Get Mystery Box with random crypto!

፩ ሃይማኖት

የቴሌግራም ቻናል አርማ and_haymanot — ፩ ሃይማኖት
የቴሌግራም ቻናል አርማ and_haymanot — ፩ ሃይማኖት
የሰርጥ አድራሻ: @and_haymanot
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.62K
የሰርጥ መግለጫ

ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-12-31 19:59:14 ገድለ ተክለ ሃይማኖት ፩

@And_Haymanot
ጥያቄ ፩
ገድለ ተክለ ሃይማኖትላይ ‘ሰይጣንን አጠመቁት’ ይላል እያሉ የተሐድሶ መናፍቃን ይተቻሉ፡፡ እውን ግን ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በቁሙ ሰይጣንን አጥምቀዋልን?

መልስ፡- በቀድሞ መጻሕፍት ሥጋ ለበስ የሆኑ አጋንንት ታሪክ የታወቀ ነው፡፡ እነዚህ ሥጋ ለበስ አጋንንት የአጋንንትን ሥራ የሚሠሩ ቢሆኑም
የሚዳሰስ ሥጋ ግን አላቸው፡፡ ለምሳሌ ድርሳነ ሚካኤል ዘጥር ላይ እንደ ተገለጠው እነዚህ በሽታዎችን ሁሉ የሚያመጡ ሥጋ ለበስ አጋንንት
እንደ ሰው ሁሉ ይታመማሉ፤ ይራባሉ፤ ይሞታሉም፡፡ አንዳንድ ጊዜ በበረሐ ውስጥ አንዳንድ ጊዜም በውኃ ውስጥ ይኖራሉ፡፡

+ በገድለ ተክለ ሃይማኖትና በልደተ አበው ላይ እንዲህ ይላል “አቡነ ተክለ ሃይማኖት በእነዚህ አውራጃዎች ሲመላለስ አንድ ቀን በውኃ ዳር ዐረፍ አለ፡፡ ጋኔንም ከውኃው ወጣና ደቀ መዛሙሩን ያዘው፡፡ አሳመመውም፡፡ እርሱም ጋኔን መሆኑን ዐወቀ፡፡ በረድኡ ላይም በመስቀል ምልክት አማተበበት፡፡ ጋኔኑም ፈጥኖ ወጣ ሸሸ፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም በእጁ ያዘው፡፡ ሥራዩንም አወጣበት፡፡ ያን ጊዜም ለሁሉ ታየ፡፡ እርሱም “ማነው ስምህ?” አለው፡፡ ጋኔኑም “ባሕር አልቀም” አለው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም “ከኔ ጋር ትኖራለህን?” አለው፡፡ እርሱም ገዘረውና ወደ ታላቁ የቤተ ክርስቲያን ምሥጢረ ጥምቀት አገባው፡፡ ስሙንም ክርስቶስ ኀረዮ(ክርስቶስ መረጠው ማለት ነው) አለው፡፡ ረድእም አደረገው፡፡ ወደ በኣቱም አስገባው፡፡ እርሷም አስቦ ናት፡፡ እርሱም እግዚአብሔርን የሚወድና ወንድሞቹንም ሁሉ የሚያስደስት ሆነ፡፡” (ገድለ ተክለ ሃይማኖት፤ነሐሴ 1989 ዓ.ም፤ ምዕራፍ ፶፩፤ ገጽ. 177-178፤ Getachew Haile, Geneaology, P.11&12)

+ በጥንታውያን ሰዎች ዘንድ በአጋንንት አሠራር ተጠምደው የሚኖሩ ጣዖት አምላኪ ሰዎችን ባደሩባቸው አጋንንት ስም መጥራት የተለመደ ነው፡፡ ሰው በውስጡ ባለው ነገር ይጠራልና፡፡ ልክ ጌታ ጴጥሮስን “አንተ ሰይጣን ከኋላየ ሒድ” (ማቴ.16፡23) እንዳለው ማለት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ታሪኮች በብዙ ጥንታውያን መጻሕፍት አሉ፡፡ ሥጋ ለበስ አጋንንት የሚሏቸው እነርሱን ነው፡፡ የተለያዩ የምትሐት ነገሮችን ይሠራሉ፡፡ በባሕር ይኖራሉ፣ በእሳት ውስጥም ገብተው በደኅና ይወጣሉ፡፡ ዋሊስ ባጅ ባሰተመው የደብረ ሊባኖስ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ላይ ጸሐፊው ከሌሎቹ የአካባቢው ቅጅዎች ለየት ብሎ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ያጠመቁት ክፉ መንፈስ ያለበትን ሰው እንጂ መንፈስ የሆነውን ሰይጣን አለመሆኑን በቅዱሳት መጻሕፍት ማስረጃዎች ያብራራል፡፡ (E.A.W. Budge, The Life and Miracles of Takla Hay-manot, (London,1906), P. 80).
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
328 views16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-27 20:06:39 ​​ሃያል ነህ አንተ

ሃያል ነህ አንተ ሃያል
ደጉ መልአክ ገብርኤል /2/
ይውደቅ ይሸነፍ ጠላት
አንተ ተራዳን በእውነት /2/
በዱራ ሜዳ ላይ........ገብርኤል
ጣዎት ተዘጋጅቶ.......ገብርኤል
ሊያመልኩት ወደዱ.......ገብርኤል
አዲስ አዋጅ ወጥቶ.......ገብርኤል
ሲድራቅና ሚሳቅ አብናጎም ፀኑ
ጣዎቱን እረግጠው በእግዚአብሔር አመኑ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡እዝ፡፡፡፡፡፡
ተቆጣ ንጉሡ.......ገብርኤል
በሶስቱ ሕፃናት .......ገብርኤል
ጨምሯቸው አለ.......ገብርኤል
ወደ እቶን እሳት.......ገብርኤል
ከሰማይ ተልኮ ደረሰ መልአኩ
ከሞት አዳናቸው እሳት ሳይነኩ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡እዝ፡፡፡፡፡፡
እቶኑ ስር ሆነው........ገብርኤል
ዝማሬ ተሞሉ........ገብርኤል
ገፍተው የጣሏቸው.......ገብርኤል
በእሳቱ ሲበሉ.......ገብርኤል
አልተቃጠለችም የራሳቸው ፀጉር
አዩ መኳንንቱ የእግዚአብሔር ክብር
፡፡፡፡፡፡፡፡፡እዝ፡፡፡፡፡፡
ናቡከደነጾር........ገብርኤል
እጁን በአፋ ጫነ.......ገብርኤል
ሠለስቱ ደቂቅን........ገብርኤል
ከእሳት ስላዳነ.......ገብርኤል
ይክበር ጌታ አለ የላከው መልአኩን
ሊያመልከው ወደደ ስላየ ማዳኑን.
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እንኳን አደረሳችሁ
309 views17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-25 20:33:00
#ገድል_ያወጣል_ከገደል
ክፍል ፪
@And_Haymanot
ሼር በማድረግ ምዕመናንን የመዳን ሥራ አብረን እንስራ

