2022-12-21 18:00:12
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
‹‹እኔ እዬብ እኮ ነኝ.›› ብዬ ቃላት ከአንደበቴ ለማውጣት አፌን ስከፍት ከንፈሯ ከንፈሬን ጎረሰው…ተአምር ነው በዚህ ሀገር ስንት ሴት ጄኔራሎች አሉ…?ከእነዚህ ውስጥ ከ ጄኔራሎች ጋር ፍቅር ለመጋራት ስንት የአዳም ልጅ እድል አግኝቷል.?.ልቤ በትዕቢት ስታብጥ ታወቀኝ…፡፡እጄን በወገቧ ዙረያ ጠምጥሜ ይበልጥ ወደሰውነቴ አጣበቅኳት..ብስጭቴ ሁሉ ከጭንቅላቴ እየተነነ አየሩን ሲሞላ ታየኝ…ውስጤ ተንፈቅፍቆ መሳቅ ጀምሯል…
ከከንፈሯን አላቃ በአንድ እጇ ብቻ ወገቤን ይዛ ወደላይ አንጠለጠለችኝና አልጋው ላይ ወረወረችኝ…፡፡ወይኔ ዛሬ በቃ እስከመጨረሻው ነው…ቆይ ልብሴን ላውልቅ ብዬ ልነሳ ቀና ስል ግንባሬ ላይ ሽጉጥ ደቅናለች..መልሼ በድንጋጤ በመደንዝ አልጋው ላይ ተዘረርኩ፡
‹‹ሽጉጥ እንኳን ሊደቀንብኝ በህይወቴ በፊት ለፊቴ አይቼው አላውቅም በፊልም እና በፎቶ ብቻ ነው የማውቀው..እና የጋለው ሰውነቴ ቀዘቀዘ…››
‹‹እንዴ ምን አጠፋሁ..?››
‹‹ሌባ ነህ..››
‹‹እኔ እዬብ እኮ
ነኝ››ለስንተኛ ጊዜ ይሆን ስሜን የነገርኳት?፡፡
‹‹አዎ ልቤንም የሰረቅከው እዬብ የተባልከው አስተናጋጅ አንተ አይደለህ?››
‹‹ይቅርታ የእኔም ልብ እኮ የለም ›አልኳት በአሳዛኝ ድምፅ ሽጉጡን ከግንባሬ አንስታ ትራሷ ስር ሸጎጠችና ከጎኔ ተኛች
‹‹በፈጣሪ ምነው ምን አድርጌሽ ነው እንዲህ ምታስደነግጪኝ.?››
‹‹ይቅርታ››
‹‹እስከአሁን እንዴት ሳትተኚ››
‹‹አየጠበቅኩህ ነበር››
‹‹እንዴት …ወደቤት ሁሉ ሄጄ ተኝቼ ነበር.
‹‹እናስ?››
.እናማ እንቅልፍ አልወስድም ሲለኝ ተመልሼ መጣዋ››
‹‹መጀመሪያ ለምን ሄድክ? አኩርፈሀኝ ነበር አይደል?››
‹‹አዎ በጣም ነበር የተበሳጨሁብሽ ..ደግሞ ዛሬ ነው ያየሁት..ወታደር መሆንሽን ብትነግሪኝ ምን አለበት ?ለዘውም ጄኔራል.››
‹‹ምን ይጠቅምሀል… እኔ ከአንተ ጋ እየተገናኘሁ ያለሁት ጄኔራል ሆኜ ሳይሆን ዜና-ወርቅን ብቻ ሆኜ ነው..››
‹‹ኸረ ተይ በናትሽ..ከቀድሞ አውቄ ቢሆን ልቤን መች እንዲህ አዝረከርካት ነበር…››
‹‹ምን ወታደር አይመችህም እንዴ?.››
‹‹አረ እንደዛ ማለቴ
አይደለም ግን ይከብዳል…በተለይ ለአንቺ የሚከብድ ይመስለኛል..አለ አይደለ እኔ እንጃ ብቻ.››
‹‹ለማለት የፈለከው ገብቶኛል.ግን አታስብ በቅረብ ጡረታ ልወጣ ነው..››
