Get Mystery Box with random crypto!

CHANNEL 29

የቴሌግራም ቻናል አርማ channel29news — CHANNEL 29 C
የቴሌግራም ቻናል አርማ channel29news — CHANNEL 29
የሰርጥ አድራሻ: @channel29news
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.94K
የሰርጥ መግለጫ

For any Information related Things @Ch29Bot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-18 20:51:40 በሱዳን ጉዳይ የሃያላን ሀገራት ፍላጎትና አሰላልፍ ምን ይመስላል?

የሃያላኑ የፍላጎት ተቃርኖ ካርቱምን የእጅ አዙር ጦርነት መፋለሚያ ሜዳ ያደርጋት ይሆን ?
~ ~ ~
የሱዳን ጦርና የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ (አርኤስኤፍ) ውጊያ ዛሬ አራተኛ ቀኑን ይዟል።

አሜሪካና ሩሲያን ጨምሮ በርካታ ሀገራትም ተፋላሚዎቹ ተኩስ አቁመው ወደ ድርድር እንዲመጡ ጥሪ ማቅረባቸውን ቀጥለዋል።

ለግጭቱ የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ወደ ብሄራዊ ጦሩ መቀላቀል አለመፈለጉ እንደምክንያት ቢነሳም ከጀርባ በርካታ ገፊ ምክንያቶች እንዳሉ ተንታኞች ያምናሉ።

ከ2019ኙ መፈንቅለ መንግስት ወዲህ የሲቪል አስተዳደር ለመትከል ሞክራ ወዲያው የከሸፈባት ሀገር አደባባዮቿ ሰርክ በተቃውሞ ሰልፎች ቢሞሉም መረጋጋት አልቻለችም።

ምርጫ እስኪደረግ ድረስ የሽግግር መንግስት ለመመስረት ፖለቲከኞቿ ሲያደርጉት የከረሙት ውይይትም ወደ ፍጻሜው ሲቃረብ ኦማር ሀሰን አልበሽርን በጋራ ያስወገዱት ጀነራሎች በጠላትነት ተፈራርጀው ጦር ተማዘዋል።

በሁለቱም ወገን ያሉ “አይዞህ ባዮች” የምስራቅ አፍሪካዊቷን ሀገር መከራ ስለማብዛታቸው ነው የሚነገረው።

የሱዳን ጦር አዛዡ አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና የአርኤስኤፍ መሪው ጀነራል ሃምዳን ዳጋኦ (ሄሜቲ) ልዩነት እንዲሰፋም የተለያየ ፍላጎት ያላቸው ሀገራት ድርሻ በቀላሉ የሚታይ እንዳልሆነ ተንታኞች ይሞግታሉ።

ሩሲያ

ሩሲያ ኦማር ሃሰን አልበሽር በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣናቸው ከመነሳታቸው በፊት ከሱዳን ጋር አንድ ስምምነት ፈጽማለች፤ በፖርት ሱዳን ወታደራዊ ማዘዣ መገንባት የሚያስችል ስምምነት።

ስምምነቱ ሞስኮ 300 ወታደሮች እና አራት የጦር መርከቦቿን የምታሰፍርበትና በቀይ ባህር ቅኝት የምታደርግበትን እድል የሚፈጥር ነው።

ለ25 አመት ይቆያል የተባለው ስምምነት ካርቱምን ከሩሲያ የጦር መሳሪያ እንድታገኝ የሚያደርግ እንደነበርም አሶሼትድ ፕረስ በዘገባው ያወሳል።

ይህ ስምምነት በፓርላማ ሳይጸድቅ ግን አልበሽር በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣናቸው ተነስተዋል።
ሞስኮ ባለፉት አመታት ከሱዳን ወታደራዊ መሪዎች ጋር በስምምነቱ ዙሪያ ስትመክር ቆይታለች።

የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ መሪ ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎም ለአንድ ሳምንት በሞስኮ ቆይታ አድርገው ሲመለሱ አዎንታዊ ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል።

ሄሜቲ በዚህ ጉብኝታቸው ከቭላድሚር ፑቲን ሀገር የተገባላቸው ቃል ባይገለጽም የኦማር ሃሰን አልበሽር አስተዳደር ቀደም ብሎ የጠየቀው የጦር መሳሪያ ድጋፍ በአጻፋው እንደሚሰጣቸው የሚገምቱ ተንታኞች አሉ።

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በሱዳን ባደረጓቸው ጉብኝቶችም የወታደራዊ ጣቢያው ጉዳይ ዋነኛ መነጋገሪያ ርዕስ እንደነበር የሮይተርስ ዘገባ ያመላክታል።

ባለፈው ቅዳሜ ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ የሚመሩት ፈጥኖ ደራሽ ሃይል ከሱዳን ጦር ጋር መፋለም ሲጀምር የሩሲያ ስም አብሮ እየተነሳ ነው።

የሩሲያው ቅጥረኛ ወታደሮች አቅራቢ ዋግነር ለሄሜቲ ከለላ እየሰጠ ነው የሚሉ ሪፖርቶችም ወጥተዋል።

በሱዳን የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ ግን ሁለቱም ወገኖች ግጭት አቁመው ወደ ጠረጼዛ ዙሪያ ንግግር እንዲመለሱ ከመጠየቅ ውጪ ለሚቀርቡ ወቀሳዎች ምላሽ አልሰጠም።

አሜሪካ

የሱዳን ወቅታዊ ሁኔታን በቅርበት እየተከታተልኩ ነው ብላለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አንቶኒዮ ብሊንከንም ከጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ ጋር በስልክ መምከራቸው ተገልጿል።

በውይይቱ በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለማንቀሳቀስና ንጹሃንን ለመጠበቅ ለ24 ስአት ተኩስ ለማቆም ተስማምተናል ያሉት ሄሜቲ፥ የአልቡርሃን ጦር ድብደባውን ገፍቶበታል ሲሉ ከሰዋል።

ይህንን አለማቀፍ ህግ የመጣስና ሌሎች ጉዳዮች በተመለከተ ከአሜሪካ ጋር በቀጣይ እንመክርበታለን የሚል መልዕክታቸውንም በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

ይህም ከዋሽንግተን የተለየ ድጋፍ ያላቸው መስሎ መታየትን መፈለጋቸውን አልያም ከብሊንከን ጋር ባደረጉት ውይይት የተገባላቸው ቃል ስለመኖሩ የሚያመላክተው ነገር እንደሚኖር ይታመናል።

የዋሽንግተን ግልጽ አሰላለፍ እስካሁን በይፋ ባይገለጽም ፍላጎቷ ግን ግልጽ ነው፤ ሩሲያ በፖርት ሱዳን ልትገነባው ያሰበችውን ወታደራዊ ጣቢያ ከንቱ ማድረግ። ለዚህም አሸናፊ ይሆናል ብላ ላመነችበት ሃይል ድጋፍ ልታደርግ እንደምትችል ነው ወታደራዊ ተንታኞች የሚያነሱት።

ሄሜቲ ከሁለቱ ባላንጣ ሃያላን ሀገራት ድጋፍ እንዳላቸው ቢነገርም ወይም መስለው ቢታዩም፥ የሱዳንን ጦር የሚመሩት ጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃንም በፊናቸው አጋር አላቸው።

ከአሜሪካ እና ሩሲያ ባሻገር የጎረቤት እና የቀጠናው ሀገራት ፍላጎትና የሃይል አሰላለፍ ሱዳንን እንደ ዩክሬን የሃያላኑ የእጅ አዙር መፋለሚያ ምድር እንዳያደርጋት ያሰጋል።

የሱዳናውያን የለውጥ አቢዮት በውጭ ሃይላት ጣልቃገብነት እንዳይጠለፍም ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል እየተባለ ነው።

ምንጭ ~ #አል_ዐይን_ኒውስ
2.7K viewsEl Tigre, 17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 13:28:02

5.5K viewsEl Tigre, 10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 11:26:01
My love
6.2K viewsEl Tigre, 08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 10:17:11
#ፋኖዬ_ውርደትህ_ቀጥሏል..

ከጎንደር ተነስቶ ፊንፊኔ ሊገባ የነበረ ፋኖ ደብቆ ከያዘው የጅብ ኮቴና ልብ እንዲሁም ክላሽ ጋር ሰላሌ አለልቱ ላይ በፍተሻ ተይዟል።

ከጥንቆላ ድግምትና ስልብና የሚላቀቁት መቼ ይሆን? የመከነ ኃላቀር አስተሳሰብ!
6.4K viewsEl Tigre, 07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 09:05:05
6.4K viewsEl Tigre, 06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 08:05:15 የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከጠላት ጋር መተባበርን ጨምሮ ሕወሃት በጦርነቱ ወቅት ባወጣቸው 30 ክልከላዎች የታሠሩ ግለሰቦችን ለመፍታት መወሰኑን ቪኦኤ ዘግቧል።

ውሳኔው ምርመራ ላይ የሚገኙ፣ በክስ ሂደት ያሉና በፍርድ ቤት ውሳኔ የታሠሩ ግለሰቦችን እንደሚመለከት ቢሮው መናገሩን የገለጠው ዘገባው፣ ሰው የገደሉ፣ ጾታዊ ጥቃት ያደረሱ ወይም ከኤርትራ ጋር የተባበሩ ግን ውሳኔው አይመለከታቸውም መባሉን ዘገባው ጠቅሷል።

በውሳኔው መሠረት የሚፈተት እስረኞች ብዛት ስንት እንደኾነ ግን ቢሮው አልተገለጠም ተብሏል።

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እስረኞችን ለመፍታት የወሰነው የሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ በእስር ላይ መቆየታቸው አስፈላጊ ስላልኾነ መኾኑን ቢሮው መግለጡን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።
6.5K viewsEl Tigre, 05:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 08:04:58 ብሪታኒያ "ሕገወጥ" ያለቻቸውን ጥገኝነት ጠያቂዎች ሩዋንዳ ውስጥ ለማስፈር ሁለቱ አገሮች የደረሱበትን ስምምነት ማሻሻላቸውን ዘ ኢስት አፍሪካን ጋዜጣ ዘግቧል።

በስምምነቱ ላይ አዲስ በተጨመረው አንቀጽ መሠረት፣ ብሪታኒያ ጥገኝነት ያልጠየቁ ስደተኞችንና ፍልሰተኞችን ጭምር ወደ ሩዋንዳ እንደምትልክ ዘገባው ጠቅሷል።

ማሻሻያው፣ ሩዋንዳ ጥገኝነት ያልጠየቁ ስደተኞችን ከተቀበለች በኋላ ወደ አገራቸው እንድትልካቸው መብት እንደሚሰጣት ዘገባው ጠቅሷል።

የብሪታኒያ ፍርድ ቤት ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ የመላኩ ውሳኔ ሕጋዊ ነው በማለት መወሰኑ ይታወሳል።
6.2K viewsEl Tigre, edited  05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 08:03:51 በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ብረት ለበስ ተሽከርካሪው " ሆን ተብሎ " በጥይት መደብደቡን ኢምባሲው ያስታወቀ ሲሆን ድርጊቱን የፈፀመው ሄሜቲ የሚመሩት RSF ቡድን መሆኑን ኤምባሲው ለአል አረቢያ ገልጿል።

ኤምባሲው ተሽከርካሪው በ100 ጥይት መደብደቡን ገልጾ ድብደባው ያደረሰው ምንም ጉዳት የለም ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ የአሜሪካ መንግሥት ጦርነት ውስጥ ካለችው ሱዳን ዜጎቹን የማስወጣት እቅድ እንደሌለው ዋይትሃውስ አሳውቋል።

በተያያዘ ዜና በሱዳን ካርቱም ሚገኙት የአውሮፓ ህብረት (EU) አምባሳደር በመኖሪያ ቤታቸው ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ተሰምቷል ።

አምባሳደሩ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ያሳወቁት የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ዲፕሎማት ጆሴፕ ቦሬል ናቸው (በትዊተር ገፃቸው)።

ቦሬል ስለ ጥቃቱ ምንም አይነት ዝርዝር ነገር ባይገልጹም አምባሳደሩ ግን " ደህና ናቸው " ብለዋል።

የዲፕሎማቲክ ቦታዎችን እና ሰራተኞችን ደህንነት ማስጠበቅ የሱዳን ባለስልጣናት ቀዳሚ ኃላፊነት ነውም ሲሉ ገልጸዋል።

ምንም እንኳን ቦሬል ፤ በሱዳን የአውሮፓ ህብረት አምባሳደርን ስም ባይፅፉም ስማቸው አይዳን ኦሃራ የሚባሉ ሲሆን የ #አየርላንድ ዲፕሎማት ናቸው።

ቦሬል ካርቱም ውስጥ የተፈፀመው ጥቃት ፤ በሌሎች ሀገራት የሚሰሩ ዲፕሎማቶች ጥበቃን የሚደነግገውን  የተመድ ስምምነት የ " ቪይና ኮንቬንሽን " በእጅጉ የጣሰ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ የአውሮፓ ህብረት ቃል አቀባይ ናቢላ ማስራሊ ለAFP በሰጡት ቃል " የሰራተኞች ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው " ብለዋል፤ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት ልዑካን ቡድን ከካርቱም እንዲወጣ እንዳልተደረገ ተናግረዋል።

ቃል አቀባይዋ ፤ በሱዳን ያለው የፀጥታ እና ደህንነት ሁኔታ እየተገመገመ ነው ብለዋል።

ተመድ በሱዳን ጦር ሠራዊትና በፈጥኖ ደራሽ ሠራዊቱ መካከል በቀጠለው ግጭት ከ180 በላይ ሰዎች መገደላቸውንና ከ1800 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን አስታውቋል።

አሜሪካ የሱዳኑ ግጭት ባስቸኳይ እንዲቆም ከጀኔራል ቡርሃንና ከጀኔራል ሞሐመድ ደጋሎ ጋር ግንኙነት እያደረገች መኾኗን አስታውቃለች።

የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በበኩሉ፣ ግጭቱ ሱዳናዊያን ብቻ የሚፈቱት የውስጥ ጉዳይ ነው ሲል ትናንት ማምሻውን አስታውቋል።

ሚንስቴሩ፣ የሱዳን ጦር ሠራዊት ወታደራዊ ጠቅላይ መምሪያውን፣ ቤተ መንግሥቱን፣ የካርቱም አውሮፕላን ማረፊያንና ብሄራዊ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጣቢያውን "አማጺ" ሲል ከፈረጀው ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት ማስለቀቁን የገለጠ ሲሆን፣ የጀኔራል ደጋሎ ኃይሎች ግን ያስተባብላሉ።
6.2K viewsEl Tigre, edited  05:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 08:03:39
5.8K viewsEl Tigre, 05:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 23:28:56
ወርቅ ህዝብ Night
1.9K views TIGRAY , edited  20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