Get Mystery Box with random crypto!

‹‹እሱስ እውነትሽን ነው፡፡ እኔም አክራሪነትን በጣም መፀየፍ ከጀምርኩ ቆየሁ፡፡በሀይማኖት አክራሪዎ | አትሮኖስ

‹‹እሱስ እውነትሽን ነው፡፡ እኔም አክራሪነትን በጣም መፀየፍ ከጀምርኩ ቆየሁ፡፡በሀይማኖት አክራሪዎች ምክንያት ሀይማኖት የሚባል ነገር እርግፍ አድርጌ ትቻለሁ…በብሄር አክራሪዎች ምክንያት ለብሄሬ ያለኝ ትርጉምና ፍላጎት ተንጠፍጥፎ ባደ ስለሆነ ብሄር አልባ አድርገውኛል፡፡፡የሀገር አክራሪዎች ደግሞ ሀገሬን ሊያሳጡኝ ጫፍ ላይ ናቸው፡፡  ›› የሚል ማብራሪያ ሰጠዋት፡፡
      
‹‹አየህ ጥሩ ገልፀኸዋል ፡፡የአክራሪዎቹን ዋና አላማ  ምንም የማይጠይቁ አባላትን ከጎናቸው ማሰለፍ እናም ከመሀከል ይሉትን ገፍተውና ተስፋ አስቆርጠው ከጫወታው ውጭ ማድረግ ነው..ከዛ ማን ይቀራል እንሱ ከነጭፍን ደጋፊዎቻው፡፡ …ተቃራኒዎቻቸውም  በተመሳሳይ የጫወታ ህግ ከነጭፍን ደጋፊዎቻቸው በዛኛው ጫፍ ይቆማሉ…..ከዛ ጦር መወራወሩና መሳሪያ መተኳኮሱ ቀላል ይሆናል…፡
.በዚሀ መሀል ሀገር ይበጠበጣል…ወታደሩ ባረባ ነገር ከአንዱ ጫፍ ወደሌላ ጫፍ እየተስፈነጠረ ሁኔታዎችን ለማስተካክል መስዋዕት መክፈሉን ይቀጥላል….ደግሞ የሚገርመው እኮ የፅንፈኞች አሰላለፍ እንደሁኔታዎች መከረባበቱ ነው፡፡አሁን በብሄራቸው መመሳሰል ምክንያት የአንድ ቡድን ማሊያ ለብሰው ለአንድ አላማ ሲፋለሙ የቆዩ  ጓደኛሞች..የጫወታው ግጥሚያ አይነት ወደሀይማኖት ሲቀየር ጭራሽ እንደማይተዋወቅ በተለያየ ቡደን ተሰለፈው እርስ በርስ ይጠዛጠዛሉ፡፡አክራሪዎች አንድ የጋራ ፀባያቸው ፀረ እኩልነት መሆናቸው ነው…በአፋቸው ቢያንበለብሉም ፈፅሞ ከሌላው ጋር እኩል መሆንን አይቀበሉም፡፡የእነሱ ሀይማኖት የሀገሪቱ የመጀመሪያ እንዲሆን ፤የእነሱ ብሄር የሀገሪቱ የበላይ እንዲሆን ወዘተ..ብቻ ነው የቀንና ሊት ህልማቸው፡፡

‹‹መፍትሄው ግን ይኖረው ይመስልሻል፡፡››

‹‹መፍሄውማ መሀከል ላይ ያሉት አንዳንተ በእነሱ ድብቅ  ሴራ በሂደቱ ተስፋ ቆርጠው ከመድረኩ እራሳቸውን ያገለሉ ወይም ጆሮቸውን ደፍነው የተኙትን ማንቃትና እነሱን ማብዛት ሲቻል ነው፡፡ ››