‹ጡረታ ምነው በዚህ ዕድሜሽ.?ለዛውም የማአረግ እድገት ባገኘሽበት ማግስት ››
‹ ምክንቱን ሌላ ጊዜ እንግርሀለሁ …ግን ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ከሰራዊቱ እሰናበትና ሌላ የሲብል ስራ ላይ የምመደብ ይመስለኛል…››
‹‹አሁን ትንሽ ቀለል አለኝ…መቼስ ጡረታ ከወጣሽ በኃላ ችላ አትይኚም አይደል?››
‹‹አይ አልልህም….ግን አንድ ልደብቅህ ማልፈልገው ነገር አለ››
ስለጄኔራሉ ፍቅረኛዋ የሆነ ነገር ልትለኝ ነው ብዬ በታፈነ ስሜት‹‹ ምን?›› ስል ጠየቅኳት
‹‹አንተን በተመለከተ በጣም የተወዛገበ ስሜት ነው የሚሰማኝ…የሆነ ድሮ የማውቀው የጠፋ ዘመዴ ወይም ወንድሜ ነው ምትመስለኝ››ብላኝ እርፍ፡፡
‹‹ባክሽ አትቀልጂ …ይሄ ደግሞ ምን ማለት ነው?፡፡››
‹‹እኔ እንጃ …ሁል ጊዜ ላገኝህና ላቅፍህ እፈልጋለው..አግኝቼ ሳቅፍህ ደግሞ ታናሽ ወንድምሽ እኮ ነው የሚል ስሜት ይተናነቀኛል፡፡››
‹‹ምነው የጠፋ ወንድም ነበረሽ እንዴ?››
‹‹ኸረ ፍፅም.. እኔ ምንም የጠፋም ያልጠፋም ወንድም ኖሮኝ አያውቅም››
ኮስተር ብዬ‹‹ተይው በቃ ይህ የእህት ነገር እጣ-
ክፍሌ አይደለም..ለጊዜው ጓደኞች ከሆን ይበቃል›› አልኳት …ውስጤ ግን ምንም አይነት ከእሷ ጋር ጓደኛ የመሆን ጉጉት የለውም…
በተረጋጋ አንደበት‹‹እንደዛ ከሆነ እንተኛ››አለችኝ፡፡
‹‹ደስ ይለኛል›አልኳት፡፡
እሺ ብላ አልጋው ላይ ቆመች…የለበሰችውን ቢጃማ አወላለቀችና በሰማያዊ ፓንት ቆመች.እኔ በተኛሁበት ከስር ወደላይ እያየኋት ነው..ይገርማል በቴቪ በዛ ግርማ ሞገስ ያያት ሰው አሁን እንዲህ እርቃኗን ቆማ ከነሙሉ ውበቷና ደምግባቷ ቢያያት ደግሞ ምን ይል ይሆን?፡እኔም በተኛሁበት ልብሴን አወላልቄ ወደጠረጳዛው ወረወርኩና ከውስጥ ገባሁ ..ቀድማኝ ገብታ ነበር፡፡ መብራቱን አጠፈሁና ከሰውነቷ ተጣበቅኩ፡፡እና ከየት እየተንቀዠቀዠች እንደመጣች ሳላውቅ የተአምር እናት በምናቤ ተሰነቀረች…የሴት ልጅን ገላ ሳቅፍ እንዲህ አይነት የሚነዝርና የሚያሾር አይንት ስሜት ሚሰማኝ ከእሷ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ብቻ ነበር፡፡ዳሩ ነገሮች ባለምኳቸው መጠን እድገት አላሳዩም.. ሊቱን በሙሉ በመተቃቀፍ ገደብ ባይኖረውም ከዛ እልፎ ወደ ጭን መፈላለቅ ሊያድግ አልቻለም፡፡ ‹‹በፈጣሪ አሁን እኔ ምኔነው የእሷ ወንድም የሚመስለው?››ይሁን እስቲ ….ማምሻም ዕድሜ ነው ይባል የለ፡፡
