2022-12-17 21:00:03
#የዘርሲዎች_ፍቅር
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
፡
፡
#ክፍል_አምስት
ካለወትሮው እያከታተለ የሚወርደው ዝናብ የሐመርን ምድር:
የወሮን መንደር የብርሃን ጥላ አልብሷታል" ሰማዩ ላይ በጨርቅ እንደተጠቀለለ ህፃን ዳመናው እየተገለባበጠ
ምርር ብሎ እየጮኸ
ብልጭታው በሁሉም አቅጣጫ ይፈነጣጠቃል
ከክቧ የሐመሮች ጎጆ የሚትጎለጎለው
ከሚጥመለመለው ጥቁር ዳመና ጋር እየተደባለቀ ይጠፋል ፍየሎች በጎች ጥጆች ገና ከበረታቸው አልወጡም በከብቶች አንገት የተንጠለጠለው የኤሊ ድንጋይ ከብቶቹ በተንቀሳቀሱ ቁጥር
ቋቋ ቋቋ እያለ ይሰማል" መንደሯ ልብ ብለው ሲያዳምጧት ትንፋሽዋ እንደወትሮዋ ነው፤ ማነጠሱ፥ ጨዋታው፥ እንጉርጉሮው: ቀልዱ ወፍጮው፥ የወፎቹ ዝማሬ ሁሉም ከዘመናት በፊት
እንደተቃኘው ነው
የናት ጉያ ሙቀት የናፈቃቸው ሆዳቸውን የሞረሞራቸው ጥጆች ግን ከናታችን አራክቡን በሚል ሆድን በሚያላውስ ቅላፄ እ-
ም--ዋ … እም-ቡ-ዋ እያሉ የጌቶቻቸውን ጆሮና ቀልብ ለመሳብ ረሃብና ናፍቆታቸውን በለሆስታ ዜማ አለዝበው ያንጎራጉራሉ" ላሞች እንደሌሎች ከብቶች ማመንዠካቸውን አቁመው ፊታቸውን ወደ ጥጆቻቸው አዙረው ዐይናቸውን እያቁለጨለጩ: ሳጋቸውን እያሰሙ የጥጆችን ከለላ በአፍንጫቸው እያሸተቱና
እየነካኩ የናትነት አንጀታቸው ረፍት ነስቶ ያንሰፈስፋቸዋል አንተነህ ይመር ከምድጃው ጎን ካለችው ትንሽ መደብ ላይ
በቦርኮታው የቀኝ ጭኑን አስደግፎ፥ ጎኑን እሳቱን እያሞቀ እሱም
የማይሰማ ውስጡ ፈልቶ እዚያው ተኖ የሚቀረውን ሳጉን ራሱ ለራሱ ይሰማል
ባለቤቱ እሳቱን እየቆሰቆሰች ሻላው (ቆጡ) ላይ ባሰረችው ጠፍር የአንጠለጠለችውን እርጎ በቀኝ እጅዋ ወደ ፊትና ኋላ
ትንጣለች ቅቤ ለማውጣት ነጭና ጥቁር መልክ ያለው ቁርበት ከበስተ ኋላዋ ተነጥፏል ዳሚ ሰረቅ እያደረገች ስታየው ቆይታ
"ይእ! ምን ሆነሃል የኔ ጌታ?" አለችው
ቢጨንቃት" እሱ ግን ዝም አላት ዝም እየተነፈሰ ጭጭ
"ተቡኑ ልስጥህ?"