በዲ/ን ቴዎድሮስ ዘለቀ
@Konobyos
@And_Haymanot
290 views17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-24 09:35:38
#ገድል_ያወጣል_ከገደል
የገድላት ምንነትና አስፈላጊነት እንዲሁም በገድላት ዙርያ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን የምንዳስስበት ተከታታይ ትምህርት ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ ሼር በማድረግ ምዕመናንን የመዳን ሥራ አብረን እንስራ
ክፍል ፩
በዲ/ን ቴዎድሮስ ዘለቀ
@Konobyos
@And_Haymanot
337 viewsedited  06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-22 10:50:33 ተአምረ ማርያም ላይ መናፍቃን ጥያቄዎች አንዱ

☞ ጥያቄ. ነፍሳትን በበላው በበላኤ ሰብ ታሪክ ላይ።
☞ መልስ፦ የብላዔ ሰብዕ 78 ነፍስ አጥፍቶ መማሩ በማቴ10:42
"በደቀ መዝሙር ስም ቀዝቃዛ ዉሃ ቢጠጣ እውነት እላችኋለሁ
ዋጋው አይጠፋበትም" በሚለው አምላካዊ ቃል መሰረት ነው::
ተአምረ ማርያም እንደሚነግረን ስምዖን የተባለው ይህ ሰው ብዙ ነፍስ ካጠፋ በሗላ ንስሓ ገባ ተጸጸተ ልክ በቀኝ እንደተሰቀለው ወንበዴ::
በወንጌሉ መሰረት ለድሀ ከደቀመዛሙርት ሁሉ ከፍጥረት
ሁሉ በከበረችው በእመቤታችን ስም ቀዝቃዛ ዉሀ ለድሀ አጠጣ:: እመቤታችም በወንጌሉ መሰረት ማርለኝ አለችው ማረላት:: በቀኝ የተሰቀለ ከብላዔ ሰብዕ (ከዚህ ሰብ በላ) የበለጠ ይሥራ አይሥራ እኛ አናዉቅም::
ቃል ኪዳን ሲሰጥ ክርስቶስ ገደብ አላስቀመጠም (ይህንን ያህል
የገደለ አልምርም የሚል የለ)::
በደቀ መዝሙር ስም ያጠጣ አለ እንጂ:: ስለዚህ የወንበዴውን መዳንም እየተጠራጠሩ በወንጌል አምናለሁ ማለት አይቻልም:: በወንጌል ተጽፎ ነው እንጂ በቀኝ የተሰቀለው ታሪክ በተአምረ
ማርያም ቢጻፍ ኖሮ አይቀበሉትም ነበር::
በመጨረሻም መናፍቃን ከተለያዩ ገድላት፣ድርሳናት፣ተአምራት በመጥቀስ ምዕመንን ለማሰናከል ይኳትናሉና።
በተቻለ መጠን አይታለሉላቸው። ምንም እንኳን ገድሉ ተአምሩ ለማመን ከባድ ቢሆንም ክርስቲያኖች ነንና ከዚህም በላይ እንደሚደረግ እንወቅ!
ጌታ ያለውም ይህንኑ ነው።በእኔ የሚያምን ከዚህ በላይ ያደርጋል
ተብሎ ተፅፋልና!!!..... ሌሎች ጥያቄዎችን እንመለስበታለን  ይቆየን
@And_Haymanot
@And_Haymanot
256 views07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-20 19:17:36 አዎ መልስ አለን!

ተወዳጆች ሆይ መናፍቃን ለሚጠይቋቸው ጥያቄዎች ኦርቶዶክሳዊ ምላሾችን ይዘንላችሁ ቀርበናል የምትፈልጉትን ርዕስ Read more በማለት ማንበብ ትችላላችሁ።
ምላሽ የሚፈልጉ የተዋህዶ ልጆች በርካቶች ናቸውና ለሌሎች ሼር ማድረግ አንዘንጋ።

ኦርቶዶክስ መልስ አላት።
@And_Haymanot

በእንተ ቅድስት ድንግል ማርያም
ስለ ቅድስናዋ - የቅዱስ አምላክ እናት በመሆኗ
ስለ ድንግልናዋ
ምስጋና እንደሚገባት
ክብር እንደሚገባት Read more

የተሐድሶ መናፍቃን እምቤታችን ለምን ተነሳች በማለት የፍልሰታ ጾምን በእጅጉ ይተቹታል:: ሐዋርያዊ ውርርስ የሌለው እንግዳ ትምህርት እንደሆነም ይናገራሉ:: ሲያልፍም እመቤታችን አርጋለች ማለት ስሕተትም ነው ይሉናል፤ ይህንንም ያስተማረው በ 16ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረው አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ነው ይላሉ::
ለመሆኑ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዕርገት (Assumption of Mary) ትምህርት በኢትዮጵያ ሊቃውንት ብቻ የታወቀ ነው?
ትዛታው ሳሙኤልን ዕርገተ ማርያምን ሲነቅፍ የተሰጠ ምላሽ Read more

ስለ እመቤታችን ዕርገት የሚያትት በPdf የተዘጋጀ Read more

የተሃድሶ ሲናፍቃን ማርያም እንደማንኛችንም አይነት ሴት ናት በዛ ዘመን ብንኖር ከእኛ መሃል ከአንዳችን ኢየሱስ ይወለድ ነበር ብለው ያስተምራሉ ያምናሉ። Read more