…በማግስቱ ማታ
//
ከምሽቱም አምስት ሰዓት ከስራ መልስ ነው፡፡አልጋዬ ላይ ወጥቼ ከብርድልብሴ ስር ገብቼ ስለነበር ስልኬን ካስቀመጥኩበት አነሳሁና ተነጠራርቼ መብራቱን አጠፋሁ፡፡ብርድልብሱን ተከናነብኩና ሞባይሌን ከፈትኩ ፡፡ቅድም ልጄ ተአምር ልካልኝ የነበረው ቴሌግራም ከፈትኩ….እናቷ ስለእኔ የፃፈችው ቀጣይ ፀሁፍ ነው….የእሷን ፅሁፍ ማንበብ የቡና ሱስ ነው የሆነብኝ፡፡ ተመቻችቼ ማንበብ ቀጠልኩ፡፡
ግንቦታ 16/2008 ዓ.ም
እዬቤ ከእህቶቼ በላይ ነው ማቀርበው…ከእህቶቼም በላይ ነው የምወደው..እሱ ለእኔ የሚስጥር ተጋሪዬ ነው..እሱ ለእኔ የትምህርት ቤትም ጓደኛዬ ነው።እርቃኔን እህቶቼ ፊት ስቆም ሰውነቴን ይበላኛል...እዬቤ ፊት ሲሆን ግን የራሴን ሰውነት በራሴ አይን እያየሁ ነው የሚመስለኝ።ለምን እንደዛ ሆነ ?ለእኔም ለራሴ ግራ ይገባኛል። ለምሳሌ ልብስ ለእህቶቼ ተገዝቶ ለእኔ ባይገዛ ችግር የለውም..ለእኔ ተገዝቶ ለእሱ ላይገዛ ግን አይችልም።በቃ ያንን ልብስ በምንም አይነት አለብሰውም።እሱም እንደዛው ነው።አንዳንዴ ያው የሙት ልጅ ነው በሚል ስሌትም ከቤተሠቦቹ ቤት ኪራይ የሚገኝ ገንዘብ ስላለ በሚል ስሌትም ብቻ ምክንያን አላውቅም ለእሱ ለብቻው ልብስ ይገዛለታል..እሺ ብሎ ይቀበልና አጣጥፎ ያስቀምጣታል"ለእኔ እስኪገዛልኝ ስድስት ወርም ቢፈጅ አይለብሳትም ።ከዛ በቤተሠብ ሁሉ ተለመደና ለሁለታችንም መግዛት እስኪችሉ ነጥለው መግዛት አቆሙ..
ከእዬቤ ጋር እድሜያችንም ተቀራራቢ በመሆኑ ክፍላችንም አንድ ነው። የምንቀመጠውም አንድ መቀመጫ ላይ ነው።ያው ግን ለትምህርት የምንሰጠው ትኩረት በጣም የተለያየ ነው።እዬቤ ከአንደኛ ክፍል አንስቶ እስከመጨረሻው አንደኛ ወይም ሁለተኛ ነው የሚወጣው..ተሳስቶ እንኳን 3 ተኛ መውጣቱን አላስታውስም ።ብዙ አያጠናም ..ክፍል ውስጥ አስተማሪ የሚያስተምረውን በፅሞና ያዳምጣል..የቤት ስራ ሳይረሳ ይሰራል፤ ፈተና ሲቃረበ ያጠናል በቃ...እኔ ግን ተውኝ "አንድ ቤት እየኖራችሁ አንድ ክፍል እየተማራችሁ አንድ አስተማሪ እያስተማራችሁ ይሄ ሁሉ ልዩነት ምንድነው?"የአባቴ የዘወትር ጥያቄ ነበር
"ቆይ አንድ ክፍል አይደል እንዴ የምትኖሩት? ለምን አብራችሁ አታጠኑም?" አባቴ ይጠይቀዋል
‹‹ጋሼ አብረን ነው የምናጠናው..ግን እሺ አትለኝም..እያጠናን ትተኛለች..ወይም ትረብሻለች"
3.2K viewsአትሮኖስ, 15:00