Get Mystery Box with random crypto!

አይ ደሃ ህያው የሆነች ነፍሴ በድኩማን ስጋዬ ተሸንፋ ጣረ ሞትን ስትገፋ፣ ትላንት ዛሬ ሁኖ እንደ | ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹

አይ ደሃ
ህያው የሆነች ነፍሴ
በድኩማን ስጋዬ ተሸንፋ ጣረ ሞትን ስትገፋ፣
ትላንት ዛሬ ሁኖ እንደ ጉም ጭስ በኖ ጠፋ፣
መንገደኛ የሆነው እግሬ፣
በደንዳናው አካላቴ ተጨናግፎ ሲጠጋገንን፣
ፀሀይ ቀረች ድቅድቅ ዋጣት ጨረቃዋን፣
ደግሞ ዛሬ የኔ ነገር
ተስፋ ሳልቆርጥ ሳልጠረጥር
የናፈኩት ብሩህ ህልሜን ለመፈለግ አምባ ወጣሁ፣
አድማሱን ዞርኩ ተራራውን ዙሬ ቃኘው፣
በህዋው አማተርኩኝ ውቅያኖሱን እየቀዘፍኩ፣
በአውሎ ማዕበል በባህሩ ካብ እየዞርኩ፣
በጥቅጥኩ ለምለም ጫካ ከአጋም እሾህ እየገጠምኩ፣
ሳይሰለቸኝ
ሳልደክም ረጃጅም ህንፃዎችን ሁሉ ፈተሽኩ፣
ግና ህልሜ የለም
ተደብቆኝ ለባዳ ሁኗል፣
የኔነቴ ውጥን ተስፋ
ተውንጭፎ ከማጀቴ፣ሰው ለሆኑት ተመፅውቷል፣
በማይሻር በእው ነት ቃሉ
ከሌለው ላይ እያነሳ ለታደሉት ይጨመራል፣
የኔ ቢጤ ሚስጊን ደሃ
የነፍሱን ህግ ለሟች ስጋው ቀብድ ሰጥቷል፣
ላለመሞት ህልሙን ገድሎ ቀን ይቆጥራል፣
አይ ደሃ
ተፃፈ ደሱ ለተጨማሪ መሳጭ ግጥሞችና አባባሎች

https://t.me/Desupome/764
https://t.me/Desupome/764