Get Mystery Box with random crypto!

+++ ደብረ ታቦር (ቡሄ ) +++ ❖❖❖ የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተ | ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹

+++ ደብረ ታቦር (ቡሄ ) +++
❖❖❖

የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው ዘጠኝ ዓበይት የጌታ በዓላት አንዱ የደብረ ታቦር በዓል ነው። በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን የሚከበረው ይህ በዓል መሠረቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ደብረ ታቦር ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀመዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደ ፀሐይ የበራበት፣ ልብሱም እንደብርሃን ነጭ የሆነበት፣ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ነው።

ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ። እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር።

ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና፡ ተነሡ አትፍሩም አላቸው። ይህ የሆነው በደብረ ታቦር ነው ፡- ታቦር እንዴት ያለች ‘እግዚአብሔር የወደዳት’ ተራራ ናት? [ደብር ዘሠምሮ እንዲል] ሐዋርያትና ነቢያት በአንድነት ቆመው የሚተያዩባት ፤ ብሉይና ሐዲስ የተዋወቁባት ፤ ጥላና አካል የተጋጠሙባት ይህች ተራራ እንዴት የተመረጠች ናት? ‘ታቦርና አርሞናዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል’ እንደተባለ ነቢያትና ሐዋርያትን በግራ በቀኙ አድርጎ በሰማያዊ አባቱ ‘የምወደው ልጄ’ ተብሎ ሲጠራ ስሙን ሰምታ ታቦር ምንኛ ደስ ይላት ይሆን? የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት አጣን እንጂ ነቅለን ወደ ሀገራችን ከምናስገባቸው ተራሮች አንዱ ታቦር በሆነ ነበር፡፡

በታቦር ተራራ ሐዋርያትና ነቢያት በአንድ ወንበር ከሊቀ ሊቃውንት ክርስቶስ ትምህርት ተምረው ተመለሱ፡፡ ሐዋርያቱ የነቢያት ጌታ መሆኑን ሲማሩ ነቢያቱ ደግሞ የሐዋርያት አምላክ መሆኑን አወቁ፡፡ ነቢያት ደክመው የዘሩትን ከሚያጭዱ አጫጆች ሐዋርያት ጋር ተዋወቁ፡፡
ነቢያት አምላክነቱን ያውቃሉ ፤ ሐዋርያት ደግሞ ሰውነቱን ያውቃሉ፡፡ በታቦር ተራራ ግን አዲስ ትምህርት ተማሩ፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ይላል ፦ ‘‘ነቢያቱ አይተውት የማያውቁትን ሰውነቱን አይተው ተደሰቱ ፤ ሐዋርያቱ አምላክነቱን አይተው ተደሰቱ’’

ሐዋርያት ደነገጡ ፤ እነርሱ ባልነበሩበት በዮርዳኖስ የተናገረውን የእግዚአብሔር አብን ድምፅ በታቦር ተራራ ሰሙ ፤ ጴጥሮስ ‘አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ’ ያለው በሰማይ ያለው አብ ገልጦለት ነበረ ፤ አሁን በልቡ ያንን ቃል ያስቀመጠውን የአብን ድምፅ ሰምቶ ዓለቱ ስምዖን በፍርሃት ወደቀ፡፡ የጌታን ፊት አብርቶ ሲያይ ሳያይ ያመነውን አምላክነቱን አወቀ፡፡ ‘ሐዋርያት በአንድ ቀን ሁለት ፀሐይ ወጥቶ አዩ ፤ አንደኛው የተለመደችው ፀሐይ ስትሆን ሁለተኛው ደግሞ የሚያበራው የጌታ ፊት ነበር’ ይላል ቅዱስ ኤፍሬም፡፡ እውነትም ስሙን ለሚፈሩ ሐዋርያት የጽድቅ ፀሐይ ክርስቶስ በታቦር ተራራ ላይ ወጣላቸው፡፡

ቅዱስ ኤፍሬም በታቦር ተራራ ነቢያትና ሐዋርያት መገናኘታቸውን እንዲህ ሲል ያደንቃል ፦
‘የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች የሐዲስ ኪዳን ጸሐፊዎችን አዩ ፤ ቅዱሱ ሙሴ ቅዱስ ጴጥሮስን አየው የአብ እንደራሴ የወልድን አገልጋይ ተመለከተው፡፡ የብሉይ ኪዳኑ ድንግል ዮሐንስ የሐዲስ ኪዳኑን ድንግል ዮሐንስን አየው፡፡ በእሳት ሰረገላ ላይ የተሳፈረው ኤልያስ ወደ እሳታዊው ክርስቶስ ደረት የተጠጋውን ዮሐንስን አየው፡፡ የታቦር ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ሆነ ፤ ክርስቶስም ሁለቱን ኪዳናት አዋሐዳቸው!’