ጋልታምቤ መልስ ሳይሰጣት ውጭውን
አየው በጠባቧ በር በግድግዳው ቀዳዳ አየሩ ክርስስ ያለ ነው ቀዝቃዛ የሱም ልብ ቀዝቅዛለች
በሐመር ባህል የተጠየቀ ሁሉ ወዲያው የመመለስ ግዴታ የለበትም አዋቂ አስተሳሰቡ የበሰለ ከመናገሩ በፊት ልቡን ዐይኑ ላይ ማውጣት አለበት በልቦናው የሚያይ ሐሳቡ ሚዛናዊ ሆነ ክፉና ደግ ለመለየት በቃ ሃላፊነት ለመቀበል ደረሰ ማለት ነው" ጋልታምቤም በዚህ መላ
የሚስቱን ጥያቄና ጭጋጋማውን ቀን በልቦናው አየው" ልቦናው ግን ምንም እንዲል አልፈቀደለትም
ዝምታ ደግሞ በራሱ ቋንቋ ነው ዝምታና ዐይን ዝምታና ጥርስ ዝምታና ዝም በአይነቱ የተለያዬ ትርጉም አላቸው በቢጫው በሬ ምድር በሐመር።
ዳሚ የጋልታምቤን ዝምታና ዐይን አይታ የሚያሳስበው ነገር እንዳለ አውጥቶ ሊነግራት ግን እንዳልፈለገ ተረዳች ያን ጊዜ።
ይእ! ምን ሆነ? እንግዲ ተሱ ይምጣ'ንጂ እኔ ምናባቴ
ላርግለት ብላ እሷም ዝም አለች ዝም ተባባሉ እሱና እሷ እሱና እሱ: እሱና ተፈጥሮ ተዘጋጉ"
ጋልታምቤ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ሰረቅ አድርጎ አያት ልቧን ከንፈሯ ላይ ተቀምጦ አየው ፍርሃት ነፋ ልትት፤ ነፋ ልትት
ሲያደርገው ሲገፋፋው ሲያንቀጠቅጠው ሲያወዛውዘው ተመለከተው
ዳሚ ከበስተግራዋ ተሰካክተው ከተቀመጡት በጨሌ ያጌጠውን
ሾርቃ አንስታ ጠረግ ጠረግ በማድረግ ከተወዘተው እንስራ በቅል ጭልፋ ሸፈሮ ቡና ቀድታ አቀበለችው
ጋልታምቤ እግሩን አንፈራጦ ተቀበላትና ግራ ቀኝ ፊትና ኋላ ጎለል ጎለል አድርጎ አበረደው ከዚያ እፉት ብሎ ፕስስ አድርጎ አማተበ ሸፈሮ ቡና የቦርጆ ፍሬ ሽፋን ነው ደስታን ያመጣል ራስን ለማየት ከራስ ጋር ለመምከር የቆሸሸ ህሊናን
ፈውስን ለማጽዳት የሚፋጅ የሚያቃጥል ነገር ሲያጋጥም ነቅነቅ ወዝወዝ
እያደረጉ ለማብረድ ለማቀዝቀዝ ጥሩ ነው
ይህ ሐይል ያለው
ሸፈሮ የተወጠረውን ስሜት ሲያላላው፥ የታመቀ
የጋልታምቤን ትንፋሹን እያንቦለቦለ አስወጥቶ እሁ! አለ ዳሚ አየችው የደሙ
ዝውውር ተረጋግቶ ይሽከረከራል: ገፅታው ጠይቂኝ ይላል"
"ዛሬ ቀን ምን ሆነሃል?" ስትለው ትክ ብሎ አያትና ዐይኖቹን ከላይዋ ላይ አንስቶ ከራሱ ጋር ሙግት ገጠመ" ይህች ሰው
ባትሰማው ይሻል ይሆን? ይህማ የማይቀር እዳዋ ነው ከሌላ ከምትሰማው እኔ ብነግራት አይሻልም አአይ ይቅርባት ትጨነቃለች ችግሩ ደግሞ ወደሷ እየገሰገሰ ነው መከራዋን በቀስ እየደራረበች ብትሸከመው አይሻልም … ብሎ ፊቱን ወደ ዳሚ
መለሰው
"ዳሚ!"
