Get Mystery Box with random crypto!

Authority for Civil Society Organization (ACSO)

የቴሌግራም ቻናል አርማ authority_for_civil_society — Authority for Civil Society Organization (ACSO) A
የቴሌግራም ቻናል አርማ authority_for_civil_society — Authority for Civil Society Organization (ACSO)
የሰርጥ አድራሻ: @authority_for_civil_society
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.07K

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-09-23 20:59:52 በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በተከሰተው ጦርነት ለተፈናቀሉ የማህበረሰብ ክፍሎች በሶስተኛ ዙር በተደረገ የሃብ ማሰባሰብ ስራ ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ቃል ተገብቷል፡፡
ዛሬ በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል ከተለያዩ የሲቪል ማህረሰብ ድርጅቶች ጋር በተደረገ ውይይት ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ቃል ተገብቷል፡፡ ቃል የተገባው ብር ከ 20 ፐርሰንት ተሳታዎች ሲሆን 80 ፐርሰንት ተሳታፊ ድርጅቶች ወደ ተቋማቸው ሄደው በመምከር እንደሚያሳውቁ ቃል ገብተዋል፡፡ ከዚህ አንጻር የገንዘቡ መጠን በቀጣይ ከፍ እንደሚል ይጠበቃል፡፡
በመድረኩ የተለያዩ የመንግስ ተቋማት ሃላፊዎች በርካታ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
298 views17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 13:01:10
ባስልጣን መስሪያ ቤቱ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰቆጣ ከተማ የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ፡፡
*********************************************************************
በሰቆጣ ከተማ የሚከበረውን የሻደይ በዓልን ምክንያት በማድረግ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማስተባበር የትምህርት ቁሳቁሶችን እና ምግብ ነክ የሆኑ ግብዓቶችን ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉን ለከተማው የምግብ ዋስትናና አደጋ መከላከል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ያስረከቡት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንደተናገሩት የሻደይ በዓልን በጋራ ለማክበር በምንመጣበት ጊዜ መጪው ዓመት ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱበት መሆኑን በመገንዘብ ከአምስት መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ የትምህርት ቁሳቁሶችን እና ምግብ ነክ ግብዓቶችን ከተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በማስተባበር ነው ብለዋል፡፡
በድጋፉ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ግንባታ ማዕከል ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ፖል ቱት ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
317 views10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 09:17:32
የኢፌዲሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ‘ዐሻራችን ለትውልዳችን’ በሚል መሪ ቃል አራተኛውን ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ የማስቀመጥ መርሐ ግብር በቡታጂራ አካሂዷል፡፡

በፕሮግራሙ የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣የደቡብ ክልል ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች፣የከተማዋ ከንቲባ እና ነዋሪዎች ፣የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ሃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ፕሮግራሙን የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜ እንዳሉት የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ከለውጡ በኃላ በመንግሥትና በግል ባለሃብቱ የማይሸፈኑ የልማት ሥራዎችን በመተካት ወሳኝ ሚና እየተወጡ እንደሚገኙ ገልጸው ከሀገራዊ ለውጡ በፊት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እንደጸረ ሰላምና ሰላይ የሚታዩበት ሁኔታ አሁን ተቀይሮ ከመንግሥትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብርና በጋራ ሀገር የማልማት ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ሀገር የምትበለፅገው አቅምና የተፈጥሮ ሃብትን አስተባብሮ ጥቅም ላይ ማዋል ሲቻል መሆኑን ጠቁመው መርሐ ግብሩ አየር ንብረትን ለመጠበቅ ዛፍ ከመትከል ባሻገር አብሮነትንና ወንድማማችነትን በማጠናከር ኢትዮጵያውያን እርስ በእርስ እንድንተዋወቅ እድል የፈጠረ ነው ሲሉ ሚኒስትሩ አክለው ተናግረዋል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በበኩላቸው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች 4ኛውን የአረንጓዴ አሻራ የማሳረፍ አገራዊ ጥሪ መሰረት በማድረግ በዛሬው እለት በቡታጅራ ከተማ ችግኝ ለመትከል መሰባሰባቸው ዘርፉ በአገር የልማት እንቅስቃሴ ላይ በንቃትና ትርጉም ባለው መልኩ እየተሳተፈ የመሆኑ ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
421 views06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 15:18:45
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የአገልግሎት አሰጣጥ 91.34% መድረሱን እና ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ4% ብልጫ ማሳየቱ ተገለጸ፡፡

