Get Mystery Box with random crypto!

አትሮኖስ

የቴሌግራም ቻናል አርማ atronosee — አትሮኖስ
የቴሌግራም ቻናል አርማ atronosee — አትሮኖስ
የሰርጥ አድራሻ: @atronosee
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 163.71K
የሰርጥ መግለጫ

╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።
Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 40

2022-12-16 22:39:59 አዲስ አበባ ከገባሁ ከአመታት በኋላ ባለገንዘብ የሆንኩ ጊዜ ወደእሳቸው መንደር ላገኛቸው ተመልሼ ነበር። አፈላልጌ በጥቆማ እቤታቸውን ፈልጌ ሳገኝ እኔ አወቅኳቸው። ከዘራ ይዘው እያነከሱ ከበራቸው ወደቤት እየገቡ። እሳቸው ግን አላወቁኝም ነበር። ከአመታት በፊት ካየኋቸው አርጅተው። ተጎሳቁለው ነበር። ሰላም ካልኳቸው በኋላ ከከተማ መምጣቴን ስነግራቸው ወደቤታቸው ጋበዙኝ።

«ያስታውሱኝ ይሆን?» አልኳቸው

«ዓይኔ እያስቸገረኝ ነው ልጄ አላስታወስኩሽም! የማን ልጅ ነሽ?»

«ማን እንደሆንኩ እነግሮታለሁ! መጀመሪያ ግን ማንነቴን ስነግርዎት የምለውን ሰምተው እንደሚያስጨርሱኝ ቃል ይግቡልኝ!!»

«ልጄ እያስጨነቅሽኝኮ ነው!!»

«ቃል ይግቡልኝ!! የምለውን ሁሉ ይሰሙኛል?»

«እሽ ቃሌ ነው!!»

«ከብዙ ዓመት በፊት ከገበያ ሲመለሱ አንዲት ሴት እንደዘረፈችዎት አይጠፋዎትም መቼስ!»

«እንዴት ይጠፋኛል! ቤቴን እኮ ነው ያፈረሰችው! » ብለው በደንብ አዩኝና « አምሳል ነኝ እንዳትይኝና እዚህ ደም እንዳንፋሰስ!!»

«እስከመጨረሻው እሰማሻለሁ ብለው ቃል ገብተውልኝ የለ?»

«በይ ልስማዋ!!»

እግራቸው ላይ ወደቅኩ!! «ከዛን ቀን በኋላ ሳላስቦት የዋልኩ ያደርኩበት ቀን የለም! አንዲት ቀን እንኳን ፀፀት ሳይፈጀኝ አልፎ አያውቅም!! ይቅር አይበሉኝ! ግን ከዚህ በላይ አይቅጡኝ!! የምሰጦትን ገንዘብ ይቀበሉኝ!» አልኳቸው

ተነስተው በፍፁም አሉ!! ሚስታቸው ከጓዳ ትሰማ ነበር እና

«ደግም አይደል አያል! ይህች ልጅ ተጠጥታ መጣችም አይደል? እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል አቤቱ በደላችንን ይቅር በል ብለንም አይደል የምንጠልይ? ተነሽ ይበሏት በቃ!» አሉ። ከስንት ልምምጥ በኋላ እንዳኩረፉ ያመጣሁላቸውን ገንዘብ ተቀበሉኝ። አብረዋቸው ከነበሩት ሰዎች አንደኛው ማረፋቸውን ነገሩኝ! ሌላኛውን እቤታቸው ሄጄ ስላላገኘኋቸው መልዕክቴን ከገንዘቡ ጋር አስቀምጬ ተመልሼ ለአቶ አያልነህ ይቅርታዬን እንዲነግሩልኝ ለምኜ ልወጣ ስል እንዲህ አሉኝ

«ጨርሶ ይቅር ያልኩሽ እንዳይመስልሽ!! ድህነት አይኑ ይጥፋ ዛሬም ለልጆቼ ፍራንካው ስለሚያስፈልግ እንጂ ለራሴ ቢሆን እመቤቴ ምስክሬ ናት ፍንክች አላደርገውም!!» ብለውኝ ነበር። ከዓመታት በኋላ ለቅሶዬን ሊደርሱኝ የመጡት በልባቸው ይቅር የሚሉበት ፍቅር አጊንተው ቢሆን አይደል? ይቅር መባል እንዲህ ደስ እንደሚል ባውቅ ስንት ይቅርታ የምጠይቀው ነበረኝ!!

ይቀጥላል.........



ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
825 viewsTsiyon Beyene, 19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 22:39:59 #የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ሀያ አምስት)
(ሜሪ ፈለቀ)

ብዙ ነገር አጥቼ እንደነበር የተሰማኝ አሁን ላይ ነው። የእማዬን አልጋ ከበን ቡና ተፈልቶ ቆሎ እየቆረጠምን አንዱን ወሬ ስናነሳ አንዱን ስንጥል በብዙ ሳቅ እና ደግሞ በደስታ ለቅሶ የታጀበ ቀን እየዋልን ያለፉ አመታቴን አስቤ ብዙ እንደጎደለኝ ገባኝ።

ደግሞ በዚህ ሁሉ የቤተሰብ ፍቅር ታቅፌ ልቤ ክንፍ አውጥታ ጎንጥ ጋር ስትሄድ፣ የያዘኝን አያያዝ ፣ የሳመኝን መሳም ፣ የጠራኝን መጥራት አሰብ አድርጌ ብቻዬን ፈገግ ስል ባለፉት ዓመታቶቼ ብዙ እንዳለፈኝ ገባኝ። ብዙ እንዳልኖርኩ ገባኝ!!

«እትዬ ዛሬ ሌላ ሰው ሆነው በንፁህ ልብ ስለተቀበሉት ነው የሚያጎብጥ ሸክም የሆነብዎት። ቂም ባቄመና በጠለሸ ልብ ሆነው ሲቀበሉት እንዲህ አልተሰማዎት ይሆናል።» ነበር ያለው ጎንጥ እንዴት ይሄን ሁሉ ጥላቻ ተሸክሜ ኖርኩ ስለው?
በንፁህ ልብ አይደለም። በፍቅር ልብ ሳየው ነው ዓለምን እና ዙሪያዬን የማይበት መነፅር የተቀየረው። በፍቅር ዓይን!! ሁሉ እንዳለኝ የተሰማኝ፣ መኖር ደስ የሚል ነገር መሆኑን ማሰብ የጀመርኩት በፍቅር ልቤ ማየት ስጀምር ነው።

እናቴን አቀፍኳት፣ ኪዳንዬ አለኝ፣ አጎቴን አለኝ፣ ጎንጥ ይኑረኝ አይኑረኝ ባላውቅም አዎ በልቤ ውስጥ ግን ከነጥጋቡ አለኝ!! ምን እጠይቃለሁ ሌላ? አጎቴ እናታችን ስለደከመች ካጠገቧ ባንርቅ መልካም መሆኑን ስለነገረን በአካሌ ላለመሄድ ወሰንኩ። ግን ልትሞት ቀናት የቀራት እናቴን አቅፌ ልቤ አዲስአበባ መሸምጠጡ ራስወዳድነት ነው? እንደዛ እየተሰማኝኮ ራሴን እገስፃለሁ። ልቤ አልሰማኝ አለኝ እንጂ!!


