Get Mystery Box with random crypto!

እንቅልፌን ተይልኝ ቁርጥ ከሆነ መራቅሽ እውነት ከሆነ ጉዞሽ ፍፁም ላትመለሽ ከቶ ላታገኝኝ የፍቅሬ | ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹

እንቅልፌን ተይልኝ

ቁርጥ ከሆነ መራቅሽ
እውነት ከሆነ ጉዞሽ
ፍፁም ላትመለሽ ከቶ ላታገኝኝ
የፍቅሬን ጩኸት ቅንጣት ሳትሰሚኝ፣
ሂጅ አልከተልሽም
ሰተሽ የነፈግሽኝ መውደድሽ ያንቺ ነው፣
ራቂ የኔ ቤቴ ይዳብዝ ጨለማ ይውረሰው፣
ግን ደግሞ አለሜ፣
አንቺን የሌለሽበት
ድቅድቅ ያለበሰኝ የፍቅርሽ ወላፈን፣
ከጨለማ ሊለቅ ህልም አለኝ እንደሆን፣
እንቅልፌን ተይልኝ
ስጋደም አትምጪ ከህልሜ ጋር
ልሁን።
ተፃፈ ደሱሱ