Get Mystery Box with random crypto!

✎የፍቅር ጥቅሶች||™

የቴሌግራም ቻናል አርማ bast_love_quotes — ✎የፍቅር ጥቅሶች||™
የቴሌግራም ቻናል አርማ bast_love_quotes — ✎የፍቅር ጥቅሶች||™
የሰርጥ አድራሻ: @bast_love_quotes
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.09K
የሰርጥ መግለጫ

ሰው ስሜቱን ይገልፅ ዘንድ ብዕር ተሠጠው!✍💔📚◆━━━━━━━✎✦✎━━━━━━━━◆
Contact us:⤵️📞
📩 || @Bast_Love_Quotes_Robot

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-05-05 19:52:42 ...

ደሞ አንዳንዴ ጥፋት ለመባል አቅም በሌላቸው ነገሮች እንኳን ብሽቅ ፣ እርር ፣ ድብን የምትሉባቸው ሰዎች የሉም??
ሌላ ሰው ቢያደርገው ምንም የማይመስላችሁን ነገር ልክ ለነሱ ሲሆን ከሱ ሌላ ከባድ ጥፋት የሌለ ይመስል የምትናደዱባቸው ፣ ይቅርታ ቢጠይቋችሁም የማትቀበሏችው ችክ ምንችክ የሚያረጉ ስሜቶች .....

ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
6.4K views@m måkï , 16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 19:31:25
እንጠብቃለን

ብዙ ቃላቶችን በአይምሮዋችን እንስልና ከስልካችን ስክሪን ላይ ማየት ያምረናል የፈለግነውን መባል እንፈልጋለን እንጠብቃለን።

አይናችንን አይተው የሚረዱንን ሰዎች እቅፋቸው ውስጥ ሽጉጥ የሚያደርጉንን ክንዶች
እንጠብቃለን።

ትከሻችንን ቸብ ቸብ አርገው አይዞን የሚሉንን የሚያጀግኑንን የሚያበረቱንን ሰዎች
እንጠብቃለን።

ተስፋ በቆረጥንበት ሰአት አለው የሚሉንን እጃችንን ይዘው ካቆምንበት የሚያስቀጥሉንን በተስፋ ያለንበትን የሚያሳልፉንን

ብቻ አንዳንዴ እንደዚህ አይነት ሰዎችን ህይወታችን ላይ እንጠብቃለን።

ማኪ
✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
7.0K views@m måkï , 16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 20:10:13

አንዳንዴ ከስርአት የወጡ ንግግሮች በጣም ያስጠላሉ!! ለንግግራቸው ለከት የሌላቸው... እንዳመጣላቸው የሚዘላብዱ... ሰሚው ላይ የሚፈጠረውን መታወክ ለሰከንድ የማያስቡ... እግር አለኝ ብለው እንደልባቸው የሚንቦጫረቁ... መረን የለቀቁ.. ስርአት የሚባል ባለፈበት ያለፉ የማይመስሉ.... በህይወታቸው ላይ የታዩ ጥቂት ለውጦች ስልጣኔ ላይ ያደረሳቸው የሚመስላቸው..... እንዳሻቸው እንደልባቸው የሚቦኩ...  ምክር ፣  ተግሳፅን ሁሉ በንቀት የሚመልሱ. .  ሊመልሳቸው የሚለፋን የሚገፉ ,, የሚዘልፉ ብቻ እንዲህ ያሉ አስነዋሪ ሰዎች ገጥመዋችሁ አያውቁም???
          
      ብቻ ብቻ......

አወዳደቃችሁን ያሳምረው ሌላ ምን ይባላል።

ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
9.7K views@m måkï , 17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 18:29:46 ✎የፍቅር ጥቅሶች|| pinned a photo
15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 18:29:34
እንዲቀልህ 31
  
   ላንተ ተብለው ካልተፃፉ ላንተ የማይሆኑ ነገራቶች አሉ.... ዙሪያህን ልብ በል !!still አሁን ድረስ እየለፋህባቸው ያሉ ..ነገር ግን መቼም ያንተ የማይሆኑ ነገራቶች ላይ ጊዜና ጉልበትህን እያባከንክ ትገኝ ይሆናል .....ወንድሜ !!! በቃ ያንተ ከሆነ የትም አይሄድም... ሰበብ ለማድረስ ከሆነ ደግሞ እስካሁን የለፋኸው ይበቃል .....አቁም በቃ!!! መንገድ ቀይር ..አይንህን ከዛ ነገር ላይ አንሳ ...ያንተ ወደሆነው ሂድ!! ሙጭጭ አትበል ..

ላንተ ከተባለ ወጣም ፣ ወረደም ፣ አበጠም ፣ ፈረጠም የትም አይሄድም ያንተ ነው።
   ጊዜ ግን ወሳኝ ነው! አትቸኩልበት በጊዜው ይሰጥሀል።

ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
940 views@m måkï , 15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 19:39:50 ✎የፍቅር ጥቅሶች|| pinned a photo
16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 19:39:43
እንዲቀልሽ 30

ሂጂ እስኪ..... እግርሽን ብቻ ለመራመድ አትጠቀሚው.... ባታውቂው ነው እንጂ ልብም እኮ ይሄዳል..... ልብሽን ራቅ በይበት,,,,,, ከሚያሳዝኑሽ ፣ ከሚያከስሙሽ ፣ ከሚሸኑቁሩሽ ፣ ከሚያደሙሽ... ሁሉ ወደራስሽ ...ወደውስጥሽ... ከልብሽ ..ወደልብሽ.. ሂጂበት.. ተሸሸጊበት።

#ጠንክሪልኝማ

ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
1.2K views@m måkï , 16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 21:35:46 ✎የፍቅር ጥቅሶች|| pinned a photo
18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 21:34:32
እንዲቀልህ 29

አንዳንዴ መተውን መልመድ አለብህ ህመም አለው ግን ለልብህ ፊት አትስጠው ሁሉም ነገር ያልቃል ነገሮችን ከዜሮ መጀመር አታስብ ካቆምክበት ቀጥለው አራት ነጥብን ብቻ ተጠቅመህ ዝጋው።

ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
1.0K views@m måkï , 18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 15:44:07

ስለምንም ስለማንም አይደለም ዛሬ ላይ ስሜት አልባነትን ማለፍ የከበዳት እኔነት ላይ ደርሻለው።
..... ድብርት አካልና መንፈስ ለብሶ ከጎጆዬ ኑሮ ቀልሷል..... የሚወራ ፣ የሚነገር ፣ የሚተነፈስ ፣ ሁላ አልጥምሽ ብሎኛል.... እጅግ ይከፋኛል !!!በህይወቴ ላይ "እጅግ በጣም ትልቅ ዋጋ ያለውን ነገር አጥቻለው" የሱ አይነት ድጋሚ ማግኘቴን እንጃ!! ለአፅናኝ የማይመች.... አይመልሱልኝ ከባድ/.. አያፅናኑኝ አይቻል ሆኖ ነገሩ ለአፅናኝም ከብዷል።
   አዲስ ነገሮች ሰተት ብለው ህይወቴ ውስጥ ተቀላቅለዋል... መላመዱን ልለምደው አልቻልኩም!! ያጣሁት ላይ ልቤ ሄዷል... ይሄ ግራ መጋባት አይደለም!! ማዘንም አይሆንም!!
ስሜት አልባነት ይሆን እላለው?

ብቻ ብቻ...

ስለ ሁሉም እሱ ያውቃል።

ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
1.3K views@m måkï , 12:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