2022-12-19 21:00:03
#የዘርሲዎች_ፍቅር
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ካርለት ድንኳናን ዘግታ ስትፅፍ የሰው ኮቴ የሰማች መሰላትና ጆሮዋን አቁማ አዳመጠች
"ካርለት?"
"የስ" ብላ ቶሎ በማስተካከል "ዬ! አለች - እንደ ሐመር ልጃገረዶችı ካርለት የጠራት ሰው ማን እንደሆነ አውቃዋለች
ደልቲ ነው ቀብራራው ጀግና የድንኳኗን ዚፕ ከፍታ ፈገግ ብላ አየችው" ሰውነቱ በአኖ (ከኦሞ ወንዝ ዳር በመጣ የተላቆጠ አፈር)
ተዥጎርጉሯል፥ ጴሮው (መሃል አናቱ ላይ ባለው ጌጥ) ላይ የተሰካው
የቀጭኔ ላባ በንፋስ ይርገበገባል ... እሱ ግን ፊቱን ዞሮ በርኮታው
ላይ ቁጭ ብሎ ጥርሱን በልምጭ ይፍቃል"
አንቺ ንብ አደለሽ
ምነው ቀፎሽን ዘጋግተሽ መቀመጥሽ
"ደልቲ ንፋሱ: ልጆችም
እንዳያስቸግሩኝ አለችው
ፈገግ ብላ እያየችው" እሱ ግን መልሷ አልተዋጠለትም ይህች ሰው! ነፋስና ልጅ የምትጠላ ምን ልትወድ ነው እህ! ብሎ ቆሽቱ
እያረረ ሃሣቡን ሳይናገር ከታጠቀው ዝናር አንድ ቀላህ አውጥቶ
ውታፏን ከፈተና በአውራ ጣቱ ጀርባ የትንባሆ ዱቄት ፈሰስ አድርጎ ጎንበስ ብሎ በአፍንጫው ቀዳዶች ሞዠቅ ሞዠቅ አድርጎ ሽቅብ ማገና በዐይኖቹ እንባ ፍጭጭ ብሎ ደጋግሞ ካስነጠሰው በኋላ
ትንባሆውን ለካርለት አቀበላት በሐመር ሴት ልጅ ትንባሆ መሳቧ ነውር የለውም! በፍቅረኞች መካከል ትንባሆ (ሱረት) መሰጣጣት ደግሞ አንዱ የመግባባታቸው ምልክት ነው።
"ሽማግሎች ለዛሬ ከብት ውጋ ብለውኝ ይኸው በሬዬን ይዠ መጣሁ" አላት ካርለት ትንባሆው ካስነጠሳት በኋላ ምክንያቱን የሰማች ቢሆንም ከእሱ አንደበት ለመስማት ብላ።
"ምነው ምናጠፋህ?" ስትለው መፋቂያውን አኘክ አኘክ አድርጎ ተፋና ረጋ ብሎ፣
"አንች ሰው ምነው ሥርዓት ቢኖርሽ ሴት በየት አገር ነው
የወንድን ጥፋት የምትጠይቀው?" አላት ደልቲ ካርለት እንዲህ
ስታጠፋ ጎንበስ ብላ እግሯን
እንድትይዝ አድርጎ ጡቷን
እንዳይመታ እየተጠነቀቀ ሁለት ሶስት ቀን በባራዛ አርጩሜ ደህና አድርጎ እየገረፈ ቢገራት ልክ እንደ ስልጡን አህያ ትሰግር እንደነበር አስታውሶ እህ! ሽማግሎች እንዳሉትስ በመታረሚያዋ ጊዜ
ስታጠፉ እኔ እንጂ ሌላ ማን ይታዘንበታል! ብሎ አዝኖ ጢቅ አድርጎ ምራቁን ተፋና ጥርሱን ይፍቅ ገባ።
"ጎይቲ ስታለቅስ ነው የምትውል አይተሃት ታውቃለህ?"አለችው ካርለት በጥያቄዋ ጎርጉራ አንድ አዲስ ነገር ባገኝ ብላ።
"ሰማሁ! እኔን እህቴን ምን የከፋ ችግር መጣባት! አዘነ
ደልቲ።
"ለዚህ ምን መፍትሔ አለው ታዲያ?" ስትል ካርለት ደልቲ
ሰረቅ አድርጎ አይቷት
"ምን መፍትሄ ይኖረዋል ሽማግሌ ያለውን መቀበል ነው እንጂ።
"ጎይቲ ከከሎ ጋር ከተጋቡ ወዲህ እኮ ሌላ ወንድ አታውቅም "እንደገና ለዓመል ያህል ሰረቅ አድርጎ እንደዘበት አያት የለበሰችው
ቆዳ የፊተኛው ክፍል ጉያዋ ውስጥ ተሸጉጦ: የቀኝ ጭኗ ውስጥ ክፍል እንደ ጥጥ ንጥት ብሎ ታየው"
"ተታናናሽ ወንድሞቹ ጋርስ አልቀበጠችም?"
