Get Mystery Box with random crypto!

✎የፍቅር ጥቅሶች||™

የቴሌግራም ቻናል አርማ bast_love_quotes — ✎የፍቅር ጥቅሶች||™
የቴሌግራም ቻናል አርማ bast_love_quotes — ✎የፍቅር ጥቅሶች||™
የሰርጥ አድራሻ: @bast_love_quotes
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 17
የሰርጥ መግለጫ

ሰው ስሜቱን ይገልፅ ዘንድ ብዕር ተሠጠው!✍💔📚◆━━━━━━━✎✦✎━━━━━━━━◆
Contact us:⤵️📞
📩 || @Bast_Love_Quotes_Robot

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-12-02 10:10:56
እንዲቀልህ 17

ከጓደኞችህ ጋር ያለህ መስተጋብር ምን ይመስላል?
ስላንተ ምን ያህል ቦታ አላቸው???? ንግግርህን ምን ያክል ይሰሙሀል???? ስሜትህን የቱን ያክል ይረዱታል???? ፍላጎትህን ምን ያክል ያስቀድሙልሀል??? ቁጣህን እስከየት ይታገሱሀል????
በነዚህ ውስጥ የምታገኘው መልስ ሁሉ ትክክል ካልሆነ ራስህን ከዚህ ግንኙነት አርቅ። ኖሮ ያልጠቀመ ሄዶ አይጎዳምና አዳዲስ ሰዎችን ልመድ ለራስህ ባለህ ክብር ልክ ግንኙነቶችን መስርት ....መስመርህን ለሚያልፍ ምህረት አይኑርህ !!!!...ጠንካራነት ስምህ ብቻ አይሁን ማንነትህም አድርገው ሰው ባይኖርህ እንኳን ብቻህን ታምራለህ ከሚንቁህ ጋር አትወዳጅ።


ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
764 views@m måkï , 07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-01 20:09:54
እጅህን ከዘረጋህላቸው ሁሉ መልካም ምላሽን አትጠብቅ አንዳንድ እጆች ምቾትን አይሹም።

ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
1.6K views@m måkï , 17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-28 08:56:55
አንድ ወዳጄ በተደጋጋሚ እንደዚህ አይነት ፎቶዎችን ቴሌግራም ፕሮፋይሉ ላይ ያዘወትራል ታድያ እሱ ዘንድ ሁሌም ይህንን ፎቶ ሳይ ልቤ ድንግጥ ይልብኛል እንዲያጠፋውም እነግረዋለው ውስጡ ምን እንዳለ ባይገባኝም ሲያጠፋው ደስ ይለኛል እርግት እላለው

እናም አሰብኩት.... አንዳንዶች የሚገጥማቸውን ተስፋ መቁረጥ ,,,,,,,መሰበርና ,,,,,,,መውደቅ ይሆን እንዴ በዚህ መንገድ የሚገልፁት ?????ምን ያህሎቻችንስ ነን እነዚህን መሰል ፎቶዎች ከቅርባችን ካለ ሰው ስናይ ችላ ብለን የምናልፋቸው?????? ላቀዱት ነገ መንደርደሪያስ ቢሆን እያስጠነቀቁን ....እየተሰናበቱን እኛም በዝምታ እየሸኘናቸው ቢሆንስ?? እላለው!!!!

ያሰጋኛል!!!! ባጣውስ አይነት ፍርሀት.....
ዛሬ ያየነውን ነገ ላይ ማጣት በተለመደበት በዚህ ወቅት እንዲህ ምልክት የሚያሳዩን ቀዩን መስመር ልለፍ.... አልለፍ አይነት ጥያቄ ቢሆንስ እላለው..????? ዝምታችን በርቱ ይሆንላቸው ይሆን????

አንዳንዴ.... አይሆንም.. አያደርገውም ብለን የምንሞግትለት ሰው ድንገት ቢያደርገውስ ማለት አይከፋም እሱስ ሰው አይደለ??? ተስፋ መቁረጥ ቢቃኘውስ?......... ድባቴ ቢያጠቃውስ?? ይልቅ ለራቅናቸው እንቅረብ አይተን ባላየ አንለፍ እላለው!!...