ተአምሯን የሰማ ስጋውን ደሙን እንደተቀበለ ይሆንለታል Read more

       የድንግልን ትንሣኤ በኩረ ፕሮቴስታንት የኾነው ማርቲን ሉተር እንኳን በአንክሮ ያምናል ታድያ የዛሬዎቹ ስለምን ካዱ???? Read more

ድንግል ማርያምን ጨካኝ ለማድረግ የሚባዛው መልዕክት Read more

"ቅድስት ድንግል ማርያምን መውደድ ከሚገባኝ መጠን በላይ አልፌ ወድጄያት ይሆን? ብለህ ሥጋት አይግባህ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ከወደዳት በላይ ልትወዳት አትችልምና"
ቅዱስ ማክሲሚሊያን ኮልብ
@And_Haymanot
"ለሚያምን(ለማመን) ይኼ የሚጸን(የሚከብድ) ነገር አይደለም/ To believe this is no doubtful matter/." ዕርገተ ማርያም(Assumption of Mary)


በሚቀጥለው ርእሳችን ሰሞኑን መናፍቃን በሚያነሷቸው ገድላት ዙርያ ሁሉም ሊያውቀው የሚገባ መሰረታዊ ትምህርት ይዘን እንቀርባለን ተቀላቀሉን

አጠገብህ ጥያቄ ያለው ጓደኛ አለሽ/ህ
እንዲማር የምትባዘው/ዢው ወንድም/እህት ካላችሁ አሁኑኑ ላኩላቸው ማንም ባለማወቅ ከ አጠገባችን እንዲጠፋ አንፈልግም
፩ ሃይማኖት የቴሌግራም ቻናል
Share Share Share
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
277 viewsedited  16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-18 17:54:29 "ተአምሯን የሰማ ስጋውን ደሙን እንደ ተቀበለ ይሆንለታል"።

       @And_Haymanot
ለተሃድሶ መናፍቃን የተሠጠ መልሥ
(በድጋሚ የቀረበ)
ይህን ፅንሰ ሀሳብ ለመረዳት በመጀመሪያ በመቅደሙ የተፃፈውን
ቃል እንዳለ መመልከት ጠቀሜታ ይኖረዋል። አስቀድመን እንደተናገርን የታወቀ ምክንያት ኋጢአት ደዌ
ካልከለከለው በዚች ቀን ተአምሯን ሰምቶ ስጋውን ደሙን ይቀበል። ስጋውን ደሙን መቀበል ካልተቻለው ተአምሯን ሰምቶ ወደ ቤቱ ይሒድ ስጋውን ደሙን እንደተቀበለ ይሆንለታል ይደረግልኛል
በማለት ቢሰማ ይላል የዚህን አንቀጽ መልዕክት አንድ በአንድ በመተንተን ስንመለከት የሚከተሉትን ሶስት አበይት መልዕክቶች እናገኛለን።

ሀ ሥጋውን ደሙን ተቀበሉ፦

ይህ አንቀፅ በመጀመሪያ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በዋናነት የሚያስተላልፈው መልዕክት ሥጋውን ደሙን ተቀበሉ የሚል ነው። ምክንያቱም በፍትሐ ነገስት ከቀዳም ሥዑር በቀር ቅዳሜ ቅዳሜ እና እሁድ እሁድ በቤተክርስቲያን ተሰብስባችሁ ስጋውን ደሙን ተቀብላችሁ ደስ ይበላችሁ ተብሎ ታዝዟል ይህም ብቻ ብቻ ሳይሆን በበረሃ ያሉ ባህታውያን ሳይቀሩ መልዐከ እግዚአብሔር ስጋወ ደሙን ሰንበት ነው። / በዓላት-ምን ?
ለምን ? እእንዴት ? ገፅ ፵፮ እና ፷፮ / ነገር ግን በስርዐተ ቤተክርስቲያን አንድ ሰው ስጋውን ደሙን እንዳይቀበል ሊያደርጉ የሚችሉ ምክንያቶች ይኖራሉ።
እነዚህም በዚህ አንቀፅ የተገለፁት አንደኛ የታወቀ ምክንያት / እንደ ወሊድ ፤ ሀዘን ፤ ለቅሶ ፤ ...የመሳሰሉት ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ ኃጢዐት ነው።
ይከለክሉታል ተብለው ከተጠቁሱት በመጨረሻ የተገለፀው ደግሞ ደዌ ነው። አንድ ሰው በደዌ ምክንያት ነገር ከሰውነቱ እየወጣ፤ ደም እየፈሰሰው ይህን የመሰሉ ነገሮች እያሉበት ስጋወ ደሙን ላይቀበል ይችላል እነዚህ ሁሉ ግን ሰውየውን በቤተክርስቲያን
ቅፅር ተገኝቶ ከመፀለይ፤ ቅዱሳት መፀሀፍትን ምንባባት ከመስማት ግን ላይከለክሉት ይችላሉ። ስለዚህ አንድ ሰው እነዚህ ምክንያቶች ካልከለከሉት በቀር ስጋወን ደሙን ይቀበል በማለት ወንጌልን ይሰብካል እንጅ ከወንጌል የወጣ ቃል የለውም።

