Get Mystery Box with random crypto!

♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹

የቴሌግራም ቻናል አርማ desupome — ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹
የቴሌግራም ቻናል አርማ desupome — ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹
የሰርጥ አድራሻ: @desupome
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.82K
የሰርጥ መግለጫ

☞ የስብህና ልቀት ለማምጣት ከመፃህፍት ጋር እናዉጋ
☞ በዚህ ቻናል ተወዳጅ የሆኑ ግጥሞችንና አስተማሪ ታሪኮችን ይቀርቡበታል
ለሃሳብ አስተያዬታች
@Almnu6
@Almnu6
መነጋገር ይቻላል
ገጣሚ ማለት በአጭረር አነጋገር እረጅም ሃሳብን መግለፅ ነዉ፡፡

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-10 22:17:45 ..ፍቅር ነሽ......
```
ማር ነሽ ብየሻለው አንደበትሽ ጣፍጦኝ
ንግስት ብየሻለው ዉበትሽ አፍዝዞኝ
ግርማሽ አስፈርቶኝ፤
ቆንጆ ነሽ ብያለሁ ቃላት ሁሉ ቢያጥሩኝ
ወርቅ ብየሻለሁ ጥራትሽ ቢገርመኝ፤
ግን ፍቅሬ ይቅርታ!!
በማር በገለፀኩሽ
በወርቅ በመሰልኩሽ
ንግስት ነሽ ባልኩሽ፤
ግን ፍቅሬ ይቅርታ!!
ማርም ይጠገባል
ወርቅም ይለወጣል
ንግስናም ይሻራል
ሳላውቅ ነው ውዴ ይህን ሁሉ ያልኩሽ
ቆይቼ.. ቆይቼ.. ቆይይ….ቼ ሳስብሽ
የማይሰለቸው ራ'ሡ….. ፍቅር’’’ ነሽ::
ተፃፈ ደሱ ለተጨማሪ መሳጭ ግጥሞችና አባባሎች

https://t.me/Desupome/764
https://t.me/Desupome/764
539 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 20:54:45 ሞተች ይቺ ብኩን ነፍሴ፣
ዋይ ዋይ አልኩኝ አነባሁኝ ለራሴ፣
መለኮቴን ሸረሸርኩት በአለም ፍኖት ተደብቄ፣
ሰው ነህ ሲሉኝ ሰውነትን ፍፁም ፍቄ፣
አዎ እኔ ሰው አልሆንም፦
ለማይሞላ ብጣሽ ከርሴ ከደካሞች ሳንቲም የምዘሙት፣
በምግባሬ ረክሼ
ባቢሎኔን ሰርክ የማንፅ ፍጡሩን ሁሉ በቋንቋየ የምገምት፣
በሰው ዋሻ ለመጠለል ናቡቴየን የምወግር በሀሰት ፍርድ፣
እውነት ተሞሽራ
ፊቴ ስትቆም ላሰቅላት የምታጠብ ሀቅ የማልፈርድ፣
አዎ እኔ ሰው አልሆንም፦
በእግዜር አምሳል ተበጅቸ፣
የምድሩን ሁሉ ዙፋን በጄ አግኝቸ፣
ከአብረቅራቂ እንቡጥ በለስ ስለማልፆም ስለምቀጥፍ፣
ሰው አትበሉኝ
የሰው አምሳል ከሆኑት ጋር ነው ም'ሰለፍ፣

ተፃፈ ደሱ
485 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 20:17:36 አይ ደሃ
ህያው የሆነች ነፍሴ
በድኩማን ስጋዬ ተሸንፋ ጣረ ሞትን ስትገፋ፣
ትላንት ዛሬ ሁኖ እንደ ጉም ጭስ በኖ ጠፋ፣
መንገደኛ የሆነው እግሬ፣
በደንዳናው አካላቴ ተጨናግፎ ሲጠጋገንን፣
ፀሀይ ቀረች ድቅድቅ ዋጣት ጨረቃዋን፣
ደግሞ ዛሬ የኔ ነገር
ተስፋ ሳልቆርጥ ሳልጠረጥር