"ዬ!" አለችው ዐይኖችዋን ከዐይኑ ነቅላ እሳት እሳቱን እያየች አይን አፋርነቷ
ትልቁ ውበቷ ነው" ሁሌም ሲጠራት ዐይኗ
ይንከራተትና የሆነ ቦታ ገብቶ ውሽቅ ይላል" የምታየው ግን እሱን ነው።
"ዳሚ!" አላት ደግሞ
"ዬ!" አለችው ድምጿን ከረር አድርጋ እየሰማሁህ ነው'
ለማለት።
"ያች ልጅ መንጠፏ ነው ይሆን?" አላት የሃሣብ ሸክሙን በጥሶ ላይዋ ላይ በትኖ ዳሚ ጥያቄውን ስትሰማ ህሊናዋ አስደንጋጭ ነጎድጓድ ባረቀበት ክው ብላ ደነገጠች አልጮኸችም መልስም አልሰጠችም ውስጧ ግን ባንዴ ባዶ ሆነ ቀፎ ዐይኖችዋን እሳቱ ላይ ለረጅም ጊዜ ተክላ ቆየች
ጥያቄው በቀፎው ሰውነቷ
እየተንጎዳጎደ ነዘራት አመማት እንደ ሚጥሚጣ ለበለባት ... እሳቱ
ላይ የተሰካው ዐይኗ ሙቀቱ እንዳቀለጠው ሁሉ በፈሳሽ ተሞላ በእንባ በምሬት የዐይኗ ኳስ ሲንቀሳቀስ ግን እንባዋ ፈሰሰ እንባዋን ንፍጧ ጠርቶት ቁልቁል ወረደ እንባዋ ንፍጧን ተከተለው አያት ጋልታምቤ እንደገና በዐይነ-ህሊናው ራሱን አየው፤ እንደ
ከስኬ ወንዝ ወደ ውስጡ የሚሰርገው እንባው ስለማይፈስ መውጫ
ስለሌለው የሰራ አካላቱ ላይ የእንባ ጎርፍ ተኝቶበታል"
"ሁለት ዓመት ሙሉ ይኸው ወልዳ ለመሳም አልታደለችም የሐመር ሽማግሎችም ተነጠፈች በሐመር ደንብ መሰረት ለከሎ ወይ ምትክ ይሰጠው ካለበለዚያም ጥሎሹ ይመለስ እያሉ ነው" አላትና
መሬቷን ተመለከታት ዳሚ የሚለውን አልሰማችውም ከፊት ለፊቱ ተቀምጣ እሷ ግን የለችም አትንቀሳቀስም:
ጋልታምቤ ከውስጥ የዳሚ ከውጭ የላሞች ሳግ ተሰማው የጥጆች ጥሪ የጎይቲ ሰቆቃ
መሀን ሴት በሐመር ልቧ እንደ አሮጌ ቅል የተጠረማመሰ ምስጥ እንዳነካከተው ግንድ ተስፋዋ ፍርክስክስ ያለ ከዚህ መከራዋ በተጨማሪም ቤተሰቧን የመጥፎ ቤተሰብ የምታሰኝ እሷ የመጣችበትን መንገድ ለሌላው ግን የምትከለክል
እርጉም ተብላ
ከማህበራዊው ቡድን ተነጥላ ተወርውራ የምትጣል የቤተሰቧን ጎጆ
በጨለማ የምትሸፍን ናት
"የፈራሁት ደረሰ! ብላ ዳሚ የእንባዋን ውታፍ ከፈተችው
ልቧን ነደለችው ሆን ብላ ያዳፈነችውን የጭንቀት እሳት እፍ አለችው የእንባ ፈሳሽ ያገኘው ስሜቷ እንደ ደረቀ ቅጠል በውስጧ
ሲንቀለቀል ናጣት አርገፈገፋት አስቃሰታት
ስለዚህ ጋልታምቤ ጭንቀቷን ተቀምጦ ማየት ሰቀጠጠው
ከተቀመጠበት ተነስቶ ጥጆችን ከእናታቸው ያራክባቸዋል ከጥቂት ደቂቃ በኋላ አንዱ ጠብቶ ሌላው
ሊያራክባቸው ወጣ ጥጆችን
አጥብቶ ጥጋብ ይሆንና የመለያየቱ ምልክት ድራሹ ጠፍቶ መላላስና
መቦረቅ ይመጣል አንተነህ ይመር ለጎይቲ ምኑን አጥብቶ ከጭንቀቷ
ይገላግላታል! አለኝታው፡ መስታዋቱ ደስታውን እንዳያይባት መከራ
1.4K viewsአትሮኖስ, 18:00