Get Mystery Box with random crypto!

የአባቶቻችንን አደራ በመወጣት አንድነቷንና የዜጎቿን ክብር የተጠበቀ ጠንካራ አገር ለትውልድ ማስተላ | Authority for Civil Society Organization (ACSO)

የአባቶቻችንን አደራ በመወጣት አንድነቷንና የዜጎቿን ክብር የተጠበቀ ጠንካራ አገር ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ገለጹ፡፡
ለ127ኛ ጊዜ የሚከበረው የአደዋ ድል በዓል "ዓደዋ አንድነት፣ ጀግንነትና ጽናት" በሚል መሪ ቃል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከጥንታዊ አርበኞች ማህበር እና ከኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማቾች ማህበር እንዲሁም ከተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር አከበረ፡፡
በበዓሉ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣን መስርያ ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንደተናገሩት ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪክ ሂደት ውስጥ በተለያዩ ዘመናት በርካታ የህልውና ተግዳሮቶች ተደቅነውባት በኢትዮጵያዊያን በተከፈለ መስዋትነት በድል አድራጊነት ተግዳሮቶችን በሙሉ በመሻገር የፀናች ታላቅ አገር መሆኗን ገልፀዋል፡፡