ለ ቤተክርስቲያን አትቅር ፦

ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ስጋውን ደሙን መቀበል ባይቻልህ ግን ስጋውን ደሙን መቀበል አይቻለኝም ብለህ ወደ
ቤተክርስቲያን ከመሄድ አትከልከል የሚለው። ተአምረ ማርያም ከቅዳሴ በፊት ያለው የቤተክርስቲያን የፀሎት
ክፍል አንድ አካል ነው።
መቅድሙም የሚለው ፦
።።።///።።።።///።።።
#ስጋወ_ደሙን_መቀበል_ካልተቻለው_ተአምሯን_ሰምቶ_ወደ_ቤቱ_ይሂድ_ነው።
።።።///።።።።///።።።
ይህም ማለት ባትቆርብም ቤተክርስቲያን አትቅር ማለት ነው።በፀሎቱ ትምህርትና በመሳሰለው መርሀግብር ሁሉ ተሳተፍ።
ዕለቱ ሰንበትና በዓላት ከሆነ አንድ ክርስቲያን ቤተክርስቲያን ካልሄደ በዚያም ተገኝቶ ካልተማረ ካላመሰገነ ክርስትናውን በምን ይገልፀዋል ?
በዚህ አገላለፅ ተአምሯን ሰምቶ ወደ ቤቱ ይሂድ የሚለውን በአስተውሎትና በቅንነት ከተመለከትነው የሚናገረው ስለተአምሯ ብቻ አይደለም። ታአምሯን አታስታጉሉ ሲል ወደ ቤተክርስቲያን ሂዳችሁ በዚያ ካለው ባለው አገልግሎት ተሳተፉ ማለት ነው። ምክንያቱም ተአምረ ማርያምን እንዴትና መቸ እንደሚነበብ
እናውቃለን። ከተአምሩም በፊት፤ ከተአምሩም በኋላ ሌሎች ፀሎቶችና
ምንባባት አሉ። ይህን አጠቃላይ አገልግሎት ለምዕመኑ በታወቀ በተረዳ ነገር በዚህ ስያሜ ማስታወቅ ክፋትም ኋጢአትም አይደለም። ሌላው አገልግሎት በዚህ አገላለፅ ለምን ጠሩት ቢባል በትርጓሜ ውዳሴ ማርያም ላይ እንደተፃፈው ሌላውን አገልግሎት በመናቅ ማቅለል ሳይሆን ለእመቤታችን ባላቸው ፍቅር ነው።

ሐ አትጠራጠር፦

ሶስተኛውና የየመጨረሻው የዚህ አንቀፅ መልዕክት በታወቀ ምክንያት
+++ በዚች ዕለት +++ ስጋውን ደሙን መቀበል ባይቻልክ ለሌሎች የተደረገው አይደረግልኝም የዕለቱ በረከት አይደርሰኝም ብለህ አትጠራጠር የሚል ነው። መፀሀፉ የተአምራት መፀሀፍ እንደመሆኑ መጠን ተአምራትም
የሚደረገውና ተአምራትም የሚያሰኛቸው ከዘወትራዊ የህይወት ተግባራትና ድርጊቶች የተለየ ለሰው የማይቻል በእግዚአብሔር ብቻ የሚቻል ነገር መደረጉ በመሆኑ አንተም ይደረግልኛል
በማለት በዕምነት ከፀሎቱ ተካፍለህ ከተአምሯም ሰምተህ ብትሄድ #በዕለቱ የቆረቡትን ሰወች በረከት ታገኛለክ ማለት
ነው። ይህ ደግሞ በቅዱሳት መፀሀፍ የተፃፈ ነው። ራሱ ጌታችን በወንጌሉ የስናፍጭ ቅንጣት ታክል ዕምነት
ቢኖራችሁ ተራራ ማፍለስ፤ ባህር መክፈል..........
ሌላም ሌላም ትችላላችሁ ሲል አስተምሯል። ይህም በዕምነት ሀይል እግዚአብሔርን በረከተ እግዚአብሔርን
ታገኛላችሁ ከእግዚአብሔር ትገናኛላችሁ ማለት ነው። ስጋወ ደሙ በየሳምንቱ ወይም ከዚህ ባነሰም ይሁን በበዛም
የምንቀበለውም ለዚሁ ሀይለ እግዚአብሔርን ገንዘብ አድርገን ኋጢያታችን አስተስርየን በረከተ ስጋ በረከተ ነፍስ አግኝተን ለመኖር ነው። በዚያች ዕለት አልቻልክ ብሎ ባትቀበል በዕምነትም ይህን ታገኛለክና አትጠራጠር ይሉናል ሊቃውንቱ።
የየመቅደሙ መልዕክት ይኸ ሁኖ ሳለ
"አውቆ የተኛን " ቢቀሰቅሱት አይሰማም እንደሚባለው ሰወችን ሆን ብሎ ለማጠራጠር ከቅዱሳን በረከት ለመለየት አጋንንት በሰወች አድረው ሊቃውንቱ ያላሉትንና ሊሉም ያላሰቡትን
ያቀርባሉ። ቤተክርስትያኒቱ " ስጋውን ደሙን አትቀበሉ " ስጋወ ደሙን መቀበልና ስጋወደሙን ሳይቀበሉ ተአምረ ማርያምን መስማት እኩል ናቸው የሚል ትምህርት አስተምራ አታውቅም እእንዲህም አታምንም።
ተአምሯን የሚሰሙትና የሚያሰሙትም ስጋውን ደሙን የተቀበሉ ወደፊትም የሚቀበሉ ናቸው እንጅ አረማውያን ወይም በስጋወ ደሙ የሚጠራጠሩ አይደሉም።
/// ይደረግልኛል በማለት ቢሰማ /// የሚለው ጊዜ የተገደበ
ነው፡፡ ታዲያ ይህ በዕውኑ ለምዕመኑ መንፈሳዊ ህይወት መጨነቅ ወይስ ለኑፋቄ ሽፋን መፈለግ ???
ምንጭ ትምህርተ ተዋህዶ አፕሊኬሽን።
ልዑል እግዚአብሔር በተዋህዶ በረት እንድንፀና ያድርገን ለዚህም የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን ጸሎትና ምልጃ ከሁላችንም ጋር
ይሁን አሜን::
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
Join  @And_Haymanot
          @And_Haymanot
305 views14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-18 08:13:10 እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት?

የመጨረሻ ክፍል

#ማስረጃ
‹‹ ቃየል ሚስቱን አወቀ ጸነሰችም ›› ዘፍጥረት 4፥17 የሚለው ቃል በግብር
እንደቀረባት(እንደተገናኛት) የታወቀ ነው
ምክንያቱም አወቃት ብቻ ብሎ አላቆመም ‹‹ ጸነሰችም ›› ይላልና !!! ነገር ግን ዮሴፍ ድንግል ማርያምን እስክትወልድ ደረስ አላወቃትም ካለ
በኋላ ሌላ ምንም ዓይነት ተቀጽላ ቃል የለውም ፡፡ መናፍቃን በግድ እናጋባ እናዋልድ ካላሉ በቀር ጸነሰችም ወለደችም አላለም አዚያው ላያ ያበቃል አራት ነጥብ ፡፡ ‹‹‹ ድንግል ማርያም ከክርስቶስ ውጪ ልጅ የላትም ! ›››