የገባን ቀን ማታ ምናልባት ለጥንቃቄ በሚል። በኪዳን ስልክ ዋትሳፕ መልዕክት ላኩለት። ሁለት መስመር ለመፃፍ ከ20 ደቂቃ በላይ ፈጀብኝ። ለኪዳን ካልሆነ በቀር ፅፌ የማውቀው ማስፈራሪያ ወይ ቢዝነስ ነክ ነገር አልያም የሆነ መልእክት እንጂ ፍቅር ነክ ነገር እንዴት እንደሚፃፍ አላውቅም። ምን ተብሎ ነው የሚጀመረውስ? ሀይ ጎንጥ? ስሙ ደግሞ ሲጠራ ምንም የፍቅር ቅላፄ የለውም!! እንዴት ዋልክ ዓለሜ? ልበለው? አይሆንም እሱ ሲል ነው እንደሱ የሚያምርበት! ሀኒ ልበለው? ሆ ጎንጥን ሀኒ? ራሴኑ አሳቀኝ!! ያቺ የድሮ ሚስቱ እንደጠራችው ጎኔ ልበለው? ኡፍፍፍ

«ሰላም ዋልክ? እኔ ነኝ!! በጠዋት ላይህ ሳልችል ቀርቼ እማዬጋ መጥቻለሁ!! ደህና አድረህ ዋልክ?» በቃ መፃፍ የቻልኩት ይሄን ብቻ ነው። ምን አይነቷ ነፈዝ ነኝ በፈጣሪ!! ከዛማ ስልኩን አቅፌ የፃፍኩለት መልዕክት ሰማያዊ የራይት ምልክት እስኪያሳየኝ ስልኩ ላይ አፍጥጬ ቀረሁ።

«ዓለሜ ናፈቀሽ እንዴ?» ይለኛል ኪዳን ሲያበሽቀኝ

«ለምን ግን አታርፍም?» እላለሁ

«ጎንጤን ነው?» ይላል አጎቴ

«እንዴ? እኔ ብቻ ነኝ የማላውቀው ማለት ነው? አንደኛውን ሽማግሌ ልኳል አትይኝም እንዴ?»

«እዚህ ከርሞ አይደል እንዴ የሄደው? ዓይነውሃው ያስታውቃልኮ ፍቅር እንዳለበት! መች አይኑን ከርሷ ላይ አንስቶ! <ጎንጤ እርሻ ወረድ ብለን እንምጣ ?> ብለው <አይ ጋሼ ከርሷ ባልርቅ ነው የሚሻል። ደህና መሆኗን ማየት አለብኝ> ይለኛል። <እንደው ታች ሰፈር ደረስ ብለን ብንመጣስ?> ብለው <ይቅርታ ጋሼ ዛሬ ልክም አይደለች ርቄ አልሄድ> ይለኛል። ኋላማ <እኔ የምለው ጎንጤ? ትከጅላታለህ እንዴ?> እለዋለሁ ቆጣ ብሎ <ምን ማለቶት ነው!> አለኛ» እናቴን ጨምሮ ሁሉም ይስቃሉ። እንደኮረዳ እሽኮረመማለሁ።

ስልኩ መልዕክት መቀበሉን የሚገልፅ ድምፅ ሲያሰማ ከመቀመጫዬ እንደመዝለል ሁሉ ሲያደርገኝ ቡና የምታፈላው ትንሽዬ ዘመዳችን ሳትቀር በአንድ ላይ አውካኩብኝ። የትልቅ ሰው ያልሆነ ማፈር አፍሬ መልዕክቱን ለማየት ሁሉ ስግደረደር ቆየሁ።

<እኔ ደግ ነኝ! የሚቻልሽ ከሆነ ድምፅሽን ታሰሚኛለሽ?> ነው የሚለው መልዕክቱ! አሁን ይሄ እሺ ምኑ ነው የሚያስቦርቀው? በፍቅርሽ ሞቻለሁ የተባለች ኮረዳ እንኳን እኔ የምሆነውን መሆን አትሆንምኮ! ትቻቸው ወደበር ወጣሁ እና ደወልኩለት። ቶሎ አውርተሽ መጨረስ አለብሽ የተባልኩ ይመስል የተፈጠረውን ለምን ሳላየው እንደመጣሁ እማዬ ስለደከመች ወደከተማ እንደማልመለስ በጥድፊያ ትንፋሽ እስኪያጥረኝ አውርቼ ሳበቃ ሳቅ ብሎ

«ለመዝጋት ተቻኮልሽ እንዴ?» አለኝ
«አይ!» እያልኩ በቆምኩበት በጫማዬ መሬቱን እየቆፈርኩ መሆኑን አየሁ

«ደግ! ያሻሽን ያህል ጊዜ ቆይ!! » አለኝ

«አንተስ?»

«እኔ ምን እሆናለሁ?» አለኝ እኔ ማወቅ የፈለግኩት ከዛስ የሚለውን….. እኔ ያሻኝን ያህል ጊዜ እዚህ ስቆይ እሱስ? ከሆስፒታል ሲወጣ ቤት ሄዶ ይጠብቀኛል? ወይስ ያለሁበት ይመጣልኛል? ወይስ እኔ ወደማላውቀው ቤቱ ይሄድብኛል?

ያናደደኝን ወይ የተጣላኝን ሰው በጉልበት እንዴት እንደማግተው አውቅ ነበርኮ! የወደድኩትን ሰው እንዴት አባቴ አድርጌ ነው የራሴ የማደርገው? እሱን አልችልበትም!! በጉልበት ባገቱት ሰው ላይ ሙሉ ስልጣን ማራመድ ይቻላል። በፍቅር የወደቁለትን ሰው ራሱ ፈቅዶ ወደእኔ ካልቀረበ ምንድነው የማደርገው? ዝም አልኩ!!

«ዝም አልሽኝ እኮ ዓለሜ?» አለኝ ጠብቆ

«ምን እንደምል አላውቅበትም!! ያለፍከውን አላውቅም! ወደፊት ምን እንደምታስብ አላውቅም! ነገ ምን እንደምንሆን አላውቅም! አሁንም ምን እንደሆንን አላውቅም!! አላውቅህምኮ ጭራሽ! እኔ ግን እዚህ ልትሞት ያለች እናቴን አቅፌ ካንተ ሌላ ሀሳብ የለኝም!! ይሄ እንዴት ያለ መሸነፍ ነው ቆይ?» አልኩት።

«የት እሄድብሻለሁ? አለሁ አደል? ሁሉን ትደርሽበት የለ? አንች ብቻ የተሸነፍሽ አታድርጊው እንጅ!!» ብሎ ግማሽ መልስ ምን ግማሽ እሩብ መልስ ይመልስልኛል።

«እንዲህ እንድትለኝ አይደለም የምፈልገው!» ስለው እየሳቀ

«እንዴት እንድልሽ ነው የምትፈልጊ? ቁጣው የምንድነው ታዲያ?» ሲለኝ ነው እየተቆጣሁ እንደሆነ ያስተዋልኩት

«እንደምትወደኝ ነው ማወቅ የምፈልገው!! እንዳልነሳ ሆኜ በፍቅርህ ከመውደቄ በፊት እየተሰማኝ ያለው ስሜት የእኔ ብቻ እንዳልሆነ ነው ማወቅ የምፈልገው! አይሆኑ አሸናነፍ ከመሸነፌ በፊት እንደማላጣህ እርግጠኛ መሆን ነው የምፈልገው? እ?» ስለው መሳቁን ሳያቆም

«ፍቅርሽም ቁጣ ነው? እንደምወድሽማ ታውቂያለሽ! መስማቱን ከሆነ የፈለግሽ እወድሻለሁኮ ዓለሜ!! ነገ ምን እንደሚሆን ከፈጣሪ ጋር እናበጀዋለን!! ዛሬን ልውደድሽ ዓለሜ ዛሬን ውደጂኝ!!»

