Get Mystery Box with random crypto!

#የዘርሲዎች_ፍቅር ፡ ፡ #በፍቅረማርቆስ_ደስታ ፡ ፡ #ክፍል_ሁለት የወሮ መንደር ሽማግሎች | አትሮኖስ

#የዘርሲዎች_ፍቅር


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


#ክፍል_ሁለት


የወሮ መንደር ሽማግሎች ከሁለቱ መንደሮች መሃል ካለችው ትንሽ ሜዳ ግማሽ ክብ ሰርተው በርኮታቸው ላይ ተቀምጠዋል" ባለ
ጴሮው፥ ሹልሹላው፥ የሰጎን ላባ ፀጉሩ ላይ የሰካው ሁሉም በተመስጦ ስብሰባው እስኪጀምር ለውይይቱ ህሊናቸውን ይሳስላሉ  ህፃናት ከሽማግሎች ርቀው
እንቧይ እየተቀባበሉ
ይጫወታሉ ጋልታምቤ ከቤቱ ወደ ሜዳው በምትወስደው ቀጭን ጎዳና ሄዶ ከሽማግሎች ጋር ተቀላቀለ ሌሎችም ከያቅጣጫው እየመጡ
ተደባለቁ„

ረጅም ጦር የያዙት የመንደሩ አለቃ (ዘርሲ) ከተቀመጡበት
ተነሱና ከወገባቸው ከታጠቁት ዝናር ጩቤ አውጥተው ጎረምሶች
የያዙትን ለፍላፊ ፍየል በቁሙ ጉሮሮው ላይ ወጉትና ፍየሉ ሲወድቅ
ከደሙ ጦራቸው ላይ ከፈርሱ ደግሞ ባታቸውን ቀባ-ቀባ አድርገው
ሄድ መለስ: ሄድ መለስ ብለው ንግግር ጀመሩ

"ጥሩ ነው! ዝናቡ መጥቷል መሬቷ ሳር አብቅላለች፥
ተራሮች እንደ ልጃገረድ አጊጠዋል ድንጉላ ቢራቢሮዎች፥ ወፎች
ይበራሉ" ንቦች አበባቸውን እየቀሰሙ ወደ ቀፎቻችን ይተማሉ፥ ውሃ የጠማት ምድር እምትጠጣው አግኝታለች እኛም የምንጠጣውን  ከስኬ ይሰጠናል አሸዋውን ስንጭረው ውሃ መሬቷን በጧር  ስንወጋት ማሽላ እናገኛለን ዳመናውን ሰርስራ
በምትወጣው ጨረቃም ልጆቻችን ይደሰታሉ
እንግዲህ ተቀያችን: ከዚች
አባቶቻችን ካቆዩን ምድር ምን ጎደለ!" ብለው ዝም አሉ የሽማግሎች
አለቃ" እንደገና ሄድ መለስ እያሉ ሁሉንም በዐይናቸው እየቃኙ

ብዙዎቹ ተሰብሳቢዎች ዐይናቸው ያለው ሌላ ቦታ ነው ሐመር ላይ ነገር በዐይን አይገባም' ነገር የሚደመጠው በልቦና ነው፤
ልቦና ያያል ልቦና ይሰማል
ልቦና ይመራመራል ልቦና
ይወስናል" በልቦና ለማየትና ለመስማት ግን ፀጥታ ያስፈልጋል ውስጣዊ እርጋታ የሃሳብ ማዕበል የሌለበት መተራመስ የተረጋጋበት ሊሆን ይገባል" ሐመር ላይ ሽበት ብቻ
ለሽምግልና አያበቃም፤
ጀግንነት ብቻ አያስከብርም
ማህበራዊ ችግርን ለመፍታት በጥንቃቄ ውሉን ፈልጎ አግኝቶ ትብትቡን
የሚፈታ ህሊናው ቀልጣፋ ከጀግንነቱም ከፍርድ አዋቂነቱም ሁለገብ ችሎታ ያለው መሆን ያሻል  ለሽምግልና ለመታጨት

