2022-12-13 22:18:45
#የዘርሲዎች_ፍቅር
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ከእንቅልፉ ረፋዱ ላይ ነቃ ክፍሉ በብርሃን ተሞልቷል
እንደተጋደመ ማሰብ ጀመረ ተስፋ ያለው ነገር አልታየውም እዚች
አገር ከመኝታው ሲነቃ ፍንድቅድቅ የሚል የእናቱን ጡት የሚጠባ ህፃን ብቻ ነው" ሌላው ግን ህሊናውን እያከከ ምን ሰርቶ እንደሚበላ ያስባል፤ ምን ሰርቶ እንደሚኖር ያልማል ትንሹ በትልቁ ህሊና
ገብቶ መሞትን ይመኛል ሞት የሌለበትን አሸናፊነት ለማግኘት ይማስናል እና ከመኝታው ሲነሳ ጭንቀትንና ተስፋ መቁረጥን ያዛጋል
ምነው አገሬ ጭንጫ ምድር በሆነች ኖሮ ለፋን ለፋን
ምርት ግን ጠፋ ብለን እናመሃኝ ነበር ምነው ከርሰ-ምድሯ በደረቀ
ኖሮ ካለውሃ መቼስ ምን መስራት ይቻላል እንልም ነበር ካላት የከርሰ-ምድር ውሃ አስር ፐርሰንት እንኳ አለመጠቀሟን ባናውቅ
ምነው የሰው ኃይልስ ባልኖረ ምን ይደረግ
የአለንን ለመጠቀም
ሰው ያስፈልጋል እንልም ነበር የሰው ኃይል ባልኖረ ኖሮ ይህች አገር ግን ሁሉም አላት ልምላሜ ታሪክ ውበት እህ!.. የጭንቀታችን ምንጭ የሆነው ህምታ ከየት መጣ?" የእኛ ትውልድ የወሲብ የጦርነት የዝርፊያ ፊልም ማየት በቃው? እኮ ምን አለፋን በፊልም የሌለንን እናያለን በፊልም የማንኖረውን እንኖራለን ..." ብሎ ሲፈላሰፍ ቆይቶ
ከመኝታው አፈፍ ብሎ ተነሳና ወደ ተናኘ መኝታ ክፍል ሄደ ተናኘ በጠዋቱ የለችም እሱ ግን ወደ አልጋዋ ተጠጋና ጠርዙ ላይ ቁጭ አለ ራስጌዋ ካለችው ትንሽ ኮመዲኖ ላይ የእለት ውሎዋን የምትፅፍበትን ማስታወሻ አየው" ላንሳው አላንሳው ከህሊናው ጋር
ተሟገተ እረፍ እረፍና ተነስ! ህሊናው አዘዘው"
እንጃባህ! በልጄ …'
"ኦሆሆ! ጅል አትሁን አንተ አባት ማስታወሻ ደግሞ
ምሥጢር ተቀባይና አስቀማጭ ነው" አንተን አያውቅም ለአንተም
አይታዘዝም ጌታው እሷ ናት ገላጯ ፀሐፊዋ ልጅህ ናት
ለአንተ የሚሆነውን ከእሷ ጠይቅ ከእሷ ህሊና አንብብ
"ማንም ሰው ሊገልፀው የማይፈልግ የምሥጢር መቃብር ህሊናው ውስጥ አለ በሐዘን ብቻውን እንደ ጥጥ ተባዝቶ አስከፊ
መቃብሩን ተሸክሞ በፍርሃት እየራደ ከአፅም ጋር እየተፋጠጠ እጣ ፋንታው የሆነውን ዘግናኝ ህይወቱን የሚኖር አለ! ... የህሊና ውስጥ ሞት ሃዘንተኛ የማይጠይቅበት የመቃብር ሐውልት የማይታነፅበት
በየግላችን ያጣነውን መልካምም ሆነ መጥፎ የህይወት እጣ በሙሚ
ቀባብተን ሳይበሰብስ የምንቀብርበት ብቸኛው የመቃብር ሥፍራ
ህሊናችን ነው" ሁለተኛ የመቃብር ሥፍራ ደግሞ የግል ማስታወሻ
ነው" ማንም ሊያየው፥ ሊመራመርበት ሊጎበኘው ... አይችልም
ካለባለቤቱ በስተቀር ለሌላ ሰው ዝግ ነው ስለዚህ ማስታወሻዋን
አትንካው ! በሃጢያት ደም ህሊናህን አትበክለው ...'