እንኳን ፊት ሰጥቶኝ ዘጭ ለማለት እየተንደረደረ የነበረ ልቤ ዝርፍጥ ብሎ በፍቅር ነሆለለ። ከዛን ቀን በኋላ በየቀኑ ተደዋወልን!! በየቀኑ እንደሚወደኝ ነገረኝ። በየቀኑ ደጋግሜ ተሸነፍኩ። በየቀኑ ከእማዬጋ ሳቅን። በየቀኑ ድሮ ያጣነውን እቅፏን ናፍቆት መሬት ላይ አንጥፈን ለሶስት እቅፏ ውስጥ አደርን። በየቀኑ ደስ አላት!! በአስራ ሶስተኛው ቀን ጠዋት እኔና ኪዳን በቀኝና በግራዋ ሙቀቷን እየሞቅን እማዬ ዝም አለች።

እማዬን ስላጣኋት ከፋኝ። አግኝቻት ስለሞተች ደግሞ አመሰገንኩ። ኪዳንም ተመሳሳይ ስሜት ነበር የተሰማው ግን ከእኔ በላይ የእርሱ ሃዘን በረታ!! ምናልባት እኔ ለእርሱ ለመሆን ስታትር ዘመኔን ስለኖርኩ አጎደልኩበት ብዬ እንዳላስብ ዝም ብሎኝ እንጂ ሁሌም የእናቱ ናፍቆት ያንገበግበው ነበር ይሆናል። በኖረችልኝ ብሎ ሲመኝ ይሆናል የኖረው። እኔና አጎቴ ከእርሱ በርትተን እሱን ማበርታት ጀመርን።

የቀብሯ ቀን ሬሳዋ ከቤት ሲወጣ አይኖቼን ደጋግሜ አሸሁ ያየሁትን ሰው ለማጣራት። አቶ አያልነህ! ፈገግ አልኩ! ይቅር ብለውኛል ማለት ነው።
915 viewsTsiyon Beyene, 19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 21:00:04 ... ኧረ አንተ ተርፈሃል! በዚያን ሰሞን ምን የመሰለውን ጎበዝ ከበሸዳ የመጣ ሐመር ሌላ መሂና መሃል መንገድ
ተንደርድሮ ሄዶ እንደ ተዋጊ ወይፈን ከስሩ ቢያነሳው እንደ ቅንቡርስ ጥቅልል ብሎ አልተነሳም አሉ  በዚያው ቀረ! እና እንዲህ እያደቡ መጨረስ ነው እንጂ ገራም መስሎ አንድ አንዳችንን እየለቀመ
ሊፈጀን እማይደል!" ብለው አንድ ዐይናው ሽማግሌ ተናግረው ሲጨርሱ ያን የሰሙት ሽማግሎች አንገታቸውን ከፍና ዝቅ እያደረጉ አዘኑና እነማን በጥይት እንደሚደበድቡትና
እንደሚቀብሩት ተመካክረው የጎረምሶቹ ቡድን ተመረጠደ።

"ቶሎ ቶሎ እንበል'ንጂ ከብቱ መምጫው ደርሷል?" አለ ጋልታምቤ ልቡ በፍርሃት ትር ትር እያለችበት

"ጥሩ ነው!" በእጃቸው ሰበቅ የያዙት ሽማግሌ ከበስተኋላ ድምፅ አሰሙ
"ጥሩ ነው! ደልቲ ጀግና ነው
ጀግና! ግን አንድ
ራሱን ነው እስቲ እዩት የአባቶቻችንን ዱር"
ብዙ ዛፍ በመኖሩ
አይደለም ለማገዶ እንጨት ለእኛ የምንበላው ፍሬ የሚሰጠን አንድ ግዙፍ የሾላ ዛፍ ብቻ ቢኖር ምን ዋጋ አለው" አንዱ ሲደርቅና
ሲረግፍ ሌላው ካለመለመ አንዱ ፍሬው ወዳድቆ ሲበሰብስ ሌላው
ካላፈራ ይህን ጊዜ የት እንደርስ ነበር ቢያመን የምንጠቀመው ስርና
ቅጠልስ ዱር ውስጥ ብዙ ዛፍ በመኖሩ የምናገኘው አይደለም! አንድ ዛፍ ብቻ ስንቱን ይሆናል? ማገዶ የቤትና በረት መስሪያ: ጥላ
አንድ ጀግና ማለትም አንድ ግዙፍ ዛፍ ማለት ነው አንድ ዛፍ ደግሞ ስንቱን ይሆናል? ለእኛም ትልቁ አለኝታ ጀግና ሳይሆን ጀግኖች
ናቸው ጀግኖች ለድንበራችን
ትልልቆቹ ጀግኖች አባቶቻችን ናቸው
ለህልውናችን አለኝታዎች ነን እየሞቱ መልካም ነገር
ያቆዩን ልጆቻቸው የነሱን ጀግንነት ወራሽ ነን።
አደራችንን ደግሞ በትዕግሥት መፈፀም አለብን እንጂ ደንብ አፍራሽ
መሆን አይገባንም

ልበ ሙሉ አንበሳ ከሚሮጠው ቁጭ ብሎ የሚያስበው ይበዛል
አከርካሪ ሰብሬያለሁ እያለ ድንበሩን እየተወ እንደሮጠ አይኖርም፥ የአውሬነቱን የአባቱን ደንብ ሽሮ  ካሮዎች ተወንዝ የወጣ አሳ
አቅም የለውም ይላሉ
አያችሁት አባባላቸው ማማሩን! ደልቲም እንደ እያንዳዳችን የአባቱ ወራሽ ባላደራ እንጂ ሥራዬ
በቃኝ ባይ ደንብ አጉዳይ ባሻው ሯጭ ሊሆን አይችልም የሽማግሌ ልጓም አላ! አፈንጋጭን አጋድመው የሚገርፉ ጀግኖች አሉዋ! ስለዚህ ጥሎሹን እስታሁን ባለመጀመሩ ቅጣት ይገባዋል " ብለው ንግግራቸውን ጨረሱ„

ደልቲ ጥፋተኛ ነው" ሴት እንዲህ አለችኝ ብሎ ማለት
ራሱ ትልቅ ነውር ነው
ነውር! አባት ብላ ካርለት ከመረጠችው ከእኛ ከሽማግሎች ጋር መመካከር ይገባ ነበር እንጂ ራሱ ወስኖ ጭጭ
ማለቱ ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው? ስለዚህ ደልቲ ለጥፋቱ ከብት ይውጋና ጥሎሹን ነገ ዛሬ ሳይል ይጀምር  ተቅጣቱ ሌላ"  አሉ
በዝምታ ሲያዳምጡ የቆዩት ሽማግሌ

"ተው! አንቸኩል ነገር ከስሩ ውሃን ከጥሩው ይባል የለም
ያቀደው ስትባልግ: ስርዓት ስታጣ ደልቲ ካርለትን ለማግባት ቢያያት ሥርዓት ሊያሲዛት: አደብ ሊያስገዛት አስቦ ነው ልጃገረዷ
ሙሉ ሰውነቷን ስትታጠብ የኖረች መሆኗን
ግን እንደ ወንድ
የአየነው ነገር ነው" ስለዚህ ደልቲ ጥሎሽ ከፍሎ ካርለቴን አግብቶ
ፍሬ ባታፈራ የትኛዋን እህቷን ቀይሮ ሊወስድ ነው  አባቴ ብላ የመረጠችው እንደሁ ያለችው አንድ ሴት ልጅ ናት  እሷም
አግብታለች እስቲ በፊት በዚህ እንነጋገር ለቅጣት ከመቸኮላችን በፊት" አሉ አልፎ አልፎ የሚስሉት ሽማግሌ።

"እንዴት እንዴት ነው አያ ላሎምቤ ሃሣብህ?- አንድ ላም በረት ሙሉ ከብቶችን ሞልታ ያየን መስሎኝ የካርለት አባት ሚስትስ ብትሆን ስንትና ስንት የልጃገረድ ዘመዶች አሏት  ረሳኸው ወንድሜ! በቅድሚያ ካርለቴ በና ሂዳ ከተመረቀችና ለጥፋቷ ደንቡ
ከተሰራላት ደግሞ  ለምን አታፈራ  ታፈራለች ይልቅ ደልቲ ለተፈፀመው ጥፋት እንደተባለው ከብት ወግቶ ጥሎሹን ይጀምር" አሉ
አንጀት የማንበብ ችሎታ ያላቸው ሽማግሌ

እሺ አጥፍቻለው
የቦርጆን ታምር እውነትስ ማን አውቆ አታፈራም ታፈራለች ይባላል" አንዴ ሊያገባ ጠይቋል እንግዲህ
ዕድሉ ይታይና ችግር ከመጣ ሽማግሌደ የማይፈታውስ ምን ኣለ
ቅድሚያ ማሟረትም ለካርለቴ ደግ አይደለም" እንደተባለውም ደልቲ
ከብት ወግቶ ጥሎሹን ይጀምር" አሉና ሲያበቁ ፀጥታ ሰፍኖ ቆዬ።

