Get Mystery Box with random crypto!

Authority for Civil Society Organization (ACSO)

የቴሌግራም ቻናል አርማ authority_for_civil_society — Authority for Civil Society Organization (ACSO) A
የቴሌግራም ቻናል አርማ authority_for_civil_society — Authority for Civil Society Organization (ACSO)
የሰርጥ አድራሻ: @authority_for_civil_society
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.07K

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-02-10 10:05:16
በፌደራል ደረጃ የተዘጋጀው የመንግስትና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የጋራ ጉባዔ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
***********************************************************************
የሲቪል ማኅበረሰብ ድጅቶች ባለስልጣን ከሲቪል ማ ኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት እና ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ፎረም ጋር በመተባበር በፌደራል ደረጃ የመንግስትና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የጋራ ጉባዔ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በጋራ ጉባዔው ላይ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎችና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች ተሳተፊ ሆነዋል፡፡
የፍትህ ሚንስቴር ሚኒስትር ደኤታ አቶ ፍቃዱ ጸጋ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በሀገራችን ያለው ሀብት ውስን በመሆኑ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በዚህ ረገድ የማይተካ ሚና እንዳላቸው በመገንዘብ አገልግሎታቸው የተሳለጠ እንዲሆን በክልል ደረጃ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የጋራ መድረክ ተመስርቶ ላለፉት ዓመታት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ከማጎልበት አንጻር ሲያሳልጥ መቆየቱ አንስተዋል፡፡
አክለውም መድረኩ ይህንን ትብብር ወደላቀ ደረጃ የሚያደርስ፣ በውስን የሰው ሃይል እና የፋይናንስ አቅም ያለውን አስተባብሮ የሚያሰራ ፣ያለውን ውስን ሀብት በተናጠል ከመስራት ይልቅ ለጋራ ዓላማ በተገናዘበ መንገድ በትብብር ለመስራት ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸው በተለይም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ውስጥ የዜጎችን ጥቅም ለማረጋገጥ ከፌደራል መንግስት ተቋማት ጋር በመተባበር በመስራት የማይተካ ሚናችሁን እንደምትወጡ እና ከዚህ መድረክ ምስረታ በኋላ ወቅታዊ ግንኙነቶችን በማድረግ የዜጎችን ተጠቃሚነት ወደላቀ ደረጃ እንደምታደርሱ እምነቴ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
310 views07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 20:58:50

