Get Mystery Box with random crypto!

7ተኛው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና የክልል እና የፌደራል ባለድርሻ አካላት ጉባኤ | Authority for Civil Society Organization (ACSO)

7ተኛው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና የክልል እና የፌደራል ባለድርሻ አካላት ጉባኤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ በተገኙበት በድምቀት ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የክልሉ ቢሮ ሃላፊዎች የሁሉም ክልል የፋይናንስ አና ፍትህ ቢሮ ሃላፊዎችና የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕረዝዳንት ተገኝተዋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ በንግግራቸው እንደገለጹት ይህ የጋራ ጉባኤ በክልላችን ለማድረግ ስለመጣችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው በማለት አገራዊ ለውጡን ተከትሎ የሪፎርም ስራዎች ከተሰራባቸው የህግ ማዕቀፍ ውስጥ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፍ አንዱ ነው ሲሉ አንስተዋል፡፡
አያይዘውም ለውጡን ተከትሎ በአገራችን የሚገኙ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እያደረጉት ያለው እንቅቃሴ የተሻለ መሆኑን ገልፀው የክልል መንግስታትና የፌደራል መንግስት ለሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት በክልሉ የሚሰሩ ድርጅቶች በአግባቡ በመያዝ እንዲሁም አዳዲስ ድርጅቶችንም ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ አክለው ገልፀዋል፡፡