"እህ! ከብት የሚወጋበት ቀን በቋጠሮ ይሰጠዋ  ማነህ  ና ልጥ አምጣ" አሉ የሽማግሎች አለቃ ከዚያ ልጡ መጣና አስራ
አምስት ቦታ ላይ ተቋጠረ
"ጥሩ ነው!" አሉ ከበስተኋላ የተቀመጡት ሽማግሌ ለበቃቸውን እየወዘወዙ

"ጥሩ ነው! ሴት ልጅ ብሩክ መሬት ናት ተወንዱ
የተቀበለችውን ዘር ፍሬ አድርጋ ቤተሰቡን ታበዛዋለች ጀግናን ትወልዳለች ቆንጆን ትተካለች ያለሴት ጀግና የለም ቆንጆ የለም የጋዲ ዳንስ የለም ... ሴት የቦርጃ ባላደራ ናት ሽማግሌው
ንግግራቸውን ገታ አደረጉ አንተነህ ይመር መንደርደሪያ ሐሳባቸውን ሲሰማ የፈራው በመምጣቱ በድንጋጤ ክው ብሎ ቃዠ
ጨነቀው የሃሳብ ማጥ ውስጥ ተነከረ
ሴት የቦርጆ ባላደራ ናት ይሁን እንጂ ሁሉም መሬት
አንድ አይደለም‥ በጦር ወጋ ወጋ አድርገው ጥቂት ፍሬ የበተኑለት ቅዱስ መሬት ታፍሶ የማያልቅ ምርት የሚሰጥ እንዳለ ሁሉ ጭንጫ መሬትም አለ ዘሩን አበስብሶ የሚያስቀር" አንዳንድ ሴትም አለች
ማህፀኗ የተረገመ ይህች ሴት ማህፀኗ ጀግናና ቆንጆ አያፈራም ታቀዘቅዘዋለች የባሏን በረት ባዶ ታደርግበታለች ቤተሰቧን ታሳፍራለች ለዚህ ደግሞ የአባት ደንባችን መፍትሄ
አለው" ብለው ንግግራቸውን አቆሙ

ጎይቲ እንዲያው ተሳስታ ብልቷን ውሃ ማስነካቷ ይኸው ለዚህ ችግር ዳርጓታል  በሷ ስህተት
መቼም ደንባችን አይሻር
የከሎም ዕድል አይነፈግ
ስለዚህ በእሷ ምትክ ከናቷ ዘመድ ልጃገረዶች አንዷ ትለወጥለታ!" አሉ የሽማግሎች አለቃ

በሉ መቼም ይሄ ነገር እንዲህ በዛሬ ምሽት የሚያልቅ አይደለም
ከብቶችም መጥተዋል: ሌላ ቀን  ደግሞ አስበን እንምከርበታ  አሉ ከወደመሐል በዚህ
ተመራርቀው በርኮታቸውን እያንጠለጠሉ ሁሉም ተስማሙና ወደ መንደራቸው ሄዱ።
የማታዋ ጀምበር ሰማዩን በቢጫና ቀይ ቀለማት አስውባ የቡሜን
ተራራ እየታከከች ወረደች የከብቶች ቃጭል ይቅጨለጨላል
ከብቶች ያገሳሉ: እምቧ ይላሉ መንደሯ ታዜማለች

ይቀጥላል
1.5K viewsአትሮኖስ, 18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 21:00:03 #የዘርሲዎች_ፍቅር


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


#ክፍል_አራት

ዘርሲዎች ግማሽ ክብ ሰርተው ከመንደሩ ራቅ ብላ ዙሪያ ገቡን ከምታሳየው
የግራር ዛፍ ስርቁጭ ብለዋል ጩሉሌዎች
አንገታቸውን ቁልቁል ደፋ አድርገው በዛ ዙሪያ ያንዣብባሉ: ነፋሱ
ቅጠሎችን ጎንበስ ቀና እያደረገ ይነፍሳል 
ከፊት ለፊታቸው ርጥብ
ቅጠል ተነጥፏል  መሃል ላይ ጎረምሶች የተጠበሰውን የፍየል ስጋ እየቆራረጡ የፍሪንባውን ሥጋ በእድሜ ለገፉትና በጀግንነታደው ለሚታወቁት ለሌሎች ደግሞ ከተለያየውደ የስጋ አይነት እፊት ለፊታቸው ካለው ቅጠል አስቀመጡ" ህፃናት ጨዋታቸውን አቁመው ራቅ ብለው ሲቁለጨለጩ ቆይተው እደላው አልቆ መብሉ ሲጀመር ወደየአባቶቻቸው ጉያ ተሸጉጠው ዳረጎታቸውን እየተቀበሉ ከአጥንት ጋር መታገል ጀመሩ በመጨረሻ የሚበላው ከተበላ: ቀሪውን ደግሞ ጎረምሶቹ ካቀለጣጠፉት በኋላ ወጣቶቹ ቅጠሉን ሰብስበው ጥለው
ከስብሰባው አካባቢ ርቀው ሄዱ።

የሽማግሎች አለቃ ጦራቸውን ይዘው ከተቀመጡበት ተነስተው
ከፈርሱ እግራቸውን ቀባ አድርገው ወዲህ ወዲያ ወዲያ ወዲህ አሉና፣
"የአባት ደንብ ጥሩ ነው" በልክ መብላት የአባቶቻችን ባህል ነው አባቶቻችን የራበውና የጠገበ ትክክል ፍርድ አይሰጥም ይሉ
ነበር" የጠገበ ወንድ ሴት ማለት ነው መሳቅ ቧልት ይወዳል ከብቶችን አይፈቅድም ጫካውን አይቃኝም ከጓደኞቹ ጋር
አይመክርም መዝለል አይችልም መቀመጥና ማንጎላጀት ይወዳል
ትክክለኛ ፍርድ በዚህ ምክንያት አይሰጥም ይሉ ነበር አባቶቻችን" ሽማግሌው እቱፍ: እቱፍ
ብለው የጦሩን ዘንግ በምራቃቸው ቀባ ቀባ እያደረጉ ሽማግሎችን:
የአባታቸውን አገር አድማስ እየተዟዟሩ አይተው

አባቶቼ የራበውም ከጠገበ አይሻልም ይሉ ነበር የራበው ሰው ሰነፍ ነው
ሲኖረው አያውቅበትም
የወደቀችው ጀንበር:
የጠፋችው ጨረቃ ተመልሰው  የሚመጡ
አይመስሉትም እንደ
አጋሰስ ፈረስ ዘመዶቹ ለመቋቋሚያ የሰጡትን ፍየሉንም፥ በጉንም
ከብቱንም: እህሉንም ብቻውን እየበላ ነገን ዘንግቶ: ልጆቼ: የአባቴ
ምክር ሳይል ሁሉን ያሟጥጥና የሚያልበው ሲያጣ የሚበላው
ሲቸግረው ሰውን: መሬቷን: ቦርጆን: አባቶቹን ይራገማል" ሆዱን
ለመሙላት ይቀማል ይዋሻል … ፍቅር አያውቅም ዘመድ ወገን አይለይም
አያስተውልም፤ ጨካኝ ነው
በዚህ ምክንያት
አባቶቻችን የራበው ሰው ትክክል አይፈርድም ይሉ ነበር አባቶቻችን ትክክል ናቸው ወንድሞቼ ጥጋብ ልቦናን ያዛባል ረሃብ ደግሞ ተስፋ መቁረጥንና ጥላቻን ያመጣል ከሁሉም የሚከፋው ደግሞ ሁለቱም ያስዋሻሉ" ብለው በርኮታቸው ላይ ቁጭ አሉ
ዝምታው ቀጠለ ሐመር ላይ ተረትን ሽማግሌ ለሌላው ማስታወስ እንጂ አይጨርሰውም የሰሙት እኩል: የፈፀሙት እኩል … ስለሆነ ተረት ጨራሽ አዳማጭ የለውም"