354 views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 20:56:27

365 views17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-24 17:45:02 https://www.ena.et/?p=203112
422 views14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-24 13:31:11
ተቋሙ የ2015 በጀት ዓመት የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም እና የቀጣይ 6 ወራት የተከለሰ እቅድን ለባለድርሻ አካላት አቅርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በመድረኩ የፌደራል ባለድርሻ አካላት፣የተለያዩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተወካዬች እና የተቋሙ የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል፡፡
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዓለምአንተ አግደው እንደገለጹት መንግስት ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑ በማንሳት ለትርፍ ያልተቋቋሙና ለፖለቲካ ያልወገኑ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በአገራዊ የልማት እንቅስቃሴ እና በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አይነተኛ ሚና ያላቸው መሆኑ ስለሚታመን ላለፉት ዓመታት የህግ እና ተቋማዊ ሪፎርም ሲካሄድ ቆይቷል ብለዋል፡፡
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ የተሻለ አቅም እየገነቡ እና መልካም አስተዋፅኦ እያደረጉ መሆኑን በሚያደርጓቸው እንቅስቀሴዎች መገንዘብ ይቻላል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ሲማዶች በአገራዊ ወቅታዊ ጉዳይ በጦርነትና ድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎችና የህብረተሰብ ክፍሎች በገንዘብ በዐይነት እያደረጉ ያሉት ድጋፍ አንድ ለህዝብ ተጠቃሚነት ከቆመ ዘርፍ የሚጠበቅና ምስጋና የሚቸረው ጉዳይ ነው ሆኖም ሲማዶች በወቅታዊ ጉዳይም ሆነ ሀብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ እያደረጓቸው ያሉት አስተዋፅኦዎች መንግስት ከፈጠረው ምቹ ሁኔታ እና ከአገርና ህዝብ ፍላጎት አንጻር ሲታይ አሁንም ብዙ የሚቀረው እና መሻሻል የሚጠበቅበት ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
607 views10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-12 15:08:46
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፋላጎታቸውን ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ማሳወቅ እንደሚችሉ ተገለጸ፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት “የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ንቁ ተሳትፎ ለዘላቂ ሰላም፣ ሰብዓዊ መብቶች መከበርና መልካም አስተዳደር ግንባታ” በሚል መሪ ቃል ዘንድሮም ለ3ኛ ጊዜ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ይከበራል፡፡
ይህንኑ አስመልክቶ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣንና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ካውንስል በጋራ 3ኛውን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በጋዜጣዊ መግለጫው መንግስት ዘርፉን ለማጠናከር ከተሰሩ ስራዎች አንዱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንትን በማዘጋጀት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ስራዎቻቸውን እንዲያስተዋውቁ፣ የርስ በርስ ትስስርና መስተጋብርን ለማጠናከር እንዲችሉ እንዲሁም ልምድ ልውውጥ ለማድረግ ትልቅ እድል የፈጠረ እንደሆነ የሲቪል ማህበረሰብ ድርርቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ገልጸዋል፡፡
መንግስት በርካታ የህግና ተቋማዊ ሪፎርም ካደረገባቸው ዘርፎች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፍ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የግሉንና የመንግስት ሴክተሩን በማስተሳሰር ሚዛናዊ ለማድረግና ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ መሆን ይችላሉ የሚል እምነት በመኖሩ ዘርፉን ለማጠናከር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
459 views12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 12:00:07
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አደረጉ፡፡
***********************************************************************
አቶ ተስፋዬ በልጅጌ የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት የዛሬው መድረክ በሃገር አቀፍ ደረጃ ከሙሁራን ጋር የሚደረገው ውይይት አካል መሆኑን አንስተው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም በሃገረ መንግስት ግንባታው ላይ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አክለውም ድርጅቶች የዲሞክራሲ ባህል እንዲዳብር፣የሰላም እና የተቋማት ግንባታ ላይ ማገዝ አለባቸው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ዶ/ር ፍጹም አሰፋ የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር በሃገር ግንባታ የሙሁራን ሚና በሚል ርዕስ መነሻ ጽሑፍ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡
424 views09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 11:33:22 በሲቪል መማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተዘጋጁት አራት መመሪያዎች በፍትህ ሚኒስቴር እና በባለስል መስሪያ ቤቱ ድህረ ገጽ ከተለቀቁበት ጊዜ አንስቶ ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡
በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ወጥተው በፍትህ ሚንስቴር ቁጥር የተሰጣቸው መመሪያዎች ፡-
1. ስለ ድርጅቶች መዋሃድ፣ መከፋፈል፣ መለወጥና መፍረስ የወጣ መመሪያ ቁጥር 936/2015
2. የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በገቢ ማስገኛ ስራዎች ላይ የሚሰማሩበትን ሁኔታ ለመወሰኝ የወጣ መመሪያ ቁጥር 937/2015
3. የአገር በቀል ድርጅቶች ምዝገባና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 938/2015 እንዲሁም
4. የጥቅም ግጭትን ለማስቀረት የወጣ መመሪያ ቁጥር 939/2015 የሚሉት ናቸው፡፡
ሙሉ መመሪያዎቹን በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዌብሳይት፡- www.acso.gov.et
ሕጎች - ACSO
ወይም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚንስቴር ድህረ ገጽ
ህጎች (eag.gov.et)
ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
429 viewsedited  08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-27 11:08:34 https://www.ethiopianreporter.com/113716/
የሲቪል ማኅበራት ራሳቸው የሚፈጥሩትን የጥቅም ግጭት የሚፈታ ሥርዓት እንዲያበጁ የሚያስገድድ በመመርያ ወጣ
357 views08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-06 13:55:21
‹ሙስናን መታገል በተግባር›› በሚል መሪ ቃል በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለ19ኛ ግዜ በሃገራችን ደግሞ ለ18ኛ ግዜ እየተከበረ ያለውን የዓለም ዓቀፍ የጸረ ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ መልዕክት
337 views10:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