ተጨማሪ ማስረጃዎች እነሆ ፡- ሲጀመር መጽሐፍ ቅደስ በአንድም ቦታ ድንግል ማርያም ከክርስቶስ ውጪ ልጅ አላት አይልም ብሎም አያውቅም !!! መጽሐፍ ቅዱስ እውነቱን እውነት ሐሰቱንም ሐሰት የሚል መጽሐፍ ስለሆነ ያልሆነውን ሆነ አይልም የሆነውንም አይደብቅም !!! ወንጌልን ለዓለም የሰበኩ ቅዱሳን ሐዋርያትም ድንግል ማርያምን ማዕከል አድርገው አስተምረዋልና ከክርስቶስ በኋላ ልጅ ወልዳ ቢሆን ኖሮ ለምን ደበቁን ? ለምሳሌ ጌታችን ሲሰቀል በመስቀል ሥር ሆና ስማልቀሷ ፣ለዮሐንስ ስለመሰጠቷና መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ እርሷ በመሃከላቸው እንደነበረች ሲጽፉ ለምን ከጌታ ሌላ ልጅ መውለዷን አልነገሩንም? ለምንስ ደበቁን? አሁንም በዚህ አቋም ለጸናችሁ መናፍቃን እውን መለኮት ባደረበት ማኅጸን ሰው ያድርበት ይሆን? አዎ ከሆነ ያንተ ኢየሱስ ፍጡር እና ተራ ሰው እንጂ አምላክ አይደለም !!!
የኛ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ባደረበት ማኅጸን ግን ማንም….. !!! ማንም…. !!! ማንም…. !!! አያድርበትም ፡፡ በድጋሚ ልምጣባችሁ እውን ድንግል ማርያም ከክርስቶስ ውጪ ሌላ ልጅ ያስፈልጋት ይሆን ከዚያ በኋላ ብትወልድም ሰው አምላክ አይሆን? አበው እንኳ ‹‹ ሃምሳ ቢወለድ …… ከተባረከ ይበቃል አንዱ ›› ብለው የለ ታዲያ ድንግል ማርያም ከአንዱ ከብሩክ ልጇ ከክርስቶስ ሌላ ምን ሽታ ትወልድ ይሆን ?


መጽሐፍ ቅዱስ ዘለዓለማዊ ድንግልናዋን እንዴት እንዳስቀመጠ ተመልከት ፡-
1) “እቴ ሙሽራዬ የተቆለፈች ገነት የተዘጋ ምንጭ የታተመች ፈሳሽ ናት”መኃ.ዘሰ 4÷12 (ዳዊት የመንፈስ አባቷ ነውና ልጄ ይላት ነበር ሰሎሞን ደግሞ የዳዊት ልጅ ነውና እህቴ ያላታል የመንፈስ ወንድሟ ነውና)
2) “የምስራቁም በር ለዘለዓለም ተዘግቶ ይኖራል ሰውም አይገባበትም እግዚአብሔር አንዴ ገብቶበታልና” ት.ሕዝ 44÷1-2 (ምሥራቅ የተሰኘች ድንግል ማርያም ናት በርሷ ሰማይነት ክርስቶስ ፀሐይ ሆኖ ወጥቷልና) ይህን ቃል ለቤተ መቅደስ ነው ብለህ የምትከራከር ካለህ ‹‹ ለዘለዓለም የተዘጋ ቤ/መ በዚህ ምድር ላይ የለምና እራስህን አታታል!!!
3) “ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆንልኛል” ሉቃ 1÷34(ይህ የእመቤታችን አስደናቂ ንግግር ለወደፊትም እራሷን አቅባ እንደምትኖር የሚያረጋግጥ ቃል ነው ፡፡ አንድም ኃላፊ ግስ ነው የወደፊት ዓላማዋንም ያረጋግጣል) ‹‹‹ እርሱ ብቻ ልጇ እንደሆነ የክርስቶስ ምስክርነት›››
1ኛ) አይሁድ በምቀኝነት ክርስቶስን ሲሰቅሉት ከእግረ መስቀሉ ሥር የተገኘው ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ድንግል ማርያም ብቻ ነበሩ ፡፡ እመቤታችን ሌሎች ልጆች ቢኖሯት ኖሮ ‹‹ እነሆ ልጅሽ ›› ብሎ ዮሐንስን ጠብቃት ባላለውም ነበር ፡፡ በዚህ ላይ ዮሐንስም እኮ እናት ነበረችው ፡፡ ነገር ግን ድንግል ማርያም አንድያ ልጇ በመሆኑ ጌታችን ለዮሐንስ አደራ ሰጥቶአታል ፡፡
2ኛ) የኢየሩሳሌም ሴቶች ጌታችን መስቀል ተሸክሞ ሲያልፍ ተመልክተው አዝነው ሲያለቅሱ ‹‹ ለራሳችሁ እና ለልጆቻችሁ አልቅሱ ›› ተብለዋል እመቤታችንም መስቀል ሥር ሆና ታለቅስ ነበር ታዲያ ለምን ‹‹ ሄደሽ ለልጆችሽ አልቅሺ አላላትም ? ? ?
‹‹‹ ትልቅ እርምት የሚሻው የመናፍቃን ስህተት ›››‹‹ ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን? እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው? ተሰናከሉበትም›› ማቴ13÷56 የሚለውን ቃል ለማን እንደተነገረ እንኳ ሳያስተውሉ ጭራሽ ድንግል ማርያም ከክርስቶስ ሌላ ልጅ እንዳላት አድርገው ይህን አሳፋሪ ቃል ሲጠቀሙበት አይቼ እኔም አፈርኩበት !!! የዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ዓላማ አይሁድ ክርስቶስን ወንድሞች አሉት ፤
ዮሴፍ ከሟች ሚስቱ የወለዳቸውን ሁሉ ከድንግል ማርያም ነው ብለው በማሰባቸው ወይም በመናገራቸው ተሰናከሉ(ተሳሳቱ) ማለት ነው ፡፡

ታዲያ እነርሱ ክርስቶስ የዮሴፍ ልጅ ነው ፤ ድንግል ማርያምም ሌሎች ልጆች አሏት ብለው በማሰባቸው ተሳሳቱ ከተባለ ለምን አንተ ደግመህ ትሰናከላለህ??? ይህን ስህተታቸውን ሲያስረግጥ ትንሽ ወረድ ብሎ ‹‹ በአለማመናቸውም ምክንያት በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም ›› ይላል ፡፡

