Get Mystery Box with random crypto!

Authority for Civil Society Organization (ACSO)

የቴሌግራም ቻናል አርማ authority_for_civil_society — Authority for Civil Society Organization (ACSO) A
የቴሌግራም ቻናል አርማ authority_for_civil_society — Authority for Civil Society Organization (ACSO)
የሰርጥ አድራሻ: @authority_for_civil_society
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.07K

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-12-05 11:29:57
እንኳን ለዓለም አቀፍ የበጎ ፍቃደኞች ቀን አደረሳችሁ፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ በዛሬው ዕለት "solidarity through volunteering." በሚል መሪ ቃል የበጎ ፍቃደኞች ቀን እየተከበረ ይገኛል፡፡
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ፅንሰ ሃሳብ ትርጓሜው እንደ ማህበረሰቡ የዕድገት ደረጃና ከባቢያዊ ሁኔታ የሚለያይ ሲሆን በዋነኛነት ሰዎች/ ግለሰቦች ከሰብዓዊነት አመለካከት ተነስተው ለሚኖሩበት ማህበረሰብ ልማትና ለአካባቢ ደህንነት በነጻ ጊዜያቸውን፣ ገንዘባቸውን፣ጉልበታቸውን፣ እውቀታቸውንና በጐ አመለካከታቸውን የሚያውሉበት በምላሹም ትምህርትና የህይዎት ልምድ እንዲቀስሙ የሚያስችላቸው ተግባር ነው፡፡
በጎ ፍቃደኝነት ከበጎ ህሊና የሚመነጭ የተቀደሰ ተግባር ነው፡፡ ከራስ አልፎ ለሌሎች የመሆንን ፤አሳቢነትን አካፋይነትን፤ ተባባሪነትን ፤እኔ ብቻ አለማለትን ፤ተጋግዞና ተደጋግፎ መኖርን የሚገልፅ ከፍ ያለ ስብዕና መገለጫ ነው፡፡

ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ደግሞ ይህ የእርስ በርስ መደጋገፍ ለዘመናት አብሮን የኖረ ባህላችንም ጭምር ነው፡፡
ይህንን በጎ ተግባር የተለያዩ የመንግስት ተቋማት የሚያስተባብሩት ሲሆን ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅችን ባለስልጣንም በአዋጅ 1113/2011 በህብረተሰቡ ዘንድ የበጎ አድራጎት እና በጎ ግቃደኝነት ባሕል እንዲዳብር ማድረግ የሚል ተግባርና ሃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡
ከዚህም አንጻር በጎ አድራጊነት ባህል እንዲዳብር ሁላችንም በያገባኛል ስሜት ርብርብ እንድናደርግ በጎ ፍቃደኝነት ከዘመቻ ስራ ተላቆ በስርዓት፣በፖሊሲና በመዋቅር እንዲመራ ለማድረግ ተቋሙ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በቀጣይም ይህንን ቀን በማስመልከት የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ፕሮግራም የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡
መልካም ቀን!!
328 views08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 10:19:26
ዓለም ዓቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን በድሬደዋ አስተዳደር በድምቀት ተከብሯል :፡፡
በዓለም ለ31ኛ ጊዜ እንዲሁም በኢትዮጵያ ለ30ኛ ጊዜ “አካታች የፈጠራ የስራና ሽግግራዊ መፍትሄ ለኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተደራሽነት” በሚል መሪ ቃል በድሬደዋ አስተዳደር ሚንስትሮች፣ የአስተዳደሩ ከፍተኛ ኃላፊዎች እንዲሁም በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት በከፍተኛ ድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡
ከዋዜማው ጀምሮ በበርካታ ሁነቶች የታጀበው ዓለም ዓቀፉ የአካል ጉዳተኞች ቀን በድምቀት የተከበረ ሲሆን በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ በትብብር እየሰሩ ለሚገኙ አካላትና ለበዓሉ መሳካት አስተዋጽዖ ላበረከቱ የሲቪል ማህበራት እውቅናና ምስጋና ተሰጥቶበታል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣንን ጨምሮ ከተለያዩ አካላት የተሰባሰቡና በአስተዳደሩ የሚገኙ አካል ጉዳተኞች የሚገለገሉባቸው ቁሳቁሶች በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር በኩል ለአስተዳደሩ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ተበርክቷል፡፡
በነበረው መርኃ ግብር የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በተገኙበት ቸሻየር ኢትዮጵያ የተባለ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተመዘገበ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት በድሬደዋ አስተዳደር እየሰራ ያለው ስራ ተጎብኝቷል፡፡
99 views07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-01 12:20:48
‹‹ሙስናን መታገል በተግባር››
‹‹ሙስናን መታገል በተግባር›› በሚል መሪ ቃል በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለ19ኛ ግዜ በሃገራችን ደግሞ ለ18ኛ ግዜ የዓለም ዓቀፍ የጸረ ሙስና ቀን በዓል በተቋሙ ከአጠቃላይ ሰራተኛ ጋር እየተከበረ ይገኛል፡፡
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት ሀገራችን ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽንን ከማርቀቅ ጀምሮ እሰከ ማፅደቅ በነበረው ሂደት ንቁ ተሳትፎ ስታደርግ መቆየቷ እና በኋላም በዓለምአቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ለሚገኘው የፀረ-ሙስና ትግል አጋርነቷን በማሳየት ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል፡፡
ይሁንና ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በድህነት ውስጥ ባለች ሀገር “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንዲሉ ሙስናና ሌብነት የእድገታችን ማነቆ ሆኖ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያደረሰብን ይገኛል፡፡ በተለይም ሕዝብን ለማገልገል የተቋቋሙ አገልግሎት ሰጪ የሆኑ መንግስታዊ ተቋማት ከሌብነትና ብልሹ አሠራር በፀዳ መልኩ በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል ሲገባቸው ይህንን ኃላፊነታቸውን ለጊዜያዊ ጥቅም አሳልፈው በመሸጥ የሀገራችንን እድገት በእጅጉ ወደ ኋላ እየጎተቱ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
በተቋማችን አገልግሎት ስንሰጥ ያስቀመጥናቸውን ተቋማዊ እሴቶቻችን ባከበረ መልኩ በአጋርነት እና በትብብር በመስራት፣ግልጽነት እና ተጠያቂነት፣በማስፈን ቅንነት እና ታማኝነት በመላበስ፤ፕሮፈሽናሊዝምን ባከበረ መልኩ እንዲሁም፣ምላሽ ሰጪነትንና ሰብአዊነት ማዕከል አድርገን ማገልገል የሚጠበቅብን ሲሆን እንደተቋም ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በተመለከተ ዜሮ ቶለራንስ (zero-Tolerance) የሆነ መሪህን የምንከተል መሆናችንን በዚህ አጋጣሚ ለማረጋገጥ እወዳለሁ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
382 views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-23 10:02:54
416 views07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 10:00:55
በጅግጅጋ ሲካሄድ የቆየው 6ተኛው የኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን፣የፌደራልና የክልል ባለድርሻ የመንግስት ተቋማት የጋራ ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል፡፡
**********************************
በጉባኤው የክልልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በሱማሌ ክልል ተከሰቶ ለነበረው ድርቅ ድጋፍ ላደረጉ ክልሎች፣ከተማ መስተዳድርና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የምስጋና የምስክር ወረቀት በቤተ መንግስታቸው በመጋበዝ ሰጥተዋል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣንም ለሶስተኛ ዙር የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማስተባበር ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የምግብ ቁሳቁስ በክልሉ በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ አድርጓል፡፡
በጉባኤው የክልሎች ተሞክሮ፣የገንዘብ ሚኒስቴር፣የፋይናንስና ደህንነት አገልግሎት እና የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በኩል ከዘርፉ ጋር የሚያገናቸውን ተግባራት በዝርዝር አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡
500 views07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 09:58:11
6ተኛው የኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን፣የፌደራልና የክልል ባለድርሻ የመንግስት ተቋማት የጋራ ጉባኤ በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
**********************************
የክልሉ ምክትል ፕረዝዳንት አቶ ኢብራሂም ዑስማን በጉባኤው ባስተላለፉት መልዕክት የሲቪል ማህረሰብ ድርጅቶች ህብረተሰቡን በማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዬች ላይ ያለው ግንዛቤ እንዲዳብር ማድረግን ጨምሮ በሚሰሯቸው ሌሎች ዘርፈብዙ ስራዎች ለሃገር ሁለንተናዊ እድገት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ እሙን ነው ብለዋል፡፡
በዚህ ረገድ በባለፈው ዓመት በክልላችን አስከፊ ድርቅ መከሰቱን ተከትሎ ድርቁን ለማቋቋም በተደረገው ርብርብ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ በማቅረብና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ የጉዳቱን መጠን ለመቀነስ ያደረጉትን አስተዋጽኦ በመጥቀስ በድርቁ ወቅት ላሳዩት አጋርነትና ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የሶማሌ ክልልም የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶችን ያላሳተፈ እድገት እንዲሁም የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የሚፈለገውን ውጤት እንደማያመጣ ይገነዘባል በማለት ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች በእኩልነት ተጠቃሚ የሚያደርግ ዘላቂነት ያለው ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ ለሚደረገው ጥረት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በአግባቡ ሚናቸውን መወጣት የሚችሉበትን ምቹ ሁኔታ እንዲኖር በቁርጠኝነት ይሰራል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፍቃዱ ጸጋ በበኩላቸው መንግስት በዘርፉ ለውጥ እንዲመጣ የህግ ማሻሻያዎችን ብሎም የአመራር ለውጥ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ ለውጥ አስመዝግቧል ያሉ ሲሆን ሲሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም በሃገሪቱ የልማትና የመልካም አስተዳድር ጉዳዬች የማይተካ ሚና አላቸው ብለዋል፡፡
485 views06:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 09:53:41
ለሁሉም የሙያ ማህበራት በሙሉ
መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ ከታች ባለው ሊንክ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
https://docs.google.com/.../1FAIpQLSd.../viewform...
2.9K views06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 21:00:19
292 views18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 21:00:17
292 views18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 21:00:15
294 views18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