Get Mystery Box with random crypto!

Authority for Civil Society Organization (ACSO)

የቴሌግራም ቻናል አርማ authority_for_civil_society — Authority for Civil Society Organization (ACSO) A
የቴሌግራም ቻናል አርማ authority_for_civil_society — Authority for Civil Society Organization (ACSO)
የሰርጥ አድራሻ: @authority_for_civil_society
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.07K

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-18 19:35:12
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ አምሳደር ብሬናን ኒኮላን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ የአየርላንድ አምባሳደር የሆኑትን አምባሳደር ብሬናን ኒኮላን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ከአንባሳደር ብሬናን ጋር ባደረጉት ቆይታ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅተቶች ባለስልጣን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፍ እንዲጎለብት ያደረጋቸውን መጠነ ሰፊ ስራዎችን በሚመለከት ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡
የአየርላንድ መንግስት በሲቪል ማህበረሰብ ድጋፍ ፕሮግራም ሁለት በ(CSSPII) በኩል ዘርፉን በከፍተኛ ሁኔታ እየደገፈ እንደሚገኝና ይህም ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱም ሆነ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ትልቅ እገዛ እያደረገ እንደሚገኝ አንስተው ለዚህም የአየርላንድ መንግስት አስተዋጽዖ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራባቸውን የምዕራፍ ሁለት ተቋማዊ የለውጥ አጀንዳዎችን የገለጹ ሲሆን በተለይም ስኬታማ ስራዎችን ማጽናት፣ ማላቅና ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የታገዙ እንዲሆኑ ማድረግ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
396 views16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 21:26:15
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከግብር ነጻ አገልግሎት ስለሚያገኙበት ሁኔታ ውይይት ተደረገ፡፡
***********************************************************************
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ጋር በመተባበር የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ተወካዮችና የሲቪለ ማህበረሰብ ድርጅቶች ኃላፊዎች በተገኙበት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከታክስ ነጻ አገልግሎት ማግኘት ስለሚችሉበት ሁኔታ ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጀቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦን ጨምሮ በገንዘብ ሚንስቴር የፊሲካልና ፖሊሲ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙላይ ወልዱ ተገኝተዋል፡፡
575 views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 22:43:55
7ተኛው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና የክልል እና የፌደራል ባለድርሻ አካላት ጉባኤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ በተገኙበት በድምቀት ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የክልሉ ቢሮ ሃላፊዎች የሁሉም ክልል የፋይናንስ አና ፍትህ ቢሮ ሃላፊዎችና የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕረዝዳንት ተገኝተዋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ በንግግራቸው እንደገለጹት ይህ የጋራ ጉባኤ በክልላችን ለማድረግ ስለመጣችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው በማለት አገራዊ ለውጡን ተከትሎ የሪፎርም ስራዎች ከተሰራባቸው የህግ ማዕቀፍ ውስጥ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፍ አንዱ ነው ሲሉ አንስተዋል፡፡
አያይዘውም ለውጡን ተከትሎ በአገራችን የሚገኙ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እያደረጉት ያለው እንቅቃሴ የተሻለ መሆኑን ገልፀው የክልል መንግስታትና የፌደራል መንግስት ለሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት በክልሉ የሚሰሩ ድርጅቶች በአግባቡ በመያዝ እንዲሁም አዳዲስ ድርጅቶችንም ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ አክለው ገልፀዋል፡፡
304 views19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 20:29:33
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በሙሉ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡
ጉዲና ቱምሳ ፋውንዴሽን የ30ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን ምክንያ በማድረግ በፍሬንድ ሺፕ ፓርክ ባዘጋጀው ሲንፖዚየም ላይ ሁሉም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡
451 views17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 20:40:42
ማስታወቂያ ፡-
በግብርና ላይ ለሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሙሉ
ጉዳዩ፡- የኢትዮ-አግሮ የበጋ መስኖ ስንዴና የቅመማ ቅመም ኤግዚቪሽን የመክፈቻ ስነ- ስርዓት ላይ እንዲገኙ ስለመጋበዝ
421 views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 21:41:47
383 views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 21:27:44
የኢፌዴሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን "ዓደዋ አንድነት፣ ጀግንነትና ጽናት" በሚል መሪ ቃል ለ127ኛ ጊዜ የሚከበረው የዓደዋ ድል በዓል አደረሳችሁ በማለት መልዕክት ያስተላልፋል፡፡
318 views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 21:26:53
የአባቶቻችንን አደራ በመወጣት አንድነቷንና የዜጎቿን ክብር የተጠበቀ ጠንካራ አገር ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ገለጹ፡፡
ለ127ኛ ጊዜ የሚከበረው የአደዋ ድል በዓል "ዓደዋ አንድነት፣ ጀግንነትና ጽናት" በሚል መሪ ቃል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከጥንታዊ አርበኞች ማህበር እና ከኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማቾች ማህበር እንዲሁም ከተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር አከበረ፡፡
በበዓሉ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣን መስርያ ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንደተናገሩት ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪክ ሂደት ውስጥ በተለያዩ ዘመናት በርካታ የህልውና ተግዳሮቶች ተደቅነውባት በኢትዮጵያዊያን በተከፈለ መስዋትነት በድል አድራጊነት ተግዳሮቶችን በሙሉ በመሻገር የፀናች ታላቅ አገር መሆኗን ገልፀዋል፡፡
331 views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 11:54:00
Call for Applications.
For further information: https://acso.gov.et/call-for-papers
586 views08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 10:05:20
በኦሮሚያ ክልል ድርቅ በተከሰተባቸው አከባቢዎች ድጋፍ ለማድረግ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡
*********************************************************
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከኦሮሚያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ጋር በመተባበር በድርቅ ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች የሰብዓዊ ድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ያካሄደ ሲሆን በመርሃግብሩ በኦሮሚያ ክልል ፕሮጀክቶችን የሚያንቀሳቅሱ በርካታ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በንግግራቸው በሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች የበርካታ ዜጎች ሕይወት እየቀጠፈ ያለ ድርቅ መኖሩን አንስተው ለዚህ የዜጎችን ነፍስ አድን ስራ መልስ መስጠት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡
የመድረኩ ዓላማም ለዚህ የነፍስ አድን ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም ለዚህ የነፍስ አድን ስራ ምላሽ እንድትሰጡ አደራ እላለሁ ብለዋል፡፡
308 views07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