Get Mystery Box with random crypto!

.መልስ አልባ ጥያቄ.... በዚህ በኔ ዘመን በዚህ በኔ ጊዜ ሰው ማለት ምንድን ነው?ተብሎ ለሚጠየቅ | ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹

.መልስ አልባ ጥያቄ....
በዚህ በኔ ዘመን
በዚህ በኔ ጊዜ
ሰው ማለት ምንድን ነው?ተብሎ ለሚጠየቅ፣
መልስ የሚሆነው ጥያቄ ነው ሲረቅ፣
ኩሏን ተ'ኳኩላ
በቀለም ደ'ማምቃ
እንደ አደይ አበባ፣በአሪቲፊሻል ለዛ የምትፈነድቅ፣
ሴት ናት ትባላለች፣በንቅሳት ቀለም አካላቷ ቢደምቅ፣
በሂውማን ሄር ታጥራ፦
ተተፈጥሮን መንፍቃ፣መዋቢያ ፍለጋ በየሸቀጡ ሱቅ፣
ለሜካፕ ዘሙታ ውላ አድራለች ሴቷ ሰውነቷን ስትፍቅ፣
እስኪ ተመልከቱ፦
በደንብ አስተውሉ፣
ቆንጆ ነን የሚሉት
ውቦች ነን የሚሉት
በዘፈን እርከን ላይ የሚያሰሙት ዜማ፣
ለሰላምታ ራሱ
የሚሰቀጥጥ ድምፅ፣
ልክ እንደ ጅብ ጩኸት ጆሮን የሚያደማ፣

ህሊናውን ሽጦ፣አንሶና ኮስሶ ክብሩን የቀበረ፣
ሰፊ ጉድጓድ ምሶ፣በቃል ያሰረውን የእምነት ሰንሰለት፣
ለታይታ የሚያሳይ፣
ይሉኝታ አልባ ትውልድ፣
ወንድ ነው ያሉኝ'ለት፣ደርቄ ቀረሁኝ ቆምኩኝ ባለሁበት፣
በጣቶቹ ጥበብ፣ክፋትን ለክቶ፣
ሚስጊኑ ወገኑን፣በሚፈራርሰው ጉም ቋንቋው ገምቶ፣
አፈር የሚጋግር፣የወገኑ እምባ በደም ጎርፍ አቡክቶ፣
ለቃሉ የማይኖር ያልገዛው ህሊና ሰው እየተባለ፣
ፍቅር አልባውን ትውልዱ፦
ወንድ ነው ይለኛል በዘረኝነት ደዌ ተማርኮ እየዋለ፣

ግን ሰው የት ሄደ?
ልክ እንደ በፊቱ ፣ድሮ ድሮ ድንጋይ ዳቦ እያለ፣
ሰማይ እንዲህ ሳይርቅ፣ፍፁም ዝቅ እንዳለ፣
ፍቅርን የሚለግስ፣ሰውን በሰው አምሳል የሚመዝን ሁሉ፣
ያ የእምነት ባለ ኪዳን፣ትህትናን ያሰረ በማይሻር ቃሉ፣
የት ሄደ ሰው ሁሉ??
ተፃፈ ደሱ ለተጨማሪ መሳጭ ግጥሞችና አባባሎች

https://t.me/Desupome/764
https://t.me/Desupome/764