Get Mystery Box with random crypto!

✎የፍቅር ጥቅሶች||™

የቴሌግራም ቻናል አርማ bast_love_quotes — ✎የፍቅር ጥቅሶች||™
የቴሌግራም ቻናል አርማ bast_love_quotes — ✎የፍቅር ጥቅሶች||™
የሰርጥ አድራሻ: @bast_love_quotes
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.09K
የሰርጥ መግለጫ

ሰው ስሜቱን ይገልፅ ዘንድ ብዕር ተሠጠው!✍💔📚◆━━━━━━━✎✦✎━━━━━━━━◆
Contact us:⤵️📞
📩 || @Bast_Love_Quotes_Robot

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-11-09 23:17:25
ከኑረታችን ላይ እየተቀነሰ እንደዛፍ ቅርፊት ከበላያችን እድሜ እየተነሳ ግንዳችንን እያጠነከረ ቡረቃው ፣ ልፊያው ፣ ፀቡ ፣ ድብድቡ ፣ መበሻሸቁ ፣ የጨዋታ ታለንቱ ፣ ደንብና ስርአቱ ፣ እንደ አንድ የህይወት ክፍል የሸመደድናቸው የጨዋታ ህጎች ፣ መዝሙሮቻችን ፣ ችሎታዎቻችን ......እያንዳንዱን አንድ በአንድ እየዘለልን ጉርምስናን ያጠናቀቅን ጊዜ ትልቅነትን ሀ ብለን ስንጀምር ህጎቻችንን በሌላ ህጎች ስንቀይር ድንገት መለስ ያደርጉናል..... ወርቃማ ጊዜያቶቻችን ትውስ.... ፍዝዝ ባለ ትውስታ ወደዃላ ግልቢያ እንጀምራለን... ኑረታችንን ቃኘት አድርገን አጣጥመን ደግሞ ምልስ ከእውነታው ጋር ግጥምጥም........

ልጅነቴ ትላንት ያለፈ ያክል ቅርርብብ ይልብኛል ይዘው አይመልሱት ነገር የህይወት መፈገጊያው ገፃችን....

እንደምን አለህ ልጅነት?!!

ማኪ

30-2-2015

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
290 views@m måkï , edited  20:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 12:33:48 ✎የፍቅር ጥቅሶች|| pinned a photo
09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 12:33:32
እንዲቀልሽ 15

ለአልቃሻ አይኖችሽ ምክንያት እየሰጠሽ አታባብያቸው... መዳፎችሽን ለማያልቅ እንባሽ አታድክሚ...ውስጥሽ ያለውን ስብራት በእንባ ለመጠገን አትቸኩይ!! እንባሽ ላይ አትበርቺበት..... ድካምሽን አታጀግኚው... ለሀዘንሽ ፊት አትስጭው... አንዳንዴም በዝምታ እንባ ከሚያድነው በላይ ይዳናል !
ሞክሪው አለሜ።

ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
1.5K views@m måkï , 09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 20:50:34 ✎የፍቅር ጥቅሶች|| pinned a photo
17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 20:50:26
እንዲቀልህ 14

ለሚሉት አትሸበር ከቁም ነገሩ ተጠጋ ዝምታ አይስበርህ <ወንድ ልጅ ጀግና ነው> ብለው አያድክሙህ <በሆዱ ነው> ብለው አያስንፉህ ሳይገባህ መዳኛህን እንዲያርቁ አትፍቀድላቸው!! ወንድ ልጅም ሰው ነው ያለቅሳል እኮ! አልቅስ... ህመምህን አውራ.... ችግርህን ተናገር... አንተ ዘንድ ያጣኸውን መፍትሄ ሌሎች ዘንድም ፈልግ... ዝምታም ሲበዛ ገዳይ ነው... እንባህ ላይ ጠንክርልኝ።

ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
832 views@m måkï , 17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 21:04:23
እንዲቀልሽ 13

መውደድ ስለጋረደው ልብሽ እናውጋ እስኪ??!!!
የትኛው የትእግስት ጥበብሽ ነው እንዳሻቸው እየሆኑብሽ ካለነሱ ያስባለሽ ፣ የትኛው ጥንካሬሽ ነው ለሺ በደሎቻቸው ይቅርታን በነፃ የሚያሳድልሽ ፣ የቱስ የተለየ ቃል ይዞሽ ነው አንዱን ቃላቸውን ሚሊዮን ጊዜ እያጠፉ ለአንዱ ቃልሽ ፀንቶ ያስኖረሽ?? ምንስ ይሆን እንዲ በተስፋ የሞላሽ? ፣
ብቻ ምንም ይሁን ያለፍሽባቸውን መንገዶች አቅልዬ በቃሽ አልልሽም ግን ዛሬሽን ልብ በይ ያለሽን አስተውይ ምናልባት ያጣሽው ከሚመስልሽ በላይ ያለሽ ይበልጥ ይሆናል። እንደዛ ይሰማኛል።

ማኪ

✎የፍቅር ጥቅሶች||
@Bast_Love_Quotes_Robot
1.8K views@m måkï , 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 19:36:48 ውዶቼ ተመልሻለው በልብ ከልቤ ለተዋወሳችሁኝ ሁሉ አመሰግናለው ... ከዛሬ ጀምሮ በአብሮነት የምንቀጥል ይሆናል #እንዲቀልሽ 13ን ከደቂቃዎች ቡሀላ አስነብባችዃለው።

ማኪ
1.9K views@m måkï , 16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 21:35:06 ✎የፍቅር ጥቅሶች|| pinned « **እስኪ ደግሞ እንነፋፈቅ!! ላልተወሰነ ጊዜ በልብ ብቻ እንተዋወስ!! መመለሻዬ ቅርብ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለው #እንዲቀልህ/#እንዲቀልሽ አልተቋጨም ስንመለስ የምንቀጥለው ይሆናል። እስከዛው በፀሎት በዱአቹ አትርሱኝ። ማኪ ነኝ»
18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 21:35:01
**እስኪ ደግሞ እንነፋፈቅ!! ላልተወሰነ ጊዜ በልብ ብቻ እንተዋወስ!! መመለሻዬ ቅርብ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለው #እንዲቀልህ/#እንዲቀልሽ አልተቋጨም ስንመለስ የምንቀጥለው ይሆናል።

እስከዛው በፀሎት በዱአቹ አትርሱኝ።

ማኪ ነኝ
3.3K views@m måkï , edited  18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-23 10:54:09 ✎የፍቅር ጥቅሶች|| pinned «እንዲቀልህ 12 ላንተ በተመቸህና በቀለለህ መንገድ ብቻ ተጓዝ ስለሌሎች ምቾት አትጨነቅ ልብ በል ዛሬ የሰራኸው ማንነትህን ትላንት ሌሎችን ለማመቻቸት ብለህ በተጓዝከው መንገድ በተሰበረ ልብህ ምክንያት ነው። ያጠነከሩህን ክንዶች ብቻ አትርሳ መደገፍ ባለብህ ፈጣሪ ብቻ ተደገፍ እመነኝ መጣል ቀርቶ አያንገዳግድህም። አንዳንዴ ሁኔታዎች መሆን የማትፈልገውን ሰው ያደርጉሀል። ማኪ ✎የፍቅር ጥቅሶች|| …»
07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