"በሉ ተናገሩ?" አሉ ሽማግሌው ከጥቂት ቆይታ በኋላ ጥሩ ነው! ከወደ መሃል አንዱ ድምፅ አሰሙ ገልመጥ ብሎ ያዬ የለም ሁሉም ግን አባባላቸውን በጆሮው ቀልቧል።

"ጥሩ ነው!- በአካል ተለይተውን ነፍሶቻቸው ደንቡን ጥበቃ አብረውን ላሉት ወንድሞቻችን ተገቢው ደንብ የሚሰራበት
ቀን ይመረጥ ልጆቻቸውና ሚስቶቻቸው በየበረሃው የአሉትን ተባት በግና ፍየሎች ከብቶችን ያስመጡ" በየመንደሩ ለሚኖሩት ዘመድ ጓደኞችም ጥሪ ይላክ ለዚያ ደሞ ዛሬ ቀኑ ተቆርጦ ቋጠሮ ይዘጋጅ አሉ።

የሽማግሎች አለቃ ሌላ ኃሳብ አለመኖሩን በዝምታደ ጠበቁና አንድ ጎረምሳ ጠርተው ልጥ አምጣ አንተ" አሉት ልጡ መጣ
"ስንት ላይ ይቋጠር?"

"መከን ተቢ" አሉ አንድ ሽማግሌ በስተግራ በኩል
ከተቀመጡት ሰላሳ ለማለት ልጡ ሰላሳ ላይ ተቋጥሮ ለሟቹ ታናሽ ወንድም
ተሰጠው" የሽማግሎች አለቃ አንዱን ችግር
በመቋጨታቸው
"ባይሮ ኢሜ" አሉ ሽማግሎችን እግዜር
ይስጣችሁ ለማለት

"በሉ ቀጥሉ?" አሉ የስብሰባው መሪ

"ጥሩ ነው!" አለ ልጅ እግሩና የአባቱን ጠላት ገሎ በቅርቡ
ከሽማግሌዎች ጋር ለመቀመጥ እድል ያገኘው ሰለምቤ፤ "ጥሩ ነው!
ታለውሻ በቀር አባቶቻችን ከአውሬ ጋር አልኖሩም እና ካርለቴ ይዛብን የመጣችውን አውሬ በጥይት አጉኖ ራቅ አድርጎ መቅበር ነው "አለ ገና የጎረምሳነት ባህሪው ሙሉ በሙሉ ያልቀዘቀዘለት ወጣቱ ሽማግሌ አለመብሰሉ በአነጋገሩ ፍጥጥ ብሎ እየታየበት።

"ጥሩ ነው! አውሬ ማለት ከብት የሚበላ ችግር የሚፈጥር ነው የነጯ ሐመር  የካርለቴ አራት እግር አውሬ ሳይሆን መሂና
ነው የሚባል አባቶቻችን ደሞ መሂና የሚባል አውሬ አለ አላሉንም ደሞስ የካርለቴ መሂና እንደ ፈረስ እየጫነን ገበያ እያመላለሰን ነው እና መኖሩ ምን ጎዳ! አሉ ግራሯን የተደገፉት አንድ ዐይና

የአባት ደንብ እየሻርን ያ ይጎዳል ይሄ ይጠቅማል
ካልንማ ይህች አገርና ይህ ህዝብ መዓት ይመጣበታል" በነሱ ጊዜ ያልነበረ አውሬ አሁንም መኖር የለበትም " አሉ አገጫቸውን በግራ
እጃቸው ደግፈው የቆዩት ሽማግሌ ከዚያ ክርክሩ ከተለያዬ አቅጣጫ
መቅረቡ ቀጠለ

በአባቶቻችን ደንብ ፍየል ቢመጣ ፍየል ጋጥ: ከብት
ቢመጣ ከብቶች በረት ሰው ቢመጣ  ወደ ሰዎች መኖሪያ ጎጆ ይገባል እህ እንዲህ እስተሆነ ድረስ የካርለቴ መሂና የሚገባ
ፍየሎች ጋጥ ነው? ከከብቶች በረት ነው? ወይንስ ከሰዎች ጋር ጎጆ
ውስጥ! መቼም ተውሾች ጋር እየተሯሯጠ አውሬና ጠላት ይከላከላል
አይባል ይኑር ከተባለ ወገኑ ከማን ነው?  ተከብቶቹ ወይንስ ከእኛ! አሉ ከወደመሀል መፋቂያቸውን ሲያኝኩ የቆዩት ሽማግሌ

"ጥሩ ነው የሁላችሁም አስተያየት አዲስ ነገር መምጣቱ ይኸው ሁለት ሶስት ቦታ ከፋፍሎ አጨቃጨቀን ያልነበረ ነገር
ሲመጣ ያልነበረ ችግር ይፈጥራል ነጯ ሐመር የእኛ የሆነች እንግዳ ናት መሂና ያለችውን አውሬ ዱካውን ለማጥፋት በጥይትና ጦር
ደብድበን እንቅበረው ብንል እሷን እናሳዝናት ይሆናል"
ባይሆን አውሬሽን ካመጣሽበት ጫካ ጥለሽ ነይ ብንላት አይሻልም
ወንድሞቼ!" አሉ። አንተነህ ይመር  ጋልታምቤ ጎን የተቀመጡት ሽማግሌ

ተው! ተው! ይህችን ሰው ተማበራችን አታውጧት! እሷ
ሐመር ናት  የሐመር  ልጃገረድ ተቀብላማ እንደ እህቶችዋ የፍየል ቆዳ ለብሳ ለዘመዷ ለከሎ ከብት
የአባቷን ትክክለኛ ደንብ
ዝላይ ተገርፋ … እንዴት እንዴት ነው  እንደውጭ ሰው ይከፋታል ማለት! ከአባትሽ ባህልና ደንብ ውጭ ያመጣሽው አውሬ ቦርጆን ያስከፋል የአባቶቻችንንም ነፍስ ያሳዝናል እነሱ ተቆጥተው ዝናብ ከሚያጠፉብን በሽታ ከሚልኩብን አውሬሽን ቀብረነው እንረፍ
ብንላት በፍጡም አይከፋትም  ወዲያውስ ከሽማግሌ ቃል ወጥታ የት ልትደርስ ኧረ አይከፋትም!" አሉ የዘርሲዎች አለቃ ከዚያ ለረጅም ጊዜ ዝምታ ሰፍኖ ቆየ

"ጥሩ ነው! እንዳላችሁትም
ነጯ ሐመር የእኛ ናት, የእኛ
ያልሆነውን ግን ዝም ብለን ብንለቀው ምን እንደሚያመጣ አናውቅም ሲቆይ ልጆቻችንን  እሷን ጨምሮ: እኛን ይተናኮስ
አይተናኮስ ሳናውቅ እናጥፋው እስከተባባልን
ድረስ በኋላ ለቀን
ከምናሳድድ እዚሁ ገራም መስሎ አጠገባችን እንዳለ አድብቶ በጥይት ማጎን ነው የሚበጀው ካለበለዚያ
እኮ አስተውላችሁት እንደሁ
አላውቅም እንጂ አጉረምርሞ አጉረምርሞ ሰውነቱ የጋለ እንደሆን
እንደ ጥይት ከተፈተለከ
ድንጋይ አይል ውሃ ... ማን ጀግና   ያቆመዋል! ስለዚህ ሳይደነብር አዋዝተው ጎረምሶች በክላሽ ጥይት
ሆድቃውን እንዲነድሉት ማድረግ ነው"" እንዳሉ

"ይህስ እውነት ነው! በቀደም ሳላየው ሩም … ብሎ ባጠገቤ ቢያልፍ የድምፁ ወላፈን እንዴት አሽቀንጥሮ ወረወረኝ መሰላችሁ ተዚያ ንዴቱ ይሁን ድንጋጤው ሰማይ እሆን ምድር ጠፋኝ!" አሉ ሌላው አዛውንት
1.4K viewsአትሮኖስ, 18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 19:26:04 በእምነቱ ማያፍር ለእምነቱ ድምፅ ይስጥ

