Get Mystery Box with random crypto!

ሞተች ይቺ ብኩን ነፍሴ፣ ዋይ ዋይ አልኩኝ አነባሁኝ ለራሴ፣ መለኮቴን ሸረሸርኩት በአለም ፍኖት ተደ | ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹

ሞተች ይቺ ብኩን ነፍሴ፣
ዋይ ዋይ አልኩኝ አነባሁኝ ለራሴ፣
መለኮቴን ሸረሸርኩት በአለም ፍኖት ተደብቄ፣
ሰው ነህ ሲሉኝ ሰውነትን ፍፁም ፍቄ፣
አዎ እኔ ሰው አልሆንም፦
ለማይሞላ ብጣሽ ከርሴ ከደካሞች ሳንቲም የምዘሙት፣
በምግባሬ ረክሼ
ባቢሎኔን ሰርክ የማንፅ ፍጡሩን ሁሉ በቋንቋየ የምገምት፣
በሰው ዋሻ ለመጠለል ናቡቴየን የምወግር በሀሰት ፍርድ፣
እውነት ተሞሽራ
ፊቴ ስትቆም ላሰቅላት የምታጠብ ሀቅ የማልፈርድ፣
አዎ እኔ ሰው አልሆንም፦
በእግዜር አምሳል ተበጅቸ፣
የምድሩን ሁሉ ዙፋን በጄ አግኝቸ፣
ከአብረቅራቂ እንቡጥ በለስ ስለማልፆም ስለምቀጥፍ፣
ሰው አትበሉኝ
የሰው አምሳል ከሆኑት ጋር ነው ም'ሰለፍ፣

ተፃፈ ደሱ