‹‹‹ ስለ ዘለዓለማዊ ድንግልናዋ ማጠቃለያ ››› እመቤታችን እንደማንኛውም ሴት አይደለችም !!! ክርስቶስን የጸነሰችው ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ሲያበሥራት ነው ፡፡ ‹‹‹ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆንልኛል ››› በማለት እንደተናገረችው እንደሌሎች ሴቶች በዘር በሩካቤ አይደለምና ነው፡፡ ቅድስት ኤልሳቤጥም ‹‹ አንቺ ከሴቶች
ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ›› ሉቃ 13÷9 በማለት እንደተናገረችው፡፡ ቅዱስ ዳዊትም ‹‹ ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ኦ ሀገረ እግዚአብሔር ›› (የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ ባንቺ የተደረገው ምንኛ ድንቅ ነው) አንዳለ በእመቤታችን የተደረገው ልዩ ነው ፡፡ ለዚህ ዘለዓለማዊ ድንግልናዋ አንክሮ(ምሥጋና) ይገባል ፡፡
          
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
         
     @And_Haymanot
     @And_Haymanot_bot

በሚቀጥለው ደግሞ ተአምረ ማርያም መቅድም ላይ ተአምሯን የሰማ ስጋወደሙን እንደተቀበለ ይሆንለታል የሚለውን እንመለከታለን::
491 views05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-17 13:47:39 እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት?

ክፍል ሶስት

@And_Haymanot

ተወዳጆች በዚህ ርዕስ ተከታታይ ምላሽ በመዳሰስ ላይ ነን በመሆኑም ሌሎችን ልንገፋበት ወይም ልንተች ያቀረብነው ሳይሆን የጠፋችሁ እህት ወንድሞቼ በማስተዋል እንድትጓዙ ብሎም እንድትነቁም ጭምር ነው፡፡
የማርያም ልጅ ይርዳን

@And_Haymanot

‹‹‹ የ-እስከ-ትርጉም ›››

ሥጋውያኑ ‹‹ እስከን ›› ተገን አድርገው ‹‹ እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም ›› የሚለውን ቃል ፍጻሜ ላለው ነገር በማስገባት ደግመው ደጋግመው ተሰናክለውበታል፡፡ ትርጉሙ(ፍቺው) ግን ይህ አይደለም ፡፡

ለምሳሌ ፡-
1ኛ) የሣኦል ልጅ ሜልኮል ‹‹እስከሞተችበት ›› ቀን ድረስ ልጅ አልወለደችም 2ኛ ሳሙ6፥23 ፡፡ ይህም ማለት እስከመጨረሻው ልጅ አልወለደችም ማለት እንጂ ከሞተች በኋላ ወለደች ለማለት አለመሆኑ የታወቀ ነው ፡፡
2ኛ) ይህም ነገር በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ጆሮ ተሰማ ‹‹ እስከሞቱ›› ድረስ ይህ በደል በእውነት አየሰረይላቸውም ኢሳ 22፥14 ታዲያ የዚህ ትርጉም ከሞቱ በኋላ ይሰረይላቸዋል ማለት ነውን? እስከዘለዓለም አይሰረይላቸውም ለማለት እንጂ፡፡
3ኛ) ከአዳም ጀምሮ ‹‹ እስከሙሴ ›› ድረስ ሞት ነገሠ ሮሜ 5፥14 ታድያ ከሙሴ በኋላ ሞት ቀረ ማለት ነውን?
4ኛ) እግዚአብሐየር ጌታዬን ጠላቶችህ ለእግርህ መረገጫ ‹‹ እስካደርግልህ ›› ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው መዝ101፥1 ታዲያ ጌታችን ጠላቶቹን (አይሁደን) በሥልጣኑ ከረታ በኋላ በአብ ቀኝ መቀመጡ ቀረ ማለት ነው?
5ኛ) እነሆም እኔ ‹‹ እስከ ዓለም ፍጻሜ ›› ድረስ ከእናተ ጋር ነኝ ማቴ28፥20 ከዓለም ፍጻሜ በኋላ ከእናንተ ጋር አይደለሀም ማለት ነውን ?
6ኛ) ቁራውንም ሰደደው እርሱም ወጣ ውሃውም ከምድር ‹‹ እስከሚደርቅ ›› ድረስ ወዲያና ወዲህ ይል ነበር ዘፍ 8፥7 ሲል ውሃው ከደረቀ በኋላ ወዲያና ወዲህ ማለቱን ተወ ማለት ነውን? እንግዲህ ከላይ በተዘረዘረው የእስከ ትርጉም መሠረት በማቴ1፥25 የተጠቀሰው ፍጻሜ የሌለው ‹‹ እስከ ›› መሆኑን ያስረዳል ስለዚህ ዮሴፍ እመቤታችንን እስከ ፍጻሜው ድረስ በግብር አላወቃትም ነበር ማለትነው፡፡ ከዚህ ውጭ በራሱ ፍቃድ የሚረተጉም ሁሉ የረተገመ ይሁን!!!

‹‹‹ የወንድሞች ትርጉም ›››

አዲስ ኪዳን በተለያዩ ቦታዎች ላይ ጌታችንን ‹‹ ወንድሞቹ ›› እንደሆኑ ከሐዋርያት ወገን የሚጠቅሳቸው አሉ ፡፡ ይህን በመያዝ ብዙ ጥራዝ ነጠቅ አንባቢያን (መናፍቃን) ጌታ ወንድሞች እንዳሉት እና ድንግል ማርያም ከጌታ ውጭ ልጅ እንዳላት በማውራት አነስተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀታቸውን ለማንጸባረቅ ይሞክራሉ ፡፡ ነገር ግን ማንም የራሱን ግላዊ ሃሳብ ከማንጸባረቁ በፊት የመጽሐፍ ቅዱስን የአጻጻፍ ዘይቤ መረዳት ያስፈልገዋል እንላለን ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ
1ኛ) በምን ቋንቋ እንደተጻፈ ፣
2ኛ) በማን ባሕልና ዘይቤ እንደተጻፈ ፣
3ኛ) በየትኛው ዘመን እንደተጻፈ አስቀድሞ ማወቅ ለማነበብና ለመረዳት ያስችላል ምክንያቱም ሃይማኖት መሠረታዊ ጉዳይ ነውና !!! መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት ከ40 በላይ ቅዱሳን ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ አብዛኛዎቹ ዕብራውያን ናቸው፡፡ ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስን አንብቦ ለመረዳት የዕብራውያንን ባሕል በከፊልም ቢሆን መረዳት ያስፈልጋል ፡፡ ስለዚህም