ኦርቶዶክስ=
ጴንጤ=
ሙስሊም=
367 viewsENFALOT ° , 16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 19:02:17
የማንን ስልክ መጥለፍ ይፈልጋሉ?
የፍቅረኛዎን ፣ የልጆን ወይስ የጓደኛዎን

እንግዳውስ መፍትሄው ትልቁን የHACKING ቻናላችንን መቀላቀል ነው።

https://t.me/+9wYX6XZ1_U85MDQ0
477 viewsENFALOT ° , 16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 18:54:23
314 viewsENFALOT ° , 15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 18:00:14 "እና ተአምር የእኔ ልጅ ነች?"
"መቼሰ ከአንተና ከባሌ ውጭ ከሌላ ወንድ ተኝታለች ብለህ አታስብም..ነው ወይስ ታስባለህ?እንደዛ ከሆነ ያው አንተም ዲኤን.ኤ አሰርተህ ማረጋገጥ ትችላለህ።›› አለቺኝ እየተውረገረገች
"ኸረ እንደዛ ማለቴ አይደለም ...በፈጣሪ ምንድነው የምታወሪው?አሁን እቴቴ  ስሰማ ምንድነው የምትለው?››እቴቴ ማለት ለእሷ የስጋ እናቷ ለእኔ ደግሞ አሳዳጊ እናቴና አክስቴ (የእናቴ ታናሽ እህት)ነች።

"ለጊዜው ዝርዝሩን ለማንም መንገሩ አስፈላጊ አይደለም?››
"እንዴት ታደርጊያለሽ ?ሁሉም እኮ እውነቱን እስክትነግሪያቸው አይተውሽም።"
"ግድ የለም ለእኔ አታስብ..ጫናውን እችለዋለሁ....በዛ ላይ ወደአሜሪካ ለመብረር ሁለት ወር ነው የቀረኝ ...ሁለት ወር ምን ያደርጉኛል..ስጋዬን ዘልዝለው አይበሉት"
"የመስፍኔስ ጉዳይ..."
"በደፈናው ተነጋግረናል  ..ሁለቱንም ልጆች ይዞ የመሄድን ሀሳብ ለጊዜው ትተነዋል"
ደነገጥኩ ‹‹ምን ማለትሽ ነው ?ተአምርን የት ጥለሽ ልትሄጂ?"
ፈገግ አለችና‹‹ እንዴ ላንተ ለአባቷ ነዋ...አባቷ እያለ ለሌላ ለማን ጥያት እሄዳለሁ?"
"ባክሽ በዚህ በጭንቅ ጊዜ ትቀልጂያለሽ እንዴ?"አልኳት፡፡ እውነቴን ነው፡፡ በወቅቱ የዪኒሸርሲቲ የመጀመሪያ አመት ተማሪ ነበርኩ ይሄ ሁሉ ጉድ የተፈጠረው ክረምት ላይ እረፍት ሆኖ ቤተሠቤ ጋር ብዬ በመጣሁበት ቅፅበት ነው።እና እብድ ካልሆነች እንደዚህ አይነት ቀሺም ሀሳብ እንደማታስብ እርግጠኛ ነኝ።

"ለእቴቴ ጥያት እሄዳለሁ"
"አቤልንም?"አቤል ማለት ገና ከተወለደ ስድስት ወር ያላለፈው ወንድ ልጇ ነው፡፡
‹‹አይ እሱን ለእናቱ ሊሰጣቸው ነው"
‹‹እና  ልጆቹን ተከፋፈላችሁ ማለት ነው?"
"አዎ ...ጋብቻው ለጊዜው አሜሪካ እስክንገባ ባለበት ይቀጥላል...ከዛ እንፋታና በየፊናችን ህይወታችንን መምራት እንቀጥላለን።››
"ግን ከልጆች ተለይቶ መኖር አይከብድም?"
"አይ ከልጆች ይልቅ ከአንተ ተለይቶ መኖር ነው የሚከብደኝ ...ልክ ትምህርትህን እንደጨረስክ ሁኔታውን አመቻችና ተአምርን ይዘህ ትመጣለህ ..ከዛ ከዚህ ወግ አጥባቂ አፋም ህዝብ ተገላግለን  በነፃነት ሀገር የራሳችንን ነፃ ህይወት እንኖራለን"
"እንዴት ነው አሜሪካ እህትና ወንድም እንዲጋቡ ይፈቀዳል እንዴ?"
‹‹አትቀልድ .... ››
..ከምስር ጋር በዛ ተለያየን፡፡ ነገሮች ፍርጥርጥ ብለው ቅሌቴን እስክከናነብ እጄን አጣጥፌ ቁጭ ብዬ መጠበቅ አልቻልኩም፡፡ማድረግ የቻልኩት አንድ ነገር ነበር…፡፡  በማግስቱ ጨርቄን ማቄን ሳልል ስልኬን አጥፍቼ ደብረብርሀን ለቅቄ አዲስአበባ ገባሁ፡፡ትምህርት  ወደምማርበት አለማያ አልሄድኩም ።አዲስአባ ነው የመሸግኩት ።ይህን ያደረኩበት ዋና ምክንያት ምን አልባት ልፈልግ ብለው ቢሄድ እንዳያገኙኝ ነው።አዲስአበባ  የቀን ስራም መላላክም እየሠራው አንድ ወሩን አሳለፍኩና መስከረም ሲጠባ ወደ ዪኒሸርሲቲ አመራሁ..፡፡ዩኒቨርስቲ እንደረስኩ በፊት ይላክልኝ የነበረው ብር ያለማቆረጥ በባንክ ደብተሬ ይገባልኝ ስለነበር በወጪ ችግር አልነበረብኝም፡፡ከዛ ወጭ ግን ይሄው ስድስት አመት ከማንም ጋር ተገናኝቼ አላውቅም፤ የወሬ ወሬ ምስርም ወዲያው ወደአሜሪካ እንደሄደች ሰምቼያለሁ..፡፡ ቤተሠብ ሁሉ እውነቱን እንዳወቀና በተለይ አክስቴ እጅግ በጣም እንዳዘነች እና ትዳሯንም እንደፈታች ሰማሁ። እንግዲህ በእኔ በደደብ ቀሺም ስህተት ሁለት ትዳር ፈረሰ ማለት ነው..የባንክ ደብተሬንም ቢሆን ልክ ከተመረቅኩበት ወር ጀምሮ አዘጋሁት.. እንደዛ ያደረኩት እቴቴ ብር  መላኳን አንድታቆም ነው፡፡እንደውም ለምረቃ ሁለት ወር ሲቀረው…ባንክ ደብተሬ ውስጥ ከ20 ሺብር በላይ ነበር ያስገባችልኝ፡፡ያው ምረቃ ላይ ወጪ ስለሚበዛ  ለሱፍ ምናምን አስባ እንደሆነ ገባኝ…እኔ ግን ሱፉንም አልገዛሁ ምረቃ ላይም አልተገኘሁ ወረቀቴን ተቀብዬ ወደአዲሳባ ሸመጠጥኩ ብሩን ሰራ እስካገኝ ተጠቀምኩበት፡፡. ለማንኛውም ለጊዜው ትዝታዬን ላቁምና ወደእንግዳዬ ልመለሠ፡፡
////
"ሠላም ነሽ ታአምር?"
"ሠላም ነኝ አባዬ...ድምፅህን ስለሠማው ደስ ብሎኛል"

ይቀጥላል
743 viewsአትሮኖስ, 15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 18:00:12 #እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_ሰባት

