2022-06-17 22:44:54
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፍተኛ አመራርና ባለሙያዎች በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማና በተለያዩ የክልሉ ወረዳዎች የሚገኘውን The Pharo Foundation የመስክ ምልከታ ተደረገ፡፡
**********************************
The Pharo Foundation የተባለው የውጭ ድርጅት እ.ኤ.አ በ2016 በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዝግቦ እየተንቀሳቀሰ ያለ ድርጅት ነው፡፡
በክልሉ እየተተገበረ ያለውን የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመስክ የተመለከተ ሲሆን በዕለቱም ማስመረቅ ችሎዋል፡፡
ድርጅቱ በአሶሳ ከተማ Pharo Diagnostic የተሰኘውን የላብራቶሪ ማዕከል አስመርቋል፡፡
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናትና አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በምረቃ ስነስርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክ The Pharo Foundation የተሰኘው ድርጅት በአሶሳ ከተማ እና በክልሉ ወረዳዎች እያከናወናቸው የሚገኙትን በርካታ ፕሮጀክቶች መመልከት የቻልን ሲሆን በጤናው፣በግብርናው፣በትምህርት በንፁህ ውሃ አቅርቦት ላይ እየሰራ ያለው ስራ የሚያበረታታ መሆኑን ተገንዝበናል ብለዋል ፡፡
ይህ ዛሬ የሚመረቀው Pharo Diagnostic center የላብራቶሪ ማዕከል ቀደም ሲል በክልሉ በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ ችግር የነበረበትን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
953 views19:44