Get Mystery Box with random crypto!

✎የፍቅር ጥቅሶች||™

የቴሌግራም ቻናል አርማ bast_love_quotes — ✎የፍቅር ጥቅሶች||™
የቴሌግራም ቻናል አርማ bast_love_quotes — ✎የፍቅር ጥቅሶች||™
የሰርጥ አድራሻ: @bast_love_quotes
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.09K
የሰርጥ መግለጫ

ሰው ስሜቱን ይገልፅ ዘንድ ብዕር ተሠጠው!✍💔📚◆━━━━━━━✎✦✎━━━━━━━━◆
Contact us:⤵️📞
📩 || @Bast_Love_Quotes_Robot

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-10-16 20:43:43 ምክንያት ሞታ ሄጄ ባለቅስ ማላገጥ አይመስልም? ሪቾዬ ጠልቻት እኮ አይደለም። ግን ሁኔታዎች አንድ ላይ እንዳንሆን አደረጉ። ሀይማኖታችን ተለያየ። ምን ላድርግ? ምን ያህል ታፈቅረኝ እንደነበር እኮ በደንብ ነበር የምረዳዉ። መላ አካሌን የማዘዝ ስልጣን የነበረዉ ዉበት እኮ ነበራት። ግን የፈጣሪ ዉሳኔ የሀዩ አደረገኝ። እነዛ ለዛ ያላቸዉ ግጥሞቿስ? ወይኔ ሪቾዬ! አሁን ማለቃቀሱ ምን ይጠቅማል? ምንም!!
.
በሀያት አስገዳጅነት የራሄልን ለቅሶ ለመድረስ ሄድን። እስክንድር ቀድሞን ሄዶ ስለነበር ስንደርስ ተቀበለን። በጣም እየተለቀሰ ነበር። ሀጅራ ለቅሶ ልትደርስ ከኮምቦልቻ እየመጣች ነዉ። ሪቾ በመርየም ሰርግ ቀን ራሷን ያላጠፋችዉ ደስታዬን ላለማደብዘዝ ብላ መሆኑ ገባኝ። እሷ እየተሰቃየች ለኔ ድርብ ደስታ ትጨነቃለች። ለቅሶ ቤት ገብተን ትንሽ እንደተቀመጥን የራሄል አባት ወደ ሀያት መጥተዉ የሆነ ነገር አወሯት። ሀዩ ወደኔ ጠቆመቻቸዉ። አባቷ ወደኔ መጡና "ና እስኪ አንዴ!" ብለዉ ይዘዉኝ ወደ ዋናዉ ቤት ገቡ። ወደ ራሄል መኝታ ቤት ስንገባ ራሄል ተገንዛ አልጋዉ ላይ ተጋድማለች። አልተከፈነችም። ከላይ አንሶላ ለብሳለች። አባትየዉ በሩን ከዘጉት በኋላ አንሶላዉን ከፊቷ ላይ አነሱት። ራሄል ሞታለች። ሳያት እንባዬ ከአይኔ ያለማቋረጥ ፈሰሰ። ልቤ በጣም ተነክቷል። አባትየዉ የሆነ የመድሀኒት ብልቃጥ እየጠቆሙኝ "በዚህ ነዉ ራሷን ያጠፋችዉ።" አሉኝ። የሰዉ ልጅ ጤዛ ነዉ። አሁን ታይቶ በቅፅበት ዉስጥ የሚጠፋ። ግን ምንም አይነት ፈተና ቢጋረጥ ነብስ ማጥፋት በፍፁም እንደመፍትሄ ሊታይ አይገባም። ምክንያቱም ከዚህ ከተኬደ በኋላ እዛ ሰማይ ቤት የሚጠብቀንን ስቃይ ካለንበት ችግር ጋር አወዳድረን አላየነዉምና!
.
ትንሽ የአልጋዉ ራስጌ ጋር ተቀምጬ ካነባሁ በኋላ አባትየዉ አንድ ወረቀት ከኮታቸዉ የዉስጥ ኪስ ዉስጥ አዉጥተዉ ሰጡኝ።
እዛዉ ከፍቼ አነበብኩት። የራሄል ፅሁፍ ነዉ።

"እንደምወድህ ከማዉቀዉ በላይ እንደምትወደኝም አዉቅ ነበር። አንተን የኔ እንዳትሆን ያገደህ ሀይማኖታችን መለያየቱ ብቻ ነዉ። ልክ ስታጣኝ እዉነታዉን መጋፈጥ ትጀምራለህ። ሁሌም ደስተኛ ሆነህ እንድትኖር እመኝልሀለሁ። ግን ናፍቆትህን አልችለዉምና ሞት እስኪያገናኘን ካላስቸገርኩህ ቢያንስ በአመት አንድ ቀን መቃብሬ አጠገብ እየመጣህ እንድታጫዉተኝ አደራ እልሀለሁ። ተዉቤ እጠብቅሀለሁ። አፈቅርሀለሁ።" ይላል።
.
ራሄል የፃፈችዉ ደብዳቤ ዉስጥ አንድም ሀሰት አልነበረም። ግን ማነዉ ከሴቶች ጋር ጓደኝነት መስርት ያለኝ? ሴትናወንድ መካከል ተፈጥሯዊ መፈላለግ መኖሩ እንዴት ጠፋኝ? ብሽቅ ነኝ።
ራሄልን እወዳት ነበር። ግን የወደፊት ህይወትን፣ ትዳርን ሳስብ ሀይማኖታችን መለያየቱ ትዝ አለኝ። እየወደድኳት አታዛልቀኝም በሚለዉ ሀያትን መረጥኩ። እንጂ እኮ ራሄል አጠገቤ ስትቆም በራሱ መላ ሰዉነቴን ነበር የምትቆጣጠረዉ። እወዳት ነበር። የራሄልን ደብዳቤ ጥብቅ አድርጌ ያዝኩት። በህይወት እያለሁ ላልጥለዉ ለራሴ ቃል ገባሁ።
.
ይቀጥላል...
.
✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
4.5K views@m måkï , 17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-16 20:43:43 መንታ መንገድ
ክፍል አስራአንድ
(ፉአድ ሙና)
.
.
ከሀያት ጋር የተጋባንበት እና ባለሚስት የሆንኩበት ቀን አለፈ። የሴሚስተሩም እረፍት አልቆ ወደ ባህርዳር ተመለስን። በኔና በሀዩ መካከል ብዙ ነገሮች ተቀየሩ። ከድሮዉ በተለየ ብቻችንን እናሳልፋለን። እንደልቤ አቅፋታለሁ። እስማታለሁ። ታዲያ ሰዉ በሌለበት ነዉ። ማንም እና ምንም ሀዩን መንካት አይከለክለኝም። ምክንያቱም ሚስቴ ነች!!
.
ቅዳሜ ከሰዓት ብዙ ጊዜ ጣና ነዉ የምናሳልፈዉ። ለመጀመሪያ ጊዜ ከንፈሯን የሳምኳትም ጣና ዳር ተቀምጠን ነዉ። ከንፈር የሆነ ለየት ያለ ጣዕም አለዉ። ለኔ የሀዩ ከንፈር የምድር ምርጡ ጣዕም ባለቤት ነዉ። ምክንያቱም ከሀዩ ዉጪ ሌላ ሴት እንዲህ በወጉ ስሞኝ አያዉቅም። ያለዉድድር ከንፈሯ አሸንፏል። በርግጥ ሪቾ አንዴ ከንፈሬን ስማኝ ነበር ግን ላስታዉሰዉ አልፈልግም። ካስታወስኩት ብዙ ነገሮች አብረዉ ይታወሱኛል።
.
የሴሚስተሩ ማለቂያ ሲደርስ አባቴ ደዉሎ መርየም ልታገባ መሆኑን አበሰረኝ። ታናሽ እህቴ ፈለጌን ስለተከተለች ደስ አለኝ። የምታገባዉም ልጅ በስነ ምግባሩ መልካም የሚባል አይነት ነዉ። ኒካሁ በሌለሁበት ተደርጎ ሰርጉን ክረምት ስመለስ ለማድረግ ነዉ ያቀዱት። ህይወቴ በደስታ ተሞላች።
.
የሪቾ ፍቅረኛ እስክንድር ወደ ማታ ደዉሎ ላግኝህ አለኝ። ምሽቱን ሀያት ቤተ መፅሀፍ ስለነበረች ብቻዬን አገኘሁት። ግቢያችን ዉስጥ ሜንላዉንጅ የሚባለዉ ቦታ ተቀምጠን አንዳንድ ነገሮችን ካወራን በኋላ ሊያገኘኝ ወደ ፈለገበት ጉዳይ ገባን።
"ራሄልን ግን በደንብ አስተዉለሀታል?" አለኝ ትኩር ብሎ እያየኝ። እዉነት ለመናገር ከጋብቻዉ በኋላ ብዙም ትኩረቴ ወደሷ አልነበረም። በርግጥ የምግብ ሰዓቶች ላይ እንደድሮዉ አብረን ነዉ የምንበላዉ።
ዝም ስለዉ "አኩሻ ጤናዋ እየተዛባ ነዉ።" አለኝ።
"እንዴት?" አልኩት ያላስተዋልኩትን ነገር ስለነገረኝ እየተገረምኩ
"አክረሜ ገና አንተ የሀያት እንደሆንክ ካወጅክ ጀምሮ ደህና አይደለችም። ፈገግታዋ እና ጨዋታዋ ሁሉ አንተን ደስ ለማሰኘት እንጂ የእዉነት አይደለም። እየሳምኳት ራሱ የምትጠራዉ ያንተን ስም ነዉ። ዛሬም ከምንም በላይ ታፈቅርሀለች።" አለኝ።
በነገረኝ ነገር በጣም አዘንኩ። ግን ምን ማድረግ እችላለሁ? እኔ አሁን ባለትዳር ነኝ።
"ምን ማድረግ የምችል ይመስልሀል?" አልኩት እስክንድርን
"ቢያንስ ቀረብ ብለህ እንደድሮዉ አዉራት፣ አማክራት።" አለኝ። እስክንድር ምን ያህል ጉዳዩ እንዳሳሰበዉ ከፊቱ ይነበባል።
.
በነጋታዉ ክፍል ዉስጥ እየተማርን ሪቾ ራሷን ስታ ወደቀች። የተቀመጠችዉ ከአጠገቤ ስለነበር አቅፌ ከክፍሉ ይዣት ወጣሁ። እነሀያት ዉሀ ገዝተዉ መጡና ሰዉነቷን ለማቀዝቀዝ ሞከርን። ልክ እንደነቃች አይኗን ስትገልፅ እቅፌ ዉስጥ ነች። ድክም ባለ ፊቷ ላይ ፈገግታ ለመርጨት እየሞከረች "እዚህ እቅፍ ዉስጥ እንኳ ብሞትም አይቆጨኝም!" አለችኝ። ደግነቱ ሀዩ ሪቾ ስትነቃ የምትበላዉ ነገር ልግዛ ብላ ሄዳ ነበር። ከእቅፌ አዉጥቼ አስተካክዬ ላስቀምጣት ስል ገና አካላቶቿ መታዘዝ አልጀመሩም። እዛዉ እቅፌ ዉስጥ እንዳለች ማዉራት ጀመርን።
"መቼ ነዉ የጀመረሽ? ማለቴ ህመሙ?" አልኳት።
"ትንሽ ቆየ ባክህ! ጤናዬ አንተ ነበርክ ፤ የኔ እንደማትሆን ካወቅኩ ጀምሮ ሰላም አይደለሁም።" አለችኝ።
ያኔ ሽንፈቷን በፀጋ ተቀበለች ብዬ ተገርሜ ነበር። ለካ በዉስጧ አፍናዉ ነበር።
.
የሴሚስተሩ ትምህርት እንዳለቀ ለክረምት ወደ አዲስ አበባ ተመለስን። እህቴ መርየም ኒካህ አድርጋለች። አሁን ሰርጉ ሊደገስ ነዉ። ከባህርዳር እንደተመለስን ራሄል በተደጋጋሚ ልታገኘኝ እንደምትፈልግ ብትነግረኝም ሀዩ ሊከፋት ይችላል በሚል ሳላገኛት ቀረሁ። እሁዱን የመርየም ሰርግ ሊካሄድ ቅዳሜዉን ሴቶቹ እኛ ቤት ተሰብስበዉ እየጨፈሩ ነዉ። እኔ ሰርግ ላይ ሴቶቹ ሲጨፍሩ የሚሏቸዉ ግጥሞች ስለሚያዝናኑኝ በቅርብ ርቀት ከሰዒድ ጋር ሆኜ እሰማለሁ። አንድ የጎረቤታችን ልጅ እያወጣች ሌሎቹ እየተቀበሉ እንዲህ አሉ
"ሽንኩርት ከተፍ ከተፍ ፣ ሽንኩርት ከተፍ ከተፍ፣
ያላገባ ካለ ፣ አሁን ይቀላጠፍ።" ሰዒድን እያየሁት እስቃለሁ።
ኢስራዕ ማዉጣት ጀመረች፣ ሌሎቹ ይቀበላሉ
"በጎድጓዳ ሳህን፣ ይመታል አብሽ፣
የኔማ መርየሜ፣ የቀይ ድንቡሽቡሽ።
መስታወት ፊት እንጂ ፣ አያሳይም ሀገር፣
አደራ ጌታዬ ፣ የመርየምን ነገር።" አለችና ዛቻናልመና የቀላቀሉ ግጥሞችን ማዉጣት ጀመረች።
"መርየም ዘረ ብዙ ፣ መርየም ዘረ ብዙ፣
ትናገራትና ብዙ ነዉ መዘዙ።
አምናም አጨብጫቢ ፣ ዘንድሮም አጃቢ፣
ኧረ የኛን ነገር ፣ ያረቢ ያረቢ።"
.
ከሰዒዶ ጋር ግጥሞቹን ተመስጠን እያዳመጥን ሪቾ ደወለች።
"ወዬ ሪቾዬ" አልኩ ስልኩን አንስቼ።
"አክረሜ እንዴት ነህልኝ?" አለች።
"የራሄል አምላክ ይመስገን ደህና ነኝ!" አልኳት እየሳቅኩ።
"አሁን ሰፈራችሁ ነኝ። አስፓልቱ ጋር ና ላግኝህ።" አለችኝ።
ሄጄ አገኘኋት። የአባቷን መኪና ይዛ ነበር የመጣችዉ። መኪናዉ ዉስጥ ገብቼ ማዉራት ጀመርን። ቆይ ግን ምድር ላይ የቀረሁት ወንድ እኔ ብቻ ነኝ እንዴ? ይሄን የመሰለ ዉበት ይዛ እኔን ደጅ መጥናቷ ጨነቀኝ። ሪቾኮ በጣም ዉብ ናት። ድሮም ፎንቃ ይሉት ነገር መዘዙ ብዙ ነዉ። ይኸዉ ሪቾን ራሱ አሳመመብኝ።
ሪቾ ብዙ የማላዉቃቸዉ በህይወቷ ዉስጥ ተፈጥረዉ የነበሩ ነገሮችን ተረከችልኝ። ከዛም አይን አይኔን እያየች "አክረሜ ሁሌም እወድሀለሁ ግን ከዚህ በላይ መሰቃየት አልችልም። ከዚህ በኋላም የማስቸግርህ አይመስለኝም።" አለችኝ። እንባዋ ከአይኖቿ ፈሰሰ። በጣም ልቤን ነካችዉ። እጆቼ እንባዋን ሊጠርጉ ወደ ጉንጮቿ ሄዱ። ያዘቻቸዉ! ሁለቱንም መዳፎቼን ሳመቻቸዉ። ልቤ ስፍስፍ ብሏል። እጆቼን በኃይል ጎትታ ከንፈሮቼን ወደ ከንፈሮቿ አስጠጋች። ልቤ ቀጥ አለ። የማስቆምበት አቅም አልነበረኝም። ሁሉ ነገሬን ተቆጣጥራዋለች። ወዲያዉ ስልኬ ጠራ። ተመስገን ሙዷን አወረደዉ። ለቀቀችኝና መሪዉ ላይ ተኛች። ሀዩ ነበረች የደወለችዉ። አነሳሁት። ቤት እንደመጣች እና ቶሎ እንድመጣ ነገረችኝ። ዛሬ ያዉ የባሏ እህት ሰርግ ዋዜማም አይደል? ለሊቱን ከእህቶቼ ጋር ሲጨፍሩ ሊያድሩ ነዉ።
ስልኩን አናግሬ ስጨርስ ራሄል ከመሪዉ ላይ ፊቷን አንስታ በሶፍት እንባዋን እየጠራረገች "በቃ ልሂድ!" አለችኝ። ትክዝ ብዬ አየኋትና "አላህ ይጠብቅሽ!" አልኳት። አትሄጂም ብዬ በሆነ ተዓምር ሚስቴ መሆኗን ባስረዳት ደስ ይለኝ ነበር። ግን እዉነታዉ ሪቾ ሚስቴ ያለመሆኗ ሀቅ ነዉ።
.
የሰርጉ ቀን አልፎ በማግስቱ ራሄል አራት ነጥብ በሚሴጅ ላከችልኝ። ትርጉሙ አልገባኝም ነበር። ስደዉልላት አታነሳም። በነጋታዉ ጠዋት ሀያት ደወለችልኝ "አኩዬ የት ነህ?" አለችኝ።
"ቤት ነኝ ሀዩዬ!" አልኳት።
"እሺ አልጋህ ላይ በወገብህ ተኛ አንዴ!" አለችኝ። ዛሬ ደሞ ምን አይነት ሮማንስ ነዉ ባካችሁ?
"አንቺ አዘሽኝ አይደለም አልጋ ላይ የጦር ጫፍ ላይ አልተኛም ብለሽ ነዉ?" አልኩ እንዳዘዘችኝ በወገቤ አልጋዉ ላይ እየተጋደምኩ።
"እሺ አኩዬ እንዳልኩህ ተኛህ?" አለችኝ።
"አዎ ሁቢ አሁን ምን ላድርግ?" አልኳት።
መጋደሜን እንዳረጋገጠች ድምጿ በሳግ እየታፈነ "አኩዬ ሪቾ ራሷን አጠፋች!" አለችኝ።
እጄ ስልኬን መሸከም ከበደዉ። ስልኬ እንደዚህ ይከብድ ነበር እንዴ? ራሄል የተገናኘን ምሽት ላይ የነገረችኝ ነገር ስንብት መሆኑ ገባኝ። ሀዩ አልጋ ላይ መሆኔን አረጋግጣ የነገረችኝ ጉዳት እንዳይደርስብኝ በመስጋት ነበር። እንደነገረችኝ የተኛሁ ቤት መጥታ እስክታስነሳኝ ድረስ አልነቃሁም። አሁን ለቅሶ ስደርስ አላፍርም? በኔ
4.1K views@m måkï , 17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-15 23:49:31 ትዳር ተፈጥሯዊ ተቋም ነዉ። የሰዉ ልጅ ስሜት በተፈጥሯዊ መንገድ መርካት አለበት። ለዚህ ደግሞ ትዳር የመጀመሪያዉ እና የመጨረሻዉ አማራጭ ነዉ። ይሄ ተቋም በቀላሉ እንዲመሰረት ወላጆች ልጆቻቸዉን ሊያግዙ ይገባል። አሁን ግን ትዉልዱ የትዳርን በር ጠርቅሞ የዝሙትን በር ከበረገደዉ ቆይቷል። የተዘጋዉ በር ሊከፈት ግድ ይላል!!
.
በነጋታዉ አምስት ሰዓት አካባቢ ወደነሀያት ቤት ሄድን። ኒካህ ስለሆነ ግርግር አላበዛንም። በሶስት መኪና ነበር የሄድነዉ። ሰዒድም ከኛ ጋር መጥቷል። እነሀያት ቤት ስንደርስ የሴቶቹ ጭፈራ ለጉድ ነዉ። መድረሳችንን ሲያዉቁ ደግሞ ጭፈራዉን የበለጠ አደመቁት። ቤተሰቦቿ በር ላይ ወጥተዉ ተቀበሉንና ወደ ዉስጥ ገባን። የሴቶቹ የጭፈራ ድምፅ ይሰማኛል። እዚህ ደግሞ ሀዩን እያሞገሱ እኔን ይነቁራሉ። ስገምት መግፊራ ትመስለኛለች አሊያም ሌላ ሰዉ የሚያወጣዉ እንዲህ አሉ
"ለምነህ ለምነህ ፣ተሀጁድ ሰግደህ
እንዲሁም አልቀረህ ሀዩን አገኘህ።" ተሀጁድ በለሊት ሰዉ በተኛበት የሚሰገድ ስግደት ነዉ።
ነቆራቸዉን ቀጠሉ
"ነጭ ትለብሳለች ፣ ነጭ ትወዳለች
እዉነት ለመናገር ትቦንሰዋለች።
እንቁላል ቢሰበር እንቁላል ይተካል፣
የኔማ ሀዩዬ ፣ አይኗ ብቻ ይበቃል።"
"ሰዒድ እየሳቀ ኧረ በግጥም ወረዱብን እኮ!" አለኝ። "ሀዩን ሊሰጡንማ ቢገርፉንም እንችለዋለን።" አልኩት እየሳቅኩ።
.
ገብተን ትንሽ እንደተቀመጥን የኒካህ ዝግጅቱ ተጀመረ።
በሀይማኖታዊ ስርዓቱ መሰረት የጋብቻ ንግግር በሀይማኖት አዋቂ ተደርጎ ሀያት ጥሎሽ የምትጠየቅበት ሰዓት ደረሰ። ለወጉ ሁለት ሺህ ብር አለች። ወዲያዉ ጥሎሹን ሰጥተን የጋብቻ ወረቀቱ ላይ ተፈራረምን። ሀዩን አገባኋት። ልክ ሀያት ያለችበት ክፍል ወረቀቱ ተልኮ ስትፈርም ሴቶቹም ግጥማቸዉን ሁለታችንንም የሚያወድስ አደረጉት
" ከዚህ እስከመስጂዱ ወርቅ ይነጠፍበት፣
አክረምና ሀዩ፣ ይመላለሱበት።
ጥቁር ይወዳሉ ጥቁር ይለብሳሉ፣
ለሀቁ ከሆነ ይመጣጠናሉ።" በድቤ ታጅቦ በሴቶቹ ዉብ ድምፅ ይቀለፃል። ከሁሉም ያሳቀኝ ግጥም
"ግቢያችሁን እጠሩት ዳር ዳሩን አጥር፣
እስከአሁን ፆመሀል ከእንግዲህ አፍጥር።" የሚለዉ ነዉ። እስከአሁን ፆመሀል ያሉት ከሚስት ጋር ሊደረጉ ከሚችሉ ነገሮች ሁሉ ነዉ። እና ይኸዉ በሀዩ አፍጥር(ፆምህን ግደፍ) ማለታቸዉ ነዉ።
.
ቤተሰቦቿ ሀዩን ለኔ መፍቀዳቸዉን ለማብሰር ግንባሯን እንድስማት እሷ ወዳለችበት ክፍል ይዘዉኝ ሄዱ። ሀዩ በጣም ተዉባ በሚያማምሩ ሴቶች ተከባ ተቀምጣለች። ራሄልም አብራት ነበረች። ሚዜ አይደለችም ግን ሀዩን አጅባ ተቀምጣለች። ዛሬ ሪቾዬን ባገባ በጣም ደስ ይለኝ ነበር። ሳያት አሳዘነችኝ። እኔን የምታጣበት ድግስ ላይ መገኘቷ ግርም ብሎኛል። ምን አይነት መቻል ይሁን ፈጣሪ የሰጣት? እስክንድር ጉዳይዋ እንዳልሆነ በደንብ አዉቃለሁ። አይኗን ከኔ ለማዞር እንዲያግዛት ነዉ የተወዳጀችዉ። ሪቾን ሳላስባንን አየኋትና የሀዩን የአይንእርግብ ገልጬ ግንባሯን ሳምኳት። ሴቶቹ እልልታዉን አስነኩት። የማህበረሰቡን እሴት ስትጠብቅ ወላጅ እንዲህ እልል እያስባለ ልጁን ያስምሀል።
.
ይቀጥላል...
.
✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
4.3K views@m måkï , 20:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-15 23:49:31 መንታ መንገድ
ክፍል አስር
(ፉአድ ሙና)
.
.
ከሀያት ጋር ከታረቅንና ለመጋባት ከወሰንን በኋላ በአራታችን መካከል የነበረዉ የቀድሞዉ የጓደኝነት መንፈስ ተመለሰ።
ከሀያት ጋር ኒካህ ለማሰር መወሰኔን ቀድሜ ደዉዬ የነገርኩት ለሰዒድ ነበር። ለልብ ጓደኛዬ! የእዉነት እኔ ሳይሆን እሱ የሚያገባ ያህል ነበር የተደሰተዉ። በነገራችን ላይ እህቶቼ መርየምና ኢስራዕ ከኔ ጋር ያላቸዉ ቅርበት ጨምሯል። ቢያንስ በሳምንት ሶስት ቀን ይደዉሉልኛል።
.
የሀያት እህት መግፊራ ደወለችልኝና "የክፍለ ዘመኑን ምርጥ ዉሳኔ ነዉ የወሰንከዉ!" አለችኝ እየሳቀች። እሷም እንደእህቷ ፍልቅልቅ ናት።
"የእህትሽን ባል እንዲህ ነዉ የምታናግሪዉ? አክብሪኝ እንጂ!" አልኳት እየሳቅኩ። በዉሳኔያችን በጣም መደሰቷን ነግራኝ አንዳንድ ነገሮችን አወራን።
እኔ የመጀመሪያ ስራ ብዬ ያቀድኩት እህቶቼን ከሀዩ ጋር ማስተዋወቅ ነዉ። እነሱ ከወደዷት እናቴ ላይ በጣም ተፅዕኖ ይፈጥራሉ። ለነገሩ ከእናቴ ጋር ቀረቤታም ስለሌለኝ እነሱዉ ቢጨርሱልኝ ይሻላል። ለእህቶቼ ዉሳኔዬን ነግሬ የሀያትን ፎቶ ቫይበር ላይ ላኩላቸዉ። በፎቶ ወደዋት ሊሞቱ ምንም አልቀራቸዉም። ስልኳን ሰጥቼያቸዉ ተዋወቋት። በዉሳኔያችን መደሰታቸዉንም ነገሯት። ይህቺ የደስታናየሀዘን መግለጫ በመንግስታት ብቻ ሳይሆን በግለሰብም ደረጃም አለች።
.
ከእህቶቼ ጋር በደንብ ካስተዋወቅኳት በኋላ ለአባቴ ደዉዬ ነገርኩት። አባዬ "ኒካህ ማሰርህ ደስ ይለኛል ግን የልጅቷን መልክ ብቻ አይተህ ከሆነ አይሆንም።" አለኝ። በሱ የደረሰዉ በኔ እንዳይደገም ብሎ ይመስለኛል። እናቴ ቆንጆ ናት ግን ምንም ስርዓት የላትም። ይኸዉ ህይወቱን ሙሉ ስታቆስለዉ እና ሲደበድባት አለች። ከዚህ ቀደምም ወደፊት ሳገባ ስነ ምግባሯ ያማረ ሴት እንድመርጥ መክሮኝ ያዉቃል። እኔም ከሀዩ ጋር ያለንን ቅርበት ፣ ስነ ስርዓቷን ፣ ሀይማኖቷ ላይ ያላትን እዉቀት ስነግረዉ "እንደዛ ከሆነች መህር(ጥሎሽ) አንድ ሚሊየን ብር ብትጠይቅህ ደስ እያለኝ እኔ እሰጥሀለሁ።" አለኝ። አባቴ ስልኳን ወስዶ ሀያትን አወራት። የሀያት ቤተሰቦችም ደዉለዉ ብዙ ነገር አወሩኝ። እንግዲህ መተጫጨቱ ተጧጡፏል።
እናቴ ቅር እንዳይላት ብዬ ደወልኩና ኒካህ ለማሰር ማሰቤን ነገርኳት። "ልጅቷ ከየት ናት?" አለችኝ አስቀድማ! ሰዉ አሁን ብሔር ላይ ምን እንዲህ ያጣድፈዋል? ድሮም እኮ እናቴ ሸሯ ይቀድማል። ግን ደስ የሚለዉ የሀዩ ቤተሰቦችና የእናቴ ብሔር ተመሳሳይ ነበር። እንጂማ አይሆንም ብላ ቀዉጢ ትፈጥር ነበር። አዲስ አበባ ታድጎ እንዴት ብሔር እንደ ዋና መስፈርት ይታያል? ድድብና ነዉ!
.
የሀዩ እና የእኔ ቤተሰቦች እነ ሀያት ቤት ተገናኝተዉ ጉዳዩ ላይ መከሩበት። ኒካህ ልክ ሴሚስተሩ አልቆ በመጣን በሳምንቱ እንዲደረግ እና ትምህርታችንን እስከምንጨርስ በየቤታችን እንድንኖር ወሰኑ። ይህ ሁሉ ነገር ሲካሄድ እኔና ሀዩ ባህርዳር ነን።
.
ዉሳኔያቸዉን ስንሰማ ትዳር ምን ያህል ቤተሰብ የበላይ ጠባቂዉ ሆኖ ሲደግፈዉ ደስ እንደሚል ተረዳን። ምናለ ሁሉም በስሜት ተቃጥሎ ፍቅረኛ የሚሉት የዝሙት መንደርደሪያ ላይ ከሚቆምና ቁልቁል ተንደርድሮ ዝሙት ዉስጥ ከሚዘፈቅ ቤተሰብ አጋብቶ ራሳቸዉን ሲችሉ አብረዉ መኖር እንዲጀምሩ ቢያደርግ? ማህበራዊ ቀዉሱን በጣም መቀነስ ይቻል ነበር።
አሁን እኔናሀዩ ፈተና ጨርሰን ወደ ሸገር ስንመለስ ኒካህ እናስራለን። ይሄ ማለት ሀዩ ሚስቴ ሆነች ማለት ነዉ። ኒካህ ከታሰረ በኋላ ብስማት አሊያም ብተኛት ዝሙተኛ አይደለሁም። ሚስቴ ነቻ! ግን በቤተሰቦቻችን ዉሳኔ መሰረት ትምህርት እስከምንጨርስ የምንኖረዉ በየቤታችን ነዉ።
.
ራሄል የሀያት እና የኔ ጉዳይ መስመር ሲይዝ ፤ ዘወትር ካልተነጠፍንልሽ ከሚሏት ወንዶች አንድ ጨዋ የሆነ እስክንድር የሚባል የነሱ ቸርች ልጅ ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀመረች። ከጎኗ የሲጃራ ፓኮ አዉጥቶ አንዱን የመምዘዝ ያህል ነበር ያቀለለችዉ። ድሮም እኔን ብላ እንጂ እንኳን የሱ ልትባል ቀርቶ አብሯት ስለቆመ የአደም ዘር በሙሉ የሚኮራባት አይነት ዉብ ልጅ ነች። በርግጥ ትንሽ ዉጥረቷን ለማርገብ እንዲረዳት ብላ እንጂ ልጁን አፍቅራዉ አይደለም። እስክንድር የጓደኝነት ክበባችን ዉስጥ ሲጨመር አምስት ሆንን። እስክንድር ተጫዋች ነዉ። እኔ በጣም ተመችቶኛል። ኢኮኖሚክስ የሚያጠና የሸገር ልጅ ነዉ።
.
ፈተና እንዳለቀ ወደ አዲስ ለመመለስ ተነሳን። እንደተለመደዉ ሀጅራ ወደ ኮምቦልቻ በጠዋት ሄደች። እኔ ፣ ሀዩ ፣ ሪቾ እና እስክንድር ደግሞ አራት ሰዓት አካባቢ ወደ አዲስ አበባ በረርን።
በረራዉ እንደተጀመረ ሀዩ ወደኔ ዞር አለችና "ለኒካሁ አንድ ሳምንት አብሮ መኖር ለመጀመር አንድ አመት ከአንድ ሴሚስተር ቀረን!" አለችኝ።
ገና ከአሁኑ ቀን መቁጠር መጀመሯ አሳቀኝ። ነገ አይንህ ይበራል ቢባል ዛሬን እንዴት አድሬ እንዳለዉ አይነስዉር ሆነችብኝ።
.
አዲስ አበባ በገባን በሳምንቱ እሁድ ቀን የኒካህ ዝግጅቱ እንዲደረግ ተወሰነ። እኛ ቤት የድግሱ ዝግጅት ሰርግ ነዉ የሚመስለዉ። ሞቅ አድርገዉታል። ገና ቅዳሜዉን ድንኳን ደኩነዋል። ሴቶቹ ቤት ዉስጥ ግጥም እየገጠሙ ፣ ከበሮ እየመቱ ጭፈራዉን ያስነኩታል። ሴቶቹ የሚገጥሙት ግጥም ብዙዉን እኔን የሚያሞግስ ነበር። ከሰዒድ ጋር ከሚጨፍሩበት ክፍል አጠገብ ትንሽ ቆመን ሰማናቸዉ። መርየም ታወጣለች ሌሎቹ ይቀበላሉ።
"የወንድ ልጅ ሱሪ ፣ያልቃል ከጉልበቱ፣
አክረሜን አትንኩት፣ አንድነዉ ለእናቱ።
እንጀራዉን ጋግሩ ፣ በስሱ በስሱ
አክሩ እና ሀዩዬ ፣ እንዲጎራረሱ።" ይላሉ በየመሀሉ ከበሮዉ ይደለቃል። ዜማቸዉ ቀልብን ይገዛል። የሚሏቸዉ ግጥሞች እኔን ከማሞገስ ባለፈም ላላገቡት መልዕክት የሚያስተላልፉ ነበሩ። ኢስራዕ እያወጣች ሌሎቹ እየተቀበሉ
"በፌስቡክ በዋትስአፕ ፣ ከምትጀነጅናት፣
ምትወዳት ከሆነ ፣ ኒካህ እሰርላት።" ፈገግ አልኩና "ሰዒዶ እኔ እንግዲህ ላገባ ነዉ ይሄ ላንተ ይመስላል። ምትጀነጅናት ካለች መክረዉሀል።" አልኩት።
.
እኔ ከሰዒድ ጋር ለኒካሁ ቀን የሚያስፈልጉኝን አልባሳት ገዛዝቼ ጨርሻለሁ። በተለምዶዉ ሙሽራዉ የኒካህ ቀን ሙሽራዋን ወደቤቱ የማይወስዳት ከሆነና ከዛ በኋላ በሰርግ ሊወስዳት ካሰበ ሙሽራዋ በኒካሁ ቀን ወደ ወንዱ ቤት አትሄድም። እኛ ጋር ግን አባዬ ድግስ ስለደገሰና እንዲደምቅ ስለፈለገ ሀያት መጥታ ትንሽ ድግሱን አድምቃ እንድትመለስ አባቴ ከቤተሰቦቿ ጋር ተስማምቷል።
.
ኒካሁ ነገ ሊሆን ቅዳሜ ማታ ሁለት አሮጊቶች ድንኳኑ ዉስጥ ቁጭ ብለዉ ያወራሉ። እኔ በድንኳኑ ጀርባ በኩል ነኝ። አያዩኝም።
"ቆይ ልጁ መች ከሀያ አመት ዘለለ እና ነዉ ለጋብቻ ያስሮጠዉ?" አለች አንዷ ሴትዮ
"ምን የዛሬ ልጆች ገና ቂጣቸዉን ሳይጠርጉ ነዉ ሚስት ማለት የሚጀምሩት!" አለች ሁለተኛዋ አሮጊት!
ሳላስባንን በድንኳኑ በር በኩል እያለፍኩ አሮጊቶቹ እነማን እንደሆኑ ተመለከትኩ። የአንዷ ልጅ ሳታገባ ዲቃላ አንጠልጥላ ይዛባት መጥታ አሮጊቷ እያሳደጉ እንደሆነ መርየም ነግራኝ ነበር። ታዲያ ምን ታድርግ ትዳርን እንዲህ ቅዠት አድርጋ የምታሳይ እናት ካለቻት ሌላ አማራጭ መፈለጓ አይቀሬ ነዉ።
ሁለተኛዋ ደግሞ ልጇ ብዙም ወጣ ያለ ባይሆንም ፍቅረኛ እየቀያየረ ስሜቱን ሲያስታግስ የኖረ ነዉ።
አሁን የልጆቹ ዝቅጠት መነሻ ወላጆቹ መሆናቸዉ ገባኝ። ገና ስለ ትዳር ሲነሳ የሆነ ሆረር ፊልም አድርገዉ ያሳዩሀል። አንተ መወጣት የማትችለዉ የሀላፊነት መዓት የተደረደረበት መጋዘን አድርገዉ ይነግሩሀል። ምንም ደስታ የሌለበት የችግር መሰረት አድርገዉ ይስሉልሀል። ግን እዉነታዉ ይሀ አይደለም።
4.1K views@m måkï , 20:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 19:59:39 ብዙ ህልም ነበረኝ። ቀጣይ ህይወቴን ያለምኩት አንተን የህይወቴ አንድ አካል አድርጌ ነበር። ሁሌም ከእንቅልፌ ስነሳ ማየት የምፈልገዉ አንተን ነበር። ዛሬ ግን ለአይኔም አስጠልተኸኛል። ደግሞም በፍፁም የኔ መሆን አትችልም!" አለችኝ። የኔ መሆን አትችልም ያለችኝ የማልወዳት መስሏት ከሆነ ብዬ "ለምንድነዉ ያንቺ የማልሆነዉ?" አልኳት።
ሙሉ አካሏን ወደኔ እያዞረች "ዝሙተኛ ወንዶች የዝሙተኛ ሴቶች ናቸዉ። የምትለዉን የቁርዓን አንቀፅ እኮ አንተዉ ነበርክ የምትደጋግማት። አሁን ቆሽሸሀል ለንፅህናዬ አትገባም። የኔ ላድርግህ ብል ፀቤ ከፈጣሪ ጋር ነዉ የሚሆነዉ።" አለችኝ። ሀዩ ስታወራ የከዳኋት ባሏ እንጂ ገና ለፍቅር የጠየቀችኝ አትመስልም። አንባገነን ናት። ሪቾ ግን ለማሸነፍ ነዉ የምትሞክረዉ እንደ ሀዩ አታለቃቅስም።
ዝም ብዬ ሳዳምጣት የነበረዉ ሴቶች እንደዚህ በስሜት ሲያወሩ ከወንዱ የሚፈልጉት ትኩረቱን እንጂ መልሱን አይደለም ብዬ ስላሰብኩ ነዉ። ስትጨርስ ቀስ ብዬ ማስረዳት ጀመርኩ። "አዎን ቆሻሻ ወንዶች የቆሻሻ ሴቶች ናቸዉ። ግን እኔም ራሄልም ቆሻሻዎች አይደለንም።" አልኳት።
"እንዴት ባክህ?" አለችኝ እያፈጠጠችብኝ። አሁን ለማዳመጥ ዝግጁ መሆኗ ስለገባኝ እኔናራሄል ዝሙት አለመፈፀማችንን እና የዛን ቀን የተፈጠረዉን ነገር አንድም ሳላስቀር አስረዳኋት።
ሀያት እንባ በእንባ ሆነች። ከተቀመጠችበት ብድግ አለችና መሬቱ ላይ በግንባሯ ተደፍታ ጌታዋን አመሰገነች። ለኔ ንፅህና ጌታዋን የምታመሰግን ሴት! እንደሀያት ያሉ ሴቶች ከሚሊየን አንድ ናቸዉ።
.
ቁርሱ እንደቀረበ ሀዩ እንደለመደችዉ የኔን ቆርሳ በላችብኝ። ደስ አለኝ። ታርቃኛለች ማለት ነዉ። ወዲያዉ "አኩሻ ግን" አለች።
"ግን ምን?" አልኳት ፈገግ እያልኩ።
"አሁን ታረቅን ብቻ ነዉ ሚባለዉ ወይስ?" አለች አይኗን በሀፍረት እየሰበረች።
ምን ለማለት እንደፈለገች ስለገባኝ "ሴሚስተሩ ሲያልቅ ኒካህ እናደርጋለን። እኔም ከአሁኑ ቤት እናገራለሁ አንቺም ንገሪያቸዉ።" አልኳት። በደስታ ልታብድ ምንም አልቀራትም። ወዲያዉ ስልኳን አንስታ ራሄል ጋር ደወለችና ጠራቻት። ሪቾ ስትመጣ እኔም እዛዉ አለሁ። አየችንና "ኦ ገባኝ ሀዩ አሸነፈች ማለት ነዉ?" አለችኝ። "አዎ" አልኳት አይን አይኗን እያየሁ። ሪቾ በጣም ፍትሀዊ ናት! አታለቃቅስም። ግን በጣም ትወደኛለች። እኔም ሀይማኖታችን ቢመሳሰል የመጀመሪያም የመጨረሻም ምርጫዬ ሪቾ ነበረች።
ራሄል እንደምንም ፈገግ አለችና "እንደዚህ አራታችንም የምንሰበሰብበት ቀን ናፍቆኝ ነበር።" አለች። ከዛም ራሷ የዛን ቀን እንዴት ዉጪ አብሬያት እንዳድር እንዳደረገችኝ ፣ ሀዩን ለማሳመን የተጠቀመቻቸዉን መንገዶች ተረከችልን። ሪቾ ሽንፈቷን በፀጋ መቀበሏ በጣም አስደሰተኝ። ሪቾ እኮ ጨዋ ናት ብያችሁ ነበር። ከቀናት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አራታችንም እንደድሮዉ አንድ ላይ ቁርስ በላን።
.
ይቀጥላል...
.
✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
4.6K views@m måkï , 16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 19:59:33 መንታ መንገድ
ክፍል ዘጠኝ
(ፉአድ ሙና)
.
.
ሀያት ከራሄል ጋር ከባጃጅ ስወርድ ካየችበት ቅፅበት በኋላ ስልክ ስደዉልላት አታነሳም። በነጋታዉም ወደ ክፍል አልመጣችም። በጣም ጭንቅ አለኝ። ራሄል ልታገኘኝ ስልክ ብትደዉልም ማንሳት አልፈለግኩም። ክፍል ዉስጥ ስንገናኝ እናወራለን። ራሄል ምንም አላጠፋችም ግን ሀያትን እንደነጠቀችኝ ተሰማኝ። አሁን ከራሄል እና ከሀያት ትክክለኛዋ ምርጫዬ ሀዩ መሆኗን የተፈጠረዉ ክስተት በደንብ አረጋግጦልኛል። ዶርም ብቻዬን ተቀምጬ ከሀዩ ጋር ያሳለፍናቸዉን አስደሳች ጊዜዎች አስባለሁ። በተለያዩ የሀገራችን ክልሎች ባደረግናቸዉ ጉዞዎች ዉስጥ ያሳለፍናቸዉ ወርቃማ ጊዜያት አይኔ ላይ ድቅን ይላሉ። የሀያት ፍልቅልቅ ሳቅ አይኔን ይሞላዋል። በጨዋነቷ የታጀበዉ ፈገግታዋ ትዉስ ይለኛል። ምራቋን እየዋጠች "የሌላ ስትሆን ካየሁ ግን ሰዉ አልሆንም!" ያለችኝ ትዝ ይለኝና በራሴ እበሽቃለሁ። አዎን ሀዩ እንደድሮዉ ደስተኛናተጫዋች መሆን ከብዷታል። በርግጥ ከራሄል እና ከሀያት አንዷን ሳልመርጥ በዝምታ የቆየሁት ጓደኝነታችን ሊበጠበጥ ይችላል በሚል ስጋት ነበር። ዉጤቱ ግን ፉክክር ሆኖ አረፈዉ። ፉክክሩ ደሞ ጨዋዋ ራሄልን ራሱ ራቁቷን ፊቴ እስከመቆም አደረሳት። እዉነታዉን ልመልከት ብል ኖሮማ ሀያት ከራሄል ጋር የማትነፃፀርበት አንድ ትልቅ ከኔ ጋር የሚያመሳስላት ነገር አላት። ሀይማኖታችን አንድ አይነት ነዉ። እኔ ደሞ ሀይማኖቷ ከኔ የተለየችን ሴት አላገባም። አንቺም በሀይማኖትሽ እኔም በሀይማኖቴ የሚለዉ አባባል የሚያምረዉ ዘፈን ላይ ብቻ ነዉ። መቻቻልን ለማሳየት የሀገር መሰረት የሆነዉ ቤተሰብ መናጋት የለበትም። ትዳር ልጅ የሚባል ፍሬ የሚያፈራ ተቋም ነዉ። ልጆችን ወደ አንዱ ሀይማኖት ለመዉሰድ በሚደረገዉ ሽኩቻ መሀል ልጆች ችግር ዉስጥ ሊገቡ አይገባም። ትዳሩም በሆይሆይታ ይጀመር ይሆናል እንጂ ባለመስማማት መጠናቀቁ አይቀርም። እስልምና ደግሞ የሌላ ሀይማኖት ተከታይ ማግባትን አይፈቅድም።
.
ሀዩን የተፈጠረዉ ነገር ላይ እጄ እንደሌለበት ለማስረዳት ቢያንስ እንዳገኛት ልትፈቅድልኝ ይገባ ነበር። እሷ ግን ስልኳን እንኳ አታነሳም። እንደ ድሮዉ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት አብሮ መብላት ቀረ። መንገድ ላይ ካየችኝ ራሱ መንገድ ትቀይራለች። ሀጅራ ሀያትን አንዴ እንኳን የምናገረዉን እንድትሰማኝ እንድታስማማት ብጠይቃትም ሊሳካላት አልቻለም።
.
ጁምዓ(አርብ) ትልቁ ኦዲተሪየም ዉስጥ የሚካሄደዉ የስነ ፅሁፍ ምሽት ላይ ስራዎቻችንን ለማቅረብ ከራሄል ጋር ሄድን። ዝግጅቱ ተጀምሮ ታዳሚዉ ቦታ ቦታዉን ከያዘ በኋላ ሀያት እና ሀጅራ ገብተዉ ከአቅራቢዎች መቀመጫ በስተግራ በኩል ራቅ ብለዉ ተቀመጡ። ከራሄል ጋር አብረን ያደርን ጊዜ የፃፍኩትን ግጥም ባቀርብ ለሀያት እዉነቱን ለማስረዳት እንደሚረዳኝ አሰብኩ። ገጣሚዎች እየተጠሩ ስራቸዉን ማቅረብ ጀመሩ። የሪቾ ተራ ደረሰና ወደ መድረኩ ወጣች።
"ስርየት" ብላ የግጥሙን ርዕስ አስተዋወቀችና ጉሮሮዋን ከጠረገች በኋላ ግጥሙን ማንበብ ጀመረች
"የታመመ ልቤን የሚያሽረዉ አጥቶ፣
ዘወትር ሲሰቃይ መድሀኒትን ሽቶ፣
በአንድ ለሊት ፍቅር፣ ቁስሉን አጠፋኸዉ፣
በእጅህ ልስላሴ ፣ገላዬን አከምከዉ፣
በከንፈርህ ጠዓም፣ ምሬትን ገደልከዉ፣
ገላዬ ላይ ነግሰህ ፣ ሰላሜን መለስከዉ።
ልቤ ሰላም ሲያገኝ ፣ ሀሴት ሊያገኝ ነብሴ፣
ጉድለቴን ሚደፍን ፣ የሰመመን ልብሴ
ተቸረኝ ከፍቅርህ ፣ ጠፋን ምድርን ለቀን፣
ስርየት ሆነ ያኔ ፣ ፍቅርህን ስትቸረኝ!
የኔ ነሽ ስትለኝ! " አለችና ወደ ቀጣዩ ግጥም ለመሻገር ወረቀቱን ገለፀችዉ። ሀያት ከዚህ በላይ ለመቆየት አቅም አጣች። እንባዋን በሂጃቧ እየጠረገች አዳራሹን ለቃ ወጣች። ሀጅራም ተከተለቻት። ይሄ ግጥም ሆነ ተብሎ ለሀያት አክረምን አንሶላ ተጋፍፌዋለሁ ብላ ለማሳመን ያቀረበችዉ መሆኑ ገብቶኛል። ደግሞም ተሳክቶላታል። እኔም ግጥም የማቅረብ እቅዴን ሰርዤ አዳራሹን ለቅቄ ወጣሁ። ዉጪ ላይ ሀጅራ ሀያትን አቅፋ ስታባብላት አገኘኋቸዉ። ልጠጋቸዉ ስል ሀጅራ ራሷ እንድርቅ በእጇ ምልክት ሰጠችኝ። ከሀያት ጋር ለመነጋገር ጥሩ ሰዓት አይደለም ብላ ስላሰበች ይመስለኛል እንድርቅ ምልክት ያሳየችኝ። ቆይ እኔንስ ማን ይረዳኝ? ለምን አንዴ እንኳን እንዳወራት አትፈቅድልኝም? ለምን? ብስጭቴ ጣራ ነካ። ወደ ዶርም ሄጄ ማንም እንዳያናግረኝ ተናግሬ በብርድልብሴ ተጠቅልዬ ተኛሁ። እንቅልፍ ግን የለም!
.
ጠዋት ላይ ሀጅራ ደወለችልኝ። የዛሬን አያድርገዉና ሌላ ጊዜ በዚህ ሰዓት ሀዩ ደዉላ ቁርስ አረፈድክ እያለች ትበሳጭብኝ ነበር። ሀያት እና ራሄል ላይ ላዩን ሰላም ናቸዉ ግን ዉስጥ ዉስጡን እንደድሮዉ አይመስሉኝም። ስልኩን አንስቼዉ "ሀጁ በአላህ ሀያት ላናግረዉ አለች በይኝ!" አልኳት። ምኞቴ ነበር።
"ወይ ላናግረዉ¡ ባክህ ወደ ቤት ልትመለስ ሻንጣዋን እያዘገጃጀች ነዉ የሆነ ነገር አድርግ።" አለችኝ። ሀዩ ፀፀቴን ከአቅሜ በላይ ልትከምርብኝ ነዉ! የክፍላችንን ሰቃይ በኔ ምክንያት ወደ ቤቷ ስትመለስ ከማይ ብሞት እመርጣለሁ።
"አሁን ዶርም ናት?" አልኳት ሀጅራን
"የደወልኩልህ ቁርስ ልንበላ ከግቢ ልንወጣ ስለሆነ ነዉ። እንግዲህ የሆነ ነገር አድርግ። ያለበለዚያ ትኬት ቆርጣ ወይ ዛሬ አሊያም ነገ እሄዳለሁ ብላለች።" አለችኝ። ሀዩ የሌላ ስሆን ካየችኝ ሰዉ እንደማትሆን አስቀድማ ነግራኝ ነበር። ትምህርት እስከማቋረጥ የሚያደርስ ህመም እንደፈጠርኩባት ሳስብ በጣም በራሴ ተበሳጨሁ። ሀዩን ማስቀረት ካልቻልኩ እኔ ራሴ ሰዉ አልሆንም። ሀጅራ ሲወጡ ሚስኮል እንድታደርግልኝ ተነጋግረን ስልኩን ዘጋችዉ።
.
ይገርማል ሀዩን ከአጠገቤ ማጣት እንዲህ ያመኛል ብዬ አስቤ አላዉቅም። በአቅራቢያችን ያሉ መልካም ነገሮችን ጥቅም የምንረዳዉ ስናጣቸዉ ነዉ።
ራሄል ደዉላ አብረን ቁርስ እንድንበላ ጠየቀችኝ። ራሄል በፉክክሩ ምክንያት በጓደኝነታችን መሀል የተፈጠረዉ ክፍተት እሷንም በጣም አሳስቧታል። እኔ ግን የሀጅራን ስልክ እየጠበቅኩ ስለነበር መብላት እንደማልፈልግ ነገርኳት። ራሄል ብዙ ጊዜ አልበላም ካልኳት ዉጪ ወጥታ በስርዓቱ አትበላም።
ሀጅራ ሚስኮል ስታደርግልኝ ከዶርም ተነስቼ ከግቢ ዉጪ ወዳሉት ምግብ ቤቶች ሄድኩ። ሀያት እና ሀጅራ ሁሌም የምንበላበት ቤት ቁርስ አዘዉ ተቀምጠዋል። ያይኔአበባ ለማስተናገድ ትንደፋደፋለች። የምትሰራዉ ምግብ ይጣፍጣል። ከኔ ጋር ደሞ ስለምንግባባ አንዳንዴ ቆንጆ ምግብ ስትሰራ እንድቀምስላት በእቃ ትሰጠኛለች። ሀያት እና እኔ ሁሌም ሳንዱች በወተት ነበር ቁርስ የምንበላዉ። ከነሀያት ፊት ለፊት ተቀመጥኩና ያይኔአበባን እያየሁ "ሳንዱችናወተት" አልኩ! ሀያት ቀና ብላ ስታየኝ ፊቷ ተቀየረ። ጠልታኛለች። ግን እዉነቱን ለማስረዳት ከዚህ የተሻለ ጊዜ አላገኝምና ከነበርኩበት ጠረጴዛ ተነስቼ ሀያት አጠገብ ተቀመጥኩ።
ሀዩ ምራቋን ዋጥ አደረገችና "ምን ፈለግክ?" አለችኝ።
"ሀዩ በአላህ ይሁንብሽ አንዴ ብቻ አዳምጪኝ! አንዴ ብቻ! ላስረዳሽ!" አልኩ በአይኔ እየተለማመጥኳት።
ሀዩ የንዴት ፈገግታ ፈገግ አለችና እንባዋ እየቀደማት "እንዴት እንደሳምካት ነዉ የምታስረዳኝ? እንዴት እንደረከስክላት ነዉ ወይ የምታብራራልኝ? ከኔ ጋር ለትዳር ለመተጫጨት ዝሙት ላይ እንዳንወድቅ እናትሽ ይኑሩ ምናምን አልክ። ከኔ ጋር ስትሆን ሀይማኖተኛ ሀይማኖተኛ ይሰራራሀል። እኔ እኮ በክብር አግባኝ ነበር ያልኩህ! የማግባት አቅሙ ነበረህ። ግን አንተ የትም መልከስከስን ነዉ የመረጥከዉ። እና ምኑን ነዉ የምታስረዳኝ?" አለችና እንባዋን በሂጃቧ ጠርጋ ቀጠለች
"አክረም ከአንተ ጋር
4.2K views@m måkï , 16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 09:38:38
የህይወት ታሪካችን በእርሳስ የተፃፈ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ላይ ሆኜ ብዙ ማስታወስ የማልፈልጋቸውን ትውስታዎቼን አጠፋቸው ነበር።

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
4.2K views@m måkï , 06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-13 07:25:44 ስወድህ
ልክ እንደ እናት ነው ስስቴ ለልጇ ያላትን ስስት ያክላል ስታወራኝ,,, ስታስቀኝ አለም ላይ ብቻዋን የቀረች ደስተኛ ሴት የሆንኩ ያክል ይሰማኛል... ስወድህ ገደብ አልባ ነኝ ለነገ ብዬ የማስቀረው አንዳች መውደድ የለም ሁሉንም ዝርግፍ አድርጌ አንድ ላይ ውድድ በቃ ......ቃላቶች ላንተ ሲሆን እርባና ያጡብኛል የሚመጥንህን አጣለው.. ብዙ ጊዜያትን ብእሬን ከወረቀት ላወዳጅ ስጀምረው አይምሮዬ ይፈጥንብኛል አንዱንም ሳላሰፍር እተወዋለው... ቃላቶቼ አንተን ለመግለፅ አቅም ያጣሉ እንዲሁስ ብወድህ ብዬ እተወዋለው.
አየህ!! እውነተኛ ፍቅር እንዲህ ነው ቃላት የሌለው... በዝምታ ውስጥ የሚኖር ...ዝምታ ብቻ የሚገልፀው ..በፍቅርህ ይህ ነው የገባኝ።

@queen_maki

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
344 views@m måkï , 04:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 21:52:54 በያቸዉ!" አልኳት። ዉስጤ ላይ በጣም ፍርሀት አለ።
ራሄል ስልኩን አንስታ ያልኳትን ነገረቻቸዉ።
ሀያት ወዲያዉ እኔ ጋር ደወለች። ከጀርባ የሚሰማዉ ድምፅ ተመሳሳይ ከሆነ ልትጠረጥር እንደምትችል ስለገመትኩ ራሄልን ነግሬያት እየሮጥን ደረጃዉን ወጥተን መተላለፊያዉ ላይ ሆኜ አነሳሁት።
ሀያት "አኩዬ ንቅት ብለሀል። እንቅልፍ ነሳችህ አይደል? አሁን ደዉዬላት ሆቴል አድሬያለሁ ብላለች። በቃ ፈታ ብለህ ተኛ!" አለችኝ። ወይኔ ጌታዬ ምን ዉስጥ ነዉ የገባሁት? ወዲያዉ ከራሄል ጋር ወደ መኝታ ክፍላችን ሄድን። ሪቾ ቀድማኝ ገባች። እኔ ገብቼ በሩን ከዉስጥ ቆለፍኩት። በሩን ቆልፌ ስዞር ሪቾ ልብሷን ማዉለቅ ጀምራለች። ቀሚሷን እግሮቿ ስር ለቀቀችዉ። ብድግ አለችና ሸሚዟን እንደሹራብ አወለቀችዉ። ራሄል ባዶ ራቁቷን ከፊት ለፊቴ ቆመች።
.
ይቀጥላል...
.
✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
484 views@m måkï , 18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 21:52:54 መንታ መንገድ
ክፍል ሰባት
(ፉአድ ሙና)
.
.
ከሪቾ ጋር ለስነ ፅሁፍ ምሽቱ የምናሳየዉን ግጥም አሳይተን እንደተመለስን ሀዩ ጋር ደወልኩ። በአካል ላወራት ስለፈለግኩ 'ጆኮ ግቢ' ጋር ተቀጣጠርን። 'ጆኮ ግቢ' የግቢያችን የጋዜጠኝነትና ስነ ተግባቦት ግቢ ነዉ። ጆኮ የተባለዉ ጆርናሊዝም እና ኮሚኒኬሽን የሚሉት ቃላት የመጀመሪያ ፊደል ተወስዶ ሲቆላመጥ ነዉ። ወደ አስራአንድ ሰዓት ገደማ ሆኗል። ሀዩ እንደተለመደዉ ዉቡን ሰፊ ቀሚሷን ለብሳና ቅላቷን የሚያንቦገቡገዉን ጥቁር ሂጃብ ጠምጥማ እየተፍለቀለቀች መጣች። ቅድም እንባ እየተናነቃት ስልኩን ዘግታ አሁን እንዲህ መፍለቅለቋ አስገርሞኛል። ሀዩን ለየት ባለ ስሜት አተኩሬ ተመለከትኳት። በጣም ቆንጆ ናት! ምናለ ቢያንስ ምርጫዉ ላይ ካሉት ሴቶች አንዷ አስቀያሚ በሆነች?! ለምርጫ አልቸገርም ነበር። ሁለት ቆንጆ መሀል ሆነና ምርጫዉ ከበደ። የወንድ ልጅ ልብ ደግሞ ሁለቱንም የማለት አባዜ አለበት።
ጆኮ ግቢ በር ላይ ካሉት መቀመጫዎች አንዱ ላይ እንደተቀመጥን "ሀዩዬ ቅድም በስልክ ስናወራ ድምፅሽ ጥሩ አልነበረም! ምነዉ?" አልኳት ድምጿ በሳግ የታፈነበትን ቅፅበት እያስታወስኩ!
ሀዩ ትንሽ አንገቷን አቀርቅራ ከተከዘች በኋላ "አክረሜ አንተ ግጥም ትወዳለህ። እኔ ግጥም መፃፍ አልችልም። ሪቾ ግን ጎበዝ ናት። ምናልባት በግጥሟ ቀልብህን ብትሰርቅብኝ ብዬ ፈራሁ!" አለች።
አንጀቴን በላችዉ! ቆይ ለምን አልወስንም? እኔንጃ! የሆነ ነገር አስሮ ይዞኛል።
.
በነጋታዉ ወደ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ ራሄል ኢባብ ካምፓስ ያሉ ጓደኞቿን ልታገኝ ሄደች። ኢባብ ካምፓስ ከደብረማርቆስ በኩል ወደ ባህርዳር በሚያስገባዉ መንገድ ባህርዳር እንደተገባ ያለ ካምፓስ ነዉ። ከፔዳ ካምፓስ በጣም ይርቃል። እኔ ሀያት እና ሀጅራ እስከ ማታ አንድ ሰዓት ብንጠብቃትም አልመጣችም። ስንደዉልላት እራት ከጓደኞቿ ጋር በልታ ስለምትመጣ እንድንበላ ነገረችን። እራት በጊዜ በልተን ሁለት ሰዓት ሲል ወደ ግቢ ገባን። በነጋታዉ ከሰዓት በኋላ ለማስገባዉ አሳይንመንት ፕሪንት ማድረጊያ ብር ስላልነበረኝ ግቢ በር ጋር ካለዉ ኤቲኤም ብር ለማዉጣት ስሞክር ኤቲኤም ማሽኑ አይሰራም። ይሄ ኤቲኤም ማሽን ብዙ ጊዜ ያስቸግራል። ብር ለማዉጣት ኤቲኤም ማሽኑን ስቀጠቅጥ "በቃ ነገ ታወጣለህ! ልትገነጥለዉ ነዉ እንዴ?!" አለች ሀዩ። ማሽኑ ስለማይሰራ ብር ሳላወጣ ወደ ዶርም ሄድኩ። የራሄል ዛሬ እንዲህ ማምሸት ሶስታችንንም አስጨንቆናል። እስከዛሬ ከኛ ተነጥላ እንዲህ አምሽታ አታዉቅም።
.
ዶርም ገብቼ ሱሪዬን እያወለቅኩ ራሄል ደወለች።
"ወዬ ሪቾ ግቢ ገባሽ?" አልኩ ስልኩን አንስቼ
"ኧረ አኩዬ ገና ገበያ ጋር ነዉ ያለሁት። ታክሲ የሚባል የለም። ብቻዬን ኮንትራት መያዝ ፈራሁ። ከቻልክ ቶሎ ና እና በኮንትራት እንመለሳለን።" አለችኝ። ገበያ ከፔዳ ግቢ በታክሲ የአንድ ብር መንገድ ነዉ። ኪሴ ዉስጥ ያለዉ ብር አስር ብር አይሞላም። ሰዓቴን አየሁት ሶስት ሰዓት ከሰላሳ ሶስት ይላል። የግቢያችን በር አራት ሰዓት ሲል ይዘጋል። ቶሎ ሄጄ ካላመጣኋት በር ሊዘጋባት ይችላል። ያወለቅኩት ሱሪ ዉስጥ የነበረዉን ብር ወደ ቀየርኩት ቱታ ሱሪ ከትቼ ከዶርም ወጣሁ። ከዶርም እስከ ግቢ በር ያለዉን መንገድ በሩጫ በአምስት ደቂቃ ጨረስኩት። ከግቢ እንደወጣሁ አንድ ታክሲ ቆሞ እየጫነ አገኘሁ። ታክሲዉ ዉስጥ ገባሁ። ታክሲዉ እስኪሞላ በጣም ዘገየ። ሪቾ ደወለች "አኩ ዉጪ ልታሳድረኝ ነዉ እንዴ?! የት ደረስክ?!" አለች እየተነጫነጨች
"ባክሽ ታክሲ አልሞላም ብሎ ነዉ፣ አሁን እየወጣ ነዉ መጣሁ!" አልኳት በሩ እንዳይዘጋብን በጣም ፈርቼያለሁ። የስልኬን ሰዓት ተመለከትኩት ሶስት ሰዓት ከአርባ ዘጠኝ ይላል። ደግነቱ መንገዱ ክፍት ስለሆነ ታክሲዉ ይከንፋል።
.
ገበያ ስደርስ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ከሀምሳ አራት ሆኗል። በልቤ አሁን ከታክሲዉ እንደወረድኩ ኮንትራት ከያዝን ከሀምሳ ዘጠኝ ሲል ግቢ እንደርሳለን እያልኩ አስባለሁ። ከታክሲዉ እንደወረድኩ ራሄልን ፈለግኳት የለችም። ስልክ ደወልኩ። ብዙ ከጠራ በኋላ አነሳችዉ።
"አኩ የት ነህ የሰዉ አይን በዝቶብኝ በጣም ፈርቻለሁ!" አለችኝ
"ደርሻለሁ የቱ ጋር ነሽ?" አልኳት በአይኔ እየፈለግኳት
"አየሁህ ተሻገር! ተሻገር!" አለችኝ።
አየኋት ፣ እኔ ካለሁበት ተሻግሮ ባለዉ አስፓልት ዳር ላይ ቆማ እጇን እያዉለበለበችልኝ ነበር። እየሮጥኩ ተሻገርኩ። ራሄል አጠገቧ ስደርስ በረዥሙ ተነፈሰችና መሬት ላይ ቁጢጥ አለች።
"ምነዉ ምን ሆንሽ?" አልኩ በዚህ የጥድፊያ ሰዓት መቀመጧ ገርሞኝ። ስልኳን አብርታ አሳየችኝ። አራት ሰዓት ከሁለት ይላል። ሰዓቴን ተመለከትኩት ያዉ ነዉ። እኔም አብርያት ቁጢጥ አልኩ። የኛ ግቢ ሜትሮዎች ምንም ቀልድ አያዉቁም። በሩን አራት ሰዓት ሲል ነዉ የሚጠረቅሙት።
"ምን ተሻለን?" አለች ሪቾ በፍርሀት ስሜት
"በቃ ሆቴል እንደር ኤቲኤም እዚህ ጋር ካለ ብር ላዉጣ!" ብዬ ቁጢጥ ካልኩበት ብድግ አልኩ። እጄን ወደ ኪሴ ልኬ ኤቲኤም ካርዴን ብፈልግ ኪሴ ዉስጥ የለም። ትዝ ሲለኝ ለካ ልብስ ቀይሬ ነዉ የወጣሁት።
"ኤቲኤም ካርድ አልያዝኩም። ምን ተሻለን?" አልኩ ብር መያዟን ለመጠየቅ በሚል
"የሆነ ያህል ብር ይዣለሁ ግን የሚበቃን አይመስለኝም።" አለችኝ። "ለማንኛዉም በጊዜ ማረፊያ መፈለጉ ይሻላል!" አልኳትና አልጋ መጠየቅ ጀመርን። ከገበያ አንስተን እስከ ፓፒረስ ሆቴል ድረስ ያሉ ሆቴሎችን ስንጠይቅ በሰዓቱ አልጋ አልነበራቸዉም። በመጨረሻም ፓፒረስ ሆቴል አልጋ አገኘን። ዉስጥ ገብተን የአልጋ ዋጋ ስንጠይቅ ሪቾ የያዘችዉ ብር የአንድ አልጋ ብቻ ነበር የሚችለዉ። ግራ ግብት አለኝ። እሷን እዚህ አስተኝቼ እኔ የት ልሄድ ነዉ?
.
ሪቾ የክፍሉን ቁልፍ ተቀብላ እየመጣች "አኩሻ አንዳችን የሆነ ነገር ላይ አንዳችን ደግሞ አልጋዉ ላይ እንተኛለን። ሌላ አማራጭ ይታይሃል?" አለችኝ። በርግጥ እሷ ካለችዉ ዉጪ ሌላ ምንም አማራጭ በጊዜዉ አልታየኝም ነበር። ግን ከዚህ ቀደም ብቻችንን የተገናኘንበት ምሽት ላይ በጣም ተጠግታኝ የቆመች ጊዜ ልቤ ምን ያህል ቀጥ እንዳለች አስታወስኩ። እና ዛሬ አንድ ክፍል ዉስጥ ሊያዉም ብቻችንን እንዴት ነዉ የሚያስችለኝ? ፈጣሪ ፅናቱን ይስጠኝ። ሀያት ዛሬ እኔና ራሄል ፓፒረስ ሆቴል አብረን አንድ ክፍል ዉስጥ ልናድር መሆኑን ብታዉቅ ምን ትል ይሆን? አብረን በቀን ግጥም ልናስገባ ስለሄድን እንደዛ የሆነች ይሄን ብትሰማ ምድር ነዉ የሚገለበጠዉ።
"ሪቾ እነሀያት አልደወሉልሽም?" አልኳት እንግዳ መቀበያዉ ጋር እንደቆምን
"መደወል አይገልፀዉም! አሁንም እየደወሉ ነዉ ግን ማንሳት አልችልም።" አለችኝ።
"አንስተሽ የሆነ ምክንያት ንገሪያቸዉ! ደሞ ሀያት አብረን መሆናችንን ካወቀች ሰማይ ነዉ የሚደረመስብን!" አልኳት።
" አኩሻ ሀያትን ትፈራታለህ እንዴ?" አለችኝ ኮስተር እያለች
"እፈራታለሁ አልወጣኝም ግን እንደ ጓደኝነቷ አከብራታለሁ።" አልኩ ከፊቷ እየሸሸሁ
"አይንህን ከፈት አድርገዉ። አጠገብህ እኔ አለሁ!" አለችኝ እጇን ወደ ላይ ዘርግታ እየተሽከረከረች።
አየኋት! በጣም አየኋት! ቀሚሷ በጣም አጭር ነዉ። እግሮቿ ያምራሉ። የሸሚዟ ቁልፍ ከላይ ተከፍቶ ጡቶቿን በከፊል ያሳያል። ግን ፈጣሪ ምን አድርጌዉ ነዉ እዚህ አጣብቂኝ ዉስጥ የወረወረኝ? ከባድ ፈተና ነዉ! ምናለ ከሀጅራ ጋር ከፈለገ ሳምንት አንድ ክፍል ቢያሳድረኝ? ለምንም የማንከጃጀል ሰዎች!
.
ራሄል ስልኳ አስሬ እየጮኸ ሲያስቸግራት ስልኳን እያሳየችኝ "ምን ልበላቸዉ?" አለችኝ።
"በር ተዘግቶብኝ ሆቴል አድሬያለሁ
478 views@m måkï , 18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