Get Mystery Box with random crypto!

✎የፍቅር ጥቅሶች||™

የቴሌግራም ቻናል አርማ bast_love_quotes — ✎የፍቅር ጥቅሶች||™
የቴሌግራም ቻናል አርማ bast_love_quotes — ✎የፍቅር ጥቅሶች||™
የሰርጥ አድራሻ: @bast_love_quotes
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.09K
የሰርጥ መግለጫ

ሰው ስሜቱን ይገልፅ ዘንድ ብዕር ተሠጠው!✍💔📚◆━━━━━━━✎✦✎━━━━━━━━◆
Contact us:⤵️📞
📩 || @Bast_Love_Quotes_Robot

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-01-19 20:02:50 ምን እናድርግ??.....

ውጣውረዶች እኛነታችን ላይ ስልጣን ሲኖራቸው..... እኛው ላይ የሚደረጉ ነገሮችን እኛ መወሰን የማንችልባቸው ሁኔታዎች ሲፈጠሩ .....ድንገተኛ ውሳኔዎች ሁነቶቻችን ላይ ጣልቃ ሲገቡ....... ወደፊት ብለን ያሰብነው ደስታ አፈር ሲለብስ ......ጭቅጭቅ ፣ ንትርክ ፣ በቀል ፣ እልህ ፣ ጭካኔ ፣ ጥላቻ ፣ ወደፊታችን ላይ እሻራውን ሲጥል...... ሀሳባችንን መቀየር ወደ ዃላ መመለስ ሲያቅተን.... ወደፊታችን ሲያስጠላን ....ግን ደግሞ ባንፈልግም , ባንወድም እግራችንን ወደፊት ሲራመድ ስናገኘው ምን እናድርግ???

ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
1.3K views@m måkï , edited  17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 06:36:47
እንዲቀልህ 22

ከጨረቃ ጋር ወዳጅነት ኖሮህ ያውቃል?.... ወደሰማይ አንጋጠህ አውርተህ ታውቃለህ?.... ልብህን ምን ያህል ጊዜ ቦታ ሰጥተኸዋል? ......አልሸነፍ ባይነትህ እስከየት እንዲወስድህ ፈቀድክለት?...... ፍቅርን ሽሽት ምን ያህል ርቀት ተጓዝክ?.... ፍቅርን ለማግኘትስ ምን መስዋትነት ከፈልክ? ....የቱስ ቀለለህ?

#ጀግናዬ ውጣ ውረዶችህ አድካሚ የሚሆኑብህ ስታስበው ፈገግ የሚያስብልህ ነገር ህይወትህ ላይ ከሌለ ብቻ ነው።. ድካምህን የሚያስረሳ...... ጭንቀትህን የሚያባርር .......ከሀዘንህ የሚያፅናናህ....... ምንም ይሁን ግን አንድ ነገር መውደድ አለብህ.....ከንፋስ ሽውታም ቢሆን ፍቅር ይያዝህ..... ሁሉንም ነገር ከሴቶች ጋር አታገናኘው እንጂ!!!አሀ!!!! ልብ እኮ ለወንዶችም ተሰጥቷል። .....ሰውን ውደድ ወይ ተፈጥሮን ውደድ ብቻ ምንም ይሁን ልብህን ውደድበት።

ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
889 views@m måkï , 03:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 06:05:50
እንዲቀልሽ 21

ነገሮችን ባላየ ማለፍን ልመጂ...... የማይጠቅሙሽን ነገሮች ህይወትሽ ላይ ምንም የማይጨምርና ...የማይቀንሱን ነገሮች በመዝለል ላይ በርቺ .....ትተሽ ያለፍሻቸውን ነገሮች ዞረሽ ባለማየት ላይ ጀግኚ ......ላልሆንሻቸው ስያሜዎችሽ መልስ በመስጠት ላይ አትገኚ .......በቀኖችሽ ውስጥ የሚጠቅምሽን ብቻ ዝገኚ!!!!!

#እቴ ትኩረት አልባ ሁኚ ማለቴ አይደለም ነገር ግን መርጠሽ ትኩረት ስጪ የማይጠቅምሽን እያሰብሽ እንቅልፍ አተሽ አትደሪ ነቃ በይ።

ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
257 views@m måkï , 03:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 19:12:37
ልክ እንደዚህ በሆኑ ወቅቶች ላይ የእግራችን አሻራዎች የታተሙበት ይመስል የተመላለስንባቸውን ቦታዎች ጊዜያት ሲሄዱ ትውት እርስት የምናደርጋቸው አቅጣጫቸው ሳይቀር የሚጠፉብን ቦታዎች አሉ ባሉበት የማይቆዩ የኛ መኖር አስውቧቸው የነበረ መቅረታችን ያስረጃቸው አሊያም የኛ መኖር አደብዝዞ መራቃችን ያበራቸው ያስዋባቸው ቦታዎች

በሆነ ወቅት እግር ጥሎን ድንገት ስናያቸው ደስ የሚለን ወይንም ስሜት አልባ የሚያደርገን አሊያም ያለፈውን ጊዜ የሚያስታውሰን ብቻ እንደዛ አይነት ስሜት ተሰምቷችሁ አያውቅም???

ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
242 views@m måkï , 16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 20:34:31
የማያልቀው_ገፅ

ቻው አይነት አለሁ ልብ ያደማል አይደል??? ልለይሽ አይደለም. ነገም ፣፣ ዛሬም .. አለሁ እያሉ በልብ መሰናበት ከባድ ነው!!!! እንደማይመለሱ ልባችን እየነገረን የአፋቸውን አምነን መሸኘት ሞትን የሚያስመኝ የልብ ውስጥ ቁስል ነው :የማይድኑት አይነት ,,,,,መሄዳቸው መሆኑን ከንግግራቸው በቀር ሁለመናቸው ሲያሳውቀን ካላሉት ካልተናገሩት የሚል ዝምታን የምንሰጣቸው.....ልባቸውን ከልባችን ሊለዩ ሊሰናበቱን ተዘጋጅተው የውሸት አብሮነታቸውን ሲግቱን ባልሰማ ያለፍናቸው .....በስሱ ሲሰናበቱን አጥብቀን የሸኘናቸው ነፍሶች ከዛም ከሄዱ ከምናምን ጊዜ ቡሀላ ህመም ያለውን ናፍቆት ከልባችን ውስጥ የሚያስደምጡን .....መረሳት አለመረሳታችንን ማወቅ የሚያስመኙን፣፣፣፣፣ ደግመው ቢመጡ ባቀፍናቸው ፣፣፣፣ምን ያክል እንደናፈቁን በነገርናቸው የሚያስብሉን ብቻ ብዙ ብዙ .....

.....በዝምታችን ውስጥ ያሉ ድምፆች አሉ።

ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
899 views@m måkï , 17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 13:54:28 ✎የፍቅር ጥቅሶች|| pinned «እንዲቀልሽ 20 **የኖርሻቸውን አመታት ሰርዞ ህይወትን ሀ ብሎ የሚያስጀምርሽን ሰው ስታልሚ ውለሽ ስለምታድሪው አንቺ ብናወራስ **አንዲት እርምጃን ልብሽ አልደፍር ብሎ ተራምዶም ይሁን ሮጦ ከጎንሽ እንዲገኝ የምትከጅይው ሰውዬሽ ነገርስ እንዴት እየሄደልሽ ነው?? **ባሳለፍሽው ህይወት ምክንያት ልብሽን ዝግ አድርገሽ ለቤተሰቦችሽ እና በዙሪያሽ ለሚወተውቱሽ ሰዎች ብቻ ብለሽ ትዳርን ያለፍቅርም ቢሆን ለማግኘት…»
10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 13:54:23 እንዲቀልሽ 20

**የኖርሻቸውን አመታት ሰርዞ ህይወትን ሀ ብሎ የሚያስጀምርሽን ሰው ስታልሚ ውለሽ ስለምታድሪው አንቺ ብናወራስ

**አንዲት እርምጃን ልብሽ አልደፍር ብሎ ተራምዶም ይሁን ሮጦ ከጎንሽ እንዲገኝ የምትከጅይው ሰውዬሽ ነገርስ እንዴት እየሄደልሽ ነው??

**ባሳለፍሽው ህይወት ምክንያት ልብሽን ዝግ አድርገሽ ለቤተሰቦችሽ እና በዙሪያሽ ለሚወተውቱሽ ሰዎች ብቻ ብለሽ ትዳርን ያለፍቅርም ቢሆን ለማግኘት የምትጋጋጪው ምስኪኗ እህቴስ እንደምን ከርመሻል??

**ባህልና እሴት ነው ወጉም አይፈቅድም ትዳር ከሱ ይምጣ ብለውሽ ሲያበቁ በገባሽ በወጣሽ ቁጥር ....."ኸረ አንቺ ልጅ አረጀሽ አግቢ እንጂ".... እያሉ መግቢያ መውጫ ላሳጡሽ.... አግባኝ ለማለት አቅሙን ያጣሽ.. መናቅ ይደርስብኛል የሚል ፍርሀት የናጠሽ እህቴ እንደምን ነሽ??


**ህይወት በሁሉም አቅጣጫ የጠመመችብሽ የተመኘሽው የከጀልሽው ቀርቶ ያሰብሽው የማይሳካልሽ የሚመስልሽ ......እድለቢስነት አብሮሽ የተፈጠረ ይመስል ፈተናዎች የተደራረቡብሽ .......ችግርሽን የሚረዳሽ ቀርቶ "እህ" ብሎ የሚሰማሽ ያጣሽ .....ኑሮሽ ከመውጣት መግባት ያልዘለለ ኢምንት የማይጨምር ትላንትም ዛሬም ያው የሆነብሽ እንስት ሆይ ዛሬን እንዴት አለሽ???


እኔ ምልሽ!!!
"""ነገሮችን በራስሽ ለማስተካከል ደፋ ቀና እያልሽ ስትደክሚ ፈጣሪሽን ስለምን ዘነጋሽው አለሜ??
ፈጥሮ የረሳሽ የሚመስልሽ ለምን ነው? ጥንካሬሽን የሚፈትነው በነገሮች አለመሳካት ትእግስትሽን የሚፈታተንሽ ቢመርጥሽ እንጂ ለምን ይመስልሻል???
እጅሽን አንሺ ፣ ግንባርሽን ድፊ ፣ እውነተኛ እና ትክክለኛ የልብ መቅረብን ቅረቢ፣ ተናነሺና ከፍታን ጠይቂ እሱ ዘንድ የተዘረጋ እጅ በባዶ አይመለስም እመኚኝ!!!


#ስላንተም_እንቀጥላለን!!!

ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
282 views@m måkï , 10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-24 21:05:06 ✎የፍቅር ጥቅሶች|| pinned a photo
18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-24 21:04:58
እንዲቀልህ 19

ልክ ለሆኑት ብቻ ማጨብጨብህን ተው ብዙ ስህተት መሳይ እውነቶች ተሸፍነው ሊኖሩ ይችላሉና .....እመነኝ!!! እውነት ነው ብለህ ካስደሰተህ ነገር በላይ ሀሰትነታቸው ተገልጦ እውነት ሚዛን ሲደፋ ህመሙን አትችለውም!

*ሀሰት ተብሎ ከተፈረጀው ውስጥ እውነትን ፈልግ ከፀፀት ትድናለህ።

#አንቺንም_ይመለከታል!!!

ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
904 views@m måkï , 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-22 22:28:17 ✎የፍቅር ጥቅሶች|| pinned a photo
19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