ሐዋርያት ወድቀው ‘የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት’ የሚል ቃል ከሰሙ በኋላ ሲነሡ ከክርስቶስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም፡፡ በእርግጥም ‘የምወደው ልጄ ይህ ነው’ ተብለው ማሳሰቢያ ከተሠጣቸው በኋላ ቀና ሲሉ ማግኘት ያለባቸው ‘የሚወደው ልጁን’ ክርስቶስን ብቻ ካልሆነ አዋጁ ስለማን እንደሆነ ግራ ይገባቸው ነበር ይላል ማር ኤፍሬም፡፡

ሐዋርያት ቀና ሲሉ ሙሴ የለም ፤ ኤልያስም የለም፡፡ ለነገሩ ከሙሴም ከኤልያስም የሚልቀው ጌታ ከእነርሱ ጋር ካለ ምን ይፈልጋሉ? ባልወለደው ፈርኦን የልጅ ልጅ ተብሎ ከተጠራው ሙሴ ይልቅ ባልወለደው ዮሴፍ የዮሴፍ ልጅ ተብሎ የተጠራው ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር ነው፡፡ ከፈርኦን ሰይፍ ተርፎ እስራኤልን ነጻ ካወጣው ሙሴ የሚበልጠው ከሔሮድስ ሰይፍ ተርፎ ዓለምን ነጻ ያወጣው ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር አለ፡፡ እናቱ ሞግዚቱ ሆና ካሳደገችው ሙሴ በላይ ‘እናትና ገረድ ማርያም ደስ’ ብሏት ያሳደገችው ክርስቶስ አይሻላቸውም? ግብፃዊውን ገድሎ ለማንም አትናገሩ ከሚለው ሙሴ ይልቅ ዕውራንን አብርቶ ለምፃምን አንጽቶ ፊቱ እንደ ፀሐይ አብርቶ ለማንም አትናገሩብኝ የሚለው ክርስቶስ አብሮአቸው ካለ ምን ይፈልጋሉ፡፡ ‘የቆምህበት ሥፍራ የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ’ ተብሎ ከተነገረው ሙሴ ይልቅ ‘የጌታ እግር በሚቆምበት እንሰግዳለን’ ‘የጫማህን ጠፍር እንኳን ልፈታ አይገባኝም’ እየተባለ የተዘመረለት ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር ነውና ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት የሙሴ መሔድ አላስደነቃቸውም፡፡

ኤልያስንም ስላላዩ አላዘኑም ፤ በእሳት ሰረገላ ከሔደው ኤልያስ በላይ ልብሱ እሳት ቀሚሱ እሳት የሆነው አምላክ ከእነርሱ ጋር ነው፡፡ ኤልያስ ለደቀ መዝሙሩ ወደ ሰማይ ሲሔድ መጎናጸፊያውን ትቶለት ሔዶ ነበር፡፡ የሐዋርያት መምህር ክርስቶስ ግን ሲያርግ ልብሱን አልወረወረላቸውም፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳለ እርሱ ሲያርግ ለደቀ መዛሙርቱ የተወላቸው ልብሱን ሳይሆን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ነው፡፡ ስለዚህ ኤልያስ ቢሔድ ሙሴም ቢሰወር ደቀ መዛሙርቱ ጌታችንን ከብበው ከታቦር ተራራ በደስታ ወረዱ፡፡

ማቴ. ፲፯፡፩-፭ በቤተ ክርስቲያን ደብረታቦር ከቤተክርስቲያን ውጭ አከባበሩ ቡሄ እየተባለ የሚከበረው በዓል በሀገራችን በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡ ቡሄ ሲመጣ የክረምቱ ጨለማነት አልፎ ወደ ብርሃን፣ ወደ ጥቢ የሚያመራበት፣ ወደ መፀው የሚዘለቅበት ወገግታ ፣ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት፣ የሚሸጋገርበት ወቅት በመሆኑ ከቡሄ በኋላ የጠነከረ ክረምት አይኖርም፡፡ በዚህ መሰረት የክረምቱ አፈና ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየውም በዚህ በዓል አካባቢ ስለሆነ ይቺ ዕለት 'ቡሄ' የሚለውን ስያሜ አገኘ። ቡሄ ማለት ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት፣ ብረሃን የታየበት ድምጸ መለኮት የተሰማበት ስለሆነ፤ ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓልም ይባላል፡፡

በገጠርም ሆነ በየከተማው ልጆች ጅራፋቸውን ገምደው ሲያጮሁ ይሰነብታሉ። እናቶችም ለበዓሉ ዝግጅት ስንዴ ሲለቅሙ፣ ሲፈትጉ፣ ሲፈጩ ይሰነብታሉ። መነሻ የሆናቸው ትውፊት ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ዕለት ጊዜው ምሽት ነበር፡፡ እረኞችም ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጥተዋል ፡፡ያንን ለማስታወስ «ቡሄ» ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና ችቦ በማብራት በዓሉን የሚከበረው ከዚህ በመነሣት