Get Mystery Box with random crypto!

✎የፍቅር ጥቅሶች||™

የቴሌግራም ቻናል አርማ bast_love_quotes — ✎የፍቅር ጥቅሶች||™
የቴሌግራም ቻናል አርማ bast_love_quotes — ✎የፍቅር ጥቅሶች||™
የሰርጥ አድራሻ: @bast_love_quotes
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.09K
የሰርጥ መግለጫ

ሰው ስሜቱን ይገልፅ ዘንድ ብዕር ተሠጠው!✍💔📚◆━━━━━━━✎✦✎━━━━━━━━◆
Contact us:⤵️📞
📩 || @Bast_Love_Quotes_Robot

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-10-23 10:53:51 እንዲቀልህ 12

ላንተ በተመቸህና በቀለለህ መንገድ ብቻ ተጓዝ ስለሌሎች ምቾት አትጨነቅ ልብ በል ዛሬ የሰራኸው ማንነትህን ትላንት ሌሎችን ለማመቻቸት ብለህ በተጓዝከው መንገድ በተሰበረ ልብህ ምክንያት ነው። ያጠነከሩህን ክንዶች ብቻ አትርሳ መደገፍ ባለብህ ፈጣሪ ብቻ ተደገፍ እመነኝ መጣል ቀርቶ አያንገዳግድህም።

አንዳንዴ ሁኔታዎች መሆን የማትፈልገውን ሰው ያደርጉሀል።

ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
5.9K views@m måkï , 07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-22 19:43:43 በታሪኩ ላይ ያላችሁን ማንኛውም አስተያየት በቦቱ በኩል ያድርሱን።

@Bast_Love_Quotes_Robot
5.6K views@m måkï , edited  16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-22 19:13:27 ይወት ቀረ።"
ይሄ ግጥም ራሄል ተስፋዋ ሙጥጥ ሲልናራሷን ልታጠፋ በወሰነችበት ቅፅበት የፃፈችዉ እንደሆነ ገመትኩ። "ምን ያህል እንደምወድሽ ብታዉቂ!" አልኩ በልቤ! ግን ህይወት የእዉነታ እንጂ የስሌት ጉዳይ አይደለችምና እዉነቱን ማስተናገዱ ይሻላል።
ስለዚህ ነገር አልተነገረኝም ነበር። የሪቾን ግጥሞች በዚህ መልኩ ሳያቸዉ እንድደመም አስባ ይሆናል ሀዩ ያልነገረችኝ። የራሄል ቤተሰቦች ባዩት ነገር በጣም ተደምመዋል። ምን እነሱ ብቻ እኔ ራሱ የሌለ ተደንቄያለሁ። ሌላዉ በጣም የሚገርመዉ ራሄል ለእኔ የፃፈችዉ የስንብት ደብዳቤ በትልቁ ግድግዳዉ ላይ የተፃፈበት ልዩ የመመገቢያ ክፍል መኖሩ ነዉ። ስገምት ሴቶች ባላቸዉን ለመጋበዝ የሚመርጡት ሁነኛ ቦታ የሚሆን ይመስለኛል። ስታጣኝ እዉነቱን ትጋፈጣለህ አይነት ማስፈራሪያ ሲፈልጉ ማለት ነዉ።
በሀዩ የአመራር ብቃት ተደመምኩ። በቀጣይ ደግሞ ሆቴሉ የአስጎብኚ ቡድን እንዲኖረዉ ለማድረግ አቅደዋል። ሀዩ ታቅዳለች እኔ እየሳቅኩ እፈርማለሁ።
.
ጉብኝቱን ጨርሰን ምግብ ልንበላ የምግብ አዳራሹ ዉስጥ ስንገባ ሰዒዶናኢማን ይዘዉኝ ያደረግከዉ ንግግር የፖለቲከኛ ይመስላል ብለዉ ፎገሩኝ። ሰኢዶናኢማን አንድ ወንድ ልጅ ወልደዋል። ሙሀባ ብለዉታል። የራሄል አባት በተሰራዉ ስራ የተሰማቸዉን ደስታ ገለፁልኝ። ወዲያዉ አንድ የራሄል ቤተሰብ የሆነ ልጅ መጥቶ አድናቆቱን ከገለፀልኝና በዚህ እድሜዬ እንደዚህ ለስኬት መብቃቴ እንደገረመዉ ነግሮኝ ጥያቄ አዘነበብኝ። እሱ ሀብቴ ብዙዉን የዉርስ መሆኑን አያዉቅም። ሲቀጥል ሆቴሉን በዚህ መልኩ የማስተዳድረዉ እኔ መስየዋለሁ። ሀዩ እንደሆነች አያዉቅም።
"አንድ ቆንጆ ምክር እስኪ ምከረኝ!" አለኝ ከኔናከሀዩ ጋር እየተቀመጠ
"በወንድናበሴት መካከል ተፈጥሯዊ መፈላለግ አለ። ስለዚህ ሴት ልጅ ሚስትህ እንጂ የልብ ጓደኛህ አትሁን!" አልኩት። ሀያት ሳቋን ለቀቀችዉ። እኔ ጓደኞቼ ሴቶች በመሆናቸዉ የገባሁበትን ጭንቅ እኔ ነኝ የማዉቀዉ። ራሄል ጓደኝነት በቀደደዉ መንገድ ፍቅር ላይ ወድቃ ነዉ እስከሞት የደረሰችዉ።
"አንተ ጓደኛህን አይደል እንዴ ያገባኸዉ?" አለኝ ወደ ሀያት እየጠቆመ
"አዎ ግን የሞተችዉም ጓደኛዬ ናት።" አልኩትና ወደ ሀዩ እየጠቆምኩ "እሷም ብትሆን ደስታዬ የሆነችዉ ከተጋባን በኋላ ነዉ።" አልኩት።
ልጁ ፈገግ ብሎ ልጃችንን እና ከኛ ቀጥሎ ያለዉ ጠረጴዛ ላይ የተቀመጡትን ቤተሰቦቻችንን እያየ ሳቀና "የናንተ ቤተሰብ በጣም ያስቀናል!" ብሎን እየሳቀ ከመቀመጫዉ ተነስቶ ወደ ቤተሰቦቻችን ጠረጴዛ ሄደ። የልጁ ድፍረት ገረመኝ። ራሄል በወንዱ ነገር ነዉ። ከእናቴ ጋር ማዉራት ጀመረ። ስቀን ዞር አልን።
.
ከሁለት ቀን በኋላ እኔ መኝታ ክፍል ዉስጥ ጋደም ብያለሁ። ሀዩ ራህማን ስታጫዉት ይሰማኛል። የምትለዉን ራህማ እንድትደግመዉ እያደረገች ትስቃለች።
"ረበና" አለች ሀዩ
"አፐና" ትላለች ራህማ! ሀዩ በሳቅ ፍርስ ትላለች
"ማ ኸለቅተ ሀዛ"
"ማተዛ" ትላለች ራህማ! አሁን እኔም በጣም መሳቅ ጀምሬያለሁ። ሀዩ በጣም እያዝናናት ነዉ መሰለኝ ቀጠለች።
"ባጢለን ሱብሀነክ!"
"ባክነን" አለች ራህሚ! በሷ ቤት ሀዩ ያለችዉን መድገሟ ነዉ። አንደበቷ ይጣፍጣል። ከምር ግን እንደ ልጅ ምንም የሚያስደስት ነገር የለም። ሀያት ራህማን ስታስብላት የነበረዉ የቁርዓን አንቀፅ ነዉ። "ረበና ማ ኸለቅተ ሀዛ ባጢለን ሱብሀነክ!" ነበር ያለችዉ። ትርጉሙ "ጌታችን ሆይ ይህን (ድንቅ አለም) እንዲሁ (ያለ ዓላማ) አልፈጠርከዉም ..." ማለት ነዉ። ፈጣሪ ምድርና ሰማይን እንዲህ ያስዋበዉ የስዕል ጥበቡን ለማሳየት አይሆንም። ስለዚህ በከንቱ ያልተፈጠረ ምድር ላይ ከንቱ መሆን አይገባም። ምድር በከንቱ አልተፈጠረችም። እኛም ለጨዋታ አልተፈጠርንም። ህይወታችን ቁምነገር ሊሆን ይገባል!! "የራሄል አምላክ እዉነት ተናገረ!" አልኩ አልጋዉ ላይ እንደተዘረርኩ። አልረሳት ነገር ከልቤ ታትማ ፤ የኔ አትሆን ነገር ከመቃብር ከትማ! ጌታዬን ራህማን እና ሀያትን ስለሰጠኝ አመሰግናለሁ። የተከለከልናቸዉ ከሚመስሉን ነገሮች ይልቅ የተሰጡን ዋጋ አላቸዉ።
.
ተፈፀመ!!
.
✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
5.3K views@m måkï , 16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-22 19:13:27 መንታ መንገድ
ክፍል አስራአምስት
(ፉአድ ሙና)
.
.