...በሙዚቃው ደነስኩ.. ውልቅልቅ እስክል ውስኪውን አንጠፍጥፌ ጠጣሁ"..አዎ አውቃኛለች... ፈፅሞ አልረሳችኝም...ከሁሉም ያስደሰተኝ ደግሞ ‹‹ቀናህ!!!›› የምትለዋ ቃል ነች...ምክንያቱም ቅናት እነጠቃለሁ ብሎ ከመፍራት ጋር ወይም ከመሠሠት ጋር ተያይዞ የሚመጣ ስሜት ነው።ፍርሀትም ስስትም ምንጫቸው ፍቅር ነው...እርግጠኝነት ከጎደለው ፍቅር።እና ታፈቅረኛለህ እያለችኝ ነው?ግን እንዳዛ ስላሰበች ለምንድነው እንደዚህ የፈነጠዝኩት? የእውነት እያፈቀርኳት ይሆን እንዴ ? እንዴ ከነጠላ ስሞ ሌላ ስለእሷ ምንም የማላውቃትን ሴት እንዴት ላፈቅራት እችላለሁ? ግን እኮ ፍቅር የኋላ ታሪክን አጥንቶ የወደፊት መድረሻን ገምቶ አሁን የቋሙበትን ድልዳል በሚዛን መዝኖ የሚገባበት  የምክንያትና ውጤት ቁርኝት ማሳያ አይደለም..?ፍቅር ጨርቁን እንደጣለ ዕብድ ነገረ ስራው ቅፅበታዊና ተአምራዊ ነው።ስለዚህ ሳላቃትም በፍቅሯ ብወድቅ የሚደንቅ አይደለም!ግን ዕድሜዋ ጉዳይስ? ቢያንስ 10 አመት ትበልጠኛለች? እርግጥ በዕድሜ ሰላሳም ሀምሳም የምትበልጠውን እንስት ማፍቀር የተለመደ ነው?ቢሆንም ግን ቢገለበጥ ነበር የሚያምረው ..እኔ 10 አመት ብበልጣት።

ወየጉድ አሁንኮ ነገረ ስራዬን ላየ የመጀመሪያ የፍቅር አይነጥላዬን ገና እየገለጥኩ ያለው  ጀማሪ አፍቃሪ ነው የምመስለው ፤ግን እኔ ቢያንስ አምስት አጫጭር ጣፍጭ ለወግ የሚበቁ እና አንድ ረጅም የተወሳሰበ  ልቤንም ቅስሜንም  አብሮ እንቅሽቅሽ አድርጎ የሠበረ.. በአለንጋ ተደጋግሞ በመገረፍ የተነሳ ትላልቅ ተጠላላፊ ሰንበር እንደተጋደመበት ጀርባ የእኔም ልብ በዛ ፍቅር ምክንያት ዙሪያ ጥምጥም የዞረበት ጠባሳ የተጋደመበት ሆኗል...
"ያ ፍቅር ህይወትን አስተምሮኛል ?ያ ፍቅር  ደስታን አሳይቶኛል...?ያ ፍቅር ዘመዶቼን አሳጥቶ የከተማ ስደተኛና ምፅተኛ  አድርጎኛል...ያ ፍቅር በራስ መታመኔን እንቅሽቅሽ አድርጎ  የህይወት መስመሬን ከላይ ወደታች ገለባብጦታል…ያ ፍቅር ዛሬ ቢቋረጥም ግን ትዝታ ብቻ ሆኖ የቀረ እንደይመስላችሁ፡፡ ዛሬም ጣጣው እያደነኝ ነው...፡፡

እስከህይወቴ ፍፃሜ እንደተጣባኝ የሚዘልቅ ይመስለኛል። ...ይሄው ስድስት አመት ሞላኝ ባዶ ሆኜ መኖር ከጀመርኩ ...እና አሁን የማፍቀር ስሜት ሲሰማኝ የተገረምኩት ለዛ ነው።እውነት እርቃን ገላዋን ስላሳየችኝ ...ተዳፍኖ የኖረው የወሲብ ስሜቴ ስለተወጣጠረ ነው የተምታታብኝ። ግን አንድ ሰው በህይወት ዘመኑ ስንት ጊዜ በፍቅር ፍላፃ ይወጋል..?ማወራው በወንድና ሴት መካከለል ስላለ ፆታዊ ፍቅር ነው።አንዳንድ ፍቅር አንዴ ብቻ ነው..ሌላው ጊዜያዊ ስሜት ነው ይላል፤ ብዙሀኑም ያንን ተቀብሎ ያስተጋባል።መሬት ላይ ያለው እውነታስ ምንድነው የሚያሳየው?መልሱ በእያንዳንዳችን  ልብ ውስጥ እናገኘዎለን ...የእውነት ፍቅር አንዴ ነው ብለን የምናምን ከሆነ ወይ የህይወት ጅማሮ ላይ የምንገኝ ቲኔጀሮች ነን...ወይ ደግሞ ባጋጣሚ በልጅነታችን ከአንድ ሰው ጋር የመሰረትነው ፍቅር  እስከ እርጅናችን ዘልቆልን ማጣጣም የቻልን እድለኞች ስለሆን ይሆናል።
እንጂማ በእውነታው ፍቅር ደጋግሞ ሊጎበኘን ይችላል..ለአመታት አብሮን ሊዘልቅ አልያም ለአንድ ቀን ብቻ ብልጭ ብሎ ድርግም ሊል ይችላል። አንዳንድ ፍቅር ከቃላት ልውውጥ እና ከአይን መሠራረቅ  ላያልፍ ይችላል፤ሌላው እስከስሜት መጋራትና በወሲብ እስከመደራት ድረስ ከዘለቀ በኃላ ሊቋረጥ ይችላል..እስከጋብቻ ዘልቆ ልጅ ከተወለደ በኃላም ሊሰናከል ይችላል።ታዲያ ይሄኛው ፍቅር ነበረ ይሄኛው ደግሞ ዝምብሎ ግንኙነት ነው ብለን ፍርድ የምንሰጥበት ምን አይነት ተቀባይነት ያለው የህግ አንቀፅ አለ?።

ደግሞ ተፍቅሮ የተጣመረ ሁሉ ሲለያይ የግድ ፍቅሩ ስላለቀ ነው ብለን መደምደም አንችልም... አንዳንዴ በተጣማሪዎች መካከል ፍቅሩ ሞልቶ ተርፎ ግን በሌሎች አብሮ ለመኖር ምቾት በሚነሱ ምክንያቶች የተነሳም ሳይወድ በግዳቸው ፍቅራቸውን በልባቸው ቀብረው  ጉዞቸውን  በተለያየ ጎዳና  ሊቀጥሉ የሚገደዱባቸው አያሌ አጋጣሚዎች አሉ። ምክንያቱም ለሁለት ጥንዶች አብሮ ለመኖር ፍቅር የአንበሳውን ድርሻ ይያዝ እንጂ ግን ደግሞ ብቸኛው አስፈላጊ ነገር አይደለም።

ወይ ጉድ ..በዚህች እንግዳ ሴት የተነሳ የፍቅር ኤክሰፐርት መሆን ዳዳኝ እኮ….ጠርሙሶ ውስጥ ያለችውን መጠጥ እያወዛወዝኩ ከሆቴል ወጣሁና በእኩለ ለሊት ወደቤቴ ገባሁ፡፡በፀጥታ አልጋዬ ላይ ተዘረርኩ….፡፡ወዲያው ነበር እንቅልፍ የወሰደኝ፡፡
ጥዋት
..ከእንቅልፌ ባንኜ አይኖቼን ብገልጥም ቀልጠፍ ብዬ ከአልጋዬ መውረድ አልቻልኩም። ብነሳም ምን አልባት ምሳዬን ሰርቼ ከመብላት ውጭ ሌላ የምሄድበት ቦታ የለም ።ምሳ ደግሞ አላሰኘኝም፡፡ ምን አልባት ቁርሴን ከጋሽ ሙሉአለም የተሠጠኝን ቋንጣ ፈርፍር በደንብ ስለበላሁ ይሆናል። ተንጠራራሁና ከኮመዲኖዬ ላይ rich Dad poor Dad የሚለውን መፅሀፍ አነሳሁና ማንበብ ጀመርኩ .. አንድንም አባት የሌለው ሰው ሁለት አባቶች ያሉት ሰው የፃፈውን መፅሀፍ ለማንበብ መቋመጡ የሚገርም ነው። ብቻ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ሁለት ገፅ ሳላነብ ስልኬ ጠራ አነሳሁና አየሁት..፡፡

የማላውቀው ቁጥር ነው ፡፡ላንሳው ልተወው ተወዛገብኩ።በስተመጨረሻ አነሳሁት

‹‹ሄሎ»

"ሄ...ሎ"ጥፍጥ ያለ የህፃን ድምፅ...ደነገጥኩ፡፡

‹‹ሄሎ..ሄሎ ..ማን ልበል?"