በዕብራውያን ባሕል ፡-

1ኛ) አብሮ አደግና ዘመዶችን በሥጋ እንኳ ከአንድ እናትና አባት ባይወለዱም ‹‹ ወንድም ›› ይባላሉ ዘፍ 13፥11
2ኛ) በሃይማኖት የሚመሳሰሉም ‹‹ወንድሞች ›› ይባላሉ ገላ4፥1 ‹‹ ወንድሞቼ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ››
3ኛ) በሕብረት በአንድ (ማህበር) የሚቀመጡ ‹‹ ወንድሞች ›› ይባላሉ ‹‹ ወንድሞች በሕብረት ቢቀመጡ እነሆ መልካም ነው እነሆም ያማረ ነው›› መዝ 133፥1፡፡
በተጨማሪም ሐዋርያት እርስ በርስ ‹‹ ወንድሞች ›› ይባባሉ ነበር ፡፡ ከዚህ በመነሳት ለጌታ ‹‹ ወንድሞቹ ›› ተደርገው የተጠቀሱት ሦስቱ ሐዋርያት በሥጋ የተወለዱ አይደሉም፡፡ ድንግል ማርያምም ከጌታ ውጭ ምንም ዓይነት
ልጅ የላትም !!! ልጅ ብቻም ሳይሆን ልጅ
የመውለድ ሃሳብም የላትም አልነበራትምም !!! በተጨማሪም ወንድሞቹ ተብለው የተጠቀሱት ‹‹ያዕቆብ ›› እና ‹‹ ይሁዳ ›› መልዕክቶቻቸውን ሲጽፉ ‹‹ የጌታ ባሪያ›› እያሉ ጻፉ እንጂ ‹‹ የጌታ ወንድሞች ›› ነን ብለው አልጻፉም
ማስረጃ ፡- የያዕቆብ መልእክት 1፥1 ‹‹የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ››
የይሁዳመልእክት 1፥1 ‹‹ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ ›› ስለዚህ እነዚህ ሐዋርያት ዮሴፍ ከሟች ሚስቶቹ የወለዳቸውና አብረውት ያደጉ እንጂ ከድንግል ማርያም የተወለዱ አይደሉም ፡፡ ‹‹‹እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም የሚለው ትርጉም ›››
ይህን ቃል በመጥቀስ ድንግል ማርያም ክርስቶስን ከወለደች በኋላ ዮሴፍ በግብር አውቋታል የሚሉ መናፍቃን አሉ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከወለደች በኋላ ልጅ ወልዳለች የሚል ቃል አልተጻፈም እንጂ !!! ይህን ቃል መነሻ አድርጎ ለመጀመርያ ጌዜ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን የጠየቀው በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ንጉሥ አርቃድዮስ ሲሆን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አምሥት ነገሮችን ግልጽ አድርጎለታል ፡፡ አርቃድዮስም መልሱን በሚገባ አምኗል ተረድቷል ፡፡ ዛሬም ጥያቄውን በድርቅና ሳይሆን ልክ እንደ አርቃድዮስ በየዋህነት ለጠየቀ ሁሉ መልስ የማያስፈልገው ጥያቄ ነው ፡፡ ሆኖም
ለዚህ ስህተታቸው መልስ መስጠቱ ተገቢ ነውና

አነሆ ፡- ‹‹ የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ ዮሴፍ ድንግል ማርያምን አላወቃትም ›› ማለት ፡- ዮሴፍ ድንግል ማርያም ጌታን እስከምትወልድበት ቀን ድረስ ማን እንደሆነች አላወቃትም(ማንነቷን) አልተረዳም ነበር ለማለት ነው ፡፡ ኋላ ግን ጌታን በወለደች ጊዜ በቤተልሔም እረኞች(ኖሎት) እና መላእክት በአንድነት ሲዘምሩ ፣ የሩቅ ምሥራቅ ነገሥታት(ሰብዓ ሰገል) እጅ መንሻ ይዘው መጥተው ሲሰግዱለት ፣ እንዲሁም ቤተልሔም ላይ የብርሃን ድንኳን ከምድር እስከ ሰማይ ተተክሎ ሲመለከት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት መሆኗን አወቀ (ተረዳ) እስከዚያች ቀን ድረስ ግን ማለትም ጌታን እስከምትወልድበት ቀን ድረስ ዮሴፍ ድንግል ማርያም የአምላክ
እናት መሆኗን አላወቀም ፣ አልተረዳም ነበር ለማለት ነው ፡፡

አወቀ ማለት በግብር ተገናኘ ማለት አይደለም !!! እንዲህ ከታሰበ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ የሚል ቃል አለ ፡-‹‹ ከእነርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጦ ሳለ እንጀራውን አንሥቶ ባረከው፥ ቈርሶም ሰጣቸው፤ ዓይናቸውም ተከፈተ፥ አወቁትም››ሉቃ 24፥30-31 ይህም ማለት ጌታችን መሆኑን አወቁ (ተረዱ) ከማለት ውጪ ሌላ ምን ዓይነት ትርጉም ሊኖረው ይችላል ??? (ማዕዱን ቆርሶ እስከሚሰጣቸው ድረስ ግን ጌታን አላወቁትም ነበር)ስለዚህ ማወቅ ማለት መረዳት እንጂ የግድ በግብር መገናኘት ዓይደለም !!
ይቆየን.....
ወስብሀት ለእግዚአብሔር

፩ ሃይማኖት ተዋህዶ

✞_✞_✞
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
185 views10:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 17:07:06 ​​እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት?