"ከሎ ታናሽ ወንድም እኮ የለውም ሁሉም የእሱ ታላላቆች ናቸው"" ስትለው ታናሽ ወንድም እንደሌለው እያወቀ የረሳበት ምክንያት እየገረመው
"ተዘመዱ ወንዶችስ ጋር?" ካርለት የሰጎን ላባ የሰካበት ጴሮ የተተለተለውን ሳንቃ ደረቱን እንደ አቦ ሸማኔ ቀጠን ያለ ወገቡን አይታ ምራቋን ከምላሷ ስር መጣ ዋጠችና,
"ከማንም ጋር አልቀበጠችም ካለ ከሎ በቀር" አለችው
"እህ!" ሲል ካርለት ቀጥሎ የሚለውን ለመስማት ጆሮዋን መዘዘች እሱ ግን ጭራሽ ያልጠበቀችውን ጥያቄ
"የምጠጣው ውሃ ትሰጭኝ?" አለ ከኮዳዋ በኩባያ ቀድታ ውሃ
ስትሰጠው ቀና ብሎ አይቷት
"እሱን አንች ጠጭው፤ ለኔ በሾርቃ ስጭኝ" አላት ካርለት ውሃ ለማምጣት ሄደች ደልቲ አረማመዷን÷ ዳሌዋን ወገቧን ከኋላዋ የሚወናወነውን ቆዳዋን ጥርሱን እየፋቀ አየና ምራቁን ጢቅ አድርጎ ተፋና የበረቱ ከብቶች ቀለማቸው የተለያዬ ነው ቀይ፥
ዳልቻ: ነብርማ: ነጭ የካርለትም ቀለሟ ነጭ መሆኑ ሚስቶቹን
እንደ ከብቶቹ ቀለም ማሳመሩን ሲያስብ የደስታ ስሜት ተሰማው መልሶ ደግሞ የሐመር ልጃገረዶች እንዳለቁ ሁሉ ከዚች አግድም አደግ ጋር ቢቀርብኝስ ብሎ አሰበ አንዴ ግን አገባሻለሁ ብሏል1
ስለዚህ ቃሉን ማጠፍ አልፈለገም ግዴለም አገባታለሁ ድምጿ ግን
ምነው ተዛሬ ነገ ቃናው አይጣፍጥ? ብልግናዋና ድምጿ እንጂ ሴትነቷስ እያለ ሲያስብ ካርለት ውሃ በሾርቃ ይዛለት ብቅ አለች
ከርቀት እያያት ደሞ ደህና ገብሮ የነበረው ሰውነቷ እንደ ምስጥ ንጉስ ተመልሶ ለሰለሰ እያለ ሲያስብ ካርለት ሰው ጠርቷት
ዘወር ስትል የጀርባዋ ሰንበር ታየው ከሎ ከብት ሲዘል የተገረፈችው"
ደልቲ ትንሽ ፈርጠም ብሎ ሳቅ አለ ካርለት
አላየችውም ትዝ አለው ስትገረፍ ሰውነቷ የተንቀጠቀጠው ወድቃ
የተዘረረችው
ባለጌ! ብሎ ተቆጨና መልሶ ደግሞ አዘነላት ጀርባዋ ላይ
ያሉት የግርፊያ ሰንበሮች ጥቂት ናቸው ለሐመር ልጃገረድ ደግሞ
የግርፊያ ሰንበር ሌላው ውበቷ ሲሆን ዳንስ ቦታና ጫካ ውስጥ ወንዱ
እንደ አኮርዲዎን መጫወቻ ሰንበሮቹን በጣቱ እየነካካ የፍቅረኛውን የፍቅር ቅላፄ በማስተካከል የጋራ የፍቅር ስሜት የሚፈጥሩበት ነው
ሴቷና ወንዱ
በልጃገረድ ጀርባ ላይ ባለ የግርፊያ ሰንበር ላይ ሻካራ የእጅ ጣት ጫፎችን ማንቀሳቀስ ትናጋው በፍቅረኛው ምላስ የተነካ ያህል በስሜት ንዝረት መላ ሰውነቱ ያረግዳል ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ
የግርፊያ ሰንበሯ ጀርባዋ ላይ የበዛ ዘመደ ብዙ' ካነሰ ደግሞ ዘመደ ትንሽ ናት ይባላል ብዙ ጊዜ ልጃገረዶች እርስ በርስ
ስለዚህ ሲጨዋወቱ
ይእ! ይሄ ሁሉ ማን ሲዘል የተገረፍሽው ነው? ተብላ
የተጠየቀች እንደሆነ እጅዋን አዙራ ጀርባዋን እየዳሰሰች
ይእ! ይሄ የባልዳምቤ
ይሄ የሸረምቤ ይሄ የላሎምቤ …እያለች ትዘረዝራለች ልጃገረዷ በእነዚህ ሁሉ ዘመዶችዋ ስትፎክርና ሳትፈራ ስትገረፍ ያያት ደግሞ ስንትና ስንቱ ወንድ ተመኝቷታል ከስንቱ ጋርስ ቀብጣለች ሊያገባት የፈለገውስ እንዴት እንደሚበዛ መገመቱ አይቸግርም አንድ
የሐመር ወንድ ደግሞ ሌላው የተመኛትን ያፈቀራትን የራሱ አድርጎ ከማግባት የበለጠ ትልቅ
ክብር የለም በሐመር የጋብቻ አለም።
ካርለት ግን የተገረፈችው ለአንድ ቀን ብቻ ነው፤ የዛን ቀንም ግረፉኝ ብላ አልፎከረችም ስትገረፍም ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ
ስታለቅስ በመጨረሻም ህሊናዋን ስታ ስትወድቅ ምድረ ጎረምሳ ተሳስቆባታል እንጂ ማንም ለፍቅር አልተመኛትም ደልቲ ይህን
አስታውሶ
ወዲህ ወዲያ ስትል እንደ ፍየል ጅራት ስትወናወን እንጂ እሷስ ብትሆን ስንትና ስንት ዘመዶችዋ ከብት ሲዘሉ ብትኖር ኖሮ
የመገረፉ እድል መች ያመልጣት ነበር! እያለ ሲትከነከን ካርለት
አጠገቡ ደርሳ ውሃ የያዘ ሾርቃውን አቀበለችው
እየተጉመጠመጠ ደጋግሞ ተፋና ስምጥጥ አድርጎ ጠጥቶ ባይሮ ኢሜ ብሎ
አመሰገናት እግዜር ይስጥልኝ ለማለት
ካርለት ሾርቃውን
ሾርቃውን ልትመልስ ሄደች ያን ጊዜ ደልቲ ደሙ ፈላ ነደደው ተቀብላ ፈንጠቅ አድርጋ ደፋችውና
ይህች አሳሳች! ብሎ እራሱን ለማረጋጋት እየሞከረ ከመቀመጫው ተነሳ
"ይእ! እህ የታል አያ ደልቲ? አለ አሁን ውሃ ብሎኝ
ሰጥቸው መጣሁ አላልሽኝ?" አለች ጎይቲ ከካርለት ጋር ወደ ድንኳኗ
እየተጠጉ
"ጎይቲ አሁን እኮ እዚህ ቁጭ ብሎ ስናወራ ቆይተን ውሃ ስጭኝ ብሎኝ ሰጥቸው ሾርቃውን መልሼ: አንችን ጠርቸሽ መጣን በዚህ ቅፅበት የት ሄደ?"
"ይእ! እኔን ትጠይቂያለሽ ደሞ ይልቅ አንች ምንሽ ውስጥ ከተትሽው? አያ ደልቲ መቼም ካለ ነገር እንዲህ ሹልክ ብሎ እንደ
ሌባ አይጠፋም ተቀያየማችሁ?"
"ኧረ በጭራሽ"
1.5K viewsአትሮኖስ, 18:00