«ተአምል...ነኝ»

"ተአምር"የተኛሁበት የእንጨት አልጋ ከስር እርብራብ ተቀንጥሶ ይዞኝ ወደታች እየሰመጠ መሠለኝ...፡፡ስልክ ባልያዘው ቀኝ እጄ ፍራሹን ጨምድጄ ያዝኩ....፡፡እለተ መፅአት የፊታችን እሁድ መሆኑን ተረጋገጠ የሚል አዎጅን አስከትሎ የነጋሪት ጉሰማ ብሰማ ራሱ እንዲህ ሰማይ ምድሩ አይዞርብኝ፡፡

ልጅቷ ኩልትፍትፍ ባለ ድምፅ ንግግሯን ቀጠለች
"አዎ ተአምል...ል..ጅህ"
ይሄ መቼስ ተአምር ነው....፡፡ ተአምር አሁን ስምንት አመቷ ነው።በአካል ከተያየን 6 አመት አልፎናል።ማለቴ ቀጥታ በአካል ያየዋት አቅፌ የሳምኮት :ለጥቂት ቀናትም ቢሆን ስታለቅስ ያባበልኮት የዛሬ ስድስት አመት ገና ክፉና ደጉን በቅጡ መለየት ባልቻለችበት ጊዜ ነው። ለዛውም እንደአባትና እንደልጅ እኮ አይደለም እንደ እህቴ ልጅ...እንደአጎቷ ሆኜ..፡፡ለምን እንደዛ ሆነ የእውነትም አጎቷ ስለሆንኩ፤ እንደዛም ስለመሰለኝ...፡፡ከዛ ወላጆቾ የውጭ ፕሮሰስ ጀምረው ስለነበር  ተአምር ዲ.ኤን. ኤ ምርመራ ማድረግ ግዴታ ሆነ …ተመረመረች...ውጤቱ  ለቤተሠብ በሀይለኛ መብረቅ የመመታት ያህል ድብ እዳና አስደንጋጭ ነበር... ልጅቱ የእህቴ ባል አይደለችም?
‹‹እንዴት ሆኗ...?"የህግ ሚስቱ እኮ ነች…፡፡››
"በተክሊል ነው እኮ የተጋብት"ብዙ ብዙ ተባለ... እኔ የምገባበት ጠፋኝ..ጠጋ አልኩና
በወቅቱ"ምስር ይሄ ነገር እንዴት እንደዚህ ሆነ ?››ብዬ ጠየቅኳት።
"አንተም እንደሌላው እንዴት ሆነ ብለህ ትጠይቀኛለህ?"
‹‹ምን ማለት ነው ?እንዴት አልጠይቅሽም?"
‹‹ያደረከውን ታውቃለህ ብዬ ነዋ ?››
770 viewsአትሮኖስ, 15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 13:13:28 የነቃሁት የቧንቧ ውሃ ሲወርድ ሰምቼ ነው። ኪዳን ቀድሞኝ ነቅቷል ወይም አልተኛም! አልጋው ጫፍ ላይ እንቅልፍ እንደወሰደኝ ልብስ ደርቦልኛል። ምናልባት እንቅልፍ አልወስድ ብሎት የነበረ ይሆን ብዬ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማኝ። በደቂቃዎች ውስጥ እናትህ አለችም ልትሞትም ነው የሚል መርዶ አርድቼው እኔ እንቅልፌን ስለጥጥ አደርኩ። እናቴን አግኝቻት ልትሞት መሆኑን ሳውቅ ለወራት መቀበል አቅቶኝ የሆንኩትን መሆን አስቤ ያጠፋሁ መሰለኝ። ብቅ ሲል

«ይቅርታ ቀሰቀስኩሽ እንዴ?» አለኝ

«ነግቶ የለ! ምነው እንቅልፍ አልወሰደህም እንዴ?»

«አይ ተኝቻለሁ!» ይበለኝ እንጄ የእኔን ኪዳን መች አጣሁት እንቅልፍ በአይኑ ሳይዞር ነው ያደረው። አስር ጊዜ <ደህና ነህ> እለዋለሁ። <ደህና ነኝ> ይለኛል።

«ማውራት ትፈልጋለህ ኪዳንዬ?»

«አልፈልግም! ዝም ብለን እንሂድ!» አለኝ።

ከመሄዴ በፊት ብዙ ማድረግ የምፈልጋቸው ነገሮች ነበሩኝ። ሆስፒታል ሄጄ ጎንጥን ማየት። ሻለቃው ጋር መደወል፣ ሴትየዋ ማን መሆኗን አውቄ ማግኘት….. ብዙ!! ከኪዳን የሚበልጥ ነገር የለኝም አይደል? እሱ እንዲህ በዝምታ ተለጉሞ የሚሰማውን እንኳን ሳላውቅ ራሴን ማስቀደም አልሆንልሽ አለኝ!! ክፍላችን የመጣውን ቁርስ እንደነገሩ እየለኳኮፍን መኪና ስፈልግ የሚያዘጋጅልኝ ሰው ጋር ደውዬ መኪና እንዲያመጣልኝ ካደረግኩ በኋላ የዳዊትን መኪና ሌላ ቦታ ወስዶ እንዲያቆምልኝ አደረግኩ። ለዳዊት ደውዬ መኪናውን ከቆመበት እንዲወስድ ስነግረው ምንም እንዳልጠረጠርኩ ለመምሰል ከራሴ ታገልኩ። መንገድ ከጀመርን በኋላ ሻንበሉ ደወለ። የመኪናው ባለቤት እና ልትገድለኝ የሞከረችው ሴት የተለያዩ ናቸው። ግን ሁለቱም በስማቸው የማውቃቸው አይደሉም!!

«ቢሮ ብቅ ካልሽ የሁለቱንም ፎቶ ላሳይሽ እችላለሁ!!» ብሎ ስልኩን ዘጋው!! መልዕክቱ አንድም ለመላክ አላምንሽም ነው ሁለትም ፎቶውን ለማየት ተጨማሪ ዋጋ አለው ነው። ስልኩን ዘግቼ ዝም አልኩ! ኪዳንም ምንም አልጠየቀኝም!! ዝምታው አስጨነቀኝ!! ልቤ ድንጋይ የተጫነበት እስኪመስለን ድረስ እንደከበደኝ ተጉዘን ከሰዓታት በኋላ እነእማዬጋ ደረስን!! አጎቴ ከበር እንደተቀበለን ኪዳንን እያገላበጠ ስሞ አልጠግብ አለው!!

«አቤት አንተ መድሃንያለም ምን ይሳንሃል!! አስካል ልጅሽ መጣልሽ!» እያላት ወደ ውስጥ ገባ!! እማዬ ለመነሳት በዛለ ጉልበቷ ተፍጨረጨረች። ከሁለት ቀን በፊት ካየኋት በላይ ገርጥታለች። ይብሱን የከሳችም መሰለኝ። ዝም እንዳባባሉ ፣ እንደማታው አጠያየቁ ከኪዳን ጋር ሲተያዩ አሁን የሚሆኑትን የሚሆኑ አይመስልም ነበር። ጉልበቷን አቅፎ ተንሰቀሰቀ። ፀጉሩን እየደባበሰች ተንፈቀፈቀች። እኔና አጎቴ የሁለቱን መሆን እያየን ስንነፋረቅ ቆይተን! አጎቴ ፊቱ ላይ የተዝረከረከ እንባውን ጠራርጎ ሲያበቃ ደግሞ እንዳላለቀሰ ሰው ኮስተር ብሎ

«አይ ደግም አይደል የምን ለቅሶ ነው?» አላለም?

ይቀጥላል.........



ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
1.6K viewsTsiyon Beyene, 10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