ሀዩዬ እንደሷ ቆንጆ ልጅ ወልዳልኝ ሆስፒታል ከተኛች በኋላ በሀኪሞቹ ፈቃድ ወደ ቤተሰቦቿ ቤት ወሰድናት። እናቷ ሁሉንም ነገር አዘጋጅተዉ ጨርሰዉ ነበር። ገንፎ ለሀዩ ይሰራል መግፊ በሷ እያሳበበች ትበላለች። የኔናየመግፊ የሰሞኑ ትርርባችን በገንፎዉ ጉዳይ ላይ ነዉ። ፓምፐርስ ምናምን ከመግፊ ጋር ሆነን ገዝተናል። መግፊ ሆነ ብላ ሴሪፋም አስገዝታ መሳቂያ አደረገችኝ። ለካ እስከ ስድስት ወር ከጡት ሌላ ምንም አይነት ምግብ ለህፃናት አይሰጥም።
ሀዩዬን ልጃችንን ስታጠባ አየኋት ፤ የሆነ ልብ የሚይዝ ነገር አለዉ። ልጇን ስትንከባከብ በጣም ደስ ትላለች።
.
በሰባተኛዉ ቀን ሁለት በግ አርደን ሰደቃ አወጣን። ሰደቃ ማለት ምፅዋት ማለት ነዉ። በሀይማኖታችን መሰረት ልጅ በተወለደ በሰባተኛዉ ቀን የሚደረገዉ ይህ የምፅዋት ዝግጅት አቂቃ ይባላል። በነገራችን ላይ ለልጃችን ስም ለማዉጣት በጣም ብዙ ክርክር ነበር የተፈጠረዉ። መጀመሪያ ራሄል እንድትባል ፈልጌ ነበር። ግን የሀዩም የኔም ቤተሰቦች በራስ ላይ ሀዘንን ማባባስ አያስፈልግም ብለዉ ተቆጡኝና ተዉኩት። እንደዉም የሀዩ እናት "ለሀያትም ስሜት አስብ እንጂ! ማትፈልጋት እንዳይመስላት!" ነበር ያሉኝ። ሀዩ ብዙ ነገር ስላደረገችልኝ ስሜቷን መጠበቅ ይኖርብኛል። ራሄልን ለመዘከር ሆቴሉ ይበቃል። ብዙ የስም ምርጫዎች ከቀረቡ በኋላ መጨረሻ ላይ "ራህማ" የሚለዉ የኔ ምርጫ ተቀባይነት አገኘ። እኔ ራህማ እንድትባል የፈለግኩት ከራሄል ሞት በኋላ የነበርኩበትን መጥፎ ሁኔታ ፣ አልጋ ላይ የነበረብኝን ያለመረጋጋት ችግር እና ጥፊዬን ችላ ለኖረችዉ ዉዷ ሚስቴ ሀያት ስጦታ እንዲሆን በማሰብ ነዉ። ነብዩ አዩብ(እዮብ) በሽታ ሲፈራረቅበት ፣ ሀብቱ ሁሉ ሲወድም እና ሌሎች ሚስቶቹ ትተዉት ሲሄዱ በፅናት ከጎኑ የቆየችዉ አንዷ ሚስቱ ራህማ ብቻ ነበረች። እናም የኔ ልጅ ከብዙ ችግር በኋላ የተገኘች ናትና የሚስቴን ትዕግስት ለመዘከር ራህማ አልኳት። ራህማ ማለት እዝነት ማለት ነዉ።
.
ሀጅራ ፣ እስክንድር እና የሪቾ ቤተሰቦች ፤ ቤት መጥተዉ ሀዩን አራስ ጠይቀዋታል። በነገራችን ላይ ሀጅራ ታጭታለች። በቅርቡ ማግባቷ አይቀርም። የአክስቴ ልጅ እና የዉዱ ጓደኛዬ ሰዒድ ሚስት ኢማን ሰሞኑን ከነሀያት ቤተሰቦች ቤት ጠፍታ አታዉቅም። ኢስራዕ እና መርየም ቤታቸዉ አድርገዉታል። ከመግፊራ ጋር ሆነዉ ሀዩን ያዳብሯታል። እናቴም ከአባቴ ሞት በኋላ ትንሽ ስርዓት ይዛለች። ከአክስቶቼም ጋር ታርቀዋል። ምግብ እየሰራች ለሀዩ ይዛላት ትመጣለች። ከምር ልጅ ግን የደስታ ምንጭ ነዉ። ስራ ዉዬ ማታ አይኗን እስከማይ እንዴት እንደምጓጓ! በርግጥ ለሀዩዬ ያለኝም ፍቅር በጣም ጨምሯል።
.
ጊዜዉ በሀዩ ፍቅርና በራህማ ጨዋታ ታጅቦ ነጎደ። ራህማዬ ሁለት አመት ሞላት። የራሄል ሆቴል ግንባታም ተጠናቀቀ። አጠቃላይ እቃዎቹን ሳይጨምር ለግንባታ ብቻ አስር ሚሊየን ብር አዉጥተናል። በርግጥ ቢዝነሱ አስተማማኝ ስለሆነ በአመት ዉስጥ ይመልሰዋል። በዛ ላይ ሀዩን የመሰለች የምርጥ ጭንቅላት ባለቤት ናት የምታስተዳድረዉ። የዉስጥ እቃዎቹን ከዉጭ ካስመጣንናእነሀያት ሰራተኞችን ከቀጠሩ በኋላ የሚመረቅበት ቀን ደረሰ። ሆቴሉ በአክሲዮን የተከፈተ ነዉ። የእኔ ቤተሰብ ፣ የሀያት ቤተሰብ ፣ የራሄል ቤተሰቦች ፣ እስክንድር ፣ ሰዒድ እና ሀጅራ ነን ባለድርሻዎቹ። ትልቁ ድርሻ ግን የኔ እና የሀዩ ቤተሰቦች ነዉ። የሆቴሉ የቦርድ ሰብሳቢ እኔ እንድሆን ተወስኗል። ሆቴሉን በስራ አስኪያጅነት ደግሞ ሀያት ትመራዋለች። ምክትል ስራ አስኪያጁ ልምድ ያለዉ ሰዉ ነዉ። ሀጅራ እና እስክንድርም ዉስጥ ላይ የሀላፊነት ቦታዎችን ይዘዉ ይመራሉ። ከምርቃቱ በፊት የማስታወቂያ ክፍላችን ሆቴላችን በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ እንዲተዋወቅ አደረገ። እነሀያት በስራዉ በጣም ተወጥረዋል። እኔ እንኳ የራሴን ስራ ስለምሰራ በሳምንት አንዴ ነዉ ሪፖርታቸዉን ለማዳመጥ የምሄደዉ።
.
ጠዋት ቢሮ ስገባ ፀሀፊዬ ሞጆ ደረቅ ወደብ ላይ ስላሉ እቃዎች ካወራችኝ በኋላ አንድ ደብዳቤ ሰጥታኝ ወጣች። ከራሄል ሆቴል ይላል። እነሀያት እንደላኩት ገመትኩ። ከፍቼ አነበብኩት።
"የራሄል ሆቴል የምርቃት ስነ ስርዓት በቀጣዩ ሳምንት እንደሚደረግ ይታወቃል። በመሆኑም ሆቴሉ የራሄል መታሰቢያ እንደመሆኑ በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ስለ ራሄል የሚዳስስ አጭር ፅሁፍ መቅረብ ይኖርበታል። ስለሆነም እንደ ሆቴሉ የቦርድ ሰብሳቢነትዎ በእለቱ ይህን ሀሳብ ባካተተ መልኩ የመክፈቻ ንግግር እንዲያደርጉልን በአክብሮት እንጠይቃለን። ከሰላምታ ጋር!" ይላል። ከስሩ የሀያት ፊርማ አለዉ። ረዥም ሰዓት ብቻዬን ሳቅኩ። ለምን ሳቅኩ? ሀዩ ለኔ ደብዳቤ መፃፏ ገርሞኝ! እሷ ስራ ላይ ቀልድ አታዉቅም።
.
የሆቴሉ ምርቃት ሲጠጋ ሀያት ስራ ስለበዛባት አንዳንዴ አስፈቅዳኝ እዛዉ ታድራለች። ራህማን ሁሌም ስራ ስትሄድ ይዛት ነዉ የምትሄደዉ። "አንተ እኔን እንጂ እሷን ማቀፍ አትችልበትም!" ትላለች ሀዩ። ለነገሩ ራህማ መራመድ እና ትንሽ ትንሽ መናገር ጀምራለች።
ከብዙ ዉጥረት በኋላ የራሄል ሆቴል ምርቃት ደረሰ። የዛን ቀን ሀዩ ሆቴል ስለነበር ያደረችዉ ከኢስራዕናማማ ጋር ሄድኩ። መርየም ከባሏ ጋር ሄዳለች። የሆቴላችን በር ላይ ስደርስ ድባቡ ለየት ያለ ነዉ። መኪናዬን የሆቴሉ ፓርኪንግ ጋር አቁመን ወደ ዉስጥ ገባን። ሱፍ የለበሱ ወጣቶች ወዲያዉ እየተቀላጠፉ ወደ ሆቴሉ አዳራሽ ይዘዉን ሄዱ። ብዙ ሰዉ አለ። አዳራሹ ጋር ስንደርስ ሀዩ በሩ ጋር ቆማ እንግዳ እየተቀበለች አገኘኋት። ሰላም ካለችን በኋላ ኮሌታዬን አስተካክላልኝ ወደ ተዘጋጀልን መቀመጫ ወሰደችን። እንግዳዉ ሁሉ ቦታ ቦታ ከያዘ በኋላ መድረክ መሪዉ ወደ መድረክ ወጥቶ የእለቱን ዝግጅቶች አስተዋወቀ። ከዚያም ሀያትን ወደ መድረክ ጠርቶ እኔን ንግግር እንዳደርግ እንድትጋብዘኝ አደረገ። እንግዲህ የቦርድ ሰብሳቢዉ በስራአስኪያጇ መጋበዙ ነዉ። ሀዩ ስታወራ አንቱ እያለችኝ ነበር። እኔ ሳቄን ለመቆጣጠር እየታገልኩ ነዉ።
.
