Get Mystery Box with random crypto!

በኦሮሚያ ክልል ድርቅ በተከሰተባቸው አከባቢዎች ድጋፍ ለማድረግ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተካሄ | Authority for Civil Society Organization (ACSO)

በኦሮሚያ ክልል ድርቅ በተከሰተባቸው አከባቢዎች ድጋፍ ለማድረግ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡
*********************************************************
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከኦሮሚያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ጋር በመተባበር በድርቅ ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች የሰብዓዊ ድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ያካሄደ ሲሆን በመርሃግብሩ በኦሮሚያ ክልል ፕሮጀክቶችን የሚያንቀሳቅሱ በርካታ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በንግግራቸው በሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች የበርካታ ዜጎች ሕይወት እየቀጠፈ ያለ ድርቅ መኖሩን አንስተው ለዚህ የዜጎችን ነፍስ አድን ስራ መልስ መስጠት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡
የመድረኩ ዓላማም ለዚህ የነፍስ አድን ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም ለዚህ የነፍስ አድን ስራ ምላሽ እንድትሰጡ አደራ እላለሁ ብለዋል፡፡