‹‹መንግስትስ ?›› 

‹‹እኛ ስለመንግስት የማስፈፀምና የመቆጣጠር አቅም ያለን ግንዛቤ ከእውነታው ጋር ፍፅም የተምታታ ነው።ምን አልባትም ለሺ ምናምን አመታት በነገስታት ሲገዛ የኖረ ማህበረሰብ ነገስታት ደግሞ ስልጣናቸው ከላይ የተፈቀደ የሚመርጣቸውም የሚቀባቸውም አምላክ እንደሆነ እየታመነ  ሁሉን አድራጊነትንና ሁሉን አዎቂነትን ገንዘባቸው እንደሆነ ሲወርድ ሲፈረድ  በመጣ  የክብርና የፍርሀት ስሜት ሲተዳደር የኖረ ማህበረሰብም ዛሬም መንግስት  ማለት የመጨረሻውን ወንበር የያዘው ሰውዬ እንደሆነ በደመነፍስ ማመን በሀገሪቱ ለመጣው ስኬትም ጠቅልሎ ለእሱ መስጠት ውድቀቱንም እንደዛው ጠቅልሎ  በእሱ ማሳበብ ። ሁሉን ማድረግ ይችላል ብሎ በሌለው አቅምና ችሎታ ላይ መተማመንና ተስፋ ማድረግ...ሳይፈፀም ሲገኝ ስላልቸለና አቅም አጥሮት ሳይሆን ሆነብሎ በተንኮልና በዳተኝነት  ነው ብሎ በመውሰድ መማረርና እራስን መጉዳት…ምሳሌ የምንኖርበት ከተማ ስፋቱ ምን ያህል ነው።ስንት ቀበሌ አለው?ስንት ህዝብ ይኖርበታል..?ያን ህዝብ የየእለት ደህንነት ለመጠበቅ ስንት ፓሊስ ጣቢያና ምን ያህል ፓሊስ አለ? በከተማዋ 50 የተለያየ ቦታ በአስር ደቂቃ ልዩነት አደጋ ቢደርስ እና ፓሊስ ሪፓርት ቢደረግለት ስንቱ ጋር ከምን ያህል ጊዜ በኃላ መድረስ ይችላል?የተረኛ ፓሊስ እጥረት፤የትራንስፓርት እጥረት-የተመደብት ፓሊሶች ዳተኝነት፤የአደጋዎቹ ቦታዎች ከንዑስ ፓሊስ ጣቢያዎች ያላቸው እርቀት..?
እና  ፀጥታችንን የሚጠብቀው መንግስት ነው? ደህንነታችንን እያስከበረ ያለው መንግስት ነው?አይደለም፡፡ እዚህ ላይ የመንግስት ቀጥተኛ  ሚና ኢምንት ነው።ግን ደግሞ እንደማህበረሰብ በውስጣችን ያዳበርነው መንግስትን የመፍራት…የማስፈፀም አቅሙን አጋኖ የማሰብ  ባህሪያችን እርስ በርስ እንድንከባበር አድርጎናል.. የወጡትን ህጎች የማክበር   አቅማችንም በንፅፅር ሲታይ ከፍተኛ ነው።እውነታው ግን መንግስት ህግን ለማውጣት ያለውን ብቃት ያህል እነዛ ህጎች እንዳይጣሱ ቀድሞ የመከላከል እና ሲጣሱም ተከታትሎ የመቅጣት አቅሙ ውሱን ነው።እግዚያብሄር ይመስገን ይህንን እውነት በልኩ የሚረዳ የማህበረስብ አካል ከ2 ፐርሰንት የማይበልጥ በመሆኑ መንግስት እንደሰፈር ጎረምሳ እየተኮሳተረ እና እያስፈራራ ብቻ እራሱን አስከብሮ ለረጅም ጊዜ እንዲኖር እረድቶታል፡፡
  
‹‹እና ማጠቃለያሽ ምንድነው;?››

‹‹ማጠቃለያውማ….ምን ጊዜም እራስህ በራስህ ለመጠበቅ ትጋ…ከመንግስት የምትጠብቀውን ነገር በተለይ እንደግለሰብ መንግስት ለእኔ ማድረግ አለበት ብለህ የምታስበውን ነገር  በተቻለህ መጠን ለዜሮ የተጠጋ ይሁን…ያን ጊዜ ከራስህም አልፈህ ሌሎች የእኔ የምትላቸወን ሰዎች ለመጠበቅና ለመታደግ ብቃት ይኖርሀል …በተቃራኒው መንግስት እንዲህ አደረገ...መንግስት ለምን እንዲህ አያደርግም? እያልክ በየቀኑ ስትነጫጭና ስታማርር ምትውል ከሆነ በስተመጨረሻ  የጨጓራ በሽተኛ ሆነህ ታርፈዋለህ እንጂ በህይወትህ ምንም ለውጥ አታመጣም፡›

‹አምርሮ ማማረር እኮ ወደአምርሮ መጥላት ያድጋል ...አምርሮ መጥላት ደግሞ መንግስትን ለማስወገደ እና በሌላ ለመተካት እርምጃ ለመውሰድ ይገፋፋል ፡፡››አልኳት ፈራ ተባ እያልኩ….

‹‹ችግሩ እሱ አይደል?››

‹‹እንዴት?››

‹‹በአንተ እድሜ እንኳን ስንት መንግስት ተቀየረ…?እና መንግስት በመቀያየሩ በአንተ ህይወት ላይ ያመጣው ለውጥ ምድነው..?በሀገሪቱስ..?አንዱ መንግስት ሲመጣ በዛኛው መንግስት የነበረ ሰህተትን ያስተካክል ይሆናል ግን ደግሞ ውሎ ሳያድር ተመጣጣኝ የሆነ ሌላ የራሱ ችግር ይፈጥራል..በተለይ አፍሪካ ውስጥ መንግስት መቀየር ማለት በአጠቃላይ የችግር አይነትን መቀየር ማለት ነው..››

‹‹ውይ ይብቃን የፓለቲካ መድረክ አደረግነው እኮ..››

‹‹እሺ እንደውም ደክሞኛል.ማለቴ እንቅልፌ መጥቷል እንተኛ…››

‹‹እሺ ጓደኛዬ እውነትሽን ነው እንተኛ››ተንጠራርቼ መብራቱን አጠፋሁና ልክ ከዚህ ቀደም እንደነበሩት አዳሮች አይነት አተኛኘት ተኛን፡፡

ይቀጥላል