መድረኩ ላይ ወጥቼ ንግግሬን ጀመርኩ። ሁሉም አፉን ከፍቶ ያዳምጣል።
"ዛሬ በዋናነት በስራ አስፈፃሚዎቻችን ብርታት ሆቴላችንን ለመመረቅ በቅተናል። ግን መረሳት የሌለበት፤ ሆቴሉ ትናንት አብራን በአንድ ጎዳና ላይ ስትጓዝ የነበረችናብዙ ህልም የነበራት ጓደኛችን መታሰቢያ መሆኑ ነዉ። የራሄል ዉበት በሆቴላችን አይነግቡነት ይገለፃል። የሰላ ብዕሯን የማስታወቂያ ቡድናችን ተቋማችንን ያስተዋዉቅበታል። ለሰዉ የነበራትን ፍቅር ሰራተኞቻችን እርስ በእርስ ይዋደዱበታል። እሷን መልሰን ማግኘት ባንችልም ሆቴሉን ትልቅ ደረጃ በማድረስ ከፍ አድርገን እንዘክራታለን። ራሄል ሆቴል በይፋ ተከፍቷል!!" አልኩና ከመድረኩ ወረድኩ። ታዳሚዉ ያጨበጭባል።
.
የመንግስት ባለስልጣናት ዲስኩራቸዉን ካሰሙ በኋላ ታዳሚዉ ሆቴሉን እንዲጎበኘዉ ተደረገ። በየኮሪደሩ ላይ የራሄል ፎቶ በሚያምር ፍሬም ተሰቅሏል። አንድ ጥግ ላይ ደግሞ የራሄል የተመረጡ ግጥሞች በልዩ ዲዛይን ተሰርተዉ ግድግዳዉ ላይ ተሰቅለዋል። አይኔ አንዱ ግጥም ላይ አረፈ። መንታ መንገድ ይላል አርዕስቱ
"መንታ መንገድ ፊት ቆሞ ፈራጁ፣
ምረጥ ተባለ ከመንገዶቹ፣
ግራዉን መንገድ እየወደደዉ
ለሀይማኖት ሲል ቀኙን መረጠዉ።
ቀኝ በጎ ነዉ ሲባል የሰማ፣
ነገዉን ብሎ ግራዉን ያማ፣
ሚስኪን አፍቃሪ ፍቅሩን ተቀማ።
ግራዉ ፈራጁን ማግኘት ቢነፈግ፣
ፈገግታ ሰጡት ለቅሶ ሚሸሽግ።
ሳቀ ሳቀና አንብቶ አንብቶ፣
ፈራጅን ሲያልም ዉሎ አምሽቶ፣
ተስፋ ሲቆርጥ ፣ ፈርሶ አደረ፣
ከተጠራበት ፣ ከህ
4.5K views@m måkï , 16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-20 18:54:35 መመኝ። ከአይኔ እንባ ፈሰሰ። "ኧረ በፀጋ አይለቀስም! አላህን ፍራ!" አሉኝ የሀዩ እናት። ሰዒዶ ከክፍሉ ራቅ ብሎ ወዳለ መቀመጫ ወሰደኝ። ሰዒድ እያየኝ ይስቃል። "ልጅም አባትም አልቅሳችሁ እንዴት ይሆናል!" አለኝ እየሳቀ!
ንግግሩ እያሳቀኝ "እሱን ኢማን ስትወልድልህ ትቀምሰዋለህ!" አልኩት።
ወዲያዉ የማዋለጃዉ ክፍል በር ሲከፈት አየን። ከተቀመጥንበት ተነሳን። ከክፍሉ አንድ ዉሀ ሰማያዊ የህክምና ልብስ የለበሰች ሴት ወጥታ እነመግፊራን ማናገር ጀመረች። ወደ ክፍሉ በፍጥነት እየተራመድን ተጠጋን። የህፃን ልጅ ለቅሶ ይሰማል። የነመግፊራ ፊት ላይ ደስታ ይነበባል። ወዲያዉ መሬት ላይ በግንባሬ ተደፍቼ ጌታዬን አመሰገንኩ። እነመግፊን ተከትዬ ወደ ማዋለጃ ክፍሉ ገባሁ። ሀዩዬ ፊቷ በላብ ተጠምቆ ተጋድማለች። ስታየኝ ፈገግ አለች። ተንደርድሬ ሄጄ አልጋዉ አጠገብ ተንበርክኬ እጇን ያዝኩት። ጠጋ ብዬ ግንባሯን ሳምኳት።
"ደሞ አሁን ቆንጆ የሴት ስም እንፈልግ!" አለች መግፊራ! ልጄ ሴት ነበረች። ደስ አለኝ። ደስታዬ ወደር የለዉም። በጣም ደስስስስ አለኝ።
"ያንተንም ጉድ እናየዋለን ሰዒዶ!" አለች ሀዩ ወደ ሰዒድ እያየች።
"እስኪ አላህ ያድርሰን!" አለ እየተሽኮረመመ።
ወዲያዉ ሀኪሞቹ ግርግሩን እንድንቀንስ እና እንድንወጣ አዘዙን። እናቷ ብቻ ቀሩ። እኔና መግፊራ ለጊዜዉ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ለመግዛት ሄድን።
.
ይቀጥላል...

.
✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
5.1K views@m måkï , 15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-20 18:54:35 መንታ መንገድ
ክፍል አስራአራት
(ፉአድ ሙና)
.
.
ራሴን ከአንድ ሰዓት ለሚበልጥ ጊዜ አላዉቅም ነበር። አይኔን ስገልጥ ነጭ አምፖል ሰማያዊ ኮርኒስ ላይ ይታየኛል። ወዲያዉ ቀና ስል ከፊት ለፊቴ ሰዒድ እና ቁርዓን ሲቀራብኝ የነበረዉ ሰዉዬ እየተመለከቱኝ ነበር።
ቁርዓን ሲቀራብኝ የነበረዉ ሰዉ ወዲያዉ ጌታዬን እንዳመሰግን አዘዘኝ። አመሰገንኩ። ወዲያዉ ወደ ጆሮዬ ተጠግቶ ለስግደት ጥሪ የሚደረገዉን አዛን እያደረገ የማጅራቴን ደምስሮች በጣቱ ነካካቸዉ።
"ሴቶች በጣም ይወዱህ ነበር?" አለኝ ኡስታዙ ሰዒድ አጠገብ እየተቀመጠ
"እንደዛ ነገር" አልኩት።
"ያይኔአበባ የምትባል ሴት ታዉቃለህ?" አለኝ አይን አይኔን እያየ።
"አዎ ዩኒቨርሲቲ ስማር የምጠቀምበት ምግብ ቤት አስተናጋጅ ናት።" አልኩት።
ሰዒድ በግርምት አንገቱን ነቀነቀ። ኡስታዙ "እዛ ቤት በጣም ጣፍጦህ የበላህበት ቀን ትዝ ይልሀል?" አለኝ።
እንደድንገት አንድ ቀን የበዓል ስጦታ ብላ ያይኔአበባ የሰጠችኝ ምግብ ትዝ አለኝ። እንደዉም ብቻዬን ዶርም ነበር የበላሁት። ኡስታዙ ሌሎች ጥያቄዎችንም ጠይቆኝ ከመለስኩለት በኋላ ድግምቱ የተሰራብኝ በያይኔአበባ እንደሆነ ነገረኝ። ያይኔአበባ ወዳኝ እንደነበር ግን ልትፎካከራቸዉ በማትችላቸዉ ቆንጆ ሴቶች ተከብቤ የነበረ በመሆኑ ድግምት እንዳሰራችብኝ ራሴን በሳትኩበት ሰዓት ዉስጤ የነበረዉ ጋኔን መናገሩን አረዱኝ። ኡስታዙ አሁን በፈጣሪ ፈቃድ ድግምቱ መክሸፉንና ዉስጤ የነበረዉ መጥፎ ስሜትም እንደሚወገድ አበሰረኝ። በሀይማኖቴ መጠንከር እንደሚኖርብኝ መክሮ ከግብረስጋ ግንኙነት በፊት ላደርጋቸዉ የሚገቡ ነገሮችን መከረኝ። .