ተቋሙ የ2014 በጀት ዓመት አፈጻጸሙን እና የ2015 በጀት ዓመት እቅድ በማኔጅመንት ደረጃ እንዲሁም ከአጠቃላይ ሰራተኛ ጋር እየገመገመ ይገኛል፡፡
127 viewsedited  12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 09:55:20
ማስታወቂያ ለሚመለከታችሁ የሲቪል ማህበረሰብ ርጅቶች በሙሉ
626 views06:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 17:13:19
844 views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 17:13:17
796 views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 17:13:16
764 views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 17:13:14 5ተኛው የኢፌዲሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና የክልልና የፌደራል ባለድርሻ አካላት የጋራ ጉባኤ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
*****************************************************************
በጉባኤው ላይ የተለያዩ ሚኒስትሮች ሚኒስትር ዴኤታ፣የፌደራልና የክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ እና ጠቅላይ አቃቤ ህጎች፣የጋሞ አባቶች እንዲሁም የተለያዩ የፌደራል የባለድርሻ ተቋማት ሃላፊዎች በጉባኤው ላይ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
የጉባኤውን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢፌዲሪ የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዬን ጢሞቲዬስ የመድረኩ መመስረት በጣም መሰረታዊ እና አስፈላጊ መሆኑን በማንሳት እንደሃገር የሞራል ሚዛን መዛባት አጋጥሞናል ይህንን ለማስተካከል አዲስ አስተሳሰብ የተላበሰ ማህበረሰብ ለመፍጠር፣እርቅ፣ማህበራዊ እሴት እንዲዳብር እና ሰላም እንዲሰፍን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፍ ውጤታማ መሆን እንደ ሃገር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው ይህንን ደግሞ ወደ ተግባር ለመለወጥ የዚህ ጉባኤ እና የቅንጅታዊ አሰራሮች በጣም አስፈላጊ ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በንግግራቸው እንደገለጹት ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንቅስቀሴ ጋር በተያያዘ ኃላፊነት ያላቸው የመንግስት አካላት በህግ የተሰጣቸው ስልጣንና ተግባር እንደተጠበቀ ሆኖ በዘርፋ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በህግ አግባብ በመንቀሳቀስ የህዝብን የላቀ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ስራ ማከናወን እንዲችሉ እንዲሁም በሀገር ዐቀፍ ደረጃ ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጎልበት እና ለሚያጋጥሙ ችግሮች የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ የሚያስችል ጉባኤ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ጉባዔው የተመሰረተበትን ዓላማ ከማሳካት አኳያ አበረታች ውጤቶች የታዩ ሲሆን ከሁሉ በላይ በአስፈጻሚ አካላት መካከል መቀራረብን የፈጠረ፣ወጥነት ያለው አሰራር ከመዘርጋት አኳያም ጠቃሚ ውጤቶች ተገኝተዋል ሲሉ አብራርተዋል፡፡
በተለይም ከአራተኛው ጉባኤ በኋላ የተጀመረው የባለሙያዎች /CSO/NGO Desk ኃላፊዎች/ እንዲሁም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የምክክርና የልምድ ልውውጥ መድረክ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አስተዳደር ጋር በተያያዘ መልካም ተሞክሮዎችን መለዋወጥ የተቻለበት መድረክ እንደነበርም አስታውሰዋል ፡፡
730 views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 11:44:34
ለ2ተኛ ጊዜ የተዘጋጀው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንትን (CSOs Week) ዛሬ ተጠናቋል፡፡
******************************************************************
ባዛርና ኤግዚቪሽኑ ከጉብኝት እና ከመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ጎን ለጎን በአራት ርዕሰ ጉዳዬች ላይ የፓናል ውይይት ተደርጓል ፡፡ ውይይቱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሰላም ግንባታ ላይ ያላቸው ሚና፣ከአዲሱ አዋጅ በኋላ የመጡ ለውጦች እንዲሁም ስርዓተ ጾታ እና ተያያዥ ጉዳዬች ተዳሰዋል፡፡
በመዝግያ መርሃ ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዓለምአንተ አግደው የተገኙ ሲሆን በንግግራቸውም ይህ ባዛርና ኤግዚቪሽን በመዘጋጀቱ ለዘርፉ እድገት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን እና ባዩት ስራ መደሰታቸውን ገልጸው ሚኒስትር መስሪያቤታቸው ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሚፈልጉት ድጋፍ ሁሉ ከጎናቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በበኩላቸው የተሳካ ባዛርና ኤግዚቪሽን በመዘጋጀት ሂደት አስተዋጽኦ ላደረጉ ድርጅቶች ፣ተሳታፊዎችና አዘጋጅ ኮሚቴዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
925 views08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