ክፍል ሁለት

@And_Haymanot

እመቤታችን ሌሎች ልጆች አሏት(ወልዳለች) በማለት ኑፋቄያቸውን ለሚዘሩ የተሃድሶዎ መናፍቃን በተከታታይ በዚህ ርእሥ የቤተክርስቲያናችንን ምላሽ ማቅረባችንን ቀጥለናል

@Konobyos

‹‹‹ የእጮኛ ትርጉም ›››

እጮኛ የሚለው ቃል ጠባቂ ማለት ነው፡፡ ሌላ ከሰው ልብ የፈለቀ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም፡፡ ለምሳሌ ‹‹እናንተን ለዘለዓለም ለእኔ እንድትሆኑ አጭቻችኋለሁ ›› ሆሴ 2፥21 ማለት ለጋብቻ ነውን? ያሳዝናል አጣመው ለተረጎሙት፡፡ አሁንም ሐዋርያው ከጌታችን ጋር ስላዋሐዳቸው ‹‹ ለእርሱ አጭቻችኋለሁ›› 2ኛ ቆሮ 11፥3 ማለቱን እናስተውል፡፡
እንደገናም ምእመናንን የከበረች ማደርያው ስላደረጋቸው ‹‹ለሰማያዊው ክብር አጭቻችኋለሁ ›› ኤፌ 5፥26 ታዲያ እንዲህ ሲል ላጋባችሁ ነው ማለት ይሆን(ሎቱ ስብሐት) ፡፡
እመቤታችን ንግሥተ ሰማይ ወምድር ነችና በ15 ዓመቷ መለኮት ተዋሐዳት ፡፡ ሲዋሐዳትም ለዮሴፍ ታጨች ሉቃ1፥26፡፡ እንግዲህ እጮኛ ማለት ትርጉሙን ያላወቁ ይወቁ እንላለን ፡፡ ነገር ግን ሰው በራሱ ፍቃድ አይተርጉም !!! ሌላው እጅግ የሚደንቀው ነገር ደግሞ ድንግል ማርያም ክርስቶስን ከመውለዷ በፊት እንጂ ከወለደች በኋላ ዮሴፍ ‹‹ እጮኛ›› ተብሎ በአንድም ስፍራ አለመጠቀሱ ነው
ማስረጃ ‹‹ ሕጻንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ ›› ማቴ 2፥3 እንዲሁም በግብጽ 3 ዓመት ከ3ወር በስደት ከቆዩ በኋላ ይህንኑ ቃል ለዮሴፍ በህልም ተነግሮት ‹‹ ሕጻኑን የሚፈልጉት ሞተዋልና ሕጻንና እናቱን ይዘህ ወደ ናዝሬት ተመለስ ›› አለው እንጂ እጮኛህን (ሚስትህን) ይዘህ
ተመለስ አላለውም ማቴ 2፥20፡፡

‹‹‹ የበኩር ትርጉም ›››

የበኩር ልጇን ወለደች የሚለው ቃል ብዙዎችን አሳስቷል ፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው በተለምዶ የበኩር ልጅ የሚባሉ የግድ ተከታይ ያላቸው መሆን አለባቸው የሚል አስተሳሰብ በመናፍቃን ክፉ ልቦና ስለሰረጸነው፡፡ ነገር ግን በተለምዶ የሚባል ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ጋር አይሰራምና እንዲህ ይታረማል
፡- ‹‹ እግዚአብሔር ሙሴን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም ከእንስሳትም ማኅጸንን የሚከፍት በኩር ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ አለው ›› ዘጸ 13፥1-2 ይህ ቃል እንደሚገልጸው በኩር የሚባሉት ለመጀመርያ ጊዜ ከእናታቸው ማኅጸን የሚወጡ መሆናቸውን እንጂ ግዴታ ተከታይ ሊኖራቸው እንደማይገባ ያረጋግጣል ፡፡ አንድም ብቻ ቢሆን የእናቱም ማኅጸን ለመጀመርያ ጊዜ ከፍቶ ከወጣ ተከታይም ባይኖረው በኩር ነው ፡፡ ይሄ የበኩር ትርጉም ካልገባን ወደ ሌላ ፤ ይልቁን ወደ ማንወጣው አዘቅት መዘፈቃችን አይቀሬ ነው ፡፡
ለምሳሌ ቆላስየስ 1፥7 ላይ ስለ ክርስቶስ ሲናገር ‹‹ ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኩር ነው ›› ይላል እዚህ ጋር በኩር የሚለው ቃል ተወዳዳሪ ላላቸው ነገሮች የሚጠቀስ ሆኖ ከቀረበ ጌታን ፍጡር አድርጎ ከፍጡራን ጋር አነጻጽሮ እርሱ ከፍጥረታት በፊት ቀደም ብሎ የተፈጠረ ፍጡር ነው እንደማለት ይሆናልና(ሎቱ ስብሐት)፡፡
እንደገናም በኩር የሚለውን ቃል በሥጋዊ ደማዊ ሃሳብ ከተረጎምነው ዕብ 1፥6 ላይ ‹‹በኩርን ወደ ዓለም ሲያገባ ›› የሚል ቃል አለ እዚህ ላይ የክርስቶስ በኩር ተብሎ መጠራት አብ ቀዳሚ ተከታይ የሌለውን የባሕርይ ልጁን ወደ መሬት ሂድ ፣ ውረድ ተወለድ ፣ ሙት ተሰቀል ብሎ እንደላከው ለመግለጽ ነው ፡፡ ታድያ አብ በኩርን ወደ ዓለም ሲልክ በኩር የሚለው ቃል ተጠቅሷልና አብም ከክርስቶስ ሌላ ልጅ አለው ማለት ነውን? እናንት ግብዞች መናፍቃን የመጽሐፍን ቃል በግርድፍ መረዳት ምን ያህል እንደሚያስት ይረዱ ድንግል ማርያምን የነኩ እየመሰላቸው ባለቤቱን መንቀፋቸው ያሳፍራል !!!
እርሷስ ክብር ይግባትና በተቃዋሚዎች አፍ አትረክስም እርሱ ባለቤቱ አንዴ አክብሯታልና ፡፡ ‹‹ የበኩር ልጇን ወለደች›› መባሉ መጀመርያና መጨረሻ የሌለውን አምላከ አዶናይ ፣ ልዑለ ባሕርይን ወለደች ማለቱ ነው፡፡

ይቀጥላል
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
Join
@Konobyos
Join
@And_Haymanot
Join
@And_Haymanot

ለሌሎች ሼር በማድረግ ኑፋቄያቸውን አብረን እንዋጋ

የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
261 views14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