"ጥሩ ነው! የአባቶቻችን መንፈስ ከእኛ ጋር አለ እንዳንራብ መከራ እንዳይበዛብን ዝንጉ እንዳንሆን የነሱ መንፈስ እንደ ዛፍ ጥላ ከለላ ይሆነናል ይሁን እንጂ በአባቶቻችን የነበረው ችግር አሁንም
አለ አሁንም የአባት ጠላት አለን አሁንም የአባት ጠላቶች እያዘናጉ የከብቶቻችንን ጅራት ሊጎትቱ የሚስቶቻችንን እጅ ሊስቡ፥ የላሞቻችንን ጡት ሊያልቡ ይፈልጋሉ ተናጋሪው  ንግግራቸውን ገተው ዙሪያ ገቡን እያዩ ፀጥ አሉ የኦሞ ወንዝ ቆሞ ያውቃል? ውሃ ታግዶ ይቆማል? ያባት
ደንብም እንዲሁ ነው፤ ሁሌም ከልጅ ወደ ልጅ ግድቡ በሽማግሎች
እየተከፈተ ከላይ እየወረደ የመጣው ወደሚቀጥለው
ትውልድ እየቶንዶለዶለ
ይፈሳል" ለዚህ ነው ከስኬ ሲጫር ውሃ: የእኛ ልብ
ሲቆፈር ደግሞ ያባት ደንብና ባህል የሚፈልቀው፤ ከእኛ መሃል ልቡ ሲቆፈር የአባት ደንብና ባህል የማያፈልቅ ደረቅ ካለ ግን ከጠላት
የተወረወረብን ድንጋይ ስለሆነ አምዘግዝገን መወርወር፥ ካካባቢያችን
ማጥፋት ይኖርብናል" ተናጋሪው ሽማግሌ ንግግራቸውን ገትተው
የተናገሩትን እንደገና በህሊናቸው አጣጣሙት።

"ወንድሞቼ የአባቶቻችን መንፈስ ከእኛ ጋር ነው
የምንሰራውን እነሱ ካቆዩን ደንብ ጋር ካላመዛዘነው እንደ ዱር ጉንዳን ማን እንደቆመብን ሳይታወቅ፤ ምንነታችንም ሳይጠየቅ አውራ እንደሌለው የሚያስተባብረው እንዳጣ ንብ በየጢሻው እንበተናለን
እንጨት ቆርጠን ሳር አጭደን ለንብ ቀፎ እየሰራን: እኛ ግን ተሰርቶ የቆየንን የአባት ደንብ ደህንነቱን
በመጠበቅ ለልጅ ልጆቻችን ማስተላለፍን ዘንግተናል" ከጉንዳን: ከንብ አንሰን የአባት ደንብ እየሻርን ነው: ትብብራችን እየላላ ነው፥ ወኔያችን ተሸንቁሮ
ንፋስ እየገባው ነው." እንደገና ቃኙት ተሰብሳቢውን  በዝምታ።

"አውሬ ይሁን ወፍ የማይታወቅ ጉድ በአራት እግሩ መንደራችን እየመጣ ሲቆም በሰፊው ሆዱ  ሴቶቻችንን እየሸፋፈኑ
እያቀፈ ሲወስድና ሲመልስ
ሴት ልጅ ወንድ የዘራውን ማብቀል  ሲሳናት እኛ አልተቃወምንም! ኧረ ተው! የተቀበልነውን የማናቀብል ጅብ አንሁን ጅብ የሚኖረውና የሚሞተውም ለሆዱ ነው የአባት ደንብ የለው ለልጄ ማለት አያውቅ አፍንጫው ጥንብ እንዳሸተተ: ሆዱ ለመብላት እንደተስገበገበ
ኖሮ ይሞታል ለልጄ ሳይል ደንብ ሳይኖረው ጥንብ እንደ አማተረ ይሞታል ለሆዱ! የተናጋሪውን ሃሳብ ከሚያዳምጡት መካከል አንዱ ሽማግሌ
የዘርሲዎች አለቃ በተናገሩ ቁጥር "ህም ህም… "አሉ በሐመር የስብሰባ ደንብ አንዱ ሲናገር ሌላው ህም ህም ካለ ልቀጥል ልናገር ማለት ስለሆነ የሽማግሎች አለቃ የንግግር እድሉንና
ተናጋሪው የሚይዘውን ጦር አቀበሉ  ተረኛው ሽማግሌ ጦሩን በቀኛቸው ይዘው ከፍየሉ ፈርስ ባታቸውንና ግንባራቸው ቀባ አድርገው እየተንቀሳቀሱ ሽማግሎችን: ህፃናትን: መንደሩን: ዙሪያ
ገቡን ቃኙት ጦሩ እጃቸውን ነዘረው ስሜታቸውን በሙቀቱ አጋጋለው፤ ወኔያቸውን እንደ ብረቱ ጫፍ አጠነከረው  የአያት
የአባቶቻቸው መንፈስ ከጦሩ ተነስቶ ወደ ልቦናቸው ተስለከለከ