ከጎንህ ነኝ ማንን ገደለ

ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
1.1K views@m måkï , 05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-27 18:54:41
በወደቅሽ ቁጥር የእንባ ትርፉ ሌላ ህመም መምዘዝ እንደሆነ እወቂ።
ትከሻን ማቅናት እድሜ ከመቁጠር ወደ መኖር የሚታደግበት ሀ ሁ ነው። ለሙሾ ወራጆች ተፈጥሮ ሁሌም ለቅሶ አታጣም።
ለእንባሽ ፊት አትስጪው።

ሳሙኤል ደረጄ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
1.2K views@m måkï , 15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-26 13:06:49 ✎የፍቅር ጥቅሶች|| pinned a photo
10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-26 13:06:34
እንዲቀልሽ 16

ማንንም እንዳትለምኚ ለምነሽ የምታቆይው ግንኙነት አይጠቅምሽም ይቅርብሽ ፈልጎ ወዶሽ ከጎንሽ ካልሆነ ልመና መፍትሄ አይሆንም ያዝ ለቀቅ ከሆነብሽ ለቀሽ አሳርፊው አንዳንዴ መጨከንን ቻይበት የዋህ ብቻ አትሁኚ ጥንካሬም ውበት አለው ልብሽን በተስፋ ብቻ አትቅጭው ሌሎች ያልሞከርሻቸው እድሎች አሉሽ እነሱን ልብ በይ።

#እህቴዋ ነገ ላይ የሚቆጭሽን የማትመልሽውን እድሜሽን አስቢ ጊዜሽን አስተውይ ለማይረባ አታባክኚው!!

ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
1.2K views@m måkï , edited  10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-22 20:35:46 አንዳንዶች ዘጠኝ ጣቶችህን ለኩሰህ ብታበራላቸው፣ አሥረኛው የታለ ብለው ይጠይቁሃል!

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
1.1K views@m måkï , 17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-19 13:14:25 ✎የፍቅር ጥቅሶች|| pinned « መልካም ልደት ለኔ ከሌሎቹ ወቅቶች በበለጠ የልደቴ ቀን ልዩ ሆኖ ይታየኛል.... ምን የተለየ ባይኖር እንኳን ጀንበር ከምሽጓ ስትወጣ ለኔ የወጣች ፣ ቀኑ ለኔ የነጋ ፣ ፀሀይ ለኔ የበራች ፣ ወፎች ለኔ የዘመሩ ፣ ንፋስ ለኔ የነፈሰ ይመስለኛል። እያንዳንዱ ነገር ለኔ የሆነ ያክል በሁኔታዎች ስደመም ስደነቅ አልፋለው..... ለልደቴ ብስራት እንደሆኑ ይሰማኛል••••• ቀናትን እየጨመረ እድሜን…»
10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-19 13:09:08 መልካም ልደት ለኔ

ከሌሎቹ ወቅቶች በበለጠ የልደቴ ቀን ልዩ ሆኖ ይታየኛል.... ምን የተለየ ባይኖር እንኳን ጀንበር ከምሽጓ ስትወጣ ለኔ የወጣች ፣ ቀኑ ለኔ የነጋ ፣ ፀሀይ ለኔ የበራች ፣ ወፎች ለኔ የዘመሩ ፣ ንፋስ ለኔ የነፈሰ ይመስለኛል። እያንዳንዱ ነገር ለኔ የሆነ ያክል በሁኔታዎች ስደመም ስደነቅ አልፋለው..... ለልደቴ ብስራት እንደሆኑ ይሰማኛል•••••
ቀናትን እየጨመረ እድሜን እየሰጠኝ ህያውነትን ለኔ መርጦ መኖርን ለሚሽልመኝ አምላኬ ምስጋናን ከማበርከት ጋር.......



ህዳር 10 የመገኘት ቀኔ

ማኪ ነኝ
10-3-2015
135 views@m måkï , 10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-16 23:06:11
ስትስቅልኝ

ኩርፊያ ምን እንደሆነ ይጠፋብኛል ማዘን የሚባለው ነገር ስለመኖሩ እጠራጠራለው ስትስቅልኝ ለአይኔ ውብ የነበሩ ሁሉ በአይኔ ሚዛን ይወድቃሉ ውብ አንተ ብቻ ትሆናለህ ፍቅር ሳቅህ ብቻ ይመስለኛል ሁሌም እንደአዲስ ፍቅር የሚያሲዝ አንዳች ምትሀት አለው
ስትስቅ ታደክመኛለህ ግራ ገባኝ እኮ አትሳቅ ልበልህ እንዴ?

ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
1.9K views@m måkï , 20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