በተፈጠረዉ ነገር እኔም ሰዒድም ተገርመናል። መኪና ዉስጥ እንደገባን ሰዒድ "በል እስኪ ዛሬ ሂድና ሞክራት እና ጉዱን እንየዉ!" አለኝ እየሳቀ። እዉነት ለመናገር በጣም ቅልል ብሎኛል።
.
ማታ ቤት ስገባ ሀዩ አኩርፋ መጅሊሱ ላይ ተቀምጣለች። ደሞ ምን ተፈጠረ? "ሀዩዬ ምን ተፈጠረ?" አልኳት ከጎኗ እየተንበረከክኩ።
"አክረሜ ልዉለድልህ ፍቀድልኝ!" አለች እያለቀሰች። የአልጋ ላይ ፀባዬ እስኪስተካከል ላለመዉለድ ወስኜ መድሀኒት እንድትወስድ አዝዣት ነበር። አይ ሀዩ! ከነዚህ የአልጋ ላይ ፀባዬ ምንም ሳትጠላኝ ልትወልድልኝ መጓጓቷ የፈጣሪ ስጦታ እንደሆነች እንዳስብ አደረገኝ። ፈገግ አልኩና "አላህ ካለ ነገ ጠዋት መልሴን እነግርሻለሁ!" አልኳት ዛሬ ማታ ሊፈጠር የሚችለዉን ሰላማዊ ለሊት ተስፋ እያደረግኩኝ።
.
ማታዉን ኡስታዙ በነገረኝ መልኩ ግንኙነት ከመፈፀማችን በፊት ሰግጄ ፀሎት አደረስኩ። ከዛም የሀዩ ጭንቅላት ላይ መዳፌን አስቀምጬ ጌታዬን ለመንኩ። ዉስጤ በእርጋታ ተሞልቷል።
ሀዩን ሳምኳት ፣ እጄ ጥፊ እንዳይቀድመዉ ፈርቼያለሁ። እየተሳሳምን በስሜት ጠፋን። እጆቼ ሰዉነቷ ላይ ተንሸራሸሩ። ልክ እንደሰዉ ተገናኘኋት። ሀዩ ፊቷ በእርካታ ተሞልቶ እየሳቀች "ጌታዬ እንደማያሳፍረኝ አዉቅ ነበር።" አለችኝ። የረዥም ጊዜ ፀሎቷ ይሄ ነበር መሰለኝ። ሁለታችንም መድገም ፈለግን! ሀይል አሰባስበን ደገምነዉ። እርካታ ጣራ ነካ! ማመን ከበደኝ። የምድርን ጣፋጩን ነገር በእርጋታ ማጣጣም ቻልኩኝ። ሀዩ እቅፌ ዉስጥ ቀለጠች። ፍልቅልቅ እያለች "አፈቅርሀለሁ።" አለችኝ። ጌታዬን አመስግኜ ሀዩን እቅፍ አድርጌ ተኛሁ።
.
በነጋታዉ ጠዋት ሀዩ ከእንቅልፍ እንደተነሳን የወሰደችዉ የመጀመሪያዉ እርምጃ የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒኖችን መጣል ነበር። አሁን ልጅ ያስፈልገናል። ጠዋቱን ሰዒዶ ደወለና "እ ጄኪጃን አደብ ገዝተህ አደርክ ወይስ?" አለኝ።
"ኧረ አልሀምዱሊላህ ዛሬ ጥፍጥናን አጣጣምኩት። አሁን ከልቤ እንድትቀምሰዉ ተመኝቼልሀለሁ።" አልኩት።
ተገናኝተን ስለጋብቻዉ ለማዉራት ተቀጣጥረን ስልኩን ዘጋዉ። ሀዩን በሙሉ አይኔ ለማየት ደፈርኩ። ግንኙነት የፈፀምን ለሊት ያዉ ስለምመታት ጠዋቱን ቀና ብዬ ላያት በጣም ነበር የምሸማቀቀዉ። ጠዋት ቁርስ እኔ ካልሰራሁ ብላትም ከለከለችኝ። ሁኔታዬ ሁሉ እያሳቃት ነዉ። ወንድነቴ ልኩን መያዙ ከሀዩ ጋር የተሻለ ቅርርብ እንዲኖረኝ አደረገኝ።
.
ጠዋቱን ሀዩን ወደ ቢሮዋ አድርሼያት እኔ ወደ ስራ ሄድኩ። የራሄል ሆቴልን ጉዳይ በተመለከተ በዋናነት እየመራችዉ ያለችዉ ሀዩ ናት። አሁን ግንባታዉ ተጀምሯል። ሀጅራም አዲስአበባ ሆና ስራዉ እንዲቀላጠፍ ለማድረግ እየጣሩ ነዉ። እስክንድር አዲስ ፍቅረኛ ይዟል። እስክንድርን ካየሁ ሁሌም ራሄል ትዝ ትለኛለች። አሁን እንኳ ሀዘኔ በጣም ደብዝዟል። ግን በጣም የገረመኝ የተሰራብኝ ድግምት ከዝሙት እኔን ለመታደግ ምክንያት መሆኑ ነዉ። ከራሄል ጋር ያደርን ለሊት ስሜቴ ሲግል በጥፊ መታኋት እና አልጋ ላይ ተዘረረች። እዛዉ እንዳለች ልገናኛት ወደ አልጋዉ ስሄድ እንደዉም አብሬያት መተኛት ያልፈለግኩ መስሏት ተፈናጥራ ተነሳች። ለመጥፎ የተደረገብኝ ለጥሩ ጠቀመኝ። ምንም የስድስት ወሩ የስቃይ ጊዜ ባይረሳም ማለት ነዉ። ለሀዩ ትዕግስት ግን ምድር ላይ የሚመጥነዉ ሽልማት አላገኘሁም።
.
ጊዜዉ ሄዶ የሰዒዶ እና የኢማን ኒካህ ደረሰ። ደስ በሚል ስነ ስርዓት የኒካህ ስነ ስርአቱ ተደረገና ከሁለት ቀን በኋላ ሰርጉ ተደገሰ። ሚዜ ነበርኩኝ። በጣም ደስ የሚል ነበር። የሰርጉ ቀን ማታዉን ሆቴል እንዳደረስናቸዉ ፈገግ ብዬ "በል ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም!" አልኩት።
ሰዒዴ ንግግሬን ጠምዝዞ "ኧረ እኛ ተዋጊ አንፈልግም!" አለኝ እየሳቀ። በጥፊ የሚማታ አንፈልግም ማለቱ እንደሆነ እኔናእሱ ተግባብተናል።
.
ጊዜዉ ሄዶ የሀዩ ሆድም ገፋ! እየደከማት ስትቸገር የሷን ስራ ከነሀጅራ ጋር እየተደጋገፍን ለመሸፈን ሞክረን እሷ ቤት እንድታርፍ አደረግን። ሀዩዬ ስታረግዝ አንዳንድ የፀባይ መቀያየሮች ቢስተዋሉባትም እንደምንም ታግሼ ተንከባከብኳት። አንዳንዴ ለአይኗ ሁሉ አስጠላታለሁ። አንዳንዴ ድብርት በጣም ይጫጫናታል። የእርግዝናዉ ፀባይ እንደሆነ ስለገባኝ ምንም ሳልበሳጭ የምትፈልገዉን ሁሉ ለማቅረብ ሞከርኩ።
.