አያገባህም፤ ለልጄ ከኔ የበለጠ ምሥጢር ጠባቂ የላትም ይህን ሲያስብ ሰቀጠጠው፤
"እሽ ልጄ የራሷ የህይወት ምሥጢር ይኖራት ይሆናል
ማወቅም አይገባኝ ይሆናል ማስታወሻዋን ማንበቤም ትልቅ የህሊና ወቀሳ ያመጣል" ግን እሷን ደግሞ ማወቅ አለብኝ በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ አስፈልጋታለሁ አለሁልሽ የማልላትን ልጄን እውነተኛ
እሷነቷን በመጠየቅ አላገኘውም የማነበው ልቆጣጠራት አይደለም
ለዚያማ ህሊናዋ የት ሄዶ የምታነበው መጽሐፍ መች አንሷት እሳትና ውኃ
ለልጄ ማወቅ ያለባትን ማሳወቅ የነበረብኝንም እሳትና ውኀ
አሳይቻታለሁ እንዴት እንደምትጠጣና እንደምታበስል ግን እያየች፥
እያነበበች እየሞከረች
ተማረች አባት ልጁን ዘለዓለም የሚያስተምር መምህር አይደለም ትምህርት አያቆምም አባትና የክፍል አስተማሪ ግን የማስተማሩ እድላቸው የሆነ ደረጃ ላይ ያቆማል ከዚያ መማማር በመጨረሻ ደግሞ ይማራሉ" እና!- ከልጄ የህይወት ፈተና ልማር ተወኝ" ብሎ ህሊናውን መንጭቆት
ማስታወሻዋን ከኮሞዲኖው ላይ አነሳው
ሰርቶ መብላት ምን ነውር አለው መሰደድስ ቢሆን
ወንድማለም! ከቸገረህ ምን ያሳፍራል? እውነቴን'ኮ ነው በሃብት ደልበዋል የተባሉትስ አሜሪካኖችና አውሮፓውያን ተሰደው ለአረብ አሽከር ሆነው ብራቸውን አፍሰው አገራቸው ይገቡ የለ ..." የሚለውን የራስ ማፅናኛ አባባል አንብቦ ሌላ ገፅ ገለጠ።
"ወንድማለም! ወገቤ እስኪቆረጥ ለሰዓታት ስማስን ቀኑ ነጉዶ
ለሊቱ ጭላጭ ሰዓት እየቀረው ነው ምስጋና የሌለበት ባዶ ህይወት!
