Get Mystery Box with random crypto!

.ሞት ያስመኜ ፍቅር.... ከሩቅ አድማስ ከ'ሩቅ ከግግሩ ሰማይ በታች ስለ ፍቅር ተንበርክኬ፣ በጎደ | ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹

.ሞት ያስመኜ ፍቅር....
ከሩቅ አድማስ ከ'ሩቅ
ከግግሩ ሰማይ በታች ስለ ፍቅር ተንበርክኬ፣
በጎደለው ማንነቴ
ሙሉ ሁነሽ ስትደምቂ እኔነቴን ተማርኬ፣
ሳታውቂልኝ አፈቀርኩሽ፣
ስለ ፍቅርሽ ገጠምኩልሽ፣
በጣቶችሽ ጥበብ
የስታየን ሊለካ ምስልሽ በልቤ ጎጆውን ቀለሰ፣
ዝም ያለው ሂዎቴን
ፍቅርሽ አፍ አውጥቶ ሰርስሮት አረሰ፣
ሁሌም ታምር ሰሪው አንቺን ቀማሪ አድርጎሽ፣
እኔ ተቀማሪ
ነፍሴን ሀሴት ሞላት ጣርና ሰቀቀን ከማጀቷ ሲሸሽ፣
ጉድለቴን ስትሞይው፣
ወንድነቴን ስትረችው፣
ስለ ፅኑ ፍቅርሽ ላንጎራጉር ክራሬን አማተርኩ፣
በጥልቅ ተመስጦ
በእዝልና አራራይ ክብርሽን አወደስኩ፣
የመውደዴን ፅናት የደስታዬን ብስራት በዜማዬ ነገርኩ፣
ደግሞስ አንቺ ማለት ውዴ፣
ለእይታ ብቻ እንኳን ቀልብን የሚሰርቁ፣
በብዙ አይነት ቀለም ዉበት እዬተፉ ዉበት በሚያስንቁ፣
ዕልፍ አበባ አግኝቼ ቀልቤ ቢሰረቅም፣
እዉነት እልሻለዉ፦
አንቺን የሚመስል ከአበቦቹ ሁሉ አበባ አይገኝም፣
ከአይንሽ የሚተነዉ የፍቅር እንፋሎት፣
የመንፈስ ስንቄ ነዉ እንደ ዘዉትር ፀሎት፡፡

እንኳንስ ተበልተዉ ገና ሲያዩዋቼዉ ፣
ጣፋጭ የሚለዉ ቃል
ጣፍጦ እማይገልፃቼዉ ጥዑም ፍራፍሬ፣
ለመብላት ስጣደፍ ምላሴን ነክሼ ደም ሳዘራላቼዉ፣
መድማቴ እስኪጠፋኝ
አዎይ ጣም እያልኩኝ እጅግ ብደነቅም፣
እወዉነት እልሻለዉ
ከከንፈርሽ በላይ ከፍሩቱ ሁሉ ጥፍጥናን አላውቅም፣
ደግሞስ ብትይ ፍቅሬ፦
በእቅፍሽ ሰማዬሰማያት በገነትሽ መንበር፣
ለኔ ልበ ባተሌው ፍቅርሽ ሲዘራ ህያው ሁኜ ለመኖር፣
እጉያሽ ስር ሞቴ ይሁን
በፅድቅሽ አድማስ ሁሉ የኔ ገነት እንዲፈጠር።
ተፃፈ ደሱ ለተጨማሪ መሳጭ ግጥሞችና አባባሎች

https://t.me/Desupome/764
https://t.me/Desupome/764