Get Mystery Box with random crypto!

. አህያዋ ና አንበሳው..... ይገርማል ሲያስቡት አለች አህያዋ ከጎህ እስከ ሰርክ መሸከም ቢመራት | ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹

. አህያዋ ና አንበሳው.....
ይገርማል ሲያስቡት
አለች አህያዋ ከጎህ እስከ ሰርክ መሸከም ቢመራት፣
ከጠለሉ ሜዳ የተትረፈረፈ ግጦሽ'ን ሲያግዳት፣
የድካሟን ሲቃ
የጠኔዋን ክኒን ለአንበሳ ልትነግር ሰቆቃው ቢመራት?፣
ሄደጅ ወደ አንበሳ
አንበሳውም ገርሞት አፉን እያዛጋ ፣
ጠጋ አለ በግርምት
ስለ እርሷ መከራ ለሚስጊኗ አህያ ጨልፎ ሊያወጋ፣

አንቺኮ አህያ ሆይ፦
ህልምሽ የመከነ በማገርሽ መፍረስ፣
ቃሉን የበላ ሁል
ባ'ንቺ ንፁ ጀርባ መሃላሽን ክዶ እሾህ ሚ'ነሰንስ፣
ክብርሽ አዋርዶ መ'ነረት ከሆነ የውለታሽ ትርፉ፣
ነይ ከኔ ጋር ኑሪ የተብረከረኩ እግሮችሽ ይረፉ፣
ክፉ ሳልናገር መጥፎ ቃል ሳይወጣኝ፣
ፊቴን ሳላጠቁር ማኩረፍም ሳይቃጣኝ፣
ደረቴን ሳልደቃ ስለ ሀዘኔታ አመድ ሳልነሰንስ፣
ከመሬት ሳልተኛ ጥቁር ቂምን ሳልለብስ፣
''እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል''
ያልሽውን ረስቼ
ራስ ወዳድነትሽን ሂጅ ከጓሮዬ ለምለም ሳሩን ጋጪ፣
ደስታሽ ደስታየ ነው ልቤ ተሸነፈ አምነሽኝ ስትመጪ፣

አህያዋም በደስታ፦
ከለመለመው መስክ ለምለም ሳሯን ግጣ፣
ለጥጋባ ምስባክ ባገኘች'ው አመድ ትንሽ ተገላብጣ፣
ወደ አንበሳ ሄደች
አምሮባት በደስታ ሃሃሃሃ በሚል ደወል፣
ስብሃት ልታደርስ ምርቃት ሊሆናት
አየህ አቶ አንበሳ
እኔ አህያዋ አንገቴን አልደፋም ከቶ ለምን ብዬ፣
ቀኑ ጨለመብኝ በሚል ከንቱ ለቅሶ አይፈስም እምባዬ፣

አንበሳም በግርምት፦
ሰዓቱን ተመልክቶ አይኑን ከጭኗ ስር ወርውሮ ሲመለስ፣
ታየው የአህያዋ ሞኝነት መበያዋ ሲደርስ፣
ጠጋ አለና አንበሴ አንገቷን ጨብጦ ደሟ እንደፈሰሰ፣
እንዲህ አላት
አንቺ ሞኝ አህያ ድካምና ረሃብን መሸ'ሽሽ ባልከፋ፣
ዳሩ ምን ዋጋ አለው፦
የጉዞሽ ፍፃሜ ማረፊያውን ስቶ ፀዳል ነፍስሽ ጠፋ፣
ተፃፈ ደሱ ለተጨማሪ መሳጭ ግጥሞችና አባባሎች

https://t.me/Desupome/764
https://t.me/Desupome/764