“ለገንዘብሽ ነው ስትቆይ ያው መጥገብሽ አይቀርም ፀባይሽ ካላማረ ኮንትራትሽን ሰርዞ መተካት ነው ተሰልፎ ከሚለምነው አንዱን
እየተባልህ የዕቃ ክብር ተነፍጎህ በዘመናዊ ባርነት መኖር ወንድማለም ደከመኝ እባክህ ልተኛ! ልተኛ ማን አስተኝቶኝ ባለቤቷ እንቅልፍ ስታጣ የኔን መኝታ በር አንኳኩታ ቀስቅሳኝ
ተመልሳ መተኛት ልማዷ ነው" አንዳንዴ ሳስበው እኔ ሰራተኛዋ ብቻ ሳልሆን የእንቅልፍ ማስወሰጃ እንክብሏም ነኝ እላለሁ በል
ለሁሉም ጎኔን ላሳርፈው ማለቱ ይሻለኛል የሚለውንም አንብቦ ሌላ
ገፅ ገለጠ።
"አይ ወንድማለም! ይሄንስ እድሜ ልክህን ባታስበው
ይሻላል" ለአንተ እኔ ሁሌ ህፃን ነኝ አይደል? ግንኮ ህፃን ከሆንኩ ሁለት አስርተ ዓመታት አለፉ ግን አንተ ስለጎረምሳነት ዘመንህ
ለምንድን ነው የማታወራው? የምትወደድ ሰው ነበርህ? ወይንስ
ጨካኝ: ዋሾ! ... ሁሉንም ሁን ለምን እንደሆንህ አላውቅምና ጭፍን
ያለ የተሳሳተ ፍርድ ሰጥቼ ልወቅስህ አልሻም ያ አይነት ፍርድ መስጠት ካቆምሁ ደግሞ ቀናት ተቆጠሩ።
"ወንድዬ! የጀመርሁትን ሳልነገርህ ምን ዙሪያ ጥምጥም አዞረኝ? ማስታወሻዬን ነው አታነበው፤ግን ፈራሁህ ስፅፍ እያሰብሁህ ነው" በዚህ ዓለም የምታምኝው?'
ብባል የለኝም
የምትቀርቢው? ከተባልሁ
ግን ወንድማለምን
ነው የምለው"ይከፋህ ይሆን? ይክፋህ እንጂ የምወድህ
ስለማላምንህ ስንት የደበቅሁህ ጉድ አለ መሰለህ አንተ መቼም እንደ
አባቴ ብትሆንም
ብዙ አባቶች ድፍን ፍቅርን የምትሻ ግብዝ አባት አትመስለኝም ሁሉም ልክ እንዳለው ታውቃለህ አይደል?"
"ፍቅሬ አገረሼ ወንድዬ! አንድ ጊዜ በየሄድሁበት እያስነጠሰ የሚያሳጣ ፍቅር ይዞኝ ነበር" ያ የፍቅር ገጠመኝ አሁን ተረት ነው
የነ ጦጢትና አንበሳ ተረት የዓረብ ቤት እያፀዳሁ ግን ያ የተረት ስሜቴን ፏጨረው፤ አንዴ ይቆረጥመኛል ሌላ ጊዜ ይለበልበኛል እንደ ቁርጠት ቀስፎ አላስቆም አላስቀምጥ ይለኛል
ያንጠራራኛል እንደ ምጥ ገፍቶ ሲመጣ ደግሞ ሲቃ ነው፡ ውለጂው ነው
አንተ ወንድማለም! አሁን አሁን ሳስበው ከሱስ ነፃ ነኝ!' እያልሁ ስመፃደቅ ለካ ማፍረሻ የሌለው ሱስ ሱሰኛ ነኝ እህህህ በሱስ መጠመድ ቢሉህ መጠመድ ነው ያውም በቅርብ ባላረከው
ወደፊትም በቅርቡ በማታገኘው ሱስ የሚፋጨው የስሜት ስለት
ህሊናህን ሲበሳሳው፤ እየወጠረ ሲያከረው ነፍስህ ረፍት አጣ ውጪ
ነፍስ ግቢ ነፍስ ብትሰቃይ ምን ይሰማህ ይሆን?" ፈገግ አለ ጥያቄዋ
አፈፍ አድርጎ ተሸክሞት ወደ ኋላው ከነፈ አልፎት ወደመጣው የወጣትነት ህይወት የልጁን ምስጢር ከዚያ በላይ አንብቦ ማወቅ
ግን አልፈለገም እሷ ግን ማስታወሻዋ ላይ ስሜቷን: ውጥረቷን ረሃቧን ጥማቷን ... ዘክዝካው ነበር"
"... ወንድማለም የአለሁት ወህኒ ቤት ነው ትናንት ሃያ
529 viewsአትሮኖስ, 19:18