ጥሩ ነው! የቀጋ ፍሬ ከሾላ ዛፍ የለቀመ ማነው ሾላና
ቀጋን ደባልቆ የሚበላ ግን አስተዋይ ነው ይህ ሰው የተፈጠረው ደግሞ እዚሁ እኛ ዘንድ ቡስካ ተራራ ላይ ነው ያ ሰው እሳት
አንድዶ የሚፈልጋቸውን መልካም መልካም ሰዎች በእሳት ብርሃን
ከያካባቢው ጠራቸው
እንግዲህ አያቶቻችን የባንኪሞሮን እሳት
እያዩ ከያቅጣጫው የተሰባሰቡ ናቸው እኒያን ፍሬዎች  ቀጋና ሾላዎች ባንኪሞሮ ደባልቆ በሐመር ምድር በተናቸው"
አያቶቻችንና አባቶቻችን በቀሉ ከእኒያ ብሩክ ፍሬዎች ደግሞ እኛ በቅለን እህ! በተራችን እንድናፈራ ላደረጉን አባቶቻችን ውለታችን ምንድነው?" ብለው ዝም አሉ ሽማግሌው በጠየቁት ጥያቄ አንጀታቸው እየተላወሰ መልሱን ግን ፀጥታው ዋጠው"

"ወንድሞቼ የአባቶቻችን መልካም ሥራ የሚመለሰው ባህልና.ደንባቸውን በመጠበቅ ነው" ተዚህ ታፈነገጥን የሚያድነው እንሰሳ ላይ ማነጣጠር እንዳልቻለ አነር መሮጥ እንጂ የምንይዘው አይኖርም ሁሉም ያምረናል፤ አረንጓዴ ሁሉ ይበላል? ኮሽም: ዶቅማ ይሆናል?- የእኛ ህይወት የአባቶቻችንን ፈለግ በመከተል የሚመራ
ነው፤ እነሱ ያዩትን ዓለምና ደስታ ለማግኘት ከዱካቸው ዝንፍ ማለት የለብንም ተዚያ ታፈነገጥን ግን እሾህ አለ እንቅፋት አለ… ዳመና
ከሰማዩ ላይ ይጠፋል ከብትና ምድሯ ይነጥፋሉ በሽታ ይበዛል ከዚያ ያኔ ቀያችን አጥንት ሰላማችን ቆምጭሮ ሁከት
ይከመርበታል እፅዋት መብቀል ያቆማሉ፤  ባንኪሞሮ  የአነደደው
እሳት ይጠፋና ጥንት እንደነበረው ቀያችንን ዳፍንት ይውጠዋል
ባዶ ይሆናል! እና ተልባችን እንምከር ወንድሞቼ!" ብለው እጃቸውን
አወራጭተው ጦሩን ስመው ዝም አሉ ሌሎች ሽማግሎችም እንዲሁ
የሚሰማቸውን ሲናገሩ ቆዩና ጥፋቶች በመጀመሪያው
ተናጋሪ ተዘረዘሩ።

በአካል ለዘለዓለም
ለተለዩን በርቲና ቃላ መደረግ የሚገባው ደንብ አልተሰራላቸውም "አሉ” እንዳንል የሉም የሉም
እንዳንል ደግሞ ደንቡን የምትጠብቀው ነፍሳቸው አንዴ በወፍ ሌላ ጊዜ በአሞራ ወይንም በንፋስ … መልክ እየመጣች ከእኛ ጋር ናት ንግግራቸውን ገተው የሽማግሎችን የመንደሯን የአካባቢውን ትንፋሽ አዳመጡና

ነጯ ሐመር ይዛው የመጣችብን ስም የለሽ: ጢስ ተፊ አውሬም እዚሁ ከእኛ ጋር እየኖረ ነው ሲበላ ባናየውም ሲጋት ግን
በዐይናችን በብረቱ አይተነዋል ከዚያ እንደ ጅብ አጉረምርሞ ዐይናችን እያዬ ግማቱን ለቆብን ይሄዳል "