የናፈኩት ብሩህ ህልሜን ለመፈለግ አምባ ወጣሁ፣
አድማሱን ዞርኩ ተራራውን ዙሬ ቃኘው፣
በህዋው አማተርኩኝ ውቅያኖሱን እየቀዘፍኩ፣
በአውሎ ማዕበል በባህሩ ካብ እየዞርኩ፣
በጥቅጥኩ ለምለም ጫካ ከአጋም እሾህ እየገጠምኩ፣
ሳይሰለቸኝ
ሳልደክም ረጃጅም ህንፃዎችን ሁሉ ፈተሽኩ፣
ግና ህልሜ የለም
ተደብቆኝ ለባዳ ሁኗል፣
የኔነቴ ውጥን ተስፋ
ተውንጭፎ ከማጀቴ፣ሰው ለሆኑት ተመፅውቷል፣
በማይሻር በእው ነት ቃሉ
ከሌለው ላይ እያነሳ ለታደሉት ይጨመራል፣
የኔ ቢጤ ሚስጊን ደሃ
የነፍሱን ህግ ለሟች ስጋው ቀብድ ሰጥቷል፣
ላለመሞት ህልሙን ገድሎ ቀን ይቆጥራል፣
አይ ደሃ
ተፃፈ ደሱ ለተጨማሪ መሳጭ ግጥሞችና አባባሎች

https://t.me/Desupome/764
https://t.me/Desupome/764
540 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 10:30:13 . አህያዋ ና አንበሳው.....
ይገርማል ሲያስቡት
አለች አህያዋ ከጎህ እስከ ሰርክ መሸከም ቢመራት፣
ከጠለሉ ሜዳ የተትረፈረፈ ግጦሽ'ን ሲያግዳት፣
የድካሟን ሲቃ
የጠኔዋን ክኒን ለአንበሳ ልትነግር ሰቆቃው ቢመራት?፣
ሄደጅ ወደ አንበሳ
አንበሳውም ገርሞት አፉን እያዛጋ ፣
ጠጋ አለ በግርምት
ስለ እርሷ መከራ ለሚስጊኗ አህያ ጨልፎ ሊያወጋ፣

አንቺኮ አህያ ሆይ፦
ህልምሽ የመከነ በማገርሽ መፍረስ፣
ቃሉን የበላ ሁል
ባ'ንቺ ንፁ ጀርባ መሃላሽን ክዶ እሾህ ሚ'ነሰንስ፣
ክብርሽ አዋርዶ መ'ነረት ከሆነ የውለታሽ ትርፉ፣
ነይ ከኔ ጋር ኑሪ የተብረከረኩ እግሮችሽ ይረፉ፣
ክፉ ሳልናገር መጥፎ ቃል ሳይወጣኝ፣
ፊቴን ሳላጠቁር ማኩረፍም ሳይቃጣኝ፣
ደረቴን ሳልደቃ ስለ ሀዘኔታ አመድ ሳልነሰንስ፣
ከመሬት ሳልተኛ ጥቁር ቂምን ሳልለብስ፣
''እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል''
ያልሽውን ረስቼ
ራስ ወዳድነትሽን ሂጅ ከጓሮዬ ለምለም ሳሩን ጋጪ፣
ደስታሽ ደስታየ ነው ልቤ ተሸነፈ አምነሽኝ ስትመጪ፣

አህያዋም በደስታ፦
ከለመለመው መስክ ለምለም ሳሯን ግጣ፣
ለጥጋባ ምስባክ ባገኘች'ው አመድ ትንሽ ተገላብጣ፣
ወደ አንበሳ ሄደች
አምሮባት በደስታ ሃሃሃሃ በሚል ደወል፣
ስብሃት ልታደርስ ምርቃት ሊሆናት
አየህ አቶ አንበሳ
እኔ አህያዋ አንገቴን አልደፋም ከቶ ለምን ብዬ፣
ቀኑ ጨለመብኝ በሚል ከንቱ ለቅሶ አይፈስም እምባዬ፣

አንበሳም በግርምት፦
ሰዓቱን ተመልክቶ አይኑን ከጭኗ ስር ወርውሮ ሲመለስ፣
ታየው የአህያዋ ሞኝነት መበያዋ ሲደርስ፣
ጠጋ አለና አንበሴ አንገቷን ጨብጦ ደሟ እንደፈሰሰ፣
እንዲህ አላት
አንቺ ሞኝ አህያ ድካምና ረሃብን መሸ'ሽሽ ባልከፋ፣
ዳሩ ምን ዋጋ አለው፦
የጉዞሽ ፍፃሜ ማረፊያውን ስቶ ፀዳል ነፍስሽ ጠፋ፣
ተፃፈ ደሱ ለተጨማሪ መሳጭ ግጥሞችና አባባሎች

https://t.me/Desupome/764
https://t.me/Desupome/764
564 viewsግዮናዊዉ ዮኒ, 07:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