ሀዩ ዘጠነኛ ወሯን ከያዘች በኋላ ብዙም ከሀዩ ቤተሰቦች ቤት አልጠፋም ነበር። ቢሮ ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮችን አስተካክዬ ወደሀዩ ወላጆች ቤት እመለሳለሁ። ከሀዩ ጋር ግንኙነት መፈፀም ካቆምን ሁለት ወር ሆነን። የእዉነት አግኝቶ ማጣት ከባድ ነዉ። ወንድነቴ ሀዩን አምጣ ብሎ ሊገለኝ ምንም አልቀረዉም። ገና ወልዳ ደሞ የወሊድ ደም እስከሚቆም ግንኙነት እንደማንፈፅም ሳስበዉ ሰቀጠጠኝ። የሀዩ ገላ ናፍቆኛል።
የሀዩ ፅንስ በጣም ስለገፋ ወደ ቤተሰቦቿ ቤት ሄዳ እናቷ በጣም እየተንከባከቧት ነዉ።
ጁምዓ(አርብ) ጠዋት ላይ መግፊራ ደወለችልኝ።
"እሺ እጩ አክስት!" አልኩ ስልኩን አንስቼ
"እጩ አባት! ሚስትዎ እያማጠች ነዉ። ኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል እየሄድን ስለሆነ ቢመጡ!" አለችኝ።
መግፊ ቀልዷናምሯ አይለይም። "መግፊ እስኪ ወላሂ በይ!" አልኳት።
ወዲያዉ ስልኩን ወደ ሀዩ አስጠግታ ስታምጥ አሰማችኝ። መኪና እንደዚህ በፍጥነት መንዳት እችል ነበር እንዴ? በሀያ ደቂቃ ዉስጥ ሆስፒታል ደረስኩ። መግፊራ ጋር ደዉዬ ወጥታ ይዛኝ ገባች።
ሀዩ የማዋለጃ ክፍል ዉስጥ ናት። መግባት እንደማልችል ተነግሮኝ በር ላይ ከነመግፊር ጋር ተቀመጥኩ። ደስ የሚለዉ አዋላጆቹ ሴቶች ናቸዉ። ወንድ የሚስትህን ብልት እየነካካ ሲያዋልዳት በጣም ይቀፋል። በተቻለዉ መጠን ሴቶች ስራዉን በፍጥነት ሊቆጣጠሩት ይገባል።
የሀዩ የስቃይ ድምፅ አልፎአልፎ ይሰማኛል። ሀዩ ስትሰቃይ እኔን አመመኝ። ለሰዒዶ መንገድ ላይ እያለሁ ደዉዬ ነግሬዉ ስለነበር ደርሶ ከኛ ጋር ተቀምጧል። የሀዩ እያንዳንዷ ጩኸት በጣም አ
4.7K views@m måkï , 15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-19 19:23:23 ም አይን ለአይን ተያይተን ሳቅንና እኩል "ኢማን" አልን። ኢማን ሁሌም እኛ ቤት መጥታ እሱ ካለ እኔን ደክሞሀል ምናምን ብሎ ሰበብ ሰጥቶ እሱ ነበር ወደ ቤቷ የሚያደርሳት።
"እና አዉርታችኋላ!" አልኩት።
"ሁሉም አልቋል። ኒካህ ብቻ!" አለኝ እየሳቀ። ኢማን በጣም የምወዳት የአክስቴ ልጅ ናት። በፀባዩ የምተማመንበትን ጓደኛዬን ስለምታገባ ደስ አለኝ። የሱን ጉዳይ አዉርተን እንደጨረስን የእኔን ጉዳይ በሙሉ ነገርኩት። ሰዒድ ለኔ በጣም አዘነና "አክረሜ ይሄ ነገር ድግምት ሊሆን ይችላል። ብዙ ሴቶች ይወዱህ ስለነበር አስነክተዉህ ይሆናል።" አለኝ። ወደዱኝ ከተባሉት ሴቶች የቀረብኳቸዉ ሀያትንእናራሄልን ነዉ። ሁለቱም ደግሞ እኔን የሚጎዳ ነገር እንደማያደርጉ እርግጠኛ ነኝ። ቢሆንም ነገሮችን ማረጋገጡ ሳይሻል አይቀርም በሚለዉ በቁርዓን ህክምና ጤናዬን ልንፈትሸዉ ወሰንን።
.
በነጋታዉ ለማንም ሳንናገር እኔናሰዒዶ ወደ አንድ የቁርዓን ህክምና ማዕከል ሄድን። ብዙ ሰዉ ከኔዉ ጋር በተያያዘ ጉዳይ ማለትም በድግምት እና በአጋንንት ተበጥብጦ ህክምና ለማግኘት ተቀምጧል። በመሀል ከተማችን ዉስጥ እንደዚህ ድግምት አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑ አሳዘነኝ። ተራዬ ሲደርስ ወደ ህክምና ክፍሉ ገባሁ። ሰዒድም አብሮኝ ገባ። አንድ ነጭ ጀለቢያ የለበሰ ኡስታዝ ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ተቀምጦ ችግሬን ካዳመጠኝ በኋላ ወደ ቀጣዩ ክፍል አስገባኝ። ቀጣዩ ክፍል ሙሉ ለሙሉ ምንጣፍ የተነጠፈበት ክፍል ነበር። የመኪናዬን ቁልፍ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ የያዝኳቸዉን ነገሮች ለሰዒድ ከሰጠሁት በኋላ ሰዉየዉ ጮክ ብሎ ቁርዓን መቅራት ጀመረ። መጀመሪያ ድምፁ በጣም ያምር ነበር። ከዛም የሆነ ብስጭት ዉርር አደረገኝናድምፁ አስጠላኝ። ከዚህ በኋላ ምን እንደተፈጠረ ነቅቼ ሰዒድ እስኪነግረኝ ድረስ አላዉቅም።
.
ይቀጥላል...

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
4.6K views@m måkï , 16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-19 19:23:23 መንታ መንገድ
ክፍል አስራሶስት
(ፉአድ ሙና)
.
.
ሀያት ከተመረቀች በኋላ ቤተሰቦቿም የሰርጉን ነገር ቀድመዉ አናግረዉኝ ስለነበር የዝግጅቱ ጥድፊያ ዉስጥ ገባን። አዳራሽ መከራየት ፣ ለጊዜዉ የምንኖርበት ቤት መከራየት ፣ የቤት እቃ መገዛዛት ኧረ ስንቱ ተዘርዝሮ ይቻላል? ጣጣዉ ብዙ ነዉ። ደስ የሚለዉ የቤት ዕቃ መገዛዛቱን ኢስራዕ እና መርየም ከኢማን ጋር ሆነዉ አገዙን። እኔ ቆንጆ ቤት አግኝቼ ተከራይቻለሁ። የእናቴን ፀባይ ስለማዉቀዉ ከሀያት ጋር ብቻችንን እንድንኖር ፈለግኩ እንጂ እናቴ ከሷ ጋር እንድኖር ጠይቃኝ ነበር። ሰዒዶ የአዳራሹን ነገር ጨርሷል። የአክስቴ ልጆችም በጣም አግዘዉኛል። በተለይ ኢማን የሷ ሰርግ ነበር የሚመስለዉ። ብቻ ዋና ዋናዉን ጨርሰን የጥሪ ስራዎችን ምናምን መስራት ጀመርን። የሰርግ ጣጣ ግን ብዙ ነዉ። ከምር እንደዉም ቢቀር ያስብላል። ቀለል ያለ ድግስ ቢሆን ይሻል ነበር።

.
ከብዙ ዉጥረት በኋላ የሰርጉ ቀን ደረሰ። ይገርማል አባዬ ኒካህ ላይ ተገኝቶ ለሰርጉ ሳይደርስ ሞተ። አንደኛ ሚዜዬ ሰዒድ ነዉ። ሁለተኛናሶስተኛ ሚዜዎቼ የአጎቴ ልጆች ናቸዉ።
በሚዜዎቼ ታጅቤ ሀያትን በወጉ ከቤቷ ወሰድኳት። ሀዩ ቬሎ አምሮባታል አይገልፀዉም። አዳራሹ ሰርጋችንን ለማድመቅ በመጡ እድምተኞች ደምቋል። የሙሽራዉ ቦታ ላይ ከሚዜዎቼ ጋር ተቀምጬ ሰውን አየሁት! ይበላል፤ይጠጣል። በጣም ደስ አለኝ። በየአንዳንዷ ጉርሻ ዉስጥ ሀያትን ላይመኝ ማጣቱንና የኔ መሆኗን አብሮ የሚዉጥ መሰለኝ።
.
የሰርጉ ቀን ማታ ከሀዩዬ ጋር ሆቴል ነበር ያደርነዉ። ልክ ክፍላችን እንደገባን ሁለታችንም ትንሽ ደከም ብሎን ስለነበር ገላችንን ታጠብን። ትንሽ ቀለል አለን። እራት በልተን ከጨረስን በኋላ ከሀዩ ጋር የፍቅር ጨዋታዉ ተጀመረ። እየተሳሳምን ልብሷን ቀስ ብዬ አወለቅኩትና በጡት ማስያዣናበፓንት ብቻ አስቀረኋት። ዉበቷ ሊያቀልጠኝ ምንም አልቀረዉም። በጣም ታምራለች። ገላዋ ዉብ ነዉ። ዛሬ ለኔ ብቻ የተገለጠ፣ ማንም ያላየዉ ገላ! ልብሴን በዚህ ፍጥነት ማዉለቅ እንደምችል እስከዚህች ቅፅበት ድረስ አላዉቅም ነበር። ሀዩ እንደዛሬዋ ቀን የጓጓችለት ቀን ያለ አይመስለኝም። አልጋዉ ላይ ተጋድመን መሳሳም ጀመርን። የተቀደሰ መሳሳም! ትዳር ነዉና መልዓክት ሳይቀር በደስታ ሳይዘምሩ አይቀሩም። ስሜቴ በጣም እየጋለ መጣ። እራሴን መቆጣጠር ከበደኝ። ሳላስበዉ ሀዩን በጥፊ መታኋት እና የጡት ማስያዣዋን ከሰዉነቷ ላይ ገንጥዬ አነሳሁት። ሀዩ በጣም ደንግጣለች ግን ከስሬ ሁና የማደርገዉን ታያለች። ለመነሳት አልሞከረችም። እዛዉ እንደተንጋለለች በጥፊዬ ህመም ምክንያት ከአይኗ እንባ እየፈሰሳት የልቤን አደረስኩ።
.
ሀያትን ምንም ስሜቷን ሳልጠብቅ ነበር የተገናኘኋት። መረጋጋት ተሳነኝ። ስሜቴ ሲግል በጥፊ የመታኋት ለምን እንደሆነ አላዉቅም። ግን ከዚህ በፊት ራሄልንም መትቼያት ነበር። አሁን ትንሽ ግልፅ ሆነልኝ። አልጋ ላይ መረጋጋት አልችልም። ሀዩን ማየት በጣም አፈርኩ። ተንደርድሬ ወደ በረንዳዉ ወጣሁ። በረንዳዉ ላይ ያለዉ ዥዋዥዌ ወንበር ላይ ተቀምጬ ተንሰቅስቄ አለቀስኩ። በምድር ላይ ያለዉን የደስታ ጥግ ማጣጣም ካለመቻል በላይ ምንም ህመም ሊኖር አይችልም። የሚስትን ክብር መጠበቅ ካለመቻልናስሜቷን ለማስተናገድ ብቁ ካለመሆን በላይ ከባድ መርዶ የለም። ጌታዬ ምነዉ ሀዘኔ በዛ?
.
አልቅሼ ስገባ ሀዩ አልጋዉ ዉስጥ ገብታ ተኝታ ነበር። ፈገግ ለማለት ሞከረች። እየቀፈፈኝም ቢሆን ከአጠገቧ ሄጄ ተኛሁ። ደረቴ ላይ ልጥፍ ብላ ተኛች። ደረቴ ላይ ስትተኛ ብዙም እንዳልተከፋችብኝ በማሰብ በጣም ደስ አለኝ።
.
በነጋታዉ ከሆቴል ወደ ተከራየነዉ ቤት ሄድን። ማታ ላይም ስንደግመዉ ስሜቴ ሲግል እጄ ጥፊ መሰንዘሩንና መድፈር በሚመስል መልኩ መገናኘቴን መተዉ አልቻልኩም። ሳምንት ሙሉ አየነዉ ፣ ያዉ ነዉ።
በሳምንቱ የስነ ልቦና ባለሙያ አማከርኩኝ። የህይወት ታሪኬን ሁሉ ከፈተሸ በኋላ ምናልባት የችግሩ መንስኤ የእናትናአባቴን ድብድብ ሳይ ማደጌ ሊሆን እንደሚችል ነገረኝ። የአባቴና የእናቴ ፀብ ለኔም ተረፈ? ታዲያ ለምን ፀባዬ ግንኙነት ስፈፅም ብቻ ይቀየራል? መልስ አላገኘሁለትም።
.
ሀያት ትምህርቷን እንደመጨረሷ በተማረችበት ሙያ መስራት ትፈልጋለች። ዩኒቨርሲቲዉ ከፍተኛ ዉጤት ስላላት መምህር እንድትሆን ሊያስቀራት ፈልጎ የነበረ ቢሆንም እሷ አልተቀበለችዉም። አሁን አዲስ ሆቴል ከአዲስአበባ ዉጪ ለመክፈት አቅደናል። ሀጅራ እስክንድር እኔና ሀዩ ተሰባስበን ከመከርንበት በኋላ ሆቴሉን ራሄል ልንለዉ ወሰንን። ራሄልን የምናስታዉስበት አንድ ተቋም ይሆነናል ብለን አስበናል። ለሆቴሉ ግንባታ የኛ ቤተሰብ እና የሀዩ ቤተሰቦች በአክሲዮን መልክ ከፍተኛዉን መዋጮ አዋጣን። መሬት የከተማዉ መዉጫ ላይ አገኘን። የህንፃዉም የዲዛይን ስራ ተጀመረ።
.
ሀያትን በአግባቡ ልገናኛት አለመቻሌ እንደድሮዉ ፈታ ብዬ እንዳላወራት አደረገኝ። የተገናኘኋት ጠዋት ሀፍረት ሊዉጠኝ ይደርሳል። ምንም ሳላወራ ቁርሴን በልቼ ወደ ስራ እሄዳለሁ። ሀያት ግን ስሜቴን ስለተረዳችዉ ፈታ ልታደርገኝ ትሞክራለች። ጠዋት ወደ ስራ ስሄድ መኪናዬ ከአይኗ ሳይርቅ ወደ ቤት አትገባም። ልብሴ ሆና ሚስጥሬን ሸሽጋልኛለች።
.
አንድ ቀን ከሀያት ጋር የሀዩን ወላጆች ለመጠየቅ ወደ ቤታቸዉ ሄድን። በልተን ፣ጠጥተን ከተጫወትን በኋላ ልንሄድ ስንል የሀያት አባት ዱኣ ማድረግ ጀመሩ። ሁላችንም አሚን እንላለን። ከዱአቸዉ በጣም ልቤን የነካዉ ለሀያት ታናሽ እህት መግፊራ ያደረጉት ፀሎት ነበር። "እንደ አክረም ያለ እንከን አልባ ባል ስጣት።" ነበር ያሉት። ሀያትን አየኋት እሷም "አሚን" አለች። ስንት እንከን እንዳለብኝ እያወቀች አሚን ማለቷ ገረመኝ። ሀዩ ጉድለቴን እስከመች ትቆቋመዉ ይሆን? እየጎዳኋት እንደሆነ እየተሰማኝ ነዉ። ሀፍረቴ ጣራ እየነካ ሲመጣ ሀያትን እንድንፋታ ልጠይቃት ወሰንኩ። ከስራ እንደተመለስኩ ጭኖቿ ላይ ተኝቼ ፀጉሬን እየደባበሰችኝ "ሀዩ እኔ ከዚህ በላይ ባልጎዳሽ እና ባትሰቃዪ ደስ ይለኛል። ልፍታሽ?" አልኳት።
ሀዩ በአጭሩ ምላሹን ሰጠችኝ። ግንባሬን ሳመችና "ከብዙ ጥረት በኋላ ነዉ ያገኘሁህ። በግንኙነት ከሌላ ሰዉ ጋር በእርካታ ከመኖር ከአንተ ጋር ዘላለም እንዲህ መኖሩን እመርጣለሁ። እኔ እታገሳለሁ። አንተ ግን ደግመህ ይሄን ጥያቄ እንዳትጠይቀኝ!" አለችኝ።
.
ከሀዩ ጋር አብረን መኖር ከጀመርን አምስት ወራት ተቆጠሩ። ሀዩም አምስት ወር ሙሉ በጥፊ እየተመታች ክብሯን ባልጠበቀ መልኩ ስገናኛት ችላኝ አለች። ያለፉትን አምስት ወራት ለሊቱን ተነስቼ ጌታዬ መረጋጋትን እንዲሰጠኝ ሳልጠይቀዉ ቀርቼ አላዉቅም። ሀዩን ከተገናኘሁ በኋላ ወደ በረንዳ ሄጄ መንሰቅሰቁ የዘወትር ተግባሬ ሆኗል። ገንፎዉ ተሰጥቶህ ማንኪያዉን ስትቀማ በጣም ያሳዝናል!
.
ከሀያት ጋር ስተኛ የሚፈጠረዉን ነገር በተመለከተ ለማንም አልተናገርኩም ነበር። የመጨረሻ አማራጬ ግን ለሰዒድ ማማከር ነበር። እሱ መፍትሄ አያጣም።
ሰዒድን ለማማከር በወሰንኩ በነጋታዉ ሰዒድ ወደ ቢሮዬ የማማክርህ ጉዳይ አለኝ ብሎኝ መጣ።
እንደተቀመጠ "ሰዉየዉ እንደዳርኩህ ልትድረኝ ነዉ!" አለኝ።
"ሰዒድዬ በአላህ እኛ የቀመስነዉን ደስታ ልትቀምሰዉ ነዉ?" አልኩ የተደሰትኩ ለመምሰል እየሞከርኩ። እኔ በሀዩ ደስተኛ ብሆንም ሀዩን ግን እያስደሰትኩ አይደለም።
"ሊያዉም ልዛመድህ ነዋ!" አለኝ ፈገግ ብሎ እያፈጠጠብኝ
"ማንን? መግፊራን? አላምንም!" አልኩት። መግፊራ የሀያት እህት ናት።
"አይደለም ባንተ በኩል። አክስቶችህ ሰፈር!" አለኝ።
ሁለታችን
4.3K views@m måkï , 16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-18 19:23:42 በዘለለ እየጮኹ ማልቀስን ስለሚከለክል ሰዎቹ ዝም እንዲሉ ለመጠየቅ ሞከርኩ ግን ሊሰሙኝ አልቻሉም። ኋላ ላይ አንድ ሽማግሌ ተቆጥተዉ ወንዶቹን ስርዓት አስያዙልን። ድንኳን ዉስጥ እንደተቀመጥኩ አንድ ጎረቤታችን ጠርታ ወደ ሴቶች ድንኳን ይዛኝ ሄደች።
በእስልምና እምነት መሰረት በሰርግም ሆነ በለቅሶ ወንዶች ከሴቶች ጋር እንዲቀላቀሉ አይፈቀድም። የሴቶች ድንኳን ጋር ስደርስ ሴትየዋ "ኧረ እናትህን ተይ በላት ፊቷን ቧጣ ጨረሰችዉ። አላህም አይወደዉ!" አሉኝ። ወደ ሴቶች ድንኳን ስመለከት እናቴ ደረቷን እየደበደበች ፊቷን እየቧጠጠች ታለቅሳለች። ከአባዬ ሬሳ አርቀዉ ድንኳን ዉስጥ ያስገቧት በጣም አስቸግራ መሆኑ ገባኝ። አባቴ በህይወቱ በነበረበት ጊዜ ስታቆስለዉ ኖራ ዛሬ ታስመስላለች። እናቴ ሆና ክብሯ ባይዘኝ ባጋጫት ሁላ ደስ ይለኝ ነበር። ወይ የሀይማኖት እዉቀት የላት! ወይ ስነ ምግባር የላት፣ መልክ ብቻ!
እናቴ መምጣቴን ስታይ ትንሽ ተረጋጋች። እንዲሁ ለኔ ክብር አላት። እህቶቼን ከቤት ጠርቼ ስርዓት እንዲያስይዟት ነገርኳቸዉ።
.
አባዬ ወዲያዉ ሰባት ሰዓት ላይ ተሰግዶበት ተቀበረ። በእስልምና እምነት በሬሳ ላይ የሚሰገድ የስግደት አይነት አለ። ሬሳን ቶሎ መቅበርም ይወደዳል።
በነጋታዉ ሰው ሀዘኑ እየበረደለት ድንኳኑ ዉስጥ መጫወት ጀመረ። ግማሹ አስፈርሾ ይቅማል። ግማሹ ክብ ሰርቶ ይጫወታል። ጮክ ብሎ ሚስቅ ሁሉ ነበር። አሪፍ የቤተሰብ መሰብሰቢያ መድረክ ሆኗል። ለቅሶ መሆኑን ረሱት መሰለኝ።
ማታዉን ቤተሰብ ተሰብስቦ የአባዬን ስራ ማን ያስተዳድር በሚለዉ ላይ መከረ። መጨረሻ ላይ እኔ ላይ እምነታቸዉን ጥለዉ ትምህርቴን አቋርጬ የአባቴን ስራ እንድሰራ ወሰኑ።
.
ለቅሶዉ ቀዝቅዞ ፣ ድንኳኑ ፈራርሶ ፣ሰው እንደተበተነ ፤ ሀዩንም ወደ ባህርዳር ሸኘኋት። ቢያንስ እስኪ ሰቃያችን ትመረቅ። እኔና ሪቾ እንደሆነ ከትምህርት መስመር ወጥተናል። ትንሽ ቆይቼ እኔም ወደ ባህርዳር ሄጄ ልብሶቼን ይዤና ዊዝድሮዉ ሞልቼ ተመለስኩ። የህይወት መስመር መቼ እንደሚቀየር አይታወቅም። ትናንት ተማሪ የነበርኩት ልጅ ይኸዉ ሰራተኛ ልሆን ነዉ።
.
ስራ በጀመርኩበት የመጀመሪያዉ ቀን ማታ የሪቾን መቃብር ሄጄ ጎበኘሁ። ወደ ባህርዳር ስበር የፃፍኩትን ግጥም አነበብኩላት። ሪቾ እንዳለችዉ የእዉነትም ተዉባ እየጠበቀችኝ ይመስለኛል። እንዲህ ሱፍ ለብሼ የአባቴን መኪና ይዤ ሪቾ ብታየኝ ምን ትል ነበር? እኔንጃ ብቻ ለየት ያለ ቃል አታጣም። የሆነ ነገር ትለኝ ነበር።
.
የአባዬን ስራ እያስተዳደርኩ ቀናትም እየሮጡ ወራትም እየተገነጠሉ ሰባት ወራት አለፉና የሀዩ እና ሀጅራ ምርቃት ደረሰ። የፈጣሪ ዉሳኔ ነጠለን እንጂ እኔናሪቾም አብረን እንመረቅ ነበር።
በነገራችን ላይ የአባዬን ስራ በጣም ትርፋማ አድርጌዋለሁ። በቅርቡ እንደዉም ባለን ተቀማጭ ገንዘብ ሌላ ተጨማሪ ስራ ለማስጀመር እያሰብኩ ነዉ።
.
ቅዳሜዉን ዉዷ ሚስቴን ላስመርቅ ወደ ባህርዳር ሄድኩ።
ሀዩዬ የግቢዉን ትልቁን ዉጤት ነበር ያስመዘገበችዉ። አራት ነጥብ! በጣም አኮራችኝ። ሀዩ ግን ከመመረቋ በላይ ጓግታለት የነበረዉ አብረን የምንኖርበት ቀን መድረሱን ነዉ። በሰርግ ከቤቷ በወጉ የምትወሰድበትን ቀን! የምንጠቃለልበትን እለት!
ሀዩን ሜዳሊያ አጥልቃና ዋንጫ ይዛ ሳያት በጣም ደስ አለኝ። ሪቾ ከኛ ጋር ባለመሆኗ ግን አዘንኩ።
ሀዩ ፍልቅልቅ እንዳለች ዙሪያዋን የቆሙትን ቤተሰቦቿን እና እኔን እያየች "የሀያትን ምርቃት ከሌሎች ምርቃቶች ለየት የሚያደርገዉ በሰርጓ ዋዜማ መካሄዱ ነዉ።" አለች።
.
ይቀጥላል...

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
4.3K views@m måkï , 16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-18 19:23:42 መንታ መንገድ
ክፍል አስራሁለት
(ፉአድ ሙና)
.
.
ራሄል የፃፈችልኝን ደብዳቤ ካነበብኩ በኋላ ከለቅሶ ቤት አልጠፋሁም። ሀጅራ አዲስአበባ ደርሳ የራሄልን ሬሳ ስታይ ራሷን መቆጣጠር ከበዳት። ለረዥም ሰዓት አነባች። ትናንት ከጎኗ ትማር የነበረች ልጅ ሳይታሰብ መሞቷ ልቧን ሰበረዉ። ሀጁ ወደ ኮምቦልቻ እስክትመለስ ድረስ ያለዉን ጊዜ እነሀያት ቤት አሳለፈች።
ራሄል ዉጪ የነበሩት ዘመዶቿ እንደተሰበሰቡ በሞተች በሶስተኛዉ ቀን ተቀበረች። ዉስጤ በሀዘን ተሞልቷል። ገዳይዋ እንደሆንኩ እየተሰማኝ ነዉ። ራሄል ግን እወዳት እንደነበር እንዴት አወቀች? አዎ ገባኝ ከሀያት በተለየ ጊዜዬን ከሷ ጋር ነበር የማሳልፈዉ። አይኖቼ፣ ሁሉ ነገሬ ከአንደበቴ ዉጪ እንደምወዳት ይናገር ነበር። ከፓፒረሱ ክስተት በኋላ ግን የወደፊት ህይወትን ከግምት ዉስጥ ባስገባ መልኩ ከራሄል እና ከሀያት ምርጫዬ መሆን ያለባት ሀያት መሆኗን ወሰንኩ። ትኩረቴንም በከፊል ከራሄል ወደ ሀያት አዞርኩ። ሀያት ምንም አይጎድላትም። ግን ራሄል ልቤ ዉስጥ ነበረች።
.
በህይወት እስካለሁ ድረስ እንግዲህ ቢያንስ በአመት አንድ ጊዜ ራሄል መቃብሯን እንድጎበኝ አደራ ብላኛለች።
ግን ሰዉ መንገድ ላይ ሲያየዉ ይሳሳለት የነበረዉ ዉበቷ አፈር ገባ በቃ? ሰዉ ግን ከንቱ ነዉ። ምንም ዛሬ ቢፈካ ላለመንጠፉ ዋስትና የለዉም።
.
ሀያት ሀዘኑ እንደከበደኝ ስለገባት በቻለችዉ አቅም ብቻዬን አትተወኝም። በርግጥ ሰሞኑን አባዬ ትንሽ ስላመመዉ ስራ እሱን ተክቼ መግባቴም ለጊዜዉም ቢሆን ሀዘኔን እንድረሳዉ አድርጎኛል። ስራዉ ከአባዬ ድርጅት ጋር መስራት የሚፈልጉ አዲስ ደንበኞች ሲመጡ ተቀብሎ ማነጋገር፣ ወደብ ላይ ያሉ እቃዎችን በተመለከተ ከድርጅቱ ሀላፊዎች ጋር በመመካከር ቶሎ እንዲገቡ ማድረግ ፣ ከሻጮች ጋር መደራደር ምናምን ነዉ። ብዙ ዉሳኔዎችን በራሴ መወሰን ስለምፈራ አባዬ ጋር ደዉዬ እሱ እየነገረኝ እኔ እፈፅማለሁ። ስራዉን ከዚህ በፊት አሳይቶኝ ስለነበር ብዙም አልከበደኝም። የአባዬ ፀሀፊም ልምድ ስላላት በደንብ ታግዘኛለች። ሀዩ ከስራ ስመለስ አብራኝ አምሽታ ወደ ቤት ትሄዳለች።
ከራሄል አባት ጋርም በቅርብ እየተገናኘን እናወራለን። እስክንድርንም በተደጋጋሚ አገኘዋለሁ። በራሄል ዙሪያ የነበሩ ሰዎችን ሳወራ እሷን ያወራኋት ያህል ደስ ይለኛል። እንዳለችዉም ሳጣት ከፍቅሯ እሳት ጋር መጋፈጥ ጀምሬያለሁ። ትናፍቀኛለች። አንዳንዴ ሀያት ራሄልን እንደነጠቀችኝ እየተሰማኝ ታስጠላኛለች። እንደዉም ሀዩ ላይ በጣም ቀዝቅዤባት ነበር። ግን የሰዒዶ ምክር አባነነኝ። "እሷም ራሷን አጥፍታልህ እንዳታርፈዉ!" ነበር ያለኝ።
ቆይ አሁን ስለ ግጥም ከማን ጋር ነዉ የምወያየዉ? ራሄልን በጣም እወዳት ነበር። ካጠገቤ ስትርቅ ሁሉም ነገር ግልፅ ሆኖልኛል።
.
ቀናት ቀልድ አያዉቁም ፣ ወራትም ቀናት ሲጠራቀሙላቸዉ እብስ ከማለት ወደኋላ አይሉም። ራሄል ከሞተች ሁለት ወራት አለፉ። ክረምቱ አልቆ አዲስ አመት ተበሰረ። ራሄል የሌለችበት ባዶ አመት አዲስ አመት ተባለ።
ባህርዳር ዩኒቨርሲቲም በየቤታቸዉ የተበተኑ ተማሪዎችን ጠራ። ከሀዩእና እስክንድር ጋር ሆነን ወደባህር ዳር ሄድን። የመጨረሻ አመታችን ስለሆነ በዚህ አመት እንመረቃለን። በአዉሮፕላን እየሄድን ሪቾ ትዝ ስትለኝ አጭር ግጥም ፃፍኩ። ወደ መቃብሯ ስሄድ አነብላታለሁ።
"አንቺ የሌለሽበት ሁሉ ነገር ባዶ፣
ሰፈሩ ጭር አለ ፣በፅልመት ተጋርዶ።
ድምቀት ማለት አንቺ ፣ ስትጠፊ ገባኝ፣
ምንድነዉ ሳቃቸዉ ፣ ሰላም የሚነሳኝ?"
.
ሀያት በዉጤቷ አሁንም የክፍላችን ሰቃይ ናት። ሪቾ ሞተች እንጂ ሁለተኛዉ ትልቁ ዉጤት የሷ ነበር። ድሮ እኩል ነበርን። አሁን ግን በአንድ ትምህርት በልጣኛለች። ግን ሞታለች። ትምህርት እንደተጀመረ እስክንድርን በጣም ቀረብኩት። ራሄል ከናፈቀችኝ የማገኘዉ ብቸኛዉ ሰዉ እስክንድር ነዉ። በርግጥ ጊዜዉ ሲገፋ የራሄል ሀዘንም ቀለል ብሎልኛል። ሀያት ወደ ጣና እንደለመድነዉ ባጃጅ ተኮናትረን ከሄድን ገና ፓፒረስ ጋር ከመድረሳችን በፊት በወሬ ትጠምደኛለች። ወሬዉ ትኩረቴን ወደሷ ካልወሰደዉ ከንፈሬ ላይ ትለጠፋለች። ፓፒረስን ካየሁ ራሄል ትዝ ትለኛለች። ከራሄል ጋር ያሳለፍነዉን የፓፒረስን ምሽት ሳስታዉስ ደግሞ ፈገግታ ይርቀኛል። የሀዩም ትኩረቴን ለመስረቅ መሞከር ሪቾ ትዝ እንዳትለኝ ለማድረግ የታለመ ነዉ። ቀናችንን ሰላማዊ ለማድረግ!
.
ትምህርት ተጀምሮ ከወር በላይ እንደተማርን አባዬ በተደጋጋሚ መታመም ጀመረ። እኔናሀዩ አንዴ ወደ አዲስአበባ መጥተን ጠይቀነዉ ተመልሰናል። እኛ ስንጠይቀዉ ትንሽ ሰላም ነበር። ከተመለስን በኋላ ግን ባሰበት።
ጠይቀነዉ በተመለስን በአስራአምስት ቀኑ የአባዬ ጤንነት ጥሩ የሚባል ደረጃ ላይ መድረሱን ኢስራዕ ነገረችኝ። በየቀኑ እንደዋወላለን። በሰዓቱ እኔናሀዩ የመመረቂያ ፅሁፋችንን ምዕራፍ አንድ ለማጠናቀቅ እየተጣደፍን የነበረ መሆኑ አባዬን ደግሜ እንዳልጠይቀዉ አደረገኝ።
.
አንዳንዴ ማታ ከሀዩ ፣ ሀጁ እና እስክንድር ጋር ከተለያየን በኋላ የግቢያችን ላቭ ስትሪት ላይ ብቻዬን ዎክ አደርጋለሁ። እዚሁ መንገድ ላይ ሪቾ የፍቅር ግጥም መፃፍ ጀመርኩ ብላ ስታነብልኝ የነበረዉ ድባብ ትዉስ ይለኛል። እጆቿን ወደ ላይ ሰቅላ እየተሽከረከረች ስትጨፍር አይኔ ላይ ድቅን ትላለች። ብቻዬን ስሆን ሀዘኑን መቋቋም ይከብደኛል። ሪቾ በጣም ትናፍቀኛለች። ፓፒረስ ዉስጥ ራቁታችንን ሆነን ከንፈሬን ስትስመኝ የማልቆጣጠረዉ ስሜት በጥፊ እንድመታት እንዳደረገኝ አስታዉስና ይገርመኛል! እስከአሁን መልስ ያጣሁለት ጥያቄ! አካሌን ማን አዘዘዉ? ልቤ እኮ ሙሉ ለሙሉ ሊተኛት ፈልጎ ነበር።
.
ሀሙስ ጠዋት ላይ ኢስራዕ ደወለችልኝ። "ወዬ የኔ ሚጢጢ!" አልኳት።
"አቢ እኮ ወደ አኼራ ሄደ!" አለችኝ እያለቀሰች። አኼራ ማለት ቀጣዩ አለም ማለት ነዉ። አባቴ ሞተ? እንባዬ ፈሰሰ! ሲያመጣዉ እንግዲህ አንዴ ነዉ። አባቴን በጣም ነበር የምወደዉ። ከተረጋጋሁ በኋላ ለሀዩ ደዉዬ ነገርኳት። ሀዩ በጣም አዘነች። ሀዘኑ በጣም እንዳይጎዳኝ ፈርታለች። እኔ ግን በልኩ ነዉ ያዘንኩት። አባቴ በመሞቱ ጌታዬን አላማርርም። እድሜዉ ሄዷል። ከሀዩ ጋር አራት ሰዓት ላይ ቢዝነስ ፍላይት አግኝተን ወደ አዲስአበባ መጣን። ሰዒድ ከአየርማረፊያ ተቀብሎን የኛ ቤት ቅያስ ጋር ካደረሰን በኋላ እናቱን ለማምጣት እኛን ወደ ሰፈር የሚያስገባዉ ቅያስ ጋር አዉርዶን ሄደ። ወደ ቤት እየቀረብን ስንመጣ አንድ ሰዉዬ ፈገግ ብሎ እዚህ ሰፈር ከሆንን ለቅሶ ቤቱን እንድናሳየዉ ጠየቀን። እሺ ብለነዉ አብረን መሄድ እንደጀመርን ሰዉየዉ እየቀለደ ሊያስቀን ሞከረ። ያወቀኝ አልመሰለኝም። ለቅሶ ለመድረስ የመጣዉ ግን እኛዉ ጋር ነበር። ልክ ቤት ጋር ስንደርስ በራችን ላይ የተደኮኑትን ድንኳኖች እያሳየሁ "እዛ ቤት ነዉ!" አልኩት። ወዲያዉ ማጓራት እና እየጮኸ ማልቀስ ጀመረ። እየጮኸ እኛን ትቶን ወደ ድንኳኑ እየፈጠነ ሄደ። እዉነት ለመናገር ሳቄን ልለቀዉ ምንም አልቀረኝም። ሰዉ እንዴት ድንኳን ሲያይ ይቀየራል? ማስመሰል ምን ያደርጋል? ሀዘኑን ለመግለፅ እንደከብት ማጓራት አይጠበቅበትም እኮ! አስመሳይ!
.
ቤት እንደገባሁ ኢስራዕናመርየም አቅፈዉኝ መንሰቅሰቅ ጀመሩ። ሳያቸዉ አንጀቴን በሉት ከአይኔ እንባዬ ፈሰሰ። ወዲያዉ እነሱን አረጋግቼ የአባቴ ሬሳ ወዳለበት ክፍል ገባሁ። አባዬ ተከፍኖ በጣም ደስ የሚል ሽቶ ተቀብቷል። ያን የመሰለ መኪና እንደማይዝናሱፍ እንዳልቀያየረ ዛሬ በአቡጀዴ ተጠቀለለ። ግንባሩን ስሜዉ ወዲያዉ ወደ ድንኳን ሄድኩ። ሰው እየጮኸ ያለቅሳል። ሀይማኖታችን ከማንባት
4.1K views@m måkï , 16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