልጇን ወደ ጣውንትነት ትቀይራለች